tgindex
ALPHA
@hukii2Новости и СМИанглийский

Welcome ALPHA, the exclusive affirmation channel where we journey together towards growth, inspiration, and positivity💚

Последний пост
27 мая
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ангНиКскиК
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
603
−2 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,17%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
411
20 постов
Вовлечённость
68,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ብዙ ሰዎች ብድርን እንደ እዳ እና እንደ ስጋት ያዩታል። ይሁን እንጂ በዓለማችን ላይ ያሉ ትልልቅ ባለሀብቶች እና ቢሊየነሮች አንድን ንብረት ለመግዛት ሙሉ ገንዘብ በእጃቸው እያለ እንኳ ብድርን መምረጥ ይመርጣሉ። ለምን? ምክንያቱ "ጥሩ ብድር" (Good Debt) ሀብትን በፍጥነት ለማሳደግ የሚረዳ ትልቅ መሳሪያ ስለሆነ ነው። ባለሀብቶች ብድርን የሚመርጡባቸው 4 ዋና ዋና ምክንያቶች፦ 1. የሌላውን ሰው ገንዘብ መጠቀም (OPM - Other People's Money) ሀብታሞች የራሳቸውን ካፒታል በአንድ ቦታ ማሰር አይፈልጉም። ለምሳሌ 10 ሚሊዮን ብር ያለው ሰው አንድን መኪና ወይም ቤት በጥሬ ገንዘብ ከመግዛት ይልቅ፣ ያንን 10 ሚሊዮን ብር ለ5 የተለያዩ ንብረቶች ቅድመ ክፍያ (Down payment) በመጠቀም በብድር አምስት ንብረት ማፍራት ይችላል። ይህ "Leverage" ይባላል። በራሳቸው ገንዘብ ብቻ ከሚገዙት በላይ በብድር አማካኝነት አምስት እጥፍ ሀብት ያፈራሉ ማለት ነው። 2. የገንዘብን የመግዛት አቅም መጠበቅ (Arbitrage) አንድ ባለሀብት በእጁ ያለውን ገንዘብ 20% ወይም 25% ትርፍ በሚያስገኝ ንግድ ላይ ያውለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከመደበኛ የፋይናንስ ተቋም በዝቅተኛ ወለድ ይበደራል። ከንግዱ የሚያገኘው ትርፍ ለብድሩ ከሚከፍለው ወለድ የሚበልጥ ከሆነ፣ ባለሀብቱ የሌላውን አካል ገንዘብ ተጠቅሞ ያለምንም ወጪ ትርፍ እያገኘ ነው ማለት ነው። 3. ታክስ እና የፋይናንስ ስልት በብዙ ሀገራት የንግድ ብድር ወለድ ከታክስ የሚቀነስ ወጪ ነው። ይህ ማለት ብድር በመጠቀም የሚገዛ ንብረት የታክስ ጫናን ለመቀነስ ይረዳል። በተጨማሪም በእጅ ያለን ጥሬ ገንዘብ ለድንገተኛ አደጋዎች እና ለአዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎች "Liquid" (ዝግጁ) አድርጎ ለማቆየት ብድር ተመራጭ ነው። 4. የዋጋ ንረትን (Inflation) ለጥቅም ማዋል ባለሀብቶች የዋጋ ንረትን ይወዳሉ። ዛሬ የተበደሩት 1 ሚሊዮን ብር ከ10 ዓመት በኋላ ያለው የመግዛት አቅም ዝቅተኛ ነው። ነገር ግን በዛሬው 1 ሚሊዮን ብር የገዙት ንብረት (ለምሳሌ መኪና ወይም ቤት) ዋጋው በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። ይህ ማለት ባለሀብቱ ብድሩን የሚከፍለው ዋጋው በቀነሰ ገንዘብ ሲሆን፣ የያዘው ንብረት ግን ዋጋው የናረ ይሆናል።

