- Последний пост
- 7 июн. 2024 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከነገ ጀምሮ መንገዶች እንዲከፈቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ትዕዛዝ መሰረት ተዘግተው የሰነበቱ መንገዶች እንዲከፈቱ ሲል እዙ አሳውቋል። ሰሞኑን በነበሩ ተከታታይ ቀናቶች ለህዝብ ደህንነት ሲባል መንገዶች ተዘግተው መሰንበታቸው ይታወቃል። አሁን ከመሸ ከዕዙ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሐብቴ ወልዴ በተላከ መረጃ መሰረት ከነገ ጀምሮ መንገዶች ክፍት እንዲደረጉ እና እንቅስቃሴ እንዲጀመር ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም ከነገ ሰኔ 1/2016 ዓም ጀምሮ ተዘግተው የነበሩ ሁሉም በጎንደር ቀጠና የሚገኙ መንገዶች አገልግሎት እንዲጀምሩ ክፍት መሆናቸውን እናሳውቃለን። የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ሰለፋኖ ብቃት የተሠጠ ማረጋገጫ ‼️ #ድል_ለአማራ_ፋኖ 💪👊
#ኦሮምኛ ቋንቋ አቀላጥፎ የሚናገር፣ የህግና የፓለቲካ ሳይንስ ተማሪ/ተመራማሪ #ሞገስተሾመን ፕሮግራም "ልዩ ዝግጅት: "ኦሮሞ ሆይ፣ አማራ እየመጣብህ ነውና ተነስ" youtube.com/watch?v=aUVtzY… በጥሞና ተክታተሉት። የበሻሻው ደላላ #አብይአብይ አህመድ ከጥቂት ቀናት በፊት ነቀምት ላይ በኦሮምኛ ያደረገውን መርዘኛ ንግግር ፣ የህገ መንግስታዊ፣ ፓለቲካዊ፣ ከህዝቦች ሰላም ፣ እብሮነት ፡ ከመሪዎች ሃላፊነት አኳያና እንድምታዎቹ ምን እንደሆኑ በደንብ አቅርቦአል። አንድ ጠ/ሚ እይደልም ማንኛውም የመንግስትና የፓርቲ ሃላፊ የማይጠበቅ፣ እጅግ አሳዛኝ፣ እጅግ አደገኛ፣ ወንጀለኛ፣ መርዘኛ ንግግር ገልቦ/deconstuct ያቀረበበት ልዩ ዝግጅት ነው። Kudos to @MogesTeshome10 ፋሽስታዊው ደላላ የሁላችንን ቀልብ ለማገኘት የደለለበትን፣ የሸጠበትን፣ የተጠቀመበትን፣ ለጥቂት አመታትም ቢሆን የጠቀመውን "የኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያ" ጨዋታና ጭምብልች የመጨረሻውን እንጥፍጣፊ ፣ ነቅምቴ ላይ በኦሮምኛ ባደረገው ንግግር አውልቆ እንደጣለው ግልጽ ያድርግናል ። ነገ በሌላ አካባቢ ለህዝብ ሲናገር ደግሞ ተቃራኒውን ከመናገር የሚመልስ እንዳልሆነ ግልጽ ነው ። ሃፍረት፣ ይሉኝታ፣ ሞራልና፣ መርህ፣ እሴት የሚባሉ ለእንድ ማህበረስብ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ማእቀፎች በዚህ ፋሽስት ቤት ቦታም የላቸውም፣ ትሩጉም እልባ ናቸው። ለአሁኑ ግን ያው ያደገበትን ፣በቅርብ የሚያውቁትና እያዳልጠው ሲናገር የታዘቡት ሲነግሩን አልሰማ ብለን (እኔን ጨምሮ) ለጥቂት አመታት የተሸወድንበት ጸረ አማራ ውስጠ ውስጡን፣ የልቦና ውቅሩን ከበታችነት ስሜት የሚመነጭ "ንቀቱንም" እዚያው "የአማራ ብልጽግና " የሚባሉት በቅሎዎች በነበሩበት ፣ ዞር እያለ ወደ እነሱ እየተመለከተ በአደባባይ እቀርሽቶታል። የሞገስ ተሾመን ዝግጅት በጥሞና አዳምጣችሁ መጪው ግዜ እጅግ አስጊና ፣ ትልቅ ፈተና እንደሚሆን ጎልቶ ፣ ፍንትው ብሎ ይታያል።
