tgindex
ሰማያዊ ወግ (The tradition of heaven)

ሰማያዊ ወግ (The tradition of heaven)

Статистика

ንጉስ ዳዊት፣ ለልጁ ሰሎሞን "በርታ ሰውም ሁን!!" እንዳለው፤ ጳውሎስም "...በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት ሙሉ ሰውም ወደመሆን" እንዳለው፣ ሰው ለመሆን ሰማያዊ ወጎችን እናወጋለን።

Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
472
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
337
20 постов
Вовлечённость
71,4%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
105
1/48двое суток
120
1/72трое суток
129

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እንደ ልቤ የሚሆንልኝ። ዳዊትን ያሰለጠነው እግዚአብሔር፣ ዳዊትን እግዚአብሔር እንዴት እንዳሰለጠነው ወንድሙ እንኳን አላወቀም፣ እግዚአብሔር ሲያስታትጥቃችሁ ትጥቃችሁን ሰው አያየውም። ትንሹ ዳዊት አንዲት ግልገል በድብ ስትነጠቅ፣ ከድብ ጋር ይተናነቃል፣ ስለ በጎቹ ከአንበሳ ጋር ይታገላል፣ የአንበሳውን ክንድ እና መንጋጋ ሰብሮ ግልገሉን ያስጥላል። ትንሹ ዳዊት ሃገሩ በጠላት እንደተወረረች ሰማ። በትሩን አንጠልጥሎ ወደ ጦር ሜዳ መሰስ አለ ታላቅ ወንድሙ "የልብህን ክፋት አውቃለሁ" አለው ዳዊት ግን በሃገሩ የመጣውን ጠላት ሊተናነቅ ቆመ። ንጉሱ ሳኦል፣ የዳዊትን ትንሽነት አየ፣ በዳዊት የሚሰራውን እግዚአብሔርን ሳተ። "ቁመቱ ከስድስት ክንድ ይበልጣል፣ የምድራችን ጀግና ነው። የናስ ቁርና፣ ጥሩር ይለብሳል፣ የናስ ብረቱ አምስት ሺ ሰቅል ነው። እግሩን በነሃስ ገንባሌ ሸፍኗል፣ ትከሻው ሰፊ ነው። ጦሩ እንደ ሸማሬ ተወርውሮ ይወጋል፣ ጦሩ ስድስት መቶ ሰቅል ሙሉ ብረት ነው" እያለ ዳዊትን ለማስፈራት ሞከረ። ንጉስ የፈራው ይህ ብረት በዳዊት አይን ጠብታ ነበርች። ብዙ ሰዎች ከፊት የሚጠብቃችሁን የብረት ተራራ አድርገውታል፣ እንደ ንጉስ ሳኦል ከፊታችሁ የቆመው የእሳት ፍላፃ ሆኖባቸዋል፣ ነገሩን እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ጉልበት ተመልከቱት፣ ተከምሮ የሚታያችሁ እንደ እንቧይ ካብ የሚናድ ነው፣ የነሃስ አጥር የመሰላችሁ በምስጋና የሚፈርስ ገለባ ነው። ንጉስ ሳኦል ስለ ጎልያድ ያወራው ግዙፍ ወሬ በአንዲት ጠጠር የሚጣል ነው። የጎልያድን ጭንቅላት ለመቁረጥ ዳዊት ሰይፍ መያዝ አያስፈልገውም፣ ጎልያድ አንገቱ የሚቆረጥበትን ሰይፍ ለዳዊት ይዞለታል። ጠላት በሚያሳያችሁ የጥፋት መሳሪያ እራሱ የሚጠፋበት ነው። የምንዋጋበት መሳሪያችን የኢየሱስ ስም ነውና በሰማይ ይሁን በምድር፣ ከምድርም በታች ድል አላችሁ።...

  • 4 авг.217165

    እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው። እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን ፈጠረ፣ ሁለት ነበሩ፣ "ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሏት።" ሲል የበረከትን ቃል አስቀመጠ። ከዛ ከመብዛት ማንም አላቆማቸውም። አቤል ቃየልን ሲገል፣ ያበቃ ይመስል ነበር፣ የባቢሎን ግንብ ሲገነባ፣ እግዚአብሔር በውሃ ምድር ሲመታ ያበቃ ይመስል ነበር፣ ግን አያበቃም አንዴ እግዚአብሔር "ተባረኩ" ብሏልና እንበዛለን። በእናንተ ላይ እግዚአብሔር ያስቀመጠው የበረከት ቃል ከመሆን ማንም አያግደውም። ሳይሳካላችሁ፣ የተመኛችሁትን ሳታገኙ፣ ከምትሄዱበት ሳትደርሱ፣ የልባችሁን መሻት ሳታገኙ ምንም አትሆኑም። እግዚአብሔር ስለናንተ በስራ ላይ ነው። በዚህ ሁሉ መከራ እግዚአብሔር ልጆቹን ያኖራል። ምግብ ይወደዳል እግዚአብሔር ግን ያበላል፣ መኖሪያ ይወደዳል እግዚአብሔር ግን ያኖራል። ጠላት ያቅዳል እግዚአብሔር ያፈርሳል። ጠላት ያውጃል እግዚአብሔር አዋጅን ይሽራል። ሰው እንዳሰበልን አንሞትም በእግዚአብሔር እንኖራለን። ሰው እንዳሰበ አይበትነንም እግዚአብሔር ይሰበስበናል። ሰው እንዳሰበ አይቀማንም እግዚአብሔር ይሰጠናል። ሰው እንዳሰበ አያጎለንም እግዚአብሔር ይሞላናል። ሰው እንዳሰበ አያስቀረንም እግዚአብሔር ያደርሰናል። ሰው እንዳሰበ አይጥለንም እግዚአብሔር ያቆመናል። ሰው እንዳሰበ አያስለቅሰንም፣ እግዚአብሔር ደስታ ይሆነናል። ሰው እንዳሰበ ባዶ አንሆንም እግዚአብሔር ይሞላናል። ሰው እንዳሰበ ተንቀን አንቀርም፣ እግዚአብሔር ማእረጋችን ነው። እግዚአብሔር እየሰራ ነው። ሰው እንዳሰበ አንረሳም፣ እግዚአብሔር በጠላታችን ፊት ገበታችንን ያዘጋጅልናል፣ ፅዋችንን ያትረፈርፈዋል፣ ምስክርነትን የሚወድ አምላክ በበረከቱ ምስክርነቱን ያፍጥንላችሁ። እግዚአብሔር መልካም ብቻ ነው፣ የእግዚአብሔር መልካምነት በፊታችሁ ያልፋል።