  • йоС пОдписи

  • የነገው ጉጉት! አንድ ሰው እንደዚህ አለ፣ “የእኔ ጉጉት በወደፊቱ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የቀረውን ዘመኔን የማሳልፈው አዚያ ስለሆነ”፡፡ በትናንትናው ሕይወት ከመኖር ይልቅ ካሳለፍነው ነገር ተምሮ ማለፍ የተሻለ ነው፡፡ ከትናንቱ ከመማር ይልቅ በዚያ ላይ መኖር ኋላ ቀር ያደርጋል፡፡ በዛሬው ሕይወት ከመማረር ይልቅ በደስተኛነት መኖር የተመረጠ ነው፡፡ በዛሬ ሕይወት ደስተኛ ከመሆን ይልቅ ማማረር ተስፋ ቢስ ያደርጋል፡፡ በነገው ላይ መጓጓት ማለት ራእይንና ሕልምን መለየት፣ ወደዚያ የሚወስደንን እቅድ ማውጣት፣ ሁሉንም ነገር ከዓላማ አንጻር በመቃኘት መኖርና በየቀኑ ወደዚያ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ማለት ማለት፡፡ ከትናንት ተማሩና እደጉ!!! ዛሬን በመኖር ተደሰቱ! በእቅድና በታላቅ ጉጉት ደግሞ ወደ ነገው ተንቀሳቀሱ።

  • አንዲት ልጅ ትዳር ፍቺ ለምን በዛ ሰትል ወንድ አያቷን ጠየቀች?... ወንድ አያቷ ጥያቄዋን ከሰሙ በኋላ ሂጂና ያንቺን እና የናትሽን ቀሚስ 👗 አምጪው በማለት አዘዟት... ልጅቷም የራሷን እና የናቷን ቀሚስ 👗 ይዛ በመምጣት ለአያቷ ሰጠቻቸው ይን ጊዜ አያቷ ቀሚሶቹን ከፍ በማድረግ ምን ይታይሻል ሲሉ ጠየቋት?.. ልጅቷም ሁለት አጭር እና ረጅም ቀሚስ ነው የሚታየኝ ስትል ለአያቷ መለሰች... አያቷም፦ የናትሽ ቀሚስ እንደምትመለከችው ረዥም ነው ትዳሯም ረዝሞ አንቺን ወልዳ አሳድጋለች... ያንቺን ቀሚስ ተመልከቺ አጭር ነው! እንዴት አጭር መልበስ ጀመርኩ ብለሽ እራስሽን ጠይቀሽ ታውቂያለሽ?.. ልጅቷም የሰው ልጅ ባለባበሱ አይመዘንም ዋናው ውስጡ ንፁ ከሆነ ምን ችግር አለው ስትል አያቷት መሞገት ጀመረች... አያቷም የሰው ልጅ የአስተሳሰቡን ነው የሚኖረው ንፁ ምግብ በፖፖ ባቀርብልሽ ትመገቢያለሽ? አትመገቢም ስለዚህ ክብርሽን ጠብቂ ልጄ... ፅጌሬዳን አበባን ተመልከቺ ውብ ናት ግን ክብሯን መጠበቂያ እሾህ አላት ማንም በቀላሉ አይቀጥፋትም... አንቺ ክብርሽን ጠብቀሽ አበባ ከሆንሽ ንቡ ይመጣል ክብርሽን ካልጠበቅሽ ዝንቡ ያርፍብሻል... አስተሳሰብ ድርጊትን ይፈጥራል ድርጊት ማንነትን ይፈጥራል! አስተሳሰብሽን፣ ውሎሽን አስተካክይ የሴት ልጅ ውበቷ ክብሯ ነው‼️

  • የጠበቅነውና የሆነው ነገር ሊለያይ! በአንድ ነገር ላይ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ስሜታችንንና አንዳንዴም ገንዘባችንን አውጥተን፣ ሰርተንና ገንብተን የጠበቅነው ውጤት ሌላ ያገኘነው ውጤት ግን ሌላ ሲሆን ግር መሰኘታችን አይቀርም፡፡ ሆኖም፣ አንድን ነገር ጠብቀን የምንፈልገውና የምንጠባበቀው ውጤት ሳይሆን ሲቀር ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሸ ወሳኝ ነው፡፡ ለማንኛውም ማየት የሚገቡን ሁኔታዎች . . . 1.  ምናልባት የተሳሰተና መጀመር የሌለብንን ነገር ጀምረን ይሆናል 2.  ምናልባት ትክክለኛውን ነገር ጀምረን የተጠቀምነው ስልት ግን የተሳሳተ ይሆናል 3.  ምናልባት የተጀመረው ነገርም ሆነ የተጠቀምንበት ስልት ትክክለኛው ሆነው ሳለ የተጠባበቅነው ውጤት እውነታውን ያላገናዘበ ይሆናል ሁኔታውን በእነዚህ ሶስት ሃሳቦች ከመዘናችሁ በኋላ መቆም ያለበትን ነገር ማቆም፣ መቀየር ያለበትን ስልት መቀየር ወይም ደግሞ ውጤትንና እውነታን በማገናዘብ የአመለካከት ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

