SILTI SECONDARY SCHOOL. Offical page (Kibet)
Статистика"Eduction is the most powerful weapon to change the world " "Madiba"
- Последний пост
- 10:54
- Последнее чтение
- ещё не заходили
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 304
- 1/48двое суток
- 348
- 1/72трое суток
- 375
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
2018 REGISTRATION.....
የትምህርት ቤታቺን እንቁ አባላችንና ካፒቴናችንን #ሙዲን_ከማል የሞተር ሳይክል ግዢ የተጀመረው የምስጋና ስጦታ በታላቅ ፍቅርና አሰደናቂ ሁኔታ ቀጥሏል! የትምህርት ቤታችን አጠቃላይ ማህበረሰብ ይህ ታላቅ እድል በመጠቀም ጀግና መሪያችንን ማመስገን ይገባል:: 🏦 ደገፍ ለማድረግ የባንክ አካውንት አማራጮች፦ 🔹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 🔢 ሂሳብ ቁጥር: 1000781677179 👤 ስም: Mohammed And Sefiyu And Sani 🔹 ዳሽን ባንክ (Dashen Bank) 🔢 ሂሳብ ቁጥር: 2939210496611 👉 ይህ መልእክት ለብዙዎች እንዲደርስ #SHARE በማድረግ አሻራዎን ያስቀምጡ! #የመምህር_ውለታ #መምህር_ሙዲን_ከማል #በጎ_አድራጎት #JummaMubarak #ነገን_እንገንባ
без подписи
ነፃ የOnline ስልጠና #ክፍያየለውም መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ 5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ (5 million Ethiopian Coders) የተሰኘ ስልጠና አመቻችቷል። መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ “5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ” የተሰኘ አዲስ የስልጠና እድል አመቻችቷል። ይህ ኢኒሼቲቭ ከአይሲቲ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ኮርሶች ጥራቱና በጥልቅ ይዘቶች በሚታወቀው በኦዳሲቲ ፕላትፎርም (Udacity Platform) የፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስና ሌሎችም ከአይሲቲ ጋር የተገናኙ ኮርሶችን ከክፍያ ነፃ ማግኘት የሚያስችል ነው። ተማሪዎች እና መምህራን ያለምንም ወጪ በእነዚህ ኮርሶች በመመዝገብ ይህንን ልዩ የስልጠና እድል መጠቀም የሚችሉ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በመሳተፍና ችሎታቸውን በማጎልበት በአለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ። በዚህ ስልጠና ተመዝግበውና የትምህርት ይዘቶቹን ተምረው ያጠናቀቁ ተሳታፊዎች በአለም አቀፍ ድርጅቶች እውቅና ያለው እና የስራ እድልን በእጅጉ ሊያሳድግ ከሚችለው Udacity የምስክር ወረቀት ያገኛሉ። ትምህርት ሚኒስቴር በስልጠናው እንዴት መመዝገብና መሳተፍ እንደሚቻል የሚያሳዩ መመሪያዎችን በጽሁፍና በቪዲዮ አዘጋጅቷል። ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎችና መምህራን ይሄንን በበዙ ክፍያ ይሰጥ የነበረን ስልጠና መመሪያውን ተከትሎ ብቻ በመመዝገብ በነጻ መሰልጠን ትችላላችሁ። የመመሪያውን የቪዲዮ ሊንክ https://youtu.be/-zSmhhD5qE4 ላይ በመግባት መመልከት የምትችሉ ሲሆን በምስል የተደገፈውን መመሪያም ከዚህ ፖስት ጋር አጋርተናል። ይሄንን ጠቃሚና ነጻ የስልጠና እድል ፍላጎቱ ላላቸውና የትምህርት ዝግጅታቸው ከዚህ ስልጠና ጋር ለሚገናኝ ጓደኞቻችሁ፣ ወዳጅ ፣ ቤተሰባችሁ እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራን በማጋራት ተጨቃሚ እንዲሆኑ አድርጉ።
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ ነው አዲስ አበባ፤ ሐምሌ16/2016(ኢዜአ)፦ የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከስራ ፈጠራ ባሻገር ለአገልግሎት ዘርፍ ኢንቨስትመንት መጎልበት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡ ኢኒሼቲቩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና የኢትዮጵያ መንግስታት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 5 ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ነው፡፡ ስልጠናውም በዋናነት በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ ከኢኒሼቲቩ ማስጀመሪያው በተጓዳኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ ኢኒሼቲቩ የትምህርት ዘርፉ ብቁ ትውልድ ለመገንባት በሚያከናውነው ስራ ላይ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል፡፡ በተለይ ትውልዱ በንድፈ ሃሳብ የሚያገኛቸውን እውቀቶች በቀላሉ ወደ ተግባር እንዲለውጥ ምቹ እድል በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላል ነው ያሉት፡፡ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው ቴክኖሎጂ ከስራ ፈጠራ ጋር የሚተሳሰር ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የወጣቶችን ዲጂታል አቅም ለመገንባት የተሰጠው ትኩረት ደግሞ ግብርናን ጨምሮ የተለያዩ መስኮችን ለማዘመን የተያዘውን ውጥን እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ ነው የተናገሩት፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስትን ወክለው በፓናሉ የተሳተፉት አብዱልአዚዝ አልጃዝሪ በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እውን በማደረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ የአመራር ቁርጠኝነት መኖሩን አንደታዘቡ ተናግረዋል፡፡ ይህ ደግሞ በኢኒሼቲቩ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡ ቴክኖሎጂ የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በእጅጉ እየቀየረ ስለመሆኑ አንስተው፤ ከዚህ አኳያ ለዘርፉ ቅድሚያ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡ የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት አቅድ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያብራሩት ደግሞ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ በእቅዱ ላይ ዲጂታል ክህሎትን መሰረት ያደረገ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት እንደተሰጠው ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም ይህን እውን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢኒሼቲቩ በኢትዮጵያ ክህሎት ያለው የሰው ሃይልን በመገንባት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአገልግሎቱ ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ዘመናዊና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እውን ማድረግ መንግስት እያከናወነ ያለው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች ዲጂታል ክህሎት ማደግ እንዳለበት ጠቅሰው፤ ኢኒሼቲቩም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያውን የሚያግዝ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
без подписи
አፍሪካ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት አጋጥሟታል - ኅብረቱ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአኅጉሪቱ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት ማጋጠሙን የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት፣ የሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር መሐመድ ባልሆሲን በሰጡት መግለጫ፥ የመምህራን እጥረቱ በአኅጉሪቱ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የተቀመጠውን በትምህርት የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት አኅጉሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል። የመምህራን እጥረቱን ለመሙላትና በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ኢንቨስት የሚደረገውን በአግባቡ ለመጠቀምም ጠንካራ ጥረቶች እንደሚያስፈልጉ አስረድተዋል፡፡ በአፍሪካ የመምህራን እጥረትን ለመፍታት፣ የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ 90 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡ በአፍሪካ ያለው የትምህርት ሥርዓት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
без подписи
"ባካሄድነው ጥናት 90 በመቶ ተማሪ ኮራጅ መሆኑን ደርሰንበታል" #Ethiopia | በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ተናገረዋል፡፡ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መል የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡ ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡ ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡ ተመራማሪው፤ ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡ በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ Via EBC
без подписи
ቅዳሜ የተባለው ጉዞ ለእሁድ 2:00 ተቀይሯል መልክቱን ቴሌግራም ለማይከታተሉ መልክቱን በስልክ አድርሷቸው!!! የዶርም ምደባው እስካሁን አልደረሰንም እንደደረሰን እናሳውቃለን
без подписи
ቅዳሜ የተባለው ጉዞ ለእሁድ 2:00 ተቀይሯል መልክቱን ቴሌግራም ለማይከታተሉ መልክቱን በስልክ አድርሷቸው!!! የዶርም ምደባው እስካሁን አልደረሰንም እንደደረሰን እናሳውቃለን
naturals naturals naturals ለ12ኛ ክፍል ናቹራል ተማሪዎች ሀሙስ ቀን 4/11/2016 ከጠዋቱ 4:00 ላይ በድጋሚ ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ በሰአቱ እንድትገኙ እያሳሰብን በዚህ ኦረንቴሽን ላይ ያልተገኘ ተማሪ ት/ቤቱ ከፈተናው የሚያግድ መሆኑን እናሳውቃለን!!!
for social 12th
без подписи
без подписи
без подписи