- Последний пост
- 29 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 797
- 1/48двое суток
- 913
- 1/72трое суток
- 985
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ባልወቅስህ … ስላልተዉከኝ አይደለም። ዉርጫም ብርድ ብቻዬን ስላልገፋሁ ፥ ቃልህ እንደእርጅና ጥርስ ስላልረገፈ ፥ ከእምባዬ እልህ ስላልገባሁ ወይ ማስመሰሉን ስለቻልኩት ። ባልወቅስህ … መርሳት ስለቀለለኝ አይደለም። ትዝታህ በስለት ስለተወኝ ፥ በስምህ ስለማልደነግጥ ፥ ልቤ ለናፍቆት ስለደደረ ፥ ባረፍኩበት ስለለመድኩ።። ባልወቅስህ ስላልጠላሁህ አይደለም ስለማይገባህ እንጂ። ሳዉቀዉ ነዉ … ሰበብ የለኝም። ድሮም … ልቤ እንጂ አንተ አልጣልከኝም። . . @samuel_dereje
. . @samuel_dereje
ቀኑም ፥ ሰማዩም ጨክኖ ሃምሌ አለ! በበጋ ጸሃይን ፥ በሰኔ ተስፋሽን ሞኩ። አንቺም ቀረሽ ፥ ጸሃይዋን ዳመና በላት ፥ ተስፋሽም ነዶ አለቀ። ናፍቆትሽ ግን አልጎደለም! ልጠብቅ? . . . ንገሪኝ! ጉጉቴ ጋቢ ፥ ምኞቴ ቡሉኮ ቢሆነኝ . . . . . @samuel_dereje
. . @samuel_dereje
видео или голосовое, без подписи
ማወቅና ማድረግ ለየቅል ነዉ! ብዙ የማዉቀዉ ግን የማላደርገዉ አለ። መወሰን እየከበደኝ። መጨከን እየደከመኝ። መፀፀት እየፈራሁ . . . እልፍ ጊዜ ደግሞ እየሰነፍኩ! እንደማትመጪ አዉቃለሁ . . . ግን አልተዉኩሽም። እንደማልረሳሽ ታዉቂያለሽ. . . ግድ አላለሽም። አዎ . . . ማወቅና ማድረግ ለየቅል ነዉ! የማዉቀዉን እንደማላደርገዉ ፣ እያረኩት ፥ የማላዉቀዉ ደሞ እልፍ ነዉ። አንቺን መዉደድ እንደዛ ነዉ… . . @samuel_dereje
ሳዉቅ መዉደድ ቀላል ነበር – ወይ ነዉ ፣ ወይ አይደለም። ዛሬ ደርሶ ዉስብስብ ሆነ። አንዷ ኩሸት ከቧታል። ከበባት እንጂ ወና ነዉ። ቆማ ብታስብ ይገባታል - ግን ቆማ ለማሰብም አይገዳትም። ብልህ ናት። ከፍርሃቱጋ ማ ይላተማል። አንዱ ይቸኩላል … መዉደድ ፥ መወደድ ይፈራል ከመባል ችኩል ነዉ ቁብ የለዉም ፥ አይረጋም መባል ይቀላልና። ሞኝ ነዉ። በራሱ ጥድፊያ ፥ ራሱን ይጥላል። አብዛኛዉ … የማይጨበጥ ያሳዳል። ያልወደደዉን ፥ የሸሸ የሮጠዉን። የወደደዉ ያንስበታል። ያፈቀራት ይቀልባታል። በማታቅፈዉ ትከለላለች። በማያገኘዉ ይደበቃል። ፍሪ ነዉ የሞላዉ ፥ ኩሸቷን ገልፆ ሚወዳት ትመኛለች … ግን የለም። ችኮላዉን አልፋ የምትታገስ ይመኛል … ግን አያገኝም። ዛሬ ቀላል አይደለም። መሃል ቤት ሆኗል "ነዉ" የለም "አይደለምም”! . . @samuel_dereje
ስለጥረትህ አለም ግድ የለዉም። እልፍ ወዳቂ በሞላዉ ሃገር ለሞከረ የሚዜም እሹሩሩ የለም። ተሸናፊ ዜማ አልባ ነዉ። ለወዳቂ ሙሾ እንኳን ዉድ ነዉ። ያሬድ ቢታወስ በሰባት ዉድቀቱ አይምሰልህ ፤ በተነሳበት ስምንተኛ ነዉ። ሺ ጊዜ ጥሮ ቀና ያላለ እልፍ ያሬድ አለ። ሞክር … ካልተነሳህ - ትረሳለህ። . . @samuel_dereje
