- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 27
- 1/48двое суток
- 30
- 1/72трое суток
- 33
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ውሰደን እንዳንል ቅጣትህ አስፈራን፥ አኑረን እንዳንል ኖረን ምን አፈራን፥ ፀሎቱ ጠፍቶናል በፈለከው ምራን።
ነገን ኑረን ፥ ዛሬን ሞትን ትላንትናን እየለፋን ፥ በቀደም 'ለት ተቀበርን መሞቻና መሰንበቻው ፥ ሳይታወቅ የውል ፍቺው ቀን ልንጨብጥ በቀናችን ፥ ቀን አስጣለን መኖራችን።
እኔስ ኖሬዋለው ሲከፋኝ ሲደላኝ ከንግዲ ተወልዶ ሰው ለሚሆን ይብላኝ.
ተይው እንተወው ተይው እንተወው፤ ..... የዘመን ቃፊሩን ማለፍ አልቻልንና ይህ አለም ጥበቱ አልመጠነንና፤ ተይው እንተወው፤ ..... ውጥኑ ግብ ይሁን ጅማሬው ፍፃሜ፣ ቅፅበቷ ሙሉ እድሜሽ ወቅቷ ዘላለሜ።
እንደሰበዓሰገል ፡ ኮከብ ፡ ምሪት እንደመከተል – የሰጠሽኝ ፡ ምልክት የዐይንሽ – የቃልሽ ፡ ምሥጢር ለዛኔው ፡ እኔ ፡ ቢጠጥር ፤ ሳይገባኝ ስቀቴ ፡ እንደመራኝ ወርቅሽን ፡ በሰም ፡ ፈክሬ ሲገባኝ እሳቱ ፡ ተረፈኝ ፡ ዛሬ ። ለካ… ወደድኩሽ ፡ ብዬ ፡ ስመናቀር ሞትኩልህ ፡ ብለሽኝ ፡ ነበር ።
እንዳላጣሽ . በመኖርሽ ማለዳ ወፎች ሲዘምሩ፣ ዜማቸው ይገባኛል፤ በመኖርሽ ምሽት ጉጉት ሲያሟርት፣ ሰቀቀኑ ያስፈራኛል፤ በመኖርሽ ጨረቃን አድማስ ላይ ሳያት፣ ውበት ድምቀቷ ያጓጓኛል፡፡ . ብቻዬን የለኝም ቅኝት፣ ብቻዬን የለኝም ስስት፣ ብቻዬን የለኝም ጉጉት፣ እንዳላጣሽ፡፡
እግዚአብሔር . . . ምን መኾን ቢችል : አካል መልኩን ስሎ : ዐይኑን ያየው ዘንዳ : የሰውን ፊት ሰራ ! መስታወት ነው ብሎ።
ሞክሼ ..❗ ያ ሁሉ እግዚኦ ያ ሁሉ ቢስሚላ ያ ሁሉ ጾም ጸሎት ያ ሁሉ ምህላ ... የት ነው የሚሄደው ስሚኝ እስቲ ሀገሬ ሞክሼ አለሽ ወይ ሌላ ??
አብጄ ከሆነ ወስደሽ አስጠምቂኝ፥ አብደሽ ከሆነ ግን፣ በስተርጅና አያምርም ሀገሬ አታስቂኝ፥
አንዳንዴ አንድን ስህተት የምናርምበት ዘዴ ከስህተቱ የበለጠ ትልቅ ስህተት ይሆናል።
Toxic ppl pinned «. እኖር ብዬ ብታረድም ፣ ለመኖር ስል ብሰደድም እኖር ብዬ ብጨነቅም ፣ እኖር ብዬ ብዋረድም ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው… አንዴ እንደመኖር አይከብድም! መኖር ከመምት አይልቅም ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡ . የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል… በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡ ያልኖረ አያውቅም ሞቶ። . መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ መኖር እንጂ የሚያስከፋኝ መኖር እንጂ የገደለኝ መኖር እንጂ የበደለኝ…»
ድክም ብል በሂወት መንገድ እግሬ ቢዝል ብሰናከል ቆፈን ብለብስ ለገላዬ ቁራሽ ዳቦ ብከለከል ቀን ቢገፋኝ ካለሁበት ከከፍታ ብወረወር "አትመጥንም" ብባል በአፍ ከአመት አመት በቀን በወር አይኔ ደምን ሰርክ ቢያነባ እቅድ ግቤ ቢፋለስም ዳና ትግሌን አደብዝዘው ያለ ስሜ ቢሰጡኝ ስም.