  • 3 авг.193121

    እኔ ግን በእግዚአብሔር ፍቅርን የሚገድል ጥላቻን የሚተክል ምነው በዛ?? ምነው ዳንኪራው ከቅዳሴው በለጠ? ምነው ጥላቻ ከፍቅር በለጠ? ምነው ክፉ ዜና ጮኸ? ምነው ሰይጣን የሚወደውን ወደድን? ምነው የሰይጣን ፍሬ በየአደባባዩ ታየ። ጥላቻ የማን ነው? ግድያ የማን ነው? ድሃን ማፈናቀል የማን ነው? ህፃን ማሰቃየትና ማስራብ የማን ነው? ጦርነት የማን ነው?? ፀልየን የቆመው ጦርነት ምነው ጀመረ? እናቶች ምህላ ገብተው ያስቆሙትን ጦርነት፣ ፀሎት የማያውቁ ለምን ጀመሩት? የአንተን ሰላም ለጦርነት ተጠቀምንበት። ገዳይ እያረፈ ይጀምራል። አንተ ሰላም ስትሰጠን እኛ ለጦርነት አደረግነው። ስለዝናብ ፀልይን ሰጠኸን፣ ዝናብ ስትሰጠን እንረሳሃለን፣ አንተ ያበቀለውን እህል በልተን አንተ ላይ ጠገብን። ካለ አንተ መኖር እንደማንችል እንረሳለን። እንጀራ ቆርሰን አፍችን ብናደርስ ስለረዳኸን፣ እጁ ታጥፋ የቀረችበር፣ ጥርሱ ማኘክ እንቢ ያለችው ብዙ አለ። እየተራመዱ ድንገት እግራቸው አልታዘዝ ሲላቸው እናውቃለን። ዳዊት፣ ኤርሚያስ፣ እንባቆም፣... በመከራ ጊዜ እግዚአብሔርን በሃዘን ጠይቀውታል፣ ለምን?? ይሄ ሆነ??" ብለውታል፣ ለምን ሲባል መልስ ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ ብቸኛ መፍትሄ እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ በሚሆንብን ወደ ሰው አቤት አንልም፣ ወደ እግዚአብሔር እንገሰግሳለን እርሱም ያከናውንልናል። እንባቆም እንዳመነው እኛም እናምነዋለን። "ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።" እንባ 3:17-19

  • ቃለ እግዚአብሔር። ብዙዎችን በየትኛውም ጥበብ ልትለውጧቸው አትችሉም። ልጆቻችሁን የትኛውንም ሃብት መድባችሁ በአለም የታወቀ ዩኒቨርሲቲ ብታስተምሯቸው መለወጥ አይችሉም። መፅሀፍ ቅዱስ ሁለንተናን ይለውጣል። መፅሀፍ ቅዱስ ፈልጎ ያገኛችኋል። ለመፅሀፍ ቅዱስ ፍቅር የነበራት፣ ከቦርሳዋ መፅሀፍ ቅዱስ ጠፍቶ የማያውቅ በብዛት ቅዱሱን መፅሀፍ ስታነብ የምትታይ አንዲት ሴት፣ መፅሀፍ ቅዱሱን እንዴት እንደምታነብና እንደምትወድ ስትጠየቅ። "እኔኮ መፅሀፍ ቅዱስ አላነብም እሱ ያነበኛል፣ እኔ መፅሀፍ ቅዱስን አላፈቅርም፣ ቃሉን ሳነብ መፈቀሬን እረዳልሁ እንጂ" ስትል መልሳ ነበር። እውነት ነው፣ መፅሀፍ ቅዱስ እርሱ እራሱ መስታወት ነው። እራሳችንን ያሳየናል፣ እንደመታጠቢያ ቤት መስታወት ጉድፋችንን እንድናስወግድ ገበናችንን ሸፍኖ ያሳየናል። ሁሉ እንደ ሀዘኑ የሚፅናናበት፣ ሁሉ እንደ ድክመቱ የሚበረታበት፣ ሁሉ ከእንቅልፉ የሚነቃበት ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅዱስ አውጎስጢኖስ በስካርና በዝሙት ከኖረበት ህይወት ወደ ቅድስና የመጣው መፅሀፍ ቅዱስ አንብቦ ነው። በአግባብ ተመላለሱ። በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት" የሚለውን ክፍል አነበበ ተቀድሶ ቀረ። ሮሜ 13 ታዋቂው የወንጌል ሰባኪ ኒክ ክሩዝ ትንቢተ ኢሳያስ ወደ እኔ ተመልከቱና ዳኑ የሚለውን አነበበ፣ ከውንብድና ህይወቱ ተለወጠ። ጆን ኒውተን በከባድ ሃጥያት ደስታ በማጣት የሚኖር ሰው ነበር፣ በባሪያ ንግድ የተሳተፈ ነበር። በባህር ጉዞ እያለ በሃዘን ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፣ እግዚአብሔር እራራለት መፅሀፍ ቅዱስን አነበበ ሁላችን የምናውቀውን "Amazing Grace" የተባለውን መዝሙር ፃፈ። የእግዚአብሔር ቃል የሚያነቡትን ይለውጣል እምነታቸውን ያሳድጋል፣ ልባቸውን ያድሳል።... ይቆየን...

  • መኖሪያችን ክፉ በሆነ መንገድ በየምሽት ክለቡ የሙዚቃ ስራ እሰራ ነበር፣ የምኖረውም በዚህ ሙያ ነው፣ በዚሁ ሙያዬ ስራዎችን ለማቅረብ ከባንዶች ጋር አሜሪካ ገባን፣ ህይወቴን የምቀይርበት እድል አገፕሁ። አሜሪካ ገብተን ሆቴል እንደያዝን በመጀመሪያው ቀን እንቅልፍ አጣው፣ "መሞቻህ ነው" የሚል ድምፅ ሰማሁ፣ ሳልተኛ ነጋ። በፍጥነት ወደ ፕሮሞተሩ አቀናሁ፣ ከዚህ በኋላ ከሙዚቃ ቡድኑ መውጣቴን ነገርኩት፣ በጣም ተገረመ "ምን እያልክ ነው፣ አንተን የሚተካ ሰው የለም፣ ይሄን ስራ ጨርሰህ ታቆማለህ" አለኝ። "በጭራሽ" አልኩት። በጣም ተገርሞ አየኝ "ይሄን እድል አታበላሽ" ታምሜ መሰለው። "በደህናህ አይመስለኝም፣ ምን ትበላለህ፣ በምን ትኖራለህ?" አለኝ። እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ቃል ተናገርኩ። "መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ ነው" አልኩት። በዛው ቀን የት እንደምሄድ ሳላውቅ ከሆቴሉ ወጣሁ፣ በማላውቀው ሃገር ሁሉን ትቼ ወደ መንገድ ዳር ወጣሁ። ከዛ በኋላ እንዴት እንደሆነ በማላውቀው ሁኔታ ሁሉን ነገር እግዚአብሔር አዘጋጅቶልኝ ነበር። በጥቂት ቀን ውስጥ ካናዳ በሚገኝ ታዋቂ ቤተክርስቲያን ትልቅ የሙዚቃ ቡድን እንዳደራጅ ስራ ተሰጠኝ፣ እግዚአብሔር ሙያዬን ሳልተው እርሱን እንዳገለግል እድል ሰጠኝ። ምንም ሳይኖረኝ መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ ነው፣ ብዬ የታመንኩት አምላክ፣ ማንም ሰው በቀላሉ ሊያገኘው የማይችለውን እድል ሰጠኝ፣ ከዛ በኋላ ደስተኛ ሆንኩ፣ አሁንም ደስታዬ እየጨመረ እኖራለው። አለኝ። ይሄ የጓደኛዬ እውነተኛ ታሪክ ነው። እኛ ሁላችንም ተጓዦች ነን። የምንጓዘው በእምነት ነው። በእጃችን ካለው ስራ ይልቅ እግዚአብሔር ማመን ይገባናል። ሃዋርያት፣ ኢየሱስ ሲልካቸው፣ ምንም እንዳይዙ እንዲያምኑት ነግሯቸው ነበር ሲመለሱ ምንም አልጎደላቸውም። በእምነት እንጓዛለን ምንም አይጎልብንም።...

