ካቶሊክ CATHOLIC ኩላዊት
Статистикаየጴጥሮስ ልጆች ነን እንሞታለን እንጂ በካቶሊካዊነታችን አንደራደርም! -የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት -የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ -ገድለ ቅዱሳን እና ነገረ ማርያም - የቤተክርስቲያን ታሪክ እና ካቶሊካዊ ለዛ ያላቸው አስተማሪ ጽሁፎች ያገኙበታል። ኑ ! ወጣትነታችንን እንኑር! " እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም " ሐዋ 4:20 @holysaviour
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 295
- 1/48двое суток
- 338
- 1/72трое суток
- 364
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሚበዝኁ እለ ይሣቅዩኒ ሊተ ፤ ቀብጹኒ እምልቦሙ ከመ ዘሞተ ፤ ማርያም ኩንኒ ረዳኢተ ። የሚያሰቃዩኝ ምን ያህል በዙ እንደ ሞተ ከልባቸው ተስፋ አሳጡኝ ማርያም ሆይ ረዳት ሁኚኝ ። ✝ ሶበ ንጼውዐከ ዘልፈ ማረያም ቅረቢ ፤ እምንዳቤነ ንስቲተ ከመ ታርሕቢ ፤ ቅድመ ሕዝብኪ ሰላመ ተናበቢ ። ማርያም ሆይ ከችግራችን ታላቅቂን ዘንድ ሁሉ ጊዜ በምንጠራሽ ቀን ቅረቢ በሕዝብሽም ሁሉ ፊት ሰላምን ተናገሪ ። ሰአሊ ለነ ማርያም ፤ ሰአሊ ለነ ማርያም ፤ ኀበ ወልድኪ ኄር መድኀኔ ዓለም ። ማርያም ሆይ ለምኝልን ፤ ቸር ከሆነው ልጅሽ ከመድኃኔ ዓለም ። ✞ ቃል አጽምኢ ማርያም ንግሥት ፤ ወጽራኅነ ለብዊ መሥዋዕተ ስብሐት ፤ ተወከፊ ለነ መሓሪት ። ንግሥታችን ማርያም ሆይ ቃላችንን አድማጪ መሐሪት ሆይ ተቀበይልን ጩኸታችንም የምሥጋና መስዋዕት ነውና ። በጽባሕ ወዮም እምድኅረ ሌሊት ፤ ትምክሕትነ አንቲ ማርያም ወለተ ዳዊት ፤ ቅድሜኪ ንስግድ በፍርሀት ። የዳዊት ልጅ ማርያም ሆይ ጠዋትም አሁንም ከሌሊት በኋላም መመኪያችን አንቺው ነሽ ፤ በፊትሽ በፍርሃት እንሰግዳለን ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ፤ ብሂልየ ወጠንኩ ዘለኪ ውዳሴ ፤ ማርያም እኅቱ ለሙሴ ። የሙሴ እኅቱ ማርያም ሆይ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ብዬ ያንቺን ውዳሴ ጀመርሁ ። እምቅድመ ሰማይ ወምድር ሀልዎትኪ ፤ ፀሐይ ወወርኅ ኢቀደሙኪ መላእክተ ሰማይ ይትለአኩኪ ። ከሰማይ ና ከምድር በፊት በእግዚአብሔር ኅሊና ውስጥ ነበርሽ ፀሐይ ና ጨረቃ አልቀደሙሽም የሰማይም መላእክት ይላኩልሻል ። Channel👇 https://t.me/holysaviour GROUP👇 https://t.me/catholicfamilies
ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ ታደሰ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት በ60ኛው መደበኛ ጉባኤያቸው ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ ታደሰን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት አድርገው ሾመዋል። የጉባኤው ፕሬዝደንት በመሆን ሲያገለሉ የቆዪት የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የጡረታ እረፍትን ተከትሎ በተደረገው ምርጫ የአዲስ አበባ ሀገረስበከከት ሊቀጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴን ቀጣይ የጉባኤው ፕሬዝደንት አድርገው መርጠዋል። ብፁዕነታቸው ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎታቸውን እንደሚጀምሩም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ላለፉት 28 ዓመታት ጉባኤውን በፕሬዝደንትነት በመምራት ወደላቀ ከፍታ ላደረሱት ለብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የከበረ ምስጋናውን እያቀረበ አዲስ ለተሾሙት ፕሬዝደንት ብፁዕ ሊቀጳጳስ አቡነ ተስፋስላሴ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል። ምንጭ: የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የፌስ ቡክ ገጽ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
60ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት አመታዊ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተርክስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት 60ኛ አመታዊ መደበኛ ጉባኤያቸውን በአዲስ አበባ ሀገረስብከት የአጽናኝቷ ማርያም ገዳም ጀምረዋል። በ60ኛው መደበኛ ጉባኤያቸው የሀገሪቱን የሰላም ሁኔታ፣ የቤተክርስትያን ሐዋርያዊ ህይወት እና ህጋዊ ማዕቀፍ ጉዳይ፣ የምዕመናን፣ የወጣቶች፣የገዳማውያን እና የገዳማውያት ህይወት፣ ለተለያዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ስለሚያገለግሉ ገዳማውያን እና በጎፍቃደኞች ሁኔታ፣ የቤተክርቲያን ተቋማት የሥራ ሂደት ግምገማ፣ ከእነዚህም በተጨማሪ የጉባኤው ፕሬዝደንት የሆኑት የብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የጡረታ እረፍትን ተከትሎ በቀጣይ ጉባኤውን የሚመሩ ጳጳስ ምርጫ በዋነኝነት የሚወያዩባቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን የጉባኤው ማህበራዊ ተግባቦት ተወካይ ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ የባህርዳር ደሴ ሀገረስብከት ጳጳስ ገልጸዋል። በጉባኤው የ12ቱ ሀገረስብከቶች ጳጳሳት፣ በጡረታ እረፍት ላይ ያሉ ጳጳሳት እና የጉባኤው ጠቅላይ ጸኃፊ የተገኙ ሲሆን በወቅታዊ የሰላም ሁኔታ የአዲግራት ሀገረስብከት ጳጳስ አልተገኙም። ብፁዓን ጳጳሳቱ በየአመቱ በታህሳስ ወር እና በሐምሌ ወር መደበኛ ጉባኤያቸውን በተለያዩ ወቅታዊ ቤተክርስቲያናዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይታወቃል። 60ኛው ጉባኤያቸውም የዚህ አካል ሆኖ ቀደም ሲል በኬንያ ናይሮቢ የምስራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባኤ በወጣቶች ላይ በማተኮር ባደረገው ጉባኤ እንዲሁም ከቀናት በፊት የአፍሪካ እና የማዳጋስካር የጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚየም በሲኖዶሳዊት ቤተክርስቲያን ጉዳይ የሳለፏቸውን ውሳኔዎች ወደተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
ደብተራ ፍፅምት ዘጳውሊ ዘገብራ ከሃሊ ፤ ወማኅደሩ ለልዑል ፈለሰት እምዘይበሊ ፣ ኀበ ዘኢይበሊ ፣ በመሰንቆሁ እንዘ የኀሊ ፣ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ ። ዳዊት አባቷና የልጇ ባለሟል " ቻይ ጳውሎስ የሠራት ፍጹም ድንኳን የልዑል እግዚአብሔርም ማደሪያው የሆነች ከሚጠፋው ዓለም ወደ ማይጠፋው ፈለሰች " እያለ በመሰንቆ ዘመረ ። ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ምስለ ነፍስኪ ኢመዋቲ ፤ በተሰናእዎ አሐቲ ፤ ድንግል በክልኤ ማርያም ወለተ ማቲ ፤ ሐመረ ተርሴስ ዘሰሎሞን አንቲ ፤ እንተ አእተው ጠቢባን ወርቅ ኢያፌር ባቲ ። ለፈለሰው ሥጋሽ እና ከማትሞተው ነፍስሽ ጋር በአንዲት ስምምነት ሰላምታ ይገባል ። በሃሳብሽ ና በሥጋሽም ድንግል የሆንሽ የማቲ ልድ ማርያም ሆይ ! ጥበበኞች የተሻገሩባት ና የያፌር ወርቅ የነበረባት ፣ ያቺ በተርሴስ የነበረችው የሰለሞን መርከብ አንቺ ነሽ ። Channel👇 https://t.me/holysaviour GROUP👇 https://t.me/catholicfamilies
ካቶሊክ CATHOLIC ኩላዊት pinned a photo
видео или голосовое, без подписи
