tgindex
Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 456
+3 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,07%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
850
23 постов
Вовлечённость
58,4%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 23
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
149
1/48двое суток
170
1/72трое суток
184

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • 09|12|18 መነሳት በሌሊት ሰባት፣ ስምንት ሰዓት ያለፈውን መዓት ከመዝገብ ቤት ማውጣት... አንድ፣ ሁለት እያሉ ሁሉን መመራመር የይቅርታን ደጆች እንደገና መውረር... የሞቱ ጉዳዮች ሰዎችና ጉዶች ተጐትተው ይውጡ ይህን ስል ይነሱ! አሁን ይታወሱ። አሁን ይወቀሱ። አንዴ ገፎ ማንሳት የመርሳትን ሞራ መ'ጐንተል፣ መ'ተልተል በብስጭት ካራ እንደ ጉድ መዋኘት በንዴት ገሞራ። እፎይ............. @amadonart

  • 07|12|18 ሁለት የጠዋት ቡናዬን ጠጥቼ በመንገድ ስጓዝ ፥ 'እስከመቼ እጓዛለሁ?' የሚል ሀሳብ መጣልኝ። 'እንግዲያው ለምን አልሮጥም?' በማለት ፥ ቦታው ባልሆነ ቦታ ተንደረደርኩ። ሰዎች ዞር ዞር እያሉ ሊገመግሙኝና ሊያሳፍሩኝ ሲሞክሩ ፥ ግድ አልሰጠኝም። እንደዛም አልረካሁም። "ይሄ በቂ አይደለም!" እያልኩ የጮህኩ ይመስለኛል። "እንግዲያው ለምን አትበርም?" የሚል ድምፅ ሰማሁ። "እውነትም!... እውነትም!..." አልኩና ሁለት እጆቼን ወጥሬ ዘረጋሁ። እንደ መጠራጠርና እንደ አለማመን ሲያደርገኝ "አንተ ሰውዬ ብረር!" በማለት ራሴን አዘዝኩ። እና ተነሳሁ... አንድ ፤ እና ተንሳፈፍኩ... ሁለት ፤ እና በረርኩ... ሶ...ስት። አቅጣጫዬን እየቀያየርኩ በረርኩ። ልክ ስቀዘቅዝ ፥ ሶስተኛ ቡናዬን በሰማይ እያስቀዳሁ። ልወርድ ሲመስለኝ ፥ አራተኛ ቡናዬን እያስቀዳሁ። መ'ወንጨፍ ስፈልግ ፥ አምስተኛ ቡናዬን እያስቀዳሁ። ሳወራው ቀልድ ይመስላል። @amadonart

  • እስከመቼ ስሸሸው እኖራለሁ? በዱር በገደል፣ በአጥቢያና በሌሊት... በዋሻና በሜዳ፣ ሰው ባለበትና በሌለበት... በሚታሰብም በማይታሰብም ሰዓት... ሲከተለኝና ስሸሸው ኖርሁ... ይበቃል! እጋፈጠዋለሁ! ደስታን እጋፈጠዋለሁ! @amadonart

  • 01|12|18 እየመሰለ - ለውጥ ያለው ነገር ዕድል ፈንታዬ - የሚሽከረከር ዛሬና ነገ - የሚለያዩ ካሳና ፍርዴ - የሚተያዩ የምንበሸበሽ - በደስታ ዘመን ስለተፈተንሁ - በእንባዬ መጠን የቀንና ሌት - ያለው ፈረቃ ፍትሕ ለማብሰር - እቺ ደቂቃ የምትቆጥር... 'በቃ' ልትለኝ ኤልፒስ ምትጥር እየመሰለኝ፣ እየጠበቅሁና እየተሞኘሁ። @amadonart

  • "ፍቅር ዝርክርክና ቦርቃቃ አይደለም። የአንድ ሰው ሁለንተናነት ነው። ተኮላን የወደደ ተኮሊስት ነው። እኔን የወደደ ጅማወርቂስት ነው።" የስንብት ቀለማት | አዳም ረታ | ገፅ 67

  • 15|11|18 የፈሰሰ - ውሃ ሳ'ፍስ መቃብር ቤት ለመቃብር የተዘጋ - ዶሴ ስከፍት ባዶ ካዝና ስበረብር በማይጠቅመው ባከተመ እንዳንዣብብ እንድለፋ የዘራሁት ተስፋ ሁሉ እንደ ምንም እንዲጠፋ ተመርቅያለሁና... አእምሮዬን እንዳላዘው መምከር እንኳ እንድፈራ ያለ ሰበብ እንዲላተም ከፈለገው ግንብ ጋራ ዝም እንድልም እንዳልልም የእረፍቴን ቀን ብቻ እንዳልም ህልሜም ቅዠት እየሆነ ሳላፈራ እንድከስም ተመርቅያለሁና... @amadonart

  • ከነዓን ወደ ተባለ የጤና ምድር አእምሮ የተባለ ህዝብ መቼ ይገባል? አርባ አመት በምድረ በዳ ተንከራተተ። አንተ የእስራኤል አምላክ!