https://www.youtube.com/live/aUVtzYfAcak?si=Qcwz7bs6NUHGCIsN
ጋዜጠኛ : -እንዴት ድልድይ በጥራት መስራት አቅቷቹ በዉሀ ይወሰዳል የጭሮ ከተማ ከንቲባ :- የእግዚአብሔር ስራ ነው እዚህ ውስጥ አንገባም😂😂
#መረጃ ጎንደር- የአይምባ ተጋድሎ! አርብ ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም ትናንት ምሽት ግንቦት 1/2016 ለንሥር ብሮድካስት ከጎንደር በደረሰው መረጃ ከቀኑ 10:00 ስዓት ላይ አንድ ሙሉ ኦራል ወራሪ መከላከያ ከአዘዞ ካምፕ ተነስቶ ወደ አይምባ ጊዜያዊ ካምፕ በመሄድ ላይ እያለ አይምባ ከተማ ታክሲ ተራ ላይ በፋኖ ተከቦ የተመታ ሲሆን ኦራሉ ላይ የነበረው ሁሉ አልቋል። እስከ ምሸት አራት ሰዓት ድርስ አስከሬኑም ኦራሉም አስፓልት ላይ እንደወደቀ መረጃው ለንሥር ደርሷል። ፍኖወች ይህንን ኦፕሬሽን ከሰሩ በሗላ አይምባ ከተማ አካባቢ ያለውን ካምፕ ከበው ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ አምሽቷል። በሌላ በኩል ለንሥር ብሮድካስት በደረሰው የውስጥ መረጃ አውሬው ወራሪ መከላከያ ተብየውትናንት ባደረገው ስብሰባ አይምባ ከተማ ሁሌም ጥቃት የሚደርሰብን ለምንድን ነው በሚል የተገኘውን ሁሉ በመመታት ህዝቡ መጨፍጨፍ አለበት አለበት ከተማውንም ጭምር ማውደም አለብን በሚል ተሰብሰበው መወሰናቸውን መረጃው ደርሷል። ነዋሪው ቤቱን እየዘጋ ንብርቱን ጭምር ጥሎ ሲሰደድ ውሏል። ወራሪው አብይ አህመድ ይደመሰሳል ፋኖ ያሸንፋል። ድል ለአማራ ፋኖ ድል ለአማራ ህዝብ © ንሥር ብሮድካስት
#ሰበር_ዜና ‼️ በበለሳ፣ በሊቦ ከምከም እና ባጃ የገባው የአገዛዙ ጨፍጫፊ ታጣቂ ቡድን ዛሬ በተደረገ ውጊያ ተደመሰሰ፤ በለስ የቀናው እጅ ሰጥቷል!! የአካባቢ ማህበረሰብ ያደረገው ተጋድሎ የሚገርም ነበር!! ይዘዋቸው የገቡት ከባድ መሳሪያዎች ከጥቅም ውጭ ተደርገዋል። #StopAmharaGenocide #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪👊
✅ጎንደር ላይ የከሸፈ ፕሮፖጋንዳ ሊሠሩ አስበዋል። ከከተማዋ ዙሪያ ገባውን በወገራ በአርማጭሆ ጠገዴ፣ በቋራ መተማ ፣ በድፋን ደንቢያ አለፋ ጣቁሳ ጫንዳባ ጭልጋ አይንባ፣ በማክሰኝት በአይንባ በድፍን በለሳ እስከ ሊቦከምከም አዲስ ዘመን ሙሉ ደቡባዊ ጎንደር እየተቀጠቀጠ የሚገኘው አገዛዙና እስከ ገዳይ ቡድኑ ጎንደር ከተማ ጎሃ ሄቴል በሄሊኮፕተር በማረፍ ወይም ከኤርፖርት እስከ ጎሃ ሂል ሪዞርት ድረስ በብረት ለበስ ታንክ በመድረስ ፎቶ ለመነሳት አቅዷል። በዚህ የፎቶ መነሳት መርሃ ግብር አብይ ይገኛል እየተባለ ነው። መንገዶች ሁሉ እሾህ መሆን አለባቸው። #StopAmharaGenocide #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪👊
የጥንቃቄ መረጃ !! ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ለአንገር ጉትን ከተማና አካባቢው አዋሳኝ የሆነችው ሀሮ ሊሙ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ገብታለች ጉዟቸውን ወደ አንገር ጉትን ሊያደርጉ ስለሚችሉ የአካባቢው ማህበረሰባችን አስፈላጊወን ጥንቃቄ ያድርግ መከላከያ ተብዬው በአሻጥር አንድም ጥይት ሳይተኩስ ወደ አዋሳኝ ወረዳዎች ማለትም ኤበንቱና ወደ ቤኒሻንጉልጉምዝ ከማሽ ዞን ፈርጥጦ ወቷል ጥንቃቄ‼️ ሼኔውም ብዛት ሀይል እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል በአሁኑ ስዓትም ሀሮ ሊሙ ከተማ ውስጥ እዬጨፈሩ ይገኛሉ‼️ #StopAmharaGenocide #ድል_ለአማራ_ህዝብ 💪👊
“...ተነሥቶአል...” ማቴዎስ 28፥6 እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! መልካም የፋሲካ በአል!
ፋሲካን ከአማራ ፋኖ ከጎንደር ጋር !! May 05/2024, 1:00 pm EST phone /Zelle: 1 202 509 1952 PayPal: janwafig10@gmail.com CasjApp: 1 202 509 1952
без подписи
без подписи
አሁን በትክክል በናዝሬት ያለው ሁኔታ ከቋንቋ አንጻር ብዙ የተለየ አይደለም፡፡ ከ75% ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው ባይ ነኝ፡፡ ከአራት አመት በፊት ናዝሬት ሄጄ ነበር፡፡ ሌላውን ማህበረሰብ ልምሰል ብዬ በአውቶቢስ ነበር ከአዲስ አበባ የሄድኩት፡፡ ናዝሬት መናኸሪያ ወርጄ በባጃጅ ነበር ከተማዋን ፣ ትናንሽ መንደሮች ሳይቀር የዞርኩት፡፡ ኦሮምኛ የሚናገር አንድም አልሰማሁም፡፡ ምን አልባት ከፍታ ላይ የገነቡት፣ ከአብዛኛው የናዝሬት ህዝብ ራቅ ብሎ ያለ፣ እስር ቤት ወይንም አንድ የተለየ ነገር የሚመስለው ጨፌው ያለበት አካባቢ ካልሆነ በቀር፡፡ እዚያ ልሄድኩም፡፡ እንደዚያም ሆኖ እነርሱ ያሉትን ተቀብለን ፣ እሺ 30% አማራ ነው ናዝሬት ውስጥ ያለው ብለን ብንቀበል፣ 30% የሚሆነውም ቀላል ቁጥር አይደለም፡፡ ናዝሬት ግማሽ ሚሊዮን ደርሳለች ብንል እንኳን፣ ወደ 170 ሺሂ የሚሆነው አማራ ነው ማለት ነው፣ በነርሱ ስሌት፡፡ ይህ ህዝብ በአማርኛ አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉ በራሱ ዘረኝነትና ኢፍትሃዊነት አይደለም ?????? © ግርማ ካሳ