ሰባት አመቴ ላይ የሸሸኝ ንጋት ነበር። አለም የነጠቀችኝ ብርሃን። እሷ ግን ግድ አይላትም። ከህፃን ነጥቃ ማንም ቀማኛ አይላትም። እንዳሻት ናት . . . ተቆጪ ፥ ፈራጅ የለባትም። ስምንት አልኩ ህይወትም እንደማትከሰስ ገባኝ! - አስራ አራት የሞላኝ አመት ስለብዙ ነገሮች እጓጓ ነበር። ብዙ ቃል ነበረኝ - ከህይወት። ታደርግልኝ የምጠብቀዉ። "እመነኝ ነገ ይሆናል" ያለችኝ። እኔ አመንኩ "ነገ" ግን አልታመነም። ተስፋዬ ወና ዳከረ ፥ ጉጉቴም አልቆረጠ… አስር አምስት አልኩ ነገን ማመን ጥላ እንደሆነ አወኩ - የማይጨበጥ! - ሃያ ሳልሆን እንደሆንኩት ተዉኝ ባይ ነበርኩ። አለም ግን ከርካሚ ናት። ለሚታየዉ አበጃጀችኝ። ሙሉ ያልኩትን ጎዶሎ ፥ የቆረቆረኝን ልመድ አሉኝ። የመጣ ሁሉ ገማጋሚ ፥ ያየኝ ሁሉ ታዛቢ ሆነ። እንዳምፅ ግዜ አልሰጡኝም - ከትወናዉ አላመዱኝ። ሃያ አልኩ መድረክ የሆነችን አለም በጭንብሌ ተዋወኩ! - እስከ መች ለት … ልወድ አላመነታም ነበር። እስኪገባኝ። ምን ገባኝ… ብዙዉ ሰዉ አጥር ስር የወሸቀዉ ልብ እንዳለ። ማንም ቀዳሚ ተዘራሪ መሆን አንደማይፈልግ። እንቁ ያለዉን የራሱን ልብ እየሸሸገ ፥ አለት ባረገዉ የሌላ ልብ እንደሚሳለቅ። ገባኝ አልኩ … በጨለመ ዲስኩር ርህራሄዬን ከረከምኩ ፥ ኮረት ልብ አበጀሁ። ደነደንኩ። … ግን አላመለጥኩም። እድሜ ተዕምረኛ … ተማርኩ ። ልቤ ላይ እንደማላዝ … ህይወቴ ላይም። በምንቆጥረዉ ስንዝር ሁሉ የቻልን ይመስለናል ፥ የገባን። ይመስላል ግን አይደልም… . . @samuel_dereje
. . @samuel_dereje
እጓጓለሁ! ይሄኛዉ ቢሰምር ፥ ቢቀና ብዬ። እፈራለሁ! ሰምሮ ቢያሳሳኝ ብዬ። ገር እንዳልሆን ፥ ወና እንዳይተወኝ። ችኩል ነኝ… በኩሸት ጥድፊያ ራሴን ጥዬ… "ይኀዉ" ለማለት። አትከልይኝም?? ከራሴ እንቅፋት? . . @samuel_dereje
ነግሬሽ ነበር? ደመና ቀን እንደማልወድ? ካፊያ እንደሚጨንቀኝ ፥ ዝናብ ድብርቴ እንደነበር? ደሞም ተራ ሁነት – ተጠልዬ ፣ ኮት ደርቤ የማሳልፈዉ። ተደነቅ ሲል ጥላ ጨብጠሽ ፥ ዝናብ ላይ አጊጠሽ አይቼ ይኀዉ … ክረምት ናፋቂ ሆኛለሁ። ቀልብ አይሰንፍ . . . ሃምሌ መሃል ወለም ላለኝ ልብ የካቲት ላይ እታሻለሁ! . . @samuel_dereje
. . @samuel_dereje
አንዳንድ አሁን አሁን የሚበሉኝ ሃሳቦች ፩ We need to talk about nothing! Not in a poetic way. Literally nothing. ስላየሩ ፥ ጠዋት ስለገጠመን ነገር ፥ ማታ ስላየነዉ ህልም ፥ ስላስታወስነዉ የልጅነት ትዝታ ፥ ስለሰለቸን ወይ ሥላሳቀን ጥቃቅን እዉነት … ከነዚህ በላይ ዉብ ምን አለ? ስለተራ ነገሮች ከማዉራት በላይ የሚሻል ሃሴትስ? ሠዉን ከሃልዮቱ ፥ ከምክንያቱ በላይ በስሜቱ ያዉቁት የለ? ደሞም ያሰለቻል። ስለትላልቅ ሸክም ሃሳቦች ወሬ ሊፈጥሩ መታተር። እንደሚያራቅቁት ባዉቅም… ጥልቅ ፥ ዉብ ወዘተ እንደሚያስመስሉት። ሳልጀምረዉ ይታክተኛል። ስለጥበብ ፥ ህመም ፥ ትርጉም ፥ ሃልዮት ወዘተ … ሲያብራሩ። እዉነት ያለዉ እስከማይመስለኝ። እንዲ ያሉት ሸክም ወጎች አልፎ አልፎ ብቻ ብዙ ካወቁት ሰዉ ጋ ሲያጣቅሱት የሚያምር … የክት ጌጥ ነዉ። የዘወትር ሸማዉ ተራ ፥ ገለባ ይሉት ወግ ነዉ። ቢያንስ ለኔ! ፪ የዉሸት ዉብ ሰዉነት እየገነባን ነዉ - ሁላችን። performative authenticity ይሉት ሰዉ መሆን… መዋሸትን ፥ ማስመሰልን ፥ እንዲወደዱ መሞከርን…. እንደሚጨምር ልንረሳ እየታገልን ይመስላል። ሌላን ሊመስሉ ከመሞከር በላይ ሰዉ የሚመስል ባህሪ ምን አለ? ሰዉ ሊወደድ የሚጥር ፍጥረት ነው። መልኩን ለተመልካች ፥ ራሱን ለወዳጅ ያስተካክላል። ታዲያ ሰዉ መልኩን እንዲቀበል ሲሰብኩ ( Self Love ወዘተ ብለዉ) ለዚህ ሰዋዊ ባህሪዉ ግን ስለምን አይራሩም? “ራስን መሆን” ብሎ ተረት የለም። ማንነት