  • በክረምት... የሞቱና የምንወዳቸውን እናስባለን። የት ናቸው? በሌሊት... የሞቱና የምንወዳቸውን እንናፍቃለን። የት ናቸው? በዝናብ... የሞቱና የምንወዳቸውን እንተዝታለን። የት ናቸው?

  • 27 мая1 7112717

    19|09|18 ባቀዱት አይሄድም ቀኑ፣ ወሩ፣ አመቱ አለመ'ገመት ነው የጊዜ ስኬቱ... ትንሽ ማጉላላት ነው የአለም sense of humor ማለፍ፣ መፈ'ታተን የትዕግስትዎን መስመር ሲስቁ መቆንጠጥ ሲቆጡ መኮልኮል ማብራትና ማጥፋት ማንሳትና መዶል... መኖር ፥ ይህን ማወቅ በስቃይ መስታወት እራስን ማጫወት... @amadonart

  • 26 мая1 06582

    Death in Teheran A rich and mighty Persian once walked in his garden with one of his servants. The servant cried that he had just encountered Death, who had threatened him. He begged his master to give him his fastest horse so that he could make haste and flee to Teheran, which he could reach that same evening. The master consented and the servant galloped off on the horse. On returning to his house the master himself met Death, and questioned him, “Why did you terrify and threaten my servant?” “I did not threaten him; I only showed surprise in still finding him here when I planned to meet him tonight in Teheran,” said Death. ( A parable shared in Man's Search for Meaning )

  • 21 мая1 45756

    https://www.arte.tv/fr/videos/127975-000-A/alazar/

  • 21 мая1 46717

    https://www.arte.tv/fr/videos/127975-000-A/alazar/

  • 16 мая1 114176

    08|09|18 የቱን ቀዳዳ ዛሬ አልደፈንኩም? የቱን አካሄድ አልጠረጠርኩም? ብዬ አእምሮዬን እኔ አልጠየኩም። እንዳያብድ... @amadonart

  • 11 мая1 12731

    OCD The Aviator | Martin Scorsese

  • 4 мая1 154161

    26|08|18 ደስተኛ ሰው ትመስላለህ። ምክንያቱን ማወቅ እንችላለን? የትኛውን? ደስተኛ የሆንኩበትን ወይስ የመሰልኩበትን? ከቻልክ ሁለቱንም ብትነግረን... አንዱን ብቻ ምረጡ! በቃ እሺ የመሰልክበትን። እንዴ! የሆንኩበትን ማወቅ አትፈልጉም? አንፈልግም። አትፈልጉም? አንፈልግም። እንዴት? ደስተኛ አደለም ብላችሁ ጠርጥራችሁ ነው? አልጠረጠርንም። እና አትፈልጉም? አንፈልግም። ደስተኛ አደለም ብለው ነግረዋችሁ ነው? አይደለም። እና አትፈልጉም? ደስተኛ አይደለህም እንዴ? እንዴት? እንዴት? ደስተኛ አልመስልም አንዴ? እሱማ ትመስላለህ። እና? እና እንዴት ደስተኛ መምሰል እንደቻልክ ብትነግረን... እንዴት? ምን ማለታችሁ ነው? ልታሳብዱኝ ነው? የሐበሻ አሽሙር ነው? ገደል ግቡ! ይቅርታ... ገደል ግቡ! ገ      ደ           ል... @amadonart

  • 22|08|18 በቀን ውስጥ ፥ ስንቴ ይረበሻሉ? ስንቴ ይጨነቃሉ? ስንቴ ይደበራሉ? ስንቴ የአለም ፍፃሜን ተመኝተዋል? ስንቴ የፍርድ ቀንን ጐምጅተዋል? ስንቴ መጠበቅን፣ ተስፋ ማድረግን፣ አለማለቅን ጠልተዋል? ስንቴ ሜንታል ሄልዝዎ ተናግቷል? ስንቴ "አሁንማ አበቃልኝ" ሲሉ ቀጥለዋል? ስንቴ "ዚስ ኢዝ ዘ ኤንድ" ሲሉ "ገና መች ተነካና!" ተብለዋል? ስንቴ 'ደም' የተባለውን የወንድ እንባ አንብተዋል? ስንቴ ሞተዋል? ስንቴ ተነስተዋል? ሞኝነትዎ... እጅግ በጣም ሞኝነትዎ... @amadonart