  • ክርስቶስ ሆይ ክርስቶስ ሆይ ካንተ በላይ ውብ ቃል የለም፣ ባንተ ቃል ውብ የሆኑት ሰማይ ምድር ተፈጥረዋል። ቃልህ አንዴ ፈጥሮ አልተወንም፣ በየእለቱ ይሰራናል። "ይሁን" እያለ ውበትን የፈጠረ ቃልህ እንዴት ውብ ነው። በሰው ልብ ብዙ ነገር አለ፣ አንተ የመከርከው ቃል ብቻ ይፀናል። ክርስቶስ ሆይ ምክርህ እንዴት ውብ ነው። አንተ ስትናገር "አልሰማም" የሚል አንዳች የለም። ክርስቶስ ሆይ ተናገር እኛም እንሰማሃለን። ክርስቶስ ሆይ ኦ ድምፅህ፣ የሚያጓራውን አውሎ ነፍስ ይገስፃል። መስማት ያልቻለውን ጆሮ ይከፍታል፣ መናገር ያልቻለውን ምላስ ያናግራል። ቃልህን የሚቋቋም የለም፣ ዳጎን ቢሆን ይሰበራል፣ ኢያሪኮ ቢሆን ይፈርሳል። ክርስቶስ ሆይ ድምፅህ እንዴት ውብ ነው!!! ሙሉ ዘመኑን በአልጋ የዋለው ድምፅህን ሰምቶ ተነሳ፣ አይነ ስውር የነበረው ድምፅህን ሲሰማ አይኑ በራ። "ማን ነው የነካኝ" በሚል ቃልህ ከ12 አመት ጀምሮ ከማህፀና ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት መዳኗን በሰውነቷ አወቀች። ክርስቶስ ሆይ ያንተን ውበት ለማየት እውር የነበረው አይኑ ይበራል፣ ድምፅህን ለመስማት የደንቆሮው ጆሮ ትከፈታለች፣ አንተን ያየ ሁሉ ስላንተ ለማውራት ምላሱ ይፈታል። በዚህ ምድር አንተን የማይወድ እንዴት ምስኪን ነው!!!! አንተ እግዚአብሔር የሰጠን ርእስ ነህ፣ አንተ ክርስቶስ ታሪክ ነህ፣ እውነት ነህ፣ ትንቢት ነህ፣ እናወራሃለን፣ እንኖርሃለን፣ እንመሰክርሃለን። ስላንተ ለማውራት ምቹ ስፍራ አይባልም፣ አለማቱ ሁሉ የተጋጠመው ባንተ ነው። ስላንተ ምቹ ጊዜ አይባልም የጊዜ ባለቤት አንተ ነህ፣ ስላንተ ላናወራ አንችልም፣ ስላንተ ዝም እንዳንል እርዳን። አንተን የሰሙ ሌላ ድምፅ እንዳይሰሙ ተመኝተዋል፣ አንተ ያዩ አባቶች ሌላ እንዳያዩ ቆርጠው የእምነት ምስክርነትን ትተውልን አለፉ፣ የምድርና የሰማይ ውበት ክርስቶስ

  • ሃሌሉያ "አለም ዋንጫ" ባሳለፍነው የአለም ዋንጫ ታዋቂው ጀስቲን ቢበር በፍፃሜው ቀን ሙዚቃ ከሚያቀርቡ ዳንኪረኞች አንዱ ነበር። ብዙዎቹ በብዙ ሙዚቀኞች፣ በብዙ ዳንሰኞች፣ በብዙ ብልጭልጭ ዳንኪራቸውን አቅርበዋል። ጀስቲን ቢበር ተራው ሲደርስ አንዲት አኩስቲክ ጊታር ይዞ፣ ያለ አጃቢ "Everything Hallelujah" የተሰኘ ዘፈን አቀረበ። ያቀረበው ዘፈን በመጨረሻ አልበሙ ያወጣው ቢሆንም ሀሳቡ ግን ክፉ አይደለም፣ "በደስታ ስንደንስ ፀሀይ አየችን፣ አዲስ ቀን መጣ ሃሌሉያ፣ በውሃ እደሰታለሁ ሃሌሉያ፣ ሁሉ ደስ ይላል፣ ወደ መስክ ስወጣ፣ ውበትን ሳይ ሃሌሉያ።" "ዝናብ ከሰማይ ሲዘንብ፣ የሚነፍሰውን አየር ስተነፍስ፣ በዚህ ሁሉ ስዘምር ሃሌሉያ፣ በደስታ ሳሸበሽብ ሃሌሉያ" ይላል። ይሄ የዘፈኑ ጥቂቱ ሃሳብ ነው። በመጨረሻ ስለ አለም ዋንጫው ሃሌሉያ" እያለ ይጨርሳል። የእሱ የሙያ ጓደኞች እንደፈለጉ ባብለጨለጩት፣ ያለ ጥንቃቄ በተጠቀሙት ዳንኪራ ማንም አስተያየት አልሰጠም። ጀስቲን ቢበር ባቀረበው "Everything Hallelujah" ዘፈን ግን ብዙ አስተያየት ሰማን። አንዳንዶች "Hallelujah የአለም ዋንጫ ዘፈን አይደለም" አሉ። የአለም ዋንጫ ለምን Hallelujah ይከለክላል?? ጀስቲን ቢበር ብዙ ስኬቶችን ያገኘ፣ በመጨረሻም ደስታን ያጣ ሰው ነው፣ በዚህ በጥቂት አመታቶች ግን ትንሽ ተረጋግቶ በየስፍራው ስለ ኢየሱስ ሲያወራ ተሰምቷል፣ "አለቀለት" ከተባለ ህይወቱ ኢየሱስ እያከመው ነው። ጀስቲን ቢበር በጣም ህፃን ሁኖ አለም ያከበረችው ሰው ነው፣ አሁን የአለም ዝና ጥቅም እንደሌለው ሲመሰክር ሰምቼዋለው፣ ታድያ አለም በደገሰችው ድግስ አብዛኛው አርቲስት የሴቶችን ጭን እያሳየ በብልጭልጭ ሲደንስ እሱ ግን አንድ ጊታር ብቻ ይዞ Hallelujah ማለቱ ትልቅ ድል ነው። ማስተዋል ይስጠን።

  • ሲሰሙት ደስ የሚል!!!! በዚህ ምድር ኢየሱስን እያወቁ አለመደነቅን የመሰለ መበደል የለም። ኢየሱስ በመቅደስ እለት እለት ሲያስተምር ሁሉም በደስታ ይሰሙት ነበር፣ በዚህ ቅናት ያደረባረባቸው ሊገድሉት ይፈልጉ ፈለጉ፣ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ተንጠልጥለውበት ነበርና አልቻሉም። በእውነት ህዝቡ ሁሉ ተንጠልጥለውበት ነበር የሚለውን ሳነብ ልቤ ሀሴት ያደርጋል። በወጉ ሰላም ለማለት ፍላጎት ባጡ አገልጋዮች መሃል ስንገኝ ክርስቶስ ላይ ግን ይንጠለጠሉበት ነበር። ሉቃስ 19:47 ኢየሱስ ህዝቡን በምሳሌ ያስተምት ነበር፣ ፈሪሳውያንና የሄሮድስ ወገኖች ግን ተበሳጭተው ሊይዙት ፈለጉ፣ ህዝቡ በደስታ ግን ይሰሙት ስለነበር ማድረግ አልቻሉም። ስለ ኢየሱስ መስማት ሀሴት ነው። ከዛም በላይ የታሰሩ ይፈታሉ፣ በሽተኞች ይፈወሳሉ፣ ኢየሱስ ባለበት አጋንንት የለም፣ ኢየሱስ ደስታ ነው፣ በዚህ ምድር እውነተኛ የምስራች ተብሎ መነገር የሚገባው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ስለ ኢየሱስ ሲወራ እስረኛን ይፈታልና አሳሪው ይበሳጫል፣ በሽተኞች ይፈወሳሉና አሳማሚ ይበሳጫል፣ ክርስቶስ እሳት ያጠፋልና እሳት ጫሪዎች ደስ አይሰኙም፣ ክርስቶስ ፈውስ ነውና መድሃኒት ሻጮች ሰላም ያጣሉ። ኢየሱስ ብርሃናችን ነውና በጨለማ ያሉ ይሄን ስም መስማት አይፈልጉም። ስለ ኢየሱስ ስታወሩ ደስ የማይሰኝ የሰላም ሰው አይደለም። ነገሩ እንዲህ ነው፣ ብዙ እስረኛ ወዳሉበት ወይኒ ቤት እስረኛውን ለማስፈታት ሄዳችሁ እንበል፣ የእስር ጠባቂው ዝም ብሎ የሚያይ ይመስላችኋል?? በጭራሽ!! እስረኞች ነፃ እንዳይወጡ እስከመጨረሻው በእሳት ምላጭ ይፋለማችኋል። ኢየሱስ ነፃነት ነውና ነፃ ያልወጡ ይቃወሟችኋል። በእሳት በተያያዘ ቤት ከእሳቱ ውስጥ ሰዎችን ስናወጣ የእሳቱ ሙቀት አይንካን አንልም፣ በውሃ እየሰመጠ ያለን ሰው ከውሃው ስናወጣ ውሃው አይንካን አይባልምና።