የማይጮህለት የናዝሬት ህዝብ፣ የናዝሬት አማራ‼️ * ስለ ናዝሬት ከተማ ትንሽ ጀባ ልበላችሁ፡፡ ዘረኛው የኦሮሞ ብልጽግና ኦነጋዊዉና ጨፍላቄ አገዛዝ፣ በአሁኑ ወቅት በናዝሬት የሚኖሩ አማራዎችንና አማርኛ ተናጋሪዎች ፋኖ ናችሁ እያለ እያዋከበና እያሸበረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የኦሮሞ ብልጽኛዎች መለያቸው አንደኛ ዘረኝነታቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ሌብነትና ዘራፊነነታቸው ነው፡፡ ሶስተኛ ደግሞ በአማራውና ትናንሽ አማራዎች በሚሏቸው ላይ ያላቸው ጥላቻ ነው፡፡ ከሁለት አመታት በፊት ከህወሃት ጋር ይደረግ በነበረው ጦርነት አጋጣሚዉን በመጠቀም ከፍተኛ ኝዘብና ሃብት ከተጋሩ ሲዘርፉ ነበር፡፡ ጁንታ ናችሁ እያሉ ያልፈጸሙባቸው ግፍ የለም፡፡ አሁን ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ፋኖ ናችሁ እያሉ እየፈጸሙት ያለው፣ ብዙ ያልተወራና ያልተሸፈነ ግፍና ሰቆቃ አይጣል ነው፡፡ ብዙ የናዝሬት ወጣቶች በገፍ አስረው ደ ማይታወቅ ቦታ እየወሰዷቸው ነው፡፡ አዲስ አበባ ፒያሳ ፈረሰ ስንል፣ ናዝሬት ወገኖች ብዙ ፣ እጅግ በጣም ብዙ አስከፊ ነገሮች እየተሰሩ ነው፡፡ ሰዎቹ አግጠው፣ አፍጠው በናዝሬት በሚኖረው አማራ ላይ በጭካኔ ነው የተነሱት፡፡ ለማጥፋት፡፡ ናዝሬት የተቆርቆረችው በ1916 ዓ/ም ነው፡፡ ከጅቡቲ አዲስ አበባ በሚወስደው የባቡር መስመር ላይ በተለያዩ ቦታዎች የባቡር ጣቢያዎች ሲዘረጉ፣ እነዚህ ጣቢያዎች ከተማ ወደ መሆን አደጉ፡፡ ድሬዳዋ፣ ወለንጭቲ፣ መተሃራ፣ ሞጆ፣ አዎን ናዝሬት በሙሉ የተቆረቆሩት ከባቡር ህዲዱ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በአጭርይ አነጋገር በቀጥታን በተዘዋዋሪ መንገድም እነዚህን ከተሞች የቆረቂሩት አጤ ሚኒሊክ ነበሩ ማለት ነው፡፡ ናዝሬት የሚለውን ስያሜ የሰጡት፣ በአንዘሬት ያለው ጣቢያ ከተራ መንደርነት ትንሽ ዘመናዊ ከተማነት እንዲቀየር ሲደረግ፣ አጤ ኃይለስላሴ ነበሩ ይባል፡፡ ከዚያ በፊት ናዝሬት ከጣቢያው ውጭ ባዶ መሬት ነበረች፡፡ ቦታው እምብዛም ለርሻ አመች ስላልነበረም ብዙ ገብሬዎች በዚያ ይኖሩ አልነበረም፡፡ ከናዚዝሬት ትንሽ ራቅ ብሎ ወደ አርሲ፣ ከሞጆ በስተሰሜን ደብረ ዘይት በመሳሰሉት እንጂ፡፡ በዚያ በብዛት የነበረ ቋልቋል ነበር፡፡ በኦሮምኛ ቁላቋል ማለት አዳሚ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አዳም የሚል ቃል የመጣው ከዚያ ሳይሆን እንዳልቀረ ይነገራል፡፡ የቁል ዛቻ ያለበት ቦታ እንደማለት ነው፡፡ አዳማ የሚባል ከተማ አልነበረም፡፡ አዳሚ የሚባል የቁልቋል ዛፍ የነበረበት ቦታ እንጂ፡፡ ይሄን ብዬ በናዝሬት አሁን ስላለው