ከአራስነት ጀምሮ በተዋስናቸዉ ፥ በወረስናቸዉ ጥቃቅን ልቅምቃሚዎች የተሞላ ነዉ። ሁሉም ዉስጡን ቢያይ የተዉሶ ነዉ። የኮልኮሌዎች ድምር ነን። ልዩ ነን። በብዙ ነገሮች ደግሞ አንድ አይነት። የምንጠላ የምንወደዉ ፥ የሚያስቅ የሚያሳዝነን ፥ የሚያሳሳ የሚያስናፍቀን ፥ የሚያስቀና የሚያሸሸን ሁሉ ብዙ ሩቅ አይደለም። በእልፍ ልምምድ ለእኛ የቀረበዉን "እኛነት" መጨበጥ ከቻልን እድለኛ ነን። ብዙዉ ግን ለዛም አልታደለም። ራስን መሆን ወይ መዉደድ …… ይሉት ነገር ካለ ... ያልሰለከከ አፍንጫችንን ወይ ዞማ ያልሆነ ፀጉራችንን መቀበል አይመስለኝም። ይልቅ ለመወደድ መሻታችንን ፥ ማስመሰ ፥ ዉሸታችንንወዘተ … የጤነኛ እኛነታችን አካል መሆኑን መቀበል ነዉ። To be human is to be performative! . . . @samuel_dereje
. . @samuel_dereje
Love is a strange phenomenon, maybe the strangest of all. It bends logic, rearranges time, and makes fools out of a steady men. Midnight, but thinking of doing it again. Hearing a lier called a brain saying ... She’s one in a million. Not because of what she sees in the mirror (she always gets that part wrong) but because of the impossible feeling she stirs inside me. unruly, without a name. Something I can’t control, even if I try. Maybe that’s why I want it again. Not for the promise of forever. I knew it wouldn’t last. And yet, there’s something in me that keeps reaching for the phone, wanting to hear her voice, again. Even if it ends the same way it did before. Even if it breaks me the same way. Some things are worth losing for! even for the second time, even for the third! @samuel_dereje
. . @samuel_dereje
. @samuel_dereje
. @samuel_dereje
ማስታወሻዬን ስገልጥ የዛሬ 5 አመት የፃፍኩትን አየሁ። ጊዜዉ ሄዷል። እድሜም እንደዛዉ። ያን በፃፈዉ እኔና በማነበዉ እኔ መሃል እፍኝ የመንፈስ ለዉጥ ግን የለም። ትናንት የጠየኳቸዉ ጥያቄዎች ዛሬም ይኮሰኩሳሉ። ትናንት ያልገቡኝ ፥ ዘመን ቆጥሬም ግራ እንዳጋቡኝ ያሉ ብዙ እዉነቶች አሉኝ። የትናንት አይነት ስህተቶቼን ዛሬ እደግማለሁ። ትናንት የጠለፈኝ ዛሬም መልክ ፥ ቅርፅ ቀይሮ ያደናቅፈኛል። በርግጥ በእድሜ የጥያቄዎቼን ጩኸት በግርግር አርጌቢያለሁ ። ርቆ እንዲሰማኝ አንዳንዴም የለም ጠፍቷል እንድል። ግን ወከባዉ ሲረግብ የሚያሰተጋባዉ የዛኔዉ ጩኸት - ገደል ማሚቶ ነዉ። - ማንነትን እንደቅርፊት ልጠዉ አይገላገሉትም። ብዙ ልጠዉ ፥ ብዙ ተለዉጠዉ ግን ዞረዉ ቢይዩት ፥ ብዙዉ ያዉ ነዉ! ህይወት ይቀየራል ። ማወቅም ይጨምራል። ባህሪም ፥ መልክም ይለወጥ ይሆናል። ያቺ አስኳሏ እኛነት ግን የማያወልቋት ካባ ናት። ብትፈዝም … ትክ ላሉ … ሁሌ አለች። @samuel_dereje