  • ትዕግስት ማለት ዝም ብሎ መጠበቅ አይደለም! ተመስገን ዛሬ ቀኑ በጣም ደስ ይላል! ☀️🙏 ብዙዎቻችን ትዕግስት ሲባል "እጃችንን አጣጥፈን እድል እስኪመጣ መጠበቅ" ይመስለናል። እውነታው ግን ተቃራኒ ነው። በትክክለኛው የቢዝነስ ቋንቋ፦ "ትዕግስት ማለት ውጤቱ እስኪመጣ ድረስ ባለህ በጎ አመለካከት ጠንክረህ መስራትህን መቀጠል መቻልህ ነው።" ዛሬ የዘራኸው ዘር ነገ ዛፍ አይሆንም፤ ዛሬ የጀመርከው ቢዝነስ ነገ ሚሊየነር አያደርግህም። ተፈጥሮ እንኳ ለአንድ ህፃን መወለድ 9 ወር ትጠብቃለች። ታዲያ አንተ ለትልቅ ህልምህ ጥቂት ወራትን ለመታገስ ለምን ትቸኩላለህ? * ችግኝ ሲተከል መሬት ውስጥ ሾር መስደድ አለበት (ይህ ዝግጅትህ ነው)። * ከላይ ቅጠል ባይታይም ከስር ግን ሾል እየተሰራ ነው (ይህ ልምምድህ ነው)። አስታውስ፦ በችኮላ የፈረሰ ቤት እንጂ የቆመ ህንፃ የለም። ዛሬ ላይ የምታደርገው ጥረት ፍሬው ባይታይህ እንኳ ተስፋ አትቁረጥ። ሾር እየሰደድክ ነው! የዛሬ መልዕክቴ፦በትልቅ ትዕግስት እና በማይሰለች ጥረት ስራህን ቀጥል። ጊዜው ሲደርስ ማንም ሊያቆመው የማይችል ስኬት ታጭዳለህ! dagi_abundant #DagmawiGirma

  • ❌ስማቹን ሳትፅፉ ሰው ቢያውቅልኝ ይሄን ቢሰሙ እኮ የምትሉት ያሳለፋቹት ❤️‍🔥የፍቅር 💪🏽የጀግንነት 🫣አስፈሪ 😢አስለቃሽ 🫨Wired የሆነ 🤣አስቂኝ 🫢አሳፋሪ 😱አስደንጋጭ ታሪኮች ካላቹ እና ታሪካቹ በቲክቶክ ድህረ ገፅ እንዲነበብ እና የ ህዝቡን ሪያክሽን ❤️‍🔥💪🏽🫣😢🤣🫢🫨😱ማየት ምትፈልጉ ካላቹ @Scaredstory1 ላይ ፃፉልን

  • ገንዘብህ ሕይወትህ ነው በጥበብ ተጠቀመው! የገንዘብ_አጠቃቀም ጥበብ መጽሐፍ THE ART OF SPENDING MONEY 1️⃣ጋሻህ_ነው_ጠብቀው! አንድ ተዋጊ፣ ከጠላት የሚወረወርበትን ቀስት በጋሻው እንደሚመክተው ሁሉ፤ አንተም ከሕይወት የሚወረወርብህን ብዙውን ቀስት የምትመክተው በገንዘብህ ነው። ስለዚህ ይህ መከታህን ድሃ ከሆንክ በቅራቅንቦ፣ ሀብታም ከሆንክም በእዩልኝ ፌሽታ አታባክነው። ጋሻውን የጣለ ወታደር በብዙ ቀስቶች ተወግቶ እንደሚሞተው፣ አንተም ገንዘብህን ስታጣ ትሞታለህና ያለ ምህረት ጠብቀው። 2️⃣ጌጥህ_ነው_ያዘው! አበው 'ሰው መልክ የለውም፣ የሚመስለው ኑሮውን ነው' ይላሉ። የኑሮ ከፍታና ዝቅታ መለኪያው ደግሞ ገንዘብ ነው። ገንዘብህ ለብሰህ የምትደምቅበት፣ በልተህ የምታበራበት ጌጥህ ነውና በግምት አትበትነው። ሰርተህ ለመክበር፣ ለብሰህ ለመድመቅ እንጂ ለመጠውለግ አታውለው። 3️⃣መክበሪያህ_ነው_ተጠቀመው! ገንዘብ የሚሰራው በገንዘብ ነው። ሐሳብ ይዘህ፣ ገንዘብ ቢያጥርህ ትንገላታለህ። ገንዘብ ይዘህ ሐሳብ ብታጣ ግን በቀላሉ በገንዘብህ ትገዛለህ።  ይህን መክበሪያህን ሰርተህ ክበርበት፣ ከራስህ አልፎ ለሌላ ትረፍበት  እንጂ ለሚያልፍ ፋሽን፣ ድንገት ለሚጠፋ ቅራቅንቦ አታውጣው። 4️⃣ነጻነትህ_ነው_አታባክነው! ቢሊየነሮች እንዲህ ይላሉ''አንድ ዶላር አወጣሁ ማለት፣ አንድ ሰዓቴን ሸጥኩ ማለት ነው''። እያንዳንዷ ለአልባሌ ነገር የምታወጣትን ገንዘብ ከነጻነትህ ተሸርፋ እንደምትወጣ አስባት። ገንዘብህን ባባከንክ ቁጥር ራስህን ለባርነት እየሸጥክ እንደሆነ ተረዳ። ገንዘብህ በሰራህበት ወይም ከራስህ ጋር በቆየ ቁጥር ደግሞ ነጻነትህን እያራዘምክ ነው ማለት ነው። 5️⃣ሰላምህ_ነው_ተንከባከበው! ብዙ እንቅልፍ ያጣህባቸውን ሌሊቶች ብታስታውስ የብዙዎቹ ሰበብ ገንዘብ ማጣት ነው። ደሞዝ በገባልህ ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ ብለህ፣ ደሞዝህን ከጨረስክ በኋላ በእንቅልፍና ሰላም ማጣት ትንገላታለህ። ገንዘብህን በጥበብ ብታወጣ ግን ከዛ ስቃይ ትተርፋለህ።  ገንዘብህን በስሜት ሳይሆን በምክንያት፣ ለጊዜያዊ ደስታ ሳይሆን ለቋሚ ሰላም አውለው።