ፍልሰታ ለማርያም በኅዳር 1 ቀን 1950 ዓ.ም ር.ሊ.ጳ ፒዮስ 12ኛ በ50 ካርዲናሎች ፤ 700 ጳጳሳት ፤ 600,000 ምእመናን ፊት በሮም ከተማ ስለ ፍልሰታ ለማርያም የሚከተለውን ቀኖናዊ ትምህርት እንዲህ እያሉ እወጁ ። " በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሥልጣን በራሳችንም ሥልጣን ፣ ጸጋን የተሞላች የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ፣ ምድራዊ ጉዞዋን እንደጨረሰች በነፍስና በሥጋ ወደ ሰማያዊ ክብር እንደ ተወሰደች በእግዚአብሔር የተገለጸ ቀኖናዊ እምነት መሆኑን እንገልጻለን ፣ እናስተምራለን ፣ እናውጃለን ። " ( ንግግራቸው "ሙኒፊቸንቲሙስ ዴውስ" (MUNIFICENTSSIMUS DEUS ) ተብሎ ይጠራል ። ሰላም ለፍልሰተ ስጋኪ ምስለ ነፍስኪ ኢመዋቲ በተሰናእዎ አሐቲ ። " ለፈለሰው ስጋሽ ከማትሞተው ነፍስሽ ጋር በአንዲት ስምምነት ሰላምታ ይገባል።" እንኳን አደረሳችሁ! የፍልሰታ ማርያም ጸጋ እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን! Channel👇 https://t.me/holysaviour GROUP👇 https://t.me/catholicfamilies
ማቴ 15:21-28 የከነዓናዊቷ ሴት እምነት፦ የጽናት፣ የትህትና እና የእውነተኛ ጸሎት ኃይል አንዲት ከነዓናዊት ሴት በጋኔን ክፉኛ የተያዘችውን ልጅዋን እንዲፈውስላት ወደ ኢየሱስ እያለቀሰች ለመነች። ኢየሱስ በመጀመሪያ ዝም አላት ፤ በመቀጠልም ለእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች እንጂ እንዳልተላከ ነገራት። እርስዋ ግን በትህትና እና በጽናት ሰገደችለት፤ ይህ ታላቅ እምነቷም የክርስቶስን ልብ አሸነፈው፦ “አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ።” በማለት የልቧን መሻት ፈጸመላት። እውነተኛ እምነት በጽናት እና በትህትና ይፈተናል ይህ የወንጌል ክፍል የጸና እምነት በማንኛውም እንቅፋት ላይ እንደሚያሸንፍ ያሳየናል። ሴቲቱ ኢየሱስ እምቢ ያለ በመሰለበት አቀባበል ተስፋ አልቆረጠችም። እግዚአብሔር ጸሎታችንን ያልሰማን በሚመስለን ጊዜ የእርስዋ ትህትና እና ጽናት ለእኛ ታላቅ አርአያ ናቸው። ክርስቶስ እውነተኛ እምነትን ፈጽሞ ቸል አይልም ይልቁንም ይበልጥ እንዲጠነክር ይፈትነዋል እንጂ። 🌱 ጸሎትህ ያልተመለሰ በሚመስልበት ጊዜ ልብህንና ጽናትህን በጥንቃቄ ፈትሽ። ተስፋ ቆርጠሃል ወይስ እንደዚች ሴት በትህትናና በእምነት እየጸለይክ ነው? እግዚአብሔር ለእውነተኛ እምነት ሁልጊዜ ምላሽ ይሰጣል ምናልባት እኛ ባሰብነው መንገድ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ለታላቅ መንፈሳዊ በረከታችን ነው። የያዕቆብ ለሊት ይሁንላችሁ🥰 ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://t.me/holysaviour
ማቴ 14:22-33 በማዕበሉ መካከል በውኃ ላይ መራመድ፦ እምነት፣ ንቃት እና የተዘረጋችው የክርስቶስ እጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝቡን ካበላ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ተሻግረው እንዲሄዱ አደረገ፤ እርሱ ግን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በሌሊትም ታንኳይቱ በሞገድና በነፋስ ትወዛወዝ ነበር። ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ። ጴጥሮስም በውኃው ላይ ሄዶ ወደ እርሱ ለመምጣት ጠየቀ፤ ነገር ግን የነፋሱን ኃይል ባየ ጊዜ ፈራ፥ መስጠምም ሲጀምር፦ “ጌታ ሆይ፥ አድነኝ” ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ “አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለ ምን ተጠራጠርህ?” አለው። እውነተኛ ጥንካሬ በክርስቶስ ላይ ዓይንን መትከል ነው የሕይወት ማዕበልና አውሎ ነፋስ የማይቀር ነው። ዕድላችንን የሚወስነው የማዕበሉ አለመኖር ሳይሆን የክርስቶስ ከእኛ ጋር መሆን ነው። ጴጥሮስ መስጠም የጀመረው ዓይኑን ከኢየሱስ ላይ አንስቶ ወደ ማዕበሉና ወደ ነፋሱ ባደረገ ጊዜ ነው። እኛም ጭንቀትና ፍርሃት እምነታችንን ከእግዚአብሔር ላይ ሲያወጡት የሚገጥመን ይህ ነው — ክርስቶስ ግን ሁልጊዜ ማዕበሉን አቁሞ ሳይሆን በማዕበሉ ላይ እየተራመደ ሊያድነን ይመጣል። 