መቼ ነው አንድ ቀን ❗️ ስንጠጋው ሚሸሽ ስንቀርበው ሚርቀን ዕድሜያችንን ሁሉ ስንኖር ሚናፍቀን በተስፋ ጠቅልለው ይመጣል የሚሉን መቼ ነው ' አንድ ቀን ' ??
ላንድ አፍታ ደውዬ ድምፅሽን በይ ልስማ ካልሆነ እኔነቴ ከራሴ አይስማማ ኩራት ነው ይሉታል የሴትነት ወጉ ታድያ እንዴት ይሁኑ ባንቺ ለተወጉ እኔን አልመለሱኝ አበውም ተርተው ማየትሽን አልተውሽ መደወሌን አልተው "ሃሎ" ለማይነሳ ስልክሽ ለናፈቀኝ ድምፅሽ
በእርግጥ አውቃለሁ፤ እኔን በማሰብ እንቅልፍ የለሺም፤ አፈኑብኝ ወይ!? ገደሉብኝ ወይ!? ሳትይ አይመሽም፤ ሁሌም ፈሪ ነሽ ስለ'ኔ ጉዳይ፤ አታውቂምና ... እኔ እንደኾንኩኝ የራሴው በዳይ፤ አምሞት ይኾን ወይ!? ከፍቶት ይኾን ወይ!? በርዶት ይኾን ወይ!? ይህ ነው ዘላለም የሚያስጨንቅሽ፤ አንድም ቀን አርፎ አያውቅም ልብሽ፤ እናት ነሽና አልፈርድብሽም፤ ወትሮም የኔ’ንጅ የራስሽ ቁስል አይታይሽም፤ ሳትበይ በላሁ! ሳትጠጪ ጠጣሁ! ሳትጠግቢ ጠገብኩ! ይህ ነው አመልሽ፤ ያንሰፈስፋል ሲጠራ ስምሽ፤ እኔ እስከማውቅሽ ስቀሽ አታውቂም ፤ ስትናፍቂ እንጅ ስትደሰች አታስታውቂም፤ ዘወትር እኔ ነኝ የማስጨንቅሽ፤ የማስለቅስሽ - የምናፍቅሽ፤ መቼስ ቁስልሽ ነኝ አይደለሁ ልጅሽ።
ሰው ይነጥቃል ስጋ ከ አንበሳ መንጋጋ አምላኩን ሲጠጋ 🧎♂
ባንድ ጭንቅላት በጠባብ ደረት ስንቱን ስሸከም ስንቱን ስደርት ለመሀላንኳ ምሳሌ ሚሆን ህያው ምልክት አንድም ሳላስቀር በሁሉም ሳጌጥ አጣሁኝ የክት እግሬ በመራው በነዳው ሲሄድ ጢሻ ለጢሻ ልቤም እንደ ዘር የትም ሲበተን ባገኘው እርሻ ለፈጠረኝም ለገደለኝም ስቆም ላምልኮ ስንት ብሆን ነው?.... አንድ ሰው ብቻ አልመስልምኮ!!
ላልተኖረ ህይወት ሞት አያስፈራም ከጸሀይ በታችም አዲስ ነገር የለም 🪦❗
ይታዩኛል ብዙ ልብሶች በውስጣቸው የሉም ሰዎች ❗
видео или голосовое, без подписи