ሁኔታ ልምጣ፡፡ "እስቲ አሁን የናዝሬት ከንቲባ ማን ነው ?" በሚል የናዝሬት ከተማ አስተዳደር ኦፌሴል ድህረ ገጽ ሄድኩ፡፡ መረጃ ለማግኘት፡ ሃይሉ ጅልዴ ይባላል ከንቲባው፡፡ ፎቶው ዋና ገጹ ላይ ይታያል፡፡ ይህ ሰው በናዝሬት እየሆነ ላለው ነገር ዋና ተጠያቂ እንደሆነ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ የናዝሬት ከተማ የአዲስ አበባ ታናሽ እህት ናት፡፡ አብዛኛው ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ነው፡፡ ድህረ ገጹን ስናይ ግን፣ መረጃ ለማግኘት፣ ላቲን ወይንም ቁቤ የማባለውን የሚያነብ ሰው ካልሆነ፣ ምንም አይነት መረጃ ማግኘት አይችልም፡፡ በአማርኛ ምንም ነገር የለም፡፡ እንግሊዘኛም ትንሽ ወደ ታች ወረድ ስንል እናገኛለን፡፡ ሌላው ገጹ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ የለም፡፡ እነርሱም ራሳቸው የብሄር ብሄረሰብ የሚሉት ኮከብ ያለበትም ሳይቀር፡፡ አቶ ሃይሉ ጅልዴ የናዝሬት ከንቲባ የሆነው፣ በናዝሬት ህዝብ ተመርጦ አይደለም፡፡ በሺመልስ አብዲሳ በቀጥታ ተሹሞ ነው፡፡ የናዝሬት ከንቲባዎች በሙሉ ህዝብ መርጧቸው ሳይሆን ተሹመው ነው፡፡ ከዚያ በፊትም፣ አቶ አብርሃም አዶሌ፣ አቶ በከር ሻሌ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽ፣ አቶ ጉቱ፣ አቶ ጀማል አባስ፣ አቶ ሀብታሙ ሃይለሚካኤል፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ አቶ አሰገድ ጌታቸው ወዘተ ሁሉም የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆነው የሰሩት፣ የናዝሬት ልጆች አይደሉም፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ሆነው ከሌላ ቦታ የመጡ ናቸው፡፡ እነዚህም ከላይ እንደገለጽኩት አንዳቸውም በአዳማ ከተማ ሕዝብ አልተመረጡም። በቀጥታ በኦሮሞ ክልል ርእስ መስተዳደሮች ነው የተሾሙት። ከነዚህ ከንቲባዎች ደግሞ ጥቅት የማይባሉ ቢያንስ ወደ ስድስት ከንቲባዎች በሙስና በዘረፋ ከሃላፊነታቸው የተነሱ ናቸው፡፡ አቶ ጉቱ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። የናዝሬት/አዳማ አብዛኛው ኦሮምኛ የማይናገር ነዋሪ ከከተማዋ መስተዳደር መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት ችግር አለበት። ጉዳዮችን ለማስፈጸም ሰነዶችን ፣ ፎርሞችን ለአስተርጓሚ ከፍለው አስተርጉሞ ነው የሚያቀርቡት፡፡ ደብዳቤዎችን ወደ ላቲን/ቁቤ ለማስቀየር ለተርጓሚዎች በገጽ አንድ ሺህ ብር አካባቢ ነው የሚከፍሉት፡፡ ናዝሬት ውስጥ ላለ ስራ፣ የቅጥር ማስታወቂያ የሚወጣው ናዝሬት ከተማ ውስጥ አይደለም፡፡ ባሌ፣ አርሲ ፣ ወለጋ በመሳሰሉት