  • የስጋ ድካም ስጋ ደካማ ነው። የቱንም ያህል ብትንከባከቡት ስጋ ደካማ ነው፣ ለፀጉራችሁ በጊዜው ይሸብታል፣ ለፊታችሁ "ክሬም፣ ሰን ስክሪን" ብትጠቀሙም፣ በጊዜው መጨማደዱ አይቀርም። ዘመን ሲጨምር የቱንም ያህል እራሳችሁን ብትንከባከቡትም ታረጃላችሁ። ለጤና ተስማሚ ምግብ ብትመገቡም፣ ስጋ ከማርጀት አይመለስም፣ ብዙ ዘመን የመገባችሁት ሰውነት ጥቂት ቀን ምግብ ሲያጣ ፊታችሁ ይጠቁራል፣ አስር አመት ያለማቋረጥ በሰአቱ የመገባችሁት ሰውነት አስር ሰአት አይታገሳችሁም፣ ብዙ አመት በልቻለው ዛሬን ልታገስ አይላችሁም፣ ስጋ ውለታ ቢስ ኑው። ህፃናት ልጆቻችሁን ቀኑን ሙሉ፣ ብዙ ብታበሏቸው ወፍራምና ሞኝ ይሆናሉ፣ ጎበዞች እንዲሆኑ ብላችሁ የተመጣጠነ ምግብ ያበላችኋቸው ልጆች ጤና ያጡና፣ የወደቀ ጣሳ ማንሳት የማይችሉ ይሆናሉ። እራሳችሁን መንከባከብ ከፈለጋችሁ፣ እያረጃችሁ ስትሄዱ መለምለም ከፈለጋችሁ እየሱስ ክርስቶስን ውደዱት፣ ውበታችሁ እየጨመረ፣ ጤናችሁ እየጨመረ፣ ስኬታችሁ እየጨመረ መሄድ ትፈልጉ ይሆን? ወደ ክርስቶስ ኑ!!! እንደ ሀዋርያው ጳውሎስ፣ ጌታን ልበሱት። ጌታን የለበሱ፣ ስጋቸውን እንደ እሾህ የሚወጋ ህመም እንኳን ተሰቷቸው ደስ ይሰኙ፣ ይለመልሙ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ ፦ የዘላለም እንጀራ የሆነውን ክርስቶስን መረጠ እና፣ በድካም በረታ፣ በግርፋቱ አተረፈ፣ በሞቱ የዘላለም ህይወት አገኘ። 40 ግርፋት 5 ጊዜ ተገረፈ፣ 3 ጊዜ በበትር ተመታ፣ በድንጋይ ተወገረ፣ መርከቡ 3 ጊዜ ተሰበረ፣ በአደጋ በባህር ውስጥ አለፈ፣ ስጋው እንቅልፍ ቢያጣም፣ ወንጌሉን በመስበክ ብርቱ ነበረ፣ ሁሉን የሚገድል መርዘኛ እባብ እሱን አልገደለውም፣ ይልቅ እንደ ብናኝ ከራሱ ላይ ወደ እሳት አራገፋት። እለት እለት ስጋን የሚያደክሙትን ፈተናዎች ለማለፍና ለመበርታት የናዝሬቱ እየሱስ ክርስቶስን ብሉ።

  • በዚህ ቃል ተፅናኑ። ደካሞች እንደደከሙ አይቀሩም፣ ሀዘንተኞች እንዳዘኑ አይቀሩም፣ ፊታቸው በሃዘን ለጠቆረ እግዚአብሔር ተስፋ አለው፣ ያዘኑ ፈገግ የሚሉበት ቀን ይመጣል። ወደ እልፍኛቸው ገብተው ያለቀሱ፣ በሰው ፊት ግን በፈገግታ የዋሉ እግዚአብሔር አይቷቸዋል፣ ሀዘናቸውን ወደ ደስታ፣ ድካማቸውን ወደ ብርታት ይቀይራልና በዚህ ቃል ተፅናኑ። ግራ ለተጋቡ፣ እውነተኛ መፅናኛ እግዚአብሔር ነውና በዚህ ቃል ተፅናኑ። አሮጌው ያልፋል ሁሉን አዲስ ያደርጋልና በዚህ ቃል ተፅናኑ፣ የሰለጠነባችሁን ይሰብርላችኋልና በዚህ ቃል ተፅናኑ። ስራ ትርፍ ያላስገኘላችሁ፣ በትምህርት መሻገር ያቃታችሁ፣ ሰው ከቁም ነገር የማይጥፋችሁ፣ በምድር ሚዛን ጎደላችሁ፣ ጓደኛ የሌላችሁ፣ ቤተሰብ ችላ ያላችሁ፣ ያቆብ ሮቤልን እንዳለው "ተውት አይሙት፣ ዝም ብሎ ይኑር!" እንዳለው በቤተሰብ በዘመድ "እንዲሁ ተዉት!" ተብላችሁ የተናቃችሁ፣ ሰው እንደሚላችሁ እግዚአብሔር አይላችሁምና በዚህ ቃል ተፅናኑ። እራሱን ታምኖ የሚሰራ አምላክ የናንተን እርዳታ ሳይጠብቅ ይሰራልና በዚህ ቃል ተፅናኑ። ገብያችሁ ትንሽ ቢሆን እግዚአብሔር በረከታችሁ ነው፣ ሮጣችሁ ባይሳካላችሁ እግዚአብሔር ስኬታችሁ ነው። እግዚአብሔርን የሚያህል እረዳት አለላችሁና ሰው ምን ያደርጋችኋል። ለሰው ምንም ብትሆኑ ለአምላክ ግን በነፍስ የተገዛችሁ ውድ ናችሁ። ውድ ናችሁ!!!! የሰራችሁ የሰማይ እጅ ነው። እናንተን የሰራ ጥበበኛ ሳይሆን እራሱ ጥበብ ነው። ከሰው ፊት አትደበቁ የሚያኖራችሁ የዘላለም አምላክ ነው። ሰማይ ይፈልጋችኋል፣ ክርስቶስ ከሰማይ ዙፋኑ የመጣው ክብራችሁን ስለሚያውቅ ነው። ስትጎሉ የማይወድ ጌታ ሊፈልጋችሁ መጥቷል። መልካም ነገር ሁሉ ስለሚገባችሁ ነው ክርስቶስ በመስቀል የሞተላችሁ። በመስቀል መከራን የተቀበለው ለናንተ ነውና በዚህ ቃል ተፅናኑ።...