  • 30 апр.1 082102

    22|08|18 አዳዲስ ዜና፣ አዳዲስ ገድል በሀበሻ ምድር ከቶ እንዳይጐድል "ተነሳ ፤ ተራመድ ክንድህን አበርታ" በወገን ግንባር ላይ ማን ይስባል ቃታ? ከአንተ ውጪ? ከአንቺ ውጪ? @amadonart

  • 19|08|18 ተሰልፈዋል ይዘው መጥረቢያ አካፋ ዶማ ጦርና ዛቢያ... አይናቸው በአምሮት ይንከራተታል የመስዋ'ቱን በግ ይጠባበቃል እንግዲህ ልሂድ ፤ አላስጠብቃቸው። @amadonart

  • 26 апр.1 039287

    17|08|18 የዘወትር ጠዋት ቡናዬን የምጠጣበት ቦታ ተቀምጬ አነባለሁ። አንድ ሽማግሌ ፊት ለፊቴ ተቀምጧል። አስተናጋጇን ጠራትና ቡና በስኳር አስቀዳ። 'በዚህ እድሜያቸው ስኳር የሚጠጡ ፥ የደላቸው ሽማግሌ' አልኩና ወደራሴ ተመለስኩ። ትንሽ ቆይተው አሁንም አስተናጋጇን ጠሯት። "እዛጋ የተቀመጠው ምንድነው ያዘዘው?" አሏት እያንሾካሾኩ "ቡና" አለቻቸው "ሒሳብ እኔ ጋር ነው" "እሺ" "ጓደኛዬ ነው" "እሺ ጋሼ" "እኔ ምልሽ... ከጐኑ ያለው አብሮት ነው?" አሉ በአገጫቸው እየጠቆሙ "አዎ" "በቃ የእሱንም እከፍላለሁ" "እሺ" ብላ ሔደች። ማንበቤን ቀጥያለሁ። እንደገና ከአስር ደቂቃ በኋላ ይጠሯታል። "ምግብ አዘው ነው?" ይሏታል በታላቅ ሚስጥራዊ tone "አዎ" "ምን አዘዙ?" (በጭንቀት) "ጓደኛዎት ጨጨብሳ ነው። አብሮት ያለው እንቁላል።" "ስንት ይመጣል?" "ከቡናው ጋር 380" "አይ! አይ!" አሉና ተቆጡ። "የቡናቸውን ብቻ ቁረጭ!" ቀና ብዬ ሳያቸው ፥ አስተናጋጇ ፈገግ አለች። 200 ብራቸውን ሰጧትና ቶሎ መልሳቸውን ተቀብለው ተነሱ። ራመድ ራመድ ብለው ሰዎቹ ጋር ሲደርሱ ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጡ። የማይጠቅመንን ትንሽ ነገር አወሩና "ምግብ አዝዛችሁ ነበር እንዴ? ቡና ብቻ መስሎኝ እኮ እሱን ብቻ ከፈልሁ" "ኧረ አያስፈልግም ነበር ከቤ" አሉ አንደኛው ሰውዬ (ጓደኛቸው) "ቆይ የዚህንም ትቁረጥ ልንገራት። ማነሽ ነይማ!" "ኧረ አይሆንም ከቤ። ቡናውን ጋበዝከን አይደለም ወይ? ተው ተው ተው!" "ኧረ አይሆንም!" "በፍፁም! በፍፁም! ዝምብለህ ሂድማ እውነት" አሉ ወደ ኪሳቸው የገባ የሽማግሌው እጅ ፥ እንዳይወጣ በጉልበት ይዘው። አጠገባቸው ደርሳ የነበረችው አስተናጋጅ ፥ እንደኔ ቁልጭ ቁልጭ ትላለች። "በይ ተይው እንግዲህ... እምቢ አሉ" አሏት ሽማግሌው እየተረጋጉ "ዝምብለህ እኮ ነው ከቤ። ልጆች እንዴት ናቸው ይልቅ?" "ደህና ናቸው ይመስገን። እማዋይሽ ተሻላት?" "አሁንማ በጣም። እግዚአብሔር ይመስገን!" "እመጣለሁ እያልኩ ይኸውልህ..." "ጊዜው እኮ ነው። መች ይሞላል?" ወዘተ... ወደ ማንበቤ ተመለስኩ። @amadonart

አማዶን — tgindex