ቦታዎች ነው፡፡ ከ15 አመት በፊት በተደረገው የህዝብ ቆጠራ 75% የሚሆነው ነዋሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ አልነበረም፡፡ ከ15 አመት በፊት የተደረገው ሆን ተብሎ የአማራ ቁጥር እንዲያንስ በተደረገው ህዝብ ቆጠራ፣ 39 ኦሮሞዎች፣ 34 አማራዎች ነበር የሚሞሩት፡፡ ኦሮሞ ወይም ውህድ ኢትዮጵያዊ፣ ጉራጌ ወዘተ ሆነው አማርኛ ተናጋሪዎች ስለነበሩ፣ የአማርኛ ተናጋሪው ቁጥር ከአማራዎች ቁጥር ብዙ ጊዜ በከተሞች ከፍ ይላል፡፡ 60% አማርኛ ተናጋሪ ነበር፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪው 25% ብቻ ነበር፡፡ እርሱም ደግሜ እላለሁ ቁጥሩ ተጋኖ ነው፡፡ የኦሮሞ ብሄረተኞች በናዝሬት አሁን ኦሮሞ 46% ነው ብለው ይከራከራሉ፡፡ አማራችን ደግሞ ከ60 በመቶ ወደ 31 በመቶ ያወርዷቸዋል፡፡ እርግጥ ነው፣ በርካታ አማራዎች፣ ወይም ውህድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ፣ በናዝሬት የአፓርታይድ አሰራር ስለሆነ ያለው፣ ኦሮሞ መባል ጥቅም ስላለው፣ ኦሮሞ አለመሆን ጉዳት፣ መገደልም መፈናቀል ስለሆነ፣ ኦሮሞ ነን ማለት ጀምረዋል፡፡ በወለጋ "ወላሂ አማራ መሆን አቆማለሁ" እንዳለችዋ ልጅ ፣ ብዙዎች ለደህንነታቸው ሲሉ "ኦሮሞ" ሆነዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ የአማራ ቁጥር ቀንሶ የኦሮሞ ቁጥር ቢጨምር በተወሰነ መልኩ ሊጨምር ይችላል፡፡ እርግጥ ነው ዴሞግራፊን ለመለወጥ በሚል ከሌሎች የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦሮሞ አስፍረዋል፡፡ ሆኖም የኦሮሞ ብሄረተኞች የሚሉትን ያህል ግን የአማራ ቁጥር አላነሰም፡፡ አሁንም በናዝሬት አማራዎች በቁጥር አንደኛ ናቸው፡፡ አንደኛ አዲስ አበባ እየሰፋች በመምጣቷ፣ ፈጣኑ መንገድ በመሰራቱ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬት የገቡ አማራዎች ብዙ ናቸው፡፡ ናዝሬት የአዲስ አበባ 'አካል" እየሆነች በመሆኑ፡፡ ሁለተኛ ከአርሲ፣ ከባሌ ከሸዋ ራቅ ባሉ የኦሮሞ ክልል ይኖሩ የነበሩ አማራዎች በዘር ፖለቲካዉና በግፍና ሰቆቃ ምክንያት እየሸሹ፣ እየተፈናቀሉ በብዛት የመጡት ወደ አዲስ አበባባና አዲስ አበባ ዙሪያ ወዳሉት እንደ ናዝሬት ወዳሉ ከተሞች ነው፡፡ በመሆኑም የዲሞግራፊ ለውጥ ለማድረግ ተብሎ የመጡትን የሚያጣጣ ኦሮሞ ያልሆነ ማህበረሰብ በግሉ በብዛት ወደ ናዝሬት መጥቷል፡፡
ሰበር ዜና! አርብ ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ሰንበት ደብር ወደሚባል ጊዜአዊ ካምፕ እንዲገቡ ከተደረጉ 84 የብአዴን አድማ ብተናወች ውሰጥ 34ቱ ዛሬ ምሽቱን ከድተዋል። ንሥር ከቦታው ለማረጋገጥ ችሏል። © ንሥር ብሮድካስት መረጃ #StopAmharaGenocide #ድል_ለአማራ_ፋኖ 💪👊