  • የእግዚአብሔር በአላት። የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ባርነት እንደወጣ በየመንገዱ በአል ያደርግ ነበር፣ ድንኳን የመትከል በአል፣ ድንኳን የማንሳት በአል፣ የሞሎት የኮከቦች በአል፣ የወርቅ ጥጃ በአል፣ የሞአብና ምድያም መስዋእት በአል፣ የመናፍስት መጠየቅ በአል፣ ለአማልክት መስዋእት ማቅረብ በአል፣ የልጆች መስዋእት ለሞሎክ በአል... እጅግ ብዙ በአላትን ከአህዛብ ተቀብለው ሲያከብሩ ይውሉ ነበር። እግዚአብሔር ለእርስቱ የመረጠው ህዝብ ያገኘውን ሁሉ የሚያከብር ሆነ፣ የሌሎች አማልክትን በአል ያክበራሉ። በኛ ዘመን ብዙ የአህዛብ በአል ሳይታወቀን እየወረሰን ነው፣ ገና ትምህርት ለሚጀምሩ ህፃናት በየቤቱ በአል ይደረጋል፣ በተባበሩት መንግስታት አማካይነት ብዙ የስላቅ በአላት አሉ። የውሸት ቀን፣ የትራስ ቀን፣ የሰነፍ ቀን፣ የፒዛ ቀን፣ የቸኮሎት ቀን... እኚህን የመሰሉ አስቂኝ ቀኖች ይከበራሉ፣ አላማቸውም ገብያ ነው፣ እኛም እናከብራቸዋለን። ሰማይ ሳይሆን ገብያ የሚመራውን በአል እናከብራለን። ክርስቲያን እግዚአብሔርን ያህል አፍቃሪ፣ ክርስቶስን ያህል ባለፀጋ መንፈስ ቅዱስን ያህል አፅናኝ እያለው፣ ቀኖችን በአህዛብ አምላክ አይዋጅም። ለእግዚአብሔር የምስጋና ቀን ማወጅ ትልቅ በረከት ነው፣ አህዛብ እንደሚያደርጉ በየወቅቱ ለመብላትና ለመጨፈር መነሳት እግዚአብሄራዊ አይደለም። ኢሳያስ፣ መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ። ይላል እግዚአብሔር ብሎ ተናግሯል። ኢሳ 1:14 ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ መልካም ነው፣ ለእግዚአብሔር የምስጋና ቀን ማወጅ ድንቅ ነው፣ በእግዚአብሔር በራሱ ደስ መሰኘት መባረክ ነው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የሌለበት፣ ክርስቶስ የሌለበት በአል ብክነት ነው። የስላሴን በአል ያከበራችሁ፣ ክብር አይጉደልባችሁ።

  • የኔ ምስክርነት። ፪ (እግዚአብሔር አይቷል።) የሥነ ልቦና ጉዳት እውነት መሆኑን የምመሰክር ነኝ፣ ሁሉ ቢችል በተግባር ባይችል በዘዴ የስነ ልቦና ጥቃት አድራሽ ነው። ያለፈው ህይወቴ ልክ እንዳሁኑ ሁኖ ይሰማኛል። ጌታ እንዲህ ያደረገ ይመስለኛል። ሁል ጊዜ ፊቴ የተገተረውን ትልቅ ቋጥኝ "ግፋው" የሚለኝ ልክ እንዳለኝ ያን ቋጥኝ ስገፋ ብውልም ቋጥኙ ንቅንቅ የማይል። ጌታ ያደረገው ፊቴ የተገተረውን ቋጥኝ ማንሳት አይደለም፣ እሱ ያደረገው፣ እኔን ማጠንከር ነው፣ አሁን እኔ ጠንካራ ነኝ፣ ፊቴ በተነጠፉት ብዙ ችግሮች መሃል ጌታ ብርቱ አድርጎኛል፣ በዘመኔ የሚገዳደሩኝን ሁሉ ክርስቶስ አይቷልና ብርቱ ያደርገኛል። ሰዎች ድሮ ባሳለፍኩት ችግር ዛሬም እንደ ድሮ እንደሚያዩኝ አስተውያለሁ፣ ጌታ ሰውን እንደሚለውጥ እረስተዋል። ያ የድሬ ህፃንነቴን ዛሬም በእኔ ላይ ያዩታል። በድሮ ስህተቴ ዛሬም እነሱ ልክ እንደሆኑ ያስባሉ። ሁሉ መለወጡን አውቃለሁ፣ ኢየሱስ ለውጦኛል። ክፉ መናፍስት እንዳሉ የምመሰክር ነኝ፣ ክፉ መናፍስት ሰዎችን በተለያዩ ክፉ ልማድ እንደሚጠምዱ አውቃለሁ፣ ክፉ መናፍስት ጩኾ የሚወጣው ብቻ እንዳይመስላችሁ፣ መፅሀፍ ቅዱስ ቤታችሁ እያለ ካላነበባችሁ፣ የቅዱሳን ህብረትን ከናቃችሁ፣ ሰዎች ለእግዚአብሔር ሲዘምሩ ምንም ካልተሰማችሁ የጌታን ስም ስትሰሙ ችላ ካላችሁ ክፉ መናፍስትን ጠርጥርሩ። ሰዎች ሁሉ ከዚህ እንዲጠበቁ እመሰክራለሁ። ለእየሱስ ስሜት አትጡ። ሐዘንና ጥፋት እውነት መሆናቸውን እመሰክራለሁ፣ ነገር ግን ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ኃያሉ ኢየሱስ እንዳለም እመሰክራለሁ፣ "ይሄ ሀዘን" ካልኩበት በርትቻለሁ። "የጥፋት መጨረሻ" ካልኩበት ተስፋን ተሞልቼ አይቻለሁ። ፈገግታዬን የቀማ "በዛው ቀርቷል" ስል ጌታዬ አፌን በሳቅ ሞልቶኝ አይቻለሁ። ይሄን ያደረገ እግዚአብሔር እንደሆነ የምመሰክር ነኝ።...

  • በርጤሜዎስ እና የሰፈራችን ለማኝ። እንዲህ ያለ ነገር በየሰፈራችሁ ሰምታችሁ ይሆናል፣ እኛ ከመወለዳችን በፊት በልመና የሚተዳደሩ፣ አስፋልት ዳር የላስኪት ቤት ሰርተው ይኖራሉ፣ እዛው ይለምናሉ፣ እዛው ይኖራሉ። ልጆች ሆነን ወደ ትምህርት ቤት ስንሄድ እናያቸዋለን፣ እኚህን የኔ ብጤ ሰላም እንላቸዋለን እሳቸውም "ልጆቼ" ይሉናል። አንድ ቀን ግን የሆነ ነገር ተከሰተ። በጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስንሄድ ፖሊስና ህዝቡ የአባባን የላስቲክ ቤት ከቦ ቆሟል፣ ስንጠጋ ለካ አባባ ሞተው ተገኝተው ነው። ማታ ሞተው አደሩ። እሬሳቸውን አምፑላንስ መጥቶ ወሰደው። በኋላ አስገራሚ ነገር አየን፣ የአባባን ቤት የሞላው ቡትቶ ወጥቶ ወጥቶ ወጥቶ አላልቅ አለ። የሚያስገርመው ከዛች ደሳሳ ጎጆ ዘመናቸውን ሙሉ የለመኑት ሳንቲም ከብዛቱ የተነሳ በማዳበሪያ ታፈሰ። ለቁጥር የሚያታክት አሮጌ ብሮች ታፍሶ ወጣ፣ በኋላ እንደሰማነው ብሩ ሲቆጠር ብዙ ሺ ሁኖ ነበር፣ አባባ ህይወታቸውን የሚቀይር ብር የነበራቸው ቢሆንም ከቡትቶዋቸው ጋር ኖረው ሞቱ። በርጤሜዎስ እንደዚህ ያለ ሰው ነበር፣ በርጤሜዎስ ጌታን ባያገኝ ኖሮ፣ ከኮተቱ አይገላገልም ነበር። እሱ ግን እንደፈራችን ለማኝ አልነበረም፣ ጌታን እንዳየ "እባክህ እራራልኝ" ብሎ ጮኸ፣ ጌታም ራራለት። የእየሱስ ኮቴ ሲሰማ አብዝቶ ተጣራ፣ እስከ ዛሬ የሰበሰብኩትን ሳይል ኮተቱን ጥሎ ወደ ጌታ ገሰገሰ፣ አይኑ በራለት፣ ጌታን ተከተለ። በዚህ ዘመን የሚያዋጣን ላይጠቅመን የሰበሰብነውን ቡትቶ መጣል ነው። የማይጠቅም ነገር ተሸክሞ የሚጠቅመንን ኢየሱስን መጣል አይበጀነም። ጌታን መከተል የማይጠቅም ቡትቶ ያስጥላል፣ እርሱን ለመከተል ስንነሳ የተቀመጥንበት ብዙ ኮተት ይራገፋል። ከጌታ ጋር ስንሆን ነው ያለንን በደስታ ልንጠቀም የምንችለው። ጌታ ከሌለ የማንጠቀምበት ቡትቶ ውስጥ ነን።