  • I AM NO MILLIONAIRE I AM BILLIONAIRE

  • አንድ ፕሮፌሰር ወደ ክፍል ገብቶ ሰሌዳው ላይ 1 ቁጥርን ጽፎ ወደ ተማሪዎቹ ዞረ... ይህ አንድ ቁጥር #ባህሪህን ይወክላል ትልቅ ዋጋ ሊኖርህ ይችላል... ከዛ አጠገቡ '0' ጨመረበት እነዚህ #ስኬቶችህ ናቸው፡፡ ከባህሪህ ጎን ሲቆሙ ዋጋህ በአስር እጥፍ ያድጋል... ሌላ 0 ፃፈ ይህ #ልምድ ነው።  አሁን መቶ ሆነ ተጨማሪ ዜሮዎች ብቅ አሉ። #ስኬት፣ #ፍቅር፣ #ሃላፊነት... ፕሮፌሰሩ እንዲህ ሲሉ ገለፁ እያንዳንዱ አዲስ ዜሮ  የሰውን ዋጋ ሊጨምር ይችላል... ከዚያም 1 ቁጥርን አጠፋ። ሰሌዳ ላይ የቀሩት ባዶ ዜሮዎች ብቻ ናቸው። ከዚያም በተረጋጋ ሁኔታ እንዲህ አለ... #ባህሪህን ካጣህ ሌላው ነገር ከንቱ ይሆናል ያለዚያ ሁሉም ስኬቶችህ ዜሮዎች ናቸው። ትምህርት እና ስኬት አስፈላጊ ነው #ባህሪ ግን ሁሌም ይቀድማል!

  • አሳ ለማጥመድ ስትሄድ የምትይዘው ምግብ የምትወደውን ዳቦ ሳይሆን አሳው የሚወደውን ትል ነው። አንድ ሰው አንድን ነገር እንዲያደርግልህ ከፈለግህ እኔ ስለምፈልግ አድርግልኝ ከማለት ይልቅ ይህን ነገር ማድረጉ ለእሱ ትልቅ ጥቅም እንዳለው ማሳየት አለብህ። ምክንያቱም ሰዎች የሚንቀሳቀሱት ለራሳቸው ጥቅም ነው። ለምሳሌ፦ ልጅህ ትምህርት እንዲያጠና ከፈለግህ፤ "አጥና ብዬሃለሁ!" ብሎ ከመጮህ ይልቅ እሱ መሆን የሚፈልገውን ነገር ፓይለት ወይም ኢንጂነር በማስታወስ   ፓይለት ለመሆን ሂሳብ መስራት አለብህ" ብሎ በፍላጎቱ በኩል መግባት ትልቅ ለውጥ አለው