በጉራጌ ዞን ያለው ዘር ተኮር ጥቃትና አፈና!‼️ ***** የአብን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ የነበረው አቶ ምኒልክ ሀይሌ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ መታፈናቸው ተሰማ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዞኑ ከኦሮሚያ ክልልና አዲስ አበባ ቀጥሎ አማራዎች እየታደኑ የሚታፈኑበት አካባቢ ከሆነ ውሎ አድሯል። በአካባቢው አማራዎችን ብቻ በማንነታቸው ለይቶ ወደ ጨለማ ቤት ማጋዙና ደብዛቸውን ማጥፋቱ የተለመደ ሆኗል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ከነበረው ከአቶ ምኒልክ ሐይሌ በተጨማሪ ከሰሞኑን ብቻ የሚከተሉት አማራዎች በሌሊት መታፈናቸው ታውቋል። 1) ዘመተ አይፎክሩ - የአበሸጌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ባለሙያ የነበረ፣ 2) ዳሰለኝ ወርቁ - የአበሸጌ ወረዳ ህብረት ስራ ማህበር ኦዲተር ባለሙያ 3) ጋሻው አንተን አየሁ - የአንቡላንስ ሹፌር 4) ወርቁ - ነጋዴ ተቋራጭ 5) ግርማ ሀይለኛው - ነጋዴ 6) ስንታየሁ ሞላ - የወልቂጤ ሞባይል ሴንተር ባለቤት 7) ፀጋዬ ምስጌ 😎 አሻግሬ 9) ብዙአየሁ ሀብታሙ በስም ከተጠቀሱት ባሻገር ሌሎች ከ70 በላይ በጉራጌ ዞን የተወለዱ ነገር ግን በማንነት አማራ የሆኑ ወጣቶች በማዕከላዊ ክልል በጉራጌ ዞን ታፍነው የት እንደተወሰዱ እስካሁን አለመታወቁን የአካባቢው ምንጮቻችን መረጃ ያስረዳል። ይህንን የጥቂት የፋሽስቱ ስርዓት አገልጋዮች ድርጊት የጉራጌ ህዝብ ሊያወግዘውና ከወንድሞቹ ጎን በመቆም ፀረ-ጭቆና አቋሙን እንዲያሳይ እንጠይቃለን። ከዚህ በተጨማሪም የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡም ከኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስአበባና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በጉራጌ ዞን የሚደረጉትን ዘር ተኮር ጥቃቶችንና አፈኖዎችን እንዲመረምርና ድርጊቱ እንዲያወግዝ እንጠይቃለን።
без подписи
ኢትዮ 360 በሚያዚያ 25/2016 የዛሬ ምናለ የቀጥታ ስርጭቱ "የወልቃይት ጉዳይና በሁሉም አቅጣጫ ድል የቀናው የፋኖ ትግል!"በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ መረጃዎችን ወደ እናንተ ያደርሳል።የኢትዮ 360 የሚኒሊክ ሳተላይት ቴሌቪዥንን፣የዩቲዩብ፣የረምብል፣የቲዩተር፣የቴሌግራም፣የፌስቡክና ሌሎች ገጾቹን ሰብስክራይብ፣ላይክ፣ሼር፣ሪቲዩት፣ሪፖስትና ፎሎው በማድረግ እንዲሁም ኢትዮ 360ን በገንዘብና በሁሉም መንገድ በመደገፍ አብራችሁን ሁኑ የምንለው በአክብሮት ነው። ኢትዮ 360 Channel 94 የዛሬ መግብያ ነው ። ሰብስክራይብ 1000 መሙላት አለበት 👇👇👇👇 https://www.youtube.com/live/Xsf_ugAnTZE?si=RBjBeDbdzodE4VeU