  • 8 июл.347165

    የኔ ምስክርነት። እግዚአብሔር አይቷል። ኪሳራዎች ተከታትለው ቢመጡ፣ የምንወዳቸው ሰዎች ሁል ጊዜ ከጎኔ ይሆናሉ ያልኳቸው ባይታመኑ፣ ያመኑትን ማጣት ከራስ አካል የተቆረጠ ያህል ስሜት ሲሰማኝ እግዚአብሔር አይቷል። ሀዘን በሃዘን ላይ፣ ስቃይ በስቃይ ላይ ቢደራረብ፣ መንፈሳዊ አካላዊና አእምሮአዊ ጦርነት ውስጥ እራሴን ሳገኝ እግዚአብሔር አይቷል። እግዚአብሔር ማንንም ለዘላለም አይተውም፣ እያንዳንዷን ግፍ አይቷል። እርሱ በእኔ ላይ የተፈጸመውን እያንዳንዱን ግፍ አይቷል። እያንዳንዱን ቁስል አይቷል። እያንዳንዷ እንባ አይቷል። "ብቻዬን ነኝ!" ብዬ የተሰማኝን እያንዳንዷን ቅጽበት አይቷል። እግዚአብሔር አይቷል። እግዚአብሔር የተሸከመኝ ሰው ነኝ። የተረፍሁት ጠንካራ ስለነበርሁ አይደለም፤ እግዚአብሔር ስለተሸከመኝ ነው። ጠላት መቃብር ሊያደርግልኝ ያሰበውን ስፍራ እግዚአብሔር የምስክርነት መድረክ ያደርገዋል። ጠላት በኀፍረት ሲያራቁተኝ እግዚአብሔር ግን የክብር ልብስ አድርጎልኛል። እሱ በሃጥያት እርቃን ቢያስቀረኝም፣ እግዚአብሔር የቆዳ ልብስ አልብሶኛል፣ ያውም ውብ የፀጋ ልብስ አልብሶኛል። እግዚአብሔር አይቷልና በግድ የተጫነብኝን ዝምታ አስወግዶ፣ በኃይል የሚናገር ድምፅ ሰጠኝ፣ ተመስገን የማለት ድምፅ ሰጠኝ። እግዚአብሔር በእሳቱ ውስጥ አብሮኝ እንደተጓዘ አውቃለው፣ ስለዚህ እሳት ውስጥ ሁኜ እመሰክርለታለሁ። እግዚአብሔር እያየ ነው እላለሁ። የእኔ ምስክርነት "ፈጽሞ ወድቄ አላውቅም!" የሚል አይደለም፤ በወደቅሁ ቁጥር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳነሳኝ እናገራለሁ። የእኔ ምስክርነት "ፈጽሞ አላጣሁም" አይደለም፤ ጠላት ሊሰርቀኝ የሞከረውን እግዚአብሔር አብዝቶ እንደመለሰልኝ እናገራለሁ። እኔ ሁል ጊዜ ከሞት የተረፍሁ ሰው ነኝ፤ እኔ ይሄን የምመሰክር ህያው የእግዚአብሔር ምስክር ነኝ። .... እቀጥላለሁ

  • 6 июл.570132

    አንተ ይህን ለእኔ አደረግህ። በአሜሪካ የአሪዞና ግዛት፣ የሚገኝ ውብ ቦታ፣ ድንጋዮችና በዛፎች መካከል ወደ ተራራው የሚወጣ መንገድ አለ፣ ጌታ ኢየሱስ ወደ መስቀል እየሄደ ካለፈባቸው መንገዶች አሥራ ሁለቱን ደረጃዎች የሚያሳዩ ቅርጻ ቅርጾች ተቀምጠዋል። ይህን ቦታ ከማየቴ ከሁለት ዓመት በፊት ስለቦታው ሕልም አይቼ ነበር። በኋላ በእውነት ሳየው ወዲያውኑ አወቅሁት፣ ያሳየኝ መንፈስ ቅዱስ ነበር። ከዚያ ቦታ ጥቂት ርቀት ላይ ቤት አገኘሁ፣ ከዚያ በኋላ ወደዛ ስፍራ መሄዴን አላቋረጥኩም። ቦታው ጥገና ያስፈልገው ነበር። እየሱስ የተጓዘባቸው መታሰሚያዎች አጥሩ በመውደቅ ላይ ነበር። በዛ ያገኘሁት አረጋዊው የወደቁትን በመጠገን እንድረዳው ጠየቀኝ። አጥሮቹ ከባድ የባቡር ሃዲድ እንጨቶች ሲሆኑ በተለያየ ርዝመት ተቆርጠው የተሰሩ ነበሩ። ለመርዳት ተስማማሁ፤ ጠንካራ ወንድ ጓደኞቼ ያግዙኛል ብዬ በማሰብ። ነገር ግን ማንም አልመጣም። ቃሌን ማፍረስ ስላልፈለግሁ፣ ራሴ ልሠራው ጀመርሁ። መጀመሪያ አጫጭር እንጨቶቹን ወደ ተራራው ወጥቼ አንድ በአንድ አውርጄ ወደ ታች አመጣኋቸው። ከዚያ ግን ረጅጅሞቹና እጅግ ከባዶቹ ቀሩ። ከእነርሱ አንዱን በትከሻዬ ተሸክሜ ተራራውን መውረድ ጀመርሁ። እንጨቱ ከኋላዬ ባለው ደረጃ ተጣብቆ መሬት ላይ ጣለኝ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ደጋግሞ ጣለኝ። ያኔም፣ “እንዴት ያለችው ሞኟ ነኝ እንዴት ልሰራው ተስማማሁ?” አልኩ። ጀርባዬ ይታመም ነበር፣ በጣምም ህመም ውስጥ ነበርሁ። በዚያን ጊዜ ግን እየጸለየ የሚያሳየው የጌታ ኢየሱስ ሐውልት ዓይኔን ሳበው። በዚያ ቅጽበት እንዲህ ብዬ አሰብሁ፦ “አንተ ይህን ሁሉ ለእኔ አድርገሃል። አንተ ይሄን ተራራ ወደ ላይ ወጣኸው፣ እኔ ወደታች መጎተት አቃተኝ።" ያን ጊዜ በልባዊ አመስጋኝነት ሥራዬን ቀጠልሁ። ይሄ የረቤካ እውነተኛ ምስክርነት ነው።