  • "አራት ዓመት ሙሉ በየቀኑ ኢንቦክስ እልክላታለሁ!" ለሳያት ደምሴ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸው ወጣት ታሪክ የኢትዮጵያዋ ዝነኛ አርቲስት ሳያት ደምሴን "አፈቅራታለሁ" የሚሉ ወጣቶች ብዙ መሆናቸው ቢታወቅም፣ የዚህ ወጣት ታሪክ ግን ለየት ያለና መላውን ሶሻል ሚዲያ ያነጋገረ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል። ይህ ወጣት በቅርቡ በዩቲዩብ ቀርቦ ባደረገው ልብ የሚነካ ቃለ-መጠይቅ፣ ሳያትን ልቡ እስኪጠፋ እንደሚወዳትና ከእሷ ውጪ ሌላ ሴት ማሰብ እንደተሳነው በይፋ ገልጿል። የሚገርመውና ብዙዎችን ፈገግ ያሰኘው ግን ፍቅሩን ለመግለጽ ያሳየው አስገራሚ ፅናት ነው። ወጣቱ እንደተናገረው ላለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት አንድም ቀን ሳያቋርጥ በየቀኑ በፌስቡክ መልዕክት ይልክላታል። ይሁን እንጂ በነዚህ ሁሉ ዓመታት ውስጥ ከአርቲስት ሳያት ደምሴ አንዲትም ምላሽ አግኝቶ አያውቅም። አራት ዓመት ሙሉ በየቀኑ "እንደምን አደርሽ?" እና "አፈቅርሻለሁ" እያሉ በዝምታ መታጀብ ለብዙዎቻችን "የፅናት ሽልማት" የሚያሰጥ ትዕግስት ይመስላል። ወጣቱ ለልሹ ባለው እምነት ግን ወደኋላ አላለም። "ሳያት አንዴ ዕድሉን ሰጥታ ብታገኘኝ እና ብታውቀኝ፣ እኔን እንደምትወደኝ እርግጠኛ ነኝ" በማለት በራስ መተማመን በሞላበት ሁኔታ ተናግሯል። ይህ ሰው "In-box" ገብቶ ሰላምታ መላክን እንደ መደበኛ ሾል ተያይዞታል። ምናልባት ሳያት መልዕክቱን ያላየችው "Message Request" ውስጥ ታፍኖባት ይሆናል እንጂ፣ ይሄን ሁሉ ፅናትና ጉጉት ብታይ ኖሮ "ቢያንስ ለትዕግስቱ ምስጋና ይገባዋል" የምትል ይመስላል። በተለይ "ከእሷ ውጪ ማንንም ማሰብ አልችልም" ማለቱ ለፍቅሩ ያለውን ታማኝነት ቢያሳይም፣ አራት ዓመት ሙሉ መልስ ሳይሰጡት አሁንም ተስፋ አለመቁረጡ ግን ለብዙዎች አስገራሚ ሆኖባቸዋል። እናንተስ ለወደዳችሁት ሰው እንዲህ አራት ዓመት ሙሉ መልዕክት እየላካችሁ ዝምታን ለመታገስ ትዕግስቱ አላችሁ? ወይስ "አንድ ሳምንት ካልመለሰችልኝ ይበቃኛል" የምትሉ አይነት ናችሁ..😀

  • йоС пОдписи

  • 🔰አንድ ዝንጀሮ በእጆቹ ብዙ የኦቾሎኒ ፍሬዎችን ይዞ በመንገድ እያለፈ ነዉ። በመሃል አንዲት ፍሬ ተነጥላ ትወድቅበታለች ፤ እሷን ለማንሳት ዝቅ ሲል 20 ፍሬዎች ከእጁ ያመልጡታል ፤ በጣም ይናደድና እነዛን 20 ፍሬዎች ለማንሳት ዝቅ ሲል እጁ ላይ የነበሩት ፍሬዎች እንዳለ ይበተናሉ። 🔰አንዳንዴ በህይወታችን ብዙ ዋጋ የከፈልንላቸዉ ልናጣቸዉ በፍፁም የማንፈልጋቸዉ ነገሮች ከእኛ ቁጥጥር ዉጪ በሆነ መንገድ ከእጃችን ያመልጣሉ። እኛም ያጣነዉን ለመመለሾ ያለመታከት እንጥራለን ፤ እዉነት ነዉ በቀላሉ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም ሆኖም አንዳንድ ጊዜ እጃችን ላይ የቀሩትን ትልቅ ዋጋ ያላቸዉን ነገሮች እስኪያሳጣን ድረስ መሆን የለበትም።