የድል መረጃ ከወሎ‼️ * በቅርቡ ውህደት የፈፀሙት የወሎ ዕዝ ፋኖ እና የምስራቅ አማራ ፋኖ የነፃነት እሾህና አሜካላ የሆኑ የገዢው ቡድን ወታደሮችን እያፀዱ ወደ ደሴና ኮምቦልቻ እየገሰገሱ ነው! በሰሜን እና በደቡብ ወሎ ዞን አዋሳኝ አከባቢዎች ላይ እየተደረገ ያለው ውጊያ ቀጥሏል! በደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው በውጫሌ ከተማ ዙሪያን ጨምሮ በሮቢት፣በጎልቦ፣ በአበትና በማርየ እንዲሁም በሰሜን ወሎ ዞን ውርጌሳ ከተማ፣ኤላ፣ቀይ አፈር፣ሊብሶ፣ መሃል አምባና ቆንጥር በተባሉ አከባቢዎች ላይ ከንጋት ጀምሮ በክንደ ነበልባሎቹ የህዝብ ልጆችና በብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ ወታደሮች መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መዋሉን የአማራ ድምፅ ሚድያ የወሎ ዘጋቢዎች አረጋግጠዋል። ቀኑ ዝናባማ ነው፣ እነዛ እንደ አራስ ነብር የተሶሮፉት የወሎ ጀግኖች ከምሽግ ምሽግ እየተራመዱ በአገዛዙ ወታደር ላይ ከዝናቡ ጋር ቀላቅለው የእሳት በረዶ ሲያዘንቡበት ውለዋል። በተለይ እስከ ረፋድ ባለው በውርጌሳ ከተማና በዙሪያዋ በተደረገ ውጊያ እርምጃ የተወሰደበት ሙትና ቁስለኛ የአገዛዙ ወታደር በዚህ ምሽትም የሚያነሳው አጥቶ በየማሳው ወድቋል ሲሉም የውጊያ ባለሟሎቹ የወሎ ጀግኖች ለአማራ ድምፅ ሚድያ አሳውቀዋል። ከፋኖ ጋር የእጅ በእጅ ውጊያ ማድረግ ያቃተው አማራ ጠሉ ኃይል፡ በአሁን ሰዓት ከቀይ አፈር እስከ መሃል አምባ፣ ከሊብሶ እስከ ኤላ በከባድ መሣሪያ እየደበደበ ቢሆንም በላያቸው ላይ የሚያጓራውን መድፍና ዙ23 ከመጤፍ ያልቆጠሩት ቆንጆዎቹ፡ በያዙት ብሬንና ስናይፐር እንዲሁም ክላሽ የጠላትን ኃይል ለይተው ግንባር ግንባሩን እየመቱ እያጋደሙት ነው። ድምፅ አልባው ሚሳኤል በመባል የሚታወቀው ሻለቃ ድርሳን ብርሃኔ የሚያዋጋው ግዙፍ የፋኖ ጦር ውጫሌ ከተማ ዙሪያውን ጨምሮ በሮቢት፣በጎልቦ፣በአበትና በማርየ የገባውን የጠላት አብይ አህመድን ወታደር እንደ ደረቀ ዛፍ ቅጠል ሲያረገፈው ውሏል። በሁለቱ ዞን አዋሳኝ አከባቢዎች ላይ በሚደረገው ውጊያ የጠላትን አንገት እየቆለመሙ እየጣሉ ያሉት እንደ አዲስ በተቋቋመው የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ ልጅ እያሱ ክ/ጦር፣ መቅደላ ፅናት ክ/ጦር፣ ዞብል አምባ ክ/ጦርና የራያ ሻለቃ አናብስቶች መሆናቸውንም ነው ያረጋገጥነዉ። #StopAmharaGenocide #ድል_ለአማራ_ፋኖ 💪👊