🌱 ዛሬ በሕይወትህ ማዕበል ውስጥ ሆነህ ልብህንና አመለካከትህን በጥንቃቄ ፈትሽ። ትኩረትህ ባጋጠመህ ጭንቀትና ፍርሃት ላይ ነው ወይስ ወደ አንተ በተዘረጋችው በኢየሱስ እጅ ላይ? በእምነት እጃቸውን ለሚዘረጉለት እጁ ፈጽሞ አታጥርም። የተቀደሰ ውሎን ተመኘሁ🥰ከወደዳችሁት ይህ መልእክት ለሚያስፈልገው ሰው ላኩ🙏 ለበለጠ መንፈሳዊ ስንቅና አስተንትኖዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ! Channel👇 https://t.me/holysaviour GROUP👇 https://t.me/catholicfamilies
ካቶሊክ CATHOLIC ኩላዊት pinned «https://vt.tiktok.com/ZS423K7mx/ 👆👆👆👆 "ማር -ያም" - አማርኛ እና ጉራጊኛ ግጥም ። ተጻፈ በዮሴፍ .M ውድ ካቶሊካውያን ይህ የመጀመርያ ስራዬ ነው ፤ እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ ፤ ከወደዳችሁት ላይክ-ሼር-ሪፖስት-ኮፒ ሊንክ በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ ፤ ማስተካከል ያለብኝ ነገሮች በኮመንት ስር ጻፉልኝ!! የክርስቶስ መንግስት ይስፋ! አምልኮ እና ስግደት ለድንግል ማርያም…»
https://vt.tiktok.com/ZS423K7mx/ 👆👆👆👆 "ማር -ያም" - አማርኛ እና ጉራጊኛ ግጥም ። ተጻፈ በዮሴፍ .M ውድ ካቶሊካውያን ይህ የመጀመርያ ስራዬ ነው ፤ እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ ፤ ከወደዳችሁት ላይክ-ሼር-ሪፖስት-ኮፒ ሊንክ በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ ፤ ማስተካከል ያለብኝ ነገሮች በኮመንት ስር ጻፉልኝ!! የክርስቶስ መንግስት ይስፋ! አምልኮ እና ስግደት ለድንግል ማርያም ልጅ ብቻ ይሁን ! mechem atasafrugnim🥰
ለካቶሊኮች ወንጌልን መስበክ ማለት ሰዎችን ለመንግስተ ሰማይ ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን በዚህ አለም ውስጥ ለሰው ልጅ ህይወት ጸጋን ድኅነትን እና ፍቅርን መሻት ነው ። በተለይም በተለያየ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድነትን ማጠናከርን ያካትታል ። ምክንያቱም ተለያይቶ ክርስቶስን መስበክ ሁላችን የስብከታችን ምንጭ አድርገን ከምንጠቀበለው የወንጌል ቃል ጋር ይቃረናል። (-አይልዋርድ ሾርተር) ቻናላችንን ይቀላቀሉ! Channel👇 https://t.me/holysaviour GROUP👇 https://t.me/catholicfamilies
ካቶሊክ CATHOLIC ኩላዊት pinned «→→ ካቶሊክ እና ካቶሊካዊነት →→ ካቶሊክ ማለት ምን ማለት ነው? ካቶሊክ የሚለው ቃል የተገኘው ካቶሊኮስ (Catholicos) ወይም ካቶሊኪስሞስ (Catholikismos) ከሚሉት የግሪክ ቃላት ነው፡፡ ትርጓሜውም ሁሉንም የሚያካትት፣ ሁሉንም ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባና የሁሉም የሆነ ማለት ነው፡፡ ወይም ሁሉንም የሚያካትት ማኅበረሰብ እንደማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው Universal or…»
እነዚህን ጥያቄዎች ክቡር አባታችን ይመልሱልናል 🥰 አባን ባርካችኋቸው ጀምሩት 👇👇 1 ካቶሊክ ማለት ምን ማለት ነው? 2 ካቶሊክ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው ማን ነው? 3 ቅዱስ ኢግናጢዮስ ካቶሊክ የሚለው ቃል እንዲጠቀም ምክንያት የሆነው ምንድን ነው? 4 የእስክንድርያው ቅዱስ ቄርሎስ “ካቶሊካዊት” ማለቱ ምን ማለት ነው?