  • ጠላት ቢወጋህ… ያማል ጓደኛ ሲወጋ ይገድልሃል..🤔 ወዳጄ… የጀርባህን ጠባሳ ማን ሰራው? ጠላትህ? ወይስ አብሮህ የበላው ጓደኛህ? ብዙውን ጊዜ መልሱ “ጓደኛዬ” ነው። ጠላትማ ፊት ለፊት ነው የሚመጣው። ታየዋለህ፣ ትከላከላለህ። ጓደኛ ግን “ወንድሜ” ብለህ ስላቀፍከው፣ ቢላዋውን የት እንደደበቀ አታይም። ልብህን ከፍተህ፣ ሚስጥርህን ሰጥተህ፣ እ ቤትህ አስገብተህ… መጨረሻ ላይ ሲከዳህ፣ ህመሙ ከአጥንት ዘልቆ ይገባል። 1. የመንገድ ጓደኛ vs የህይወት ጓደኛ በህይወትህ ብዙ ሰው ታገኛለህ። አብዛኛው ሰው “የመንገድ ጓደኛ” ነው። አብሮህ ይስቃል፣ አብሮህ ይጠጣል፣ አብሮህ ይዝናናል። ግን ኪስህ ሲጎድል፣ ችግር ሲመጣ… አቅጣጫውን ይቀይራል። “አንተ ወንድሜ እኮ ነህ” የሚለው ቃል፣ ጥቅሙ እስካለ ድረስ ብቻ ነው። እውነተኛ “የህይወት ጓደኛ” ግን… አንተ በጨለማ ውስጥ ስትሆን፣ እሱ ሻማ ይዞ ይመጣል። እንደዚህ አይነት ሰው አንድ ካገኘህ… አንተ ባለጸጋ ነህ። ሺህ “አጨብጫቢ” ከመያዝ፣ አንድ “አዛኝ ወዳጅ” ይበልጣል። 2. ሚስጥርህን አትበትን “ጓደኛዬ ነው፣ ምንም አይለኝም” ብለህ የልብህን ሁሉ አትዘርገፍ። ዛሬ ጓደኛ የሆነው፣ ነገ ጠላት ሊሆን ይችላል። ዛሬ ያወራኸው ሚስጥር፣ ነገ የጥቃት መሳሪያ ሆኖ ይመጣብሃል። ሰዎች ይቀያየራሉ። ሁኔታዎች ይቀያየራሉ። ስለዚህ ልብህ የራሱ “ካዝና” ይኑረው። ለሰው የምታሳየው የፊትህን ፈገግታ እንጂ፣ የልብህን ጥልቀት አይሁን። ውሃ እንኳን ጥልቀቱ ሲታወቅ… ይደፈርሳል። 3. ይቅርታ አድርግ… ግን አትሞኝ! ጓደኛህ ካጠፋ፣ ይቅርታ አድርግ። ግን “እንደገና አማክረኝ፣ እንደገና ግደለኝ” ብለህ እድል አትስጠው። ይቅርታ ማድረግ መንፈሳዊነት ነው፤ መፈተሽ ግን ብልህነት ነው። አንድ ጊዜ እባብ የነደፈው ሰው፣ ልጥ ሲያይ ይደነግጣል ይባላል። ጥንቃቄ ፍርሃት አይደለም። የተሰበረ አመኔታ እንደተሰበረ ብርጭቆ ነው። ሊጠገን ይችላል፣ ግን ስንጥቁ መታየቱ አይቀርም። የጭሰኛው መልእክት… የሀገሬ ሰው ሆይ.... ጓደኛ ምረጥ። በብዛት ሳይሆን በጥራት። በሳቅህ ጊዜ አብሮህ የሳቀ ሳይሆን፣ በለቅሶህ ጊዜ እንባህን ያበሰልህ… እሱ ወንድምህ ነው። የቀሩት “ተመልካቾች” ናቸው። ተውኔቱ ሲያልቅ፣ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ። ብቸኝነት ከከዳተኛ ጓደኛ ይሻላል!