  • አለማዊ ድግስ ፪ ለሁሉ የሚሆን የምስራች ኢየሱስ ወቅቱ የአለም ዋንጫ የሚካሄድበት ነው፣ በቤታችን የተለያየ ቡድን እንደግፋለን። አንዱ ሲደሰት አንዱ ያዝናል። አንዱ የምደግፈው ቡድን ስለማይጫወት "አላይም" ብሎ ይተኛል። የሚደግፈው ቡድን ያሸነፈለት በደስታ ይቦርቃል፣ የተሸነፈበት ይበሳጫል የተኙትን ይረብሻል። ጉዳዩ እግር ኳስ ነውና አንቀያየምም። ሀገራቸው የተሸነፈባቸው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ በቴሌቭዥን መስኮት አይተናል፣ አሸናፊ ሀገሮችም በደስታ ሲቃ ያነባሉ አይተናል፣ እግር ኳስ ነውና አንዱ ሊያዝን አንዱ ይደሰታል። አሸናፊዎች ከደስታቸው መለስ ሲሉ በሃዘን ልባቸው የተሰበረውን ያፅናናሉ። እግር ኳስ ነው፣ አቻነት የለም፣ ወይ መሸነፍ ወይ ማሸነፍ ብቻ ነው። ለሁሉ ደስታን የማይሰጥ ስፖርት ነው። በዚህ የአለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉት ሀገራት 48 ቢሆኑም ይሄን ውድድር አሸንፎ የሚደሰተው አንድ ቡድን ብቻ ነው። ቀሪዎቹ 47 ቡድኖች በየተራ እያዘኑ ይሰናበታሉ። በዚህ ምድር ለሁሉ የምስራች የሆነ ዜና የለም። የአንዱ ደስታ የአንዱ ሀዘን ነው። የአንዱ የምስራች የአንዱ መርዶ ነው። ለአንዱ ድል ለአንዱ ሽንፈት ነው። በዚህ ምድር ለሁሉ የምስራች የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ከሰማይ የመጣ የምስራች፣ ለእረኞች የተነገረ ታላቅ የምስራች የመልአኩ ቃል "ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ" ያለለት ኢየሱስ ነው። ሉቃ 2:10 በዚህ ምድር ለሁሉ የሚሆን የምስራች አንድ ብቻ ነው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁሉ እድሜ፣ ለሁሉ እውቀት ሁሉን ደስ የሚያሰኝ የምስራች ነው። ለአንድ ቦታ ብቻ ለዚህ ስፍራ የማይባል፣ ለሁሉ ድንቅ የምስራች ኢየሱስ ነው። ስለ ኢየሱስ መስማት ለሁሉ ታላቅ የምስራች ነው። ከቶም ሀዘን የለበትም። የሁሉ ፈገግታ ኢየሱስ።....

  • 2 июл.388155

    ኢየሱስን የት አቆማችሁት?? ደጋግሞ ቢያንኳኳም ወደ በሩ የመጣ የለም። ከውስጥ የአምልኮ ድምፅ ይሰማል፣ ፀሎቱና ዝማሬው ልዩ ነው፣ ከበር ቆሞ የሚያንኳኳውን ግን የሚሰማው የለም። እራሱ ከፍቶ እንዳይገባ ከውጭ በኩል መክፈቻ የለውም። ተስፋ ቆርጦ ወደ ኋላ አፈገፈገ። አይኖቹ የሚያበሩ፣ የልብሶቹ ንጣት በቃላት የማይገለፅ፣ ፈገግታው አካባቢውን ሁሉ ወገግ የሚያደርግ ሰው ከበሩ ጥግ ቆሟል። "ምን እያደረክ ነው ልጄ?" አለኝ፣ "ወደ ውስጥ ገብቼ አብሬያቸው መሆን ፈልጌ ነበር፣ ግን አልከፈቱልኝም" አልኩት። "እኔም ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከበር ቆሜ እያንኳኳሁ ነው፣ ማንም አልከፈተልኝም" አለኝ። ማን እንደሆነ በንግግሩ ለየሁት። "ጌታ ሆይ ወደዚህ ቤት መግባት የፈለኩት አንተን ፈልጌ ነው፣ አንተም በደጅ ቆመሃል" አልኩት። ተንደርድሬ በእቅፉ ውስጥ ገባሁ፣ የምፈልገው ይሄን ነበር። በዘመናችን ያለ ክርስትና ጌታን በደጅ የተወ ይመስላል፣ ሁላችን በውስጥ ነን፣ ጌታ ግን በደጅ። ብዙ ስርአቶች እንፈፅማለን እርሱ ሳይኖር ያገኘነው ይመስለናል፣ እንስታለን። ጌታ እየሱስ እነማን ቤት እያኳኳ ይሆን?? እኛ ሁላችንም የራሳችንን አማልክት በየቤታችን ሰርተናል። እስራኤል በበረሃ እንደሳተ፣ እኛም እምነታችንን አቅልጠን ጥጃችንን ሰርተናል፣ "አምላካችን ይሄ ነው" እያልን በየቤታችን በዐል አድርገናል። በክርስቶስ ላይ ዘግቶ ክርስቶስን መፈለግ ሞኝነት ነው!! ለክርስቶስ የተዘጋ ልብ ክፍት አይደለም። የክርስቶስን ድምፅ የማያውቅ እንዴት መጣራት ቻለ? በዚህ ዘመን ክርስቶስ በልባችን ደጅ ቆሞ ሲያንኳኳ አየዋለሁ፣ በምንኖርበት ቤት ከበራፋችን ቆሞ ይታየኛል፣ ልናመልከው በቆምንበትም ቤተ መቅደስ ከደጅ ቆሞ ሲያንኳኳ በምናቤ አየዋለሁ፣ እርሱ ላይ ዘግተን እርሱን እንፈልጋለን፣ ማስተዋል ይሁንልን።....

  • የሰሊጥ አገልግሎት (የበደሉንን ይቅር እንደምንል) በወንድማማችነት ይኖሩ የነበሩት ህዝቦች በብሄር ተከፋፍለው ተገዳደሉ፣ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ያመልኩ የነበሩ ተገዳደሉ በህይወት ያሉትም ለመገዳደል ይፈላለጋሉ። ከዝች ከተማ ስልክ ተደወለልኝ "በጣም አዝነንባችኋል፣ በደጉ ዘመን ብዙ የነበራችሁት አገልጋዮች ዛሬ የላችሁም። ሰሊጥ በነበረን ጊዜ ህዝባችን ታገለግሉ የነበራችሁ፣ ዛሬ ሰሊጣችንን በጦርነት ስናጣ ቀራችሁ፣ እኛን ሳይሆን ሰሊጡን ነበር የምትፈልጉት" አለኝ፣ "ይኸው ብዙ አመት ሆነን አገልጋይ አጥተን" አለኝ። በደጉ ዘመን ህዝቡ ለአገልጋይ የፍቅር ስጦታ እያለ ብዙ የሚሰጥ ህዝብ ነበር። ዛሬ ሰው የሚሆናቸው አጡ። በደዋዩ ሰው መልእክት ልቤ ተነካ "እውነትህን ነው፣ በቃ እንመጣለን ጠብቁን" አልኩት ቦታው ምናልባት አደገኛ ሊሆን ይችላል፣ ቢሆንም ከጓደኛዬ ጋር ለመሄድ ቆረጥን። ህዝቡ ቤተ ክርስቲያኗን ሞልቶ ጠበቀን። ፕሮግራሙ ሲጀመር ህዝቡ ፊት ተንበረከክን "ይቅርታ አድርጉልን፣ እኛ የሰበክነው የሰላም ወንጌል ፍሬ ስላላፈራ፣ እኛ የሰበክነው ወንጌል መጋደልን ስላላቆመ። በችግራችሁ ጊዜ ምን ሆናችሁ? ብለን ስላልመጣን ይቅር በሉ" ብለን አለቀስን፣ ምእመኑም አብሮን አለቀሰ። ይቅርታ አደረጉልን። አንዲት ሴት እያለቀሰች፣ ወደ አንድ ሰው ጠቆመችኝ "እሱ ነው አባቴን የገደለው፣ ግን ይቅር እለዋለሁ" ብላ ወደ ስውዬው አቀናች "በዚህ ምድር አባቴን ነጥቀኸኛል፣ አሁን ደሞ እየሱስን እንድትነጥቀኝ አልፈልግም" ብላ ይቅር አለችው። በይቅርታ አለቀስን። ወደ ገዳዩ ቀርበን ፀለይን ስንፀልይ አጋንንት ከሰውዬው ላይ አጓርቶ ወጣ። ለካ ገዳዩ ሰው አይደለም። የዚህ ታሪክ መስካሪ የወንጌል አገልጋዩ ሁሴን መሃመድ ነው። በዚህ ዘመን ሰው ከአውሬ በላይ እየፈራን ነው። ሰው መንፈስ ቅዱስ ሲርቀው አውሬ ይሆናል።