  • በ2000 ዓ.ም፣ አንድ የኒውዮርክ ወጣት መኪናው ውስጥ ተቀምጦ ሳለ፣ አንድ ሰው ተጠጋና ዘጠኝ ጊዜ ተኮሰበት። አንዱ ጥይት መንጋጋውን በሳው፤ አንዱ እግሩን ሰበረው። ደም በደም ሆነ።ሁሉም ሰው ይሄ ልጅ አበቃለት አለ... የሙዚቃ ኩባንያው ውሉን አቋረጠ፣ ጓደኞቹ ራቁት፣ ብቻውን ቀረ። ሆስፒታል ተኝቶ ሳለ አንድ አስፈሪ ነገር ተከሰተ... ፍርሃቱ ጠፋ! "እንዴ! ልሞት እኮ ነበር... ግን አልሞትኩም...ታዲያ አሁን ምን ያስፈራኛል? አለቃዬ? ድህነት? ሞትን ያሸነፈ ሰው ምን ያስፈራዋል?" ብሎ አሰበ። ከሆስፒታል ሲወጣ፣ ሌላ ሰው ሆኖ ነበር... ድሮ "ሰዎች ምን ይሉኛል?" ብሎ ይጨነቅ ነበር፤ አሁን ግን ግድ የለውም። ድሮ ሙዚቃዎቹን ለሰዎች እንዲመች አድርጎ ይሰራ ነበር... አሁን ግን እኔ እንደፈለኩት ብሎ መስራት ጀመረ። ውጤቱስ? ዓለም በሙሉ ተንቀጠቀጠችለት! ሰዎች ይህንን "ፍርሃት አልባ" ጉልበት ወደዱለት። አልበሙ በሚሊዮን ተሸጠ።ይህ ልጅ 50 ሴንት ነበር... "አንተን ወደኋላ የጎተተህ የችሎታ ማነስ አይደለም፤ ፍርሃት ነው! ሰዎችን የመቀየም ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ የማሸነፍ ፍርሃት... እነዚህ ፍርሃቶች እየጎተቱህ ነው።አንበሳ የሚከበረው ደግ ስለሆነ አይደለም፤ ስለማይፈራ ነው!

  • ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ የምንማራቸው 10 ዋጋ ያላቸው ትምህርቶች ① ጓደኞችህ፣ ምንም ያህል የቀረቡ ቢሆኑም፣ ከጊዜ ጋር እየራቁ ይሄዳሉ። ② በዓለም ላይ ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ግንኙነት ከራስህ ጋር ያለህ ነው። ③ ለልፋትህ ማንም ግድ አይሰጠውም፤ ሁሉም የሚያየው ውጤቱን ብቻ ነው። ④ ህመምና ውድቀት የህይወት አካል ናቸው። ⑤ እንደ ቤት የሚሆን ነገር የለም። ⑥ ከሁሉም በላይ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ቤተሰብና ገንዘብ ናቸው። ⑦ መጽሐፍ በእውነት የሰው ልጅ ምርጥ ጓደኛ ነው። ⑧ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጭንቀትን ይቀንሳል። ⑨ በማማረርና በማልቀስ ጊዜን ማጥፋት የትም አያደርስም። ⑩ ህይወትህን የሚቀርጸው ዕድል ሳይሆን ውሳኔዎችህ ናቸው።የልጅነት ጊዜ ወርቃማው ዘመን ነው!!

  • በአንድ  ወቅት  ሄንሪ ፎርድ  ለቢዝነስ ወደ እንግሊዝ ይጓዛል። አውሮፕላን ማረፊያው እንደደረሰ  መረጃ  ወደሚሰጠው ክፍል ሄዶ በከተማው ውስጥ በጣም ርካሹን ሆቴል ጠየቀ። ጸሐፊው - የለበሰውን  ካፖርት፣ መጠነኛ ሻንጣውን  አየና ተጠራጠረ ፊቱ ብዙም አዲስ አልሆነበትም ጋዜጦች ላይ ከዚህ በፊት አይቶታል ወዲያው አስታወሰወና "ይቅርታ ጌታዬ… ሚስተር ሄንሪ ፎርድ አይደለህም?" በማለት ጠየቀ? አዎ" ፎርድ በእርጋታ መለሰ። ግራ በመጋባት ጸሐፊው እንዲህ አለ። "ዜናውን  አኮ እከታተላለሁ ልጅህ ሁል ጊዜ በዲዛይነር የተሰራ ልብስ ለብሶ በጣም ጥሩ ሆቴሎች ውስጥ እንደሚዝናና አውቃለሁ። ነገር ግን አንተ በጣም ርካሹን ቦታ እየጠየቅከኝ ሲሆን በዚያ ላይ ጊዜው ያለፈበት ኮት ለብሰህ ነው የማይህ። አንድ ቢሊየነር ለምን እንደዚህ አይነት ገንዘብ ይቆጥባል?" ፎርድ ፈገግ ብሎ መለሰ፡- "ምክንያቱም ለማያስፈልጉኝ ነገሮች ተጨማሪ ክፍያ መክፈል ፋይዳው አይታየኝም። የትም ብተኛ አሁንም ሄንሪ ፎርድ ነኝ። እና ይህ ካፖርት? የአባቴ ነበር - ግን ማንነቴን አይቀይረውም። "ሾለ ልጄ ግን ገና ወጣት ነው ። እሱ የሆነ ቦታ ላይ ቢቆይ ሰዎች ስለሚያስቡት ነገር ይጨነቃል። ግን አላውቅም። እኔ ግን ዋጋዬን አውቃለሁ። ቢሊየነር የሆንኩት ወጪ በማውጣት ሳይሆን በእውነት አስፈላጊ የሆነውን እና የማይሆነውን በማወቅ ነው።" እውነተኛ ሀብት ማሞገስ አይደለም - ዋጋህን ማወቅ ነው እና አለም በልብስህ፣ በመኪናህ ወይም በሆቴል  ክፍልህ  እንዲገልፅህ ፈጽሞ አትፍቀድ።

  • ለጀግኖቹ ! ጀግና ከፈጣሪ በታች ሆኖ ራሱን የሚሰራ ነው። ራስን መስራት ማስተዋልን እና የየእለት እንቅስቃሴ ላይ ብርቱ መሆንን ይጠይቃል ስለዚህ ራስን ለመስራት ሁልጊዜም ወደኋላ እንዳትል አሁኑኑ  መንገድህን ጀምር ! የተባረከ ቀንን ተመኘሁ🙏🙏🙏

  • አንድ ትልቅ የኮንፒዩተር ድርጂት ውስጥ የሽንት ቤት የጽዳት ሰራተኛ ሆኖ ለመስራት የአመለከተ ሰውዬ ሾል አስኪያጁ ኢንተርቪው ሲያደርገው ከቆየ በኋላ ለስራው ተቀባይነት አግኝተሃል ስለዚህ የስራ ስምሪትና ውሉን እንድንልክልህ ኢሜልህን ስጠኝ ይለዋል። ሰውዬውም ኤሜልም ኮንፒውተርም  እንደሌለው ይገልጻል። ከዚያም ማናጀሩ  ኮንፒውተር የለህም ማለት አንተ የለህም ማለት ሲሆን ከሌለህ ደግሞ ለእኛ መስራት አትችልም በማለት በሩን እፊቱ ላይ ዘጋበት። ሰውዬውም እያዘነ ከዚያ እንደወጣ እኪሱ በነበረው 10$ ዶላር 10ኪግ እንጆሪ በመግዛት ቤት ለቤት እየዞረ በመሸጥ ቀኑ መጨረሻ ላይ 20$ አተረፈ።    ከዚያም ነገሩ ቀላል እንደሆነ ሲረዳ መጠኑን በእጥፍ እየጨመረ እየሸጠ በሚያተርፈው አንድ ሳይክል ገዝቶ በዚያ እየተንቀሳቀሰ ስራውን ቀጠለ። ከዚያም ገቢው እየጨመረ ሲመጣ በመደብር መሸጥ ጀመረ። ጠንክሮ በመስራቱ ከአምስት አመታት በኋላ የትልቅ የምግብ መደብር ባለቤት ሆነ። እንዲህ እየሆነ ሲመጣ ሾለ ድርጂቱ ሾለ ወደፊቱ ማሰብ ሲጀምር ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር ውል መግባት እንዳለበት ወሰነ። ከኢንሹራንስ ኩባንያ ባለሙያው ጋር ማውራት እንደጀመሩ ተግባቡና ውሉን እንድልክልህ ኢሜልህን በማለት ይጠይቀዋል? ሰውዬውም ኢሜይልም ኮንፒውተርም የለኝም በማለት መለሰለት። የኢንሹራንስ ባለሙያውም በመደነቅ በአምስት አመት ውስጥ ትልቅ የምግብ መደብር አቋቁመህ ኢሜይል የለህም? ቢኖርህ ምን ትሆናለህ አለው። እሱም መለሰ ከአምስት አመት በፊት ኢሜይል ቢኖረኝ አሁን ድርጅት ውስጥ ሽንትቤት አጸዳ ነበር አለው። አንዳንድ ነገሮች የማይሆኑት ለበጎ ነው ወይም በምክንያት ነው። ምንአልባት አንደኛው በር ሲዘጋ ሌላኛው እየተከፈተ ይሆናልና ሁሌም በፈጣሪህ ተስፋ አትቁረጥ!! ሁሌም ተስፋህ ፈጣሪህ ከሆነና ምታመሠግን ከሆነ ትደነቃለህ ሁሌም አመሥጋኝ እንሁን