  • አለማዊ ድግስ!!! ጊዜው የአለም ዋንጫ ወቅት ነው፣ ቢሆንም ስቴድየም ገብቶ ለመመልከት እጅግ ውድ ሁኗል። በዚህ ጊዜ ድሃ ሃገራት ኳስን ማየትና መጫወት የማይችሉበት ዘመን ላይ ደርሰናል። እንደ ጥንቱ ዘመን እግር ኳስ በነፃ የሚከናወን ስፖርት መሆኑ ቀርቷል። መንግስት እንኳን የሰፈር ሜዳዎችን እያጠረ በሰአት እያስከፈለ ህፃናትን በገንዘብ ያጫውታል። ዘማች በንኪ የሚባል tik tok ላይ አጫጭር ግሩም መልእክት የሚያስተላልፍ ሰው እንዲህ አለ። "እኔ የምኖረው በአሜሪካ ነው፣ የአለም ዋንጫ እየተከናወነ ቢሆንም እያየሁ አይደለም፣ እኔ እዚህ የምሰራው ኳስ የሚያዩትን ዜጎችና እንግዶች ከኤርፖርት ወደ ሆቴል፣ ከሆቴል ወደ ስታዲየም በሹፍርና ማመላለስ ነው። እዚህ ያለ ድያስፖራ ሁሉ ስራው ይሄ ነው፣ በሹፍርና ተመልካቾችን እናመላልሳለን እንጂ ኳሱን አንመለከትም" ይላል። "እዚህ መኖራችን ከትኩረታችን ዞር አያደርገንም፣ ሁላችንም የምናስበው አንድ ቀን ጥሪት ይዘን ወደ ሀገራችን መግባት ነው፣ አለም በምታዘጋጀው ድግስ ሁሉ ትኬት የምቆርጥ ከሆነ ሀገራችን መግቢያ ቤሳቤስቲ አይኖረንም። ውድ የሆነውን የአለም ዋንጫ መግቢያ ከፍለን የምገባ ከሆነ መቼም ቢሆን ሃገራችን አንገባም" በማለት መልእክቱን ያስተላልፋል። ክርስቲያን እንደዚህ ነው። ሀገር አለን የምንጠብቃት፣ የምንናፍቃት፣ እዚህ ባለው ነገር ላይ ጉልበትም ሃብትም አናባክንም። በዚህ በምፃተኝነት በምንኖርበት ምድር ሰዎች ወደ ገቡበት ሁሉ አንገባም፣ ሰዎች ወደ ገቡበት ሁሉ ብንገባ ከሀገራችን እንቀራለን። በዚህ ምድር ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመለከቱ እንጠቁማለን፣ እንጂ አለም ደግሳ ውድ በምታስከፍለው ድግስ አንታደምም። ምድር በምታዘጋጀው ወጥመድ እንዳንታለል ሃሳቧን አንስተውም። ድግሷን ብቻ እያሰብን ሀገራችንን እንዳንረሳ ማስተዋል ይሁንልን።

  • ሰማያዊ መንግሥት ፫ ኢየሱስ መንግስቱ ከዚህ ምድር አይደለምና ተራበ፣ ተጠማ፣ ታረዘ፣ ተጎሳቆለ። ሰማይ ምድር የእርሱ ቢሆንም ምንም እንደሌለው ብቸኛ ሆነ። እልፍ አእላፍ መላእክት የሚሰግዱለት ቢሆንም ምንም እንደሌለው የህማም ሰው ሆነ። መንግስቱ ከዚህ ምድር አይደለችምና ምድርን በመዳፉ የያዘ ጌታ እጁ ሲጎተት ዝም አለ። ሁሉ በእርሱ ተጋጥሞ ሳለ ሁሉ ፊቱን ሲያዞርበት ዝም አለ። መንግስቱ ከዚህ አይደለምና የሚወዳቸው ከአጠገቡ ሲወሰዱ ዝም አለ፣ መጥምቁ ዮሃንስ እንገቱ ሲቀላ ዝም ብሎ አየ፣ እሱን የሚከተሉት አሳዳጅ ሲበዛባቸው ዝም አለ። መንግስቱ ከዚህ ምድር አይደለችምና የመረጣቸው ሃዋርያት በአደባባይ ሲሰቀሉ፣ በድንጋይ ሲወገሩ፣ ከቤተ መቅደስ ጫፍ ተወርውረው ሲፈጠፈጡ፣ በዘይት ሲቀቀሉ፣ በመጋዝ ሲሰነጠቁ ዝም አለ። ዛሬም በዘመኔ እንዲሁ ነው፣ ግፉአን ድሆችን ሲጠሉ፣ ከሚኖሩበት ስፍራ ሲያፈናቅሉ፣ ቤተ መቅደስ አፍርሰው ቤተ መንግስት ሲሰሩ ኢየሱስ ዝም ይላል፣ ሃይሉ ብዙ ቢሆንም ስለ ፍቅሩ ይታገሳል። በመንግስቱ እስኪመጣ ድረስ መንግስታትን ይታገሳል። ቅዱሳንን ሲያስጨንቁ ይታገሳል። እግዚአብሔር ሰውን እጅግ ይወዳል። ሰው ሲወድቅ ሰውን ለማዳን ሰው ሁኖ መጣ፣ ዛሬ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ሰው ነው። ሰውን መጉዳት የእግዚአብሔርን መጉዳት ነው። ሰውን መግደል መቅደስ ማፍረስ ነው። ኢየሱስ የሞተለት ሰው ሲነካ፣ ገበሬ መንገድ ሲያጣ፣ አዛውንቶች ማረፊያ ሲያጡ፣ ሴቶች በፍርሃት ሲዋጡ ፣ ወንዶች መራመጃ ሲያጡ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝም የሚለው መንግስቱ ከዚህ ስላልሆነ ነው። የነገስታት ንጉስ በቅርቡ ሃይሉን ያሳያል የዛን ጊዜ የምድር ሃያላን ዋይ ዋይ ይላሉ። የዛኔ ክፉ ጉልበተኞች ተራሮችን ደብቁን ይላሉ፣ ተራሮችን ግን ይቀልጡባቸዋል። ኢየሱስ በቅርቡ ያመኑትን ሊያስጥል ይመጣል።

ሰማያዊ ወግ (The tradition of heaven) — tgindex