ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)
Статистика🌷ይህ ቻናል የተከፈተው ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን ዋና አላማውም ምዕመናን በንስሐ ህይወት ተመላልሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድወርሱ የሚያስችል ትምህርት መስጠት ነው፡፡ 🌷💚የቅዱሳን ገድላት 🌷💛ስንክሳር 🌷♥ ቅዱሳን ስዕላት መንፈሳዊ ትምህርቶችና ጽሑፎች 🎤 ስብከቶች ............ይቀርቡበታል፡፡🌎
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 159
- 1/48двое суток
- 182
- 1/72трое суток
- 196
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
@mahiberekidusan
የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ #ሼር-ያድርጉ @mahiberekidusan @mahiberekidusan
የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ #ሼር-ያድርጉ @mahiberekidusan @mahiberekiduaan
👉 ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ በሁለተኛው ክፍል ለክርስቶስ ምሳሌ ሁኖ የቀረበውን ወፍ ታሪክ ላጋራችሁ ስለ ከራድዮን ወፍ ምን ያክል እናውቃለን "ከራድዮን ወፍ ምንድነው ከራድዮን ነጭ ወፍ ሲሆን በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው። ጠቢባን በድካም ፈልገው አድነው ይይዙታል፣ የታመመ ሰው ቢኖር ያቀርቡታል ፤ እሱም በሽተኛውን ትኩር ብሎ ያየዋል የማይድን ለሞት የቀረበ ከሆነ ፊቱን ይመለሳል፣ የሚድን ከሆነ ግን አፉን ከፍቶ ከበሽተኛው አፍ አድርጎ እስትንፋሱን ይወስዳል፣ የሰውየው ደዌ ሙሉ ለሙሉ ወደ ወፉ በእስትንፋሱ ይተላለፋል። ሰውየው ይድናል ወፉ ይታመማል። 👉ነጭ የነበረው እንደ ክሰል ይጠቁራል፣ ህመም ሲሰማው ወደ አየር ይነጠቃል ሲብስበት ወደ ባሕር ራሱን ይወረውራል። በባሕር 3 መዓልት 3 ሌሊት ቆይቶ ጽጉሩን መልጦ አዲስ ጸጉር ተክቶ ፣ድኖ፣ታድሶ፣ኃያል ሆኖ ይወጣል። ይህን ወፍ ሊቃውንቱ የክርስቶስ ምሳሌ ወይም የምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ምሳሌ አድርገውታል ከራድዮን ወፍ ---- የክርስቶስ ምሳሌ የታመመው ሰው --- የአዳም ዘር ምሳሌ ሲሆን ወፉ በዐይኑ መመልከቱ --- በክርስቶስ ላመነ ሁሉ ድኅነት ምህረት ማግኘቱ ምሳሌ ወፉ መታመሙ---- ክርስቶስ ስለ እኛ በደል መታመሙ ምሳሌ። መጥቆሩ ---- ስለእኛ ቤዛ ከኀጢአተኛ የመቆጠሩ ምሳሌ ወፉ ወደ ላይ መውጣቱ---- ክርስቶስ ከፍ ብሎ መሰቀሉ ምሳሌ ወፉ በባህር 3ቀን 3ሌሊት መኖሩ ----ክርስቶስ በከርሰ መቃብር 3ቀን 3 ሌሊት መቆየቱ ምሳሌ 👉ከራድዮን ወፍ ታድሶ ኃያል ሆኖ ከባህር መውጣቱ -ክርስቶስ በሲዖል የነበሩ ነፍሳትን አድሶ አንጽቶ ገነት አስገብቶ፤ እርሱም ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በለበሰው ሥጋ ወደ ቀደሞ መለኮታዊ ሥልጣኑ ኃይሉ መቀመጡ ምሳሌ ነው። የታደለው ወፍ የክርስቶስ ምሳሌ ሲሆን ያልታደለው የሰው ልጅ የክርስቶስ ምሳሌ መሆን ሲገባው የዲያብሎስ ምሳሌ ሆነ 🤔🤔🤔 በኦሪቱ ፈርዖን እና ሠራዊቱ በዲያብሎስ በአጋንንት ተመስለዋል ግብጽ የገሃነም ወይም የሲዖል ምሳሌ ሁናለች። @mahibrrekidusan
የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ #ሼር-ያድርጉ @mahiberekidusan @mahiberekidusan
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የአርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ #ሼር-በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዎን ይወጡ። @mahibetekidusan @mahiberekidusan @mahiberekidusan
ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan): በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ አሜን። #ጾመ_ፍልሰታ ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው። እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም #ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው። ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል። በአጠቃላይ #የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ #የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን :: ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞች እና እህቶች ሆይ ለኦርቶዶክሳዊ ወንድምዎ እህትዎ ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያናችንን ቀጥተኛ ትምህርት ያሳውቁ ይመስክሩ ። 👇👇👇👇👇👇👇👇 👇@mahiberekidusan 👇@mahiberekidusan @mahiberekidusan 👆👆👆👆👆👆👆👆 የአርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ #ሼር-በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዎን ይወጡ። @mahibetekidusan @mahiberekidusan @mahiberekidusan
#ቅዱስ_ገብርኤል እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!! በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡ በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡ ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡ መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡ መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡ እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡ ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡ አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።🙏🙏🙏Ⓜ #ይቀጥላል 💚 @mahiberekidusan 💚 💛 @mahiberekidusan 💛 ❤️ @mahiberekidusan ❤️
"እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ 'በእውነት እየባረክኹ እባርክኻለኹ:: እያበዛኹም አበዛኻለኹ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲኹም እርሱ ከታገሠ በኋላ ተስፋውን አገኘ::" ዕብ. ፮:፲፫ @mahiberekidusan
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ፣ ለቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ)፣ ለብሥራተ ልደተ ይስሐቅ፣ ለታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ኹሉ አለቃ)፣ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮጵያዊ የሃይማኖት ምሰሶ)፣ ለቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ)፣ ለአባ መቃቢስ እንዲኹም ለአባ አግራጥስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 "ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!" ዳግመኛም ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት፣ አባ ባውላ ገዳማዊ እንዲኹም ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ @mahiberekidusan 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
ቅዱስ ጳውሎስ ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል። የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19) ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ። ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ። ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ። የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት። ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል። ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው። ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @mahiberekidusan💚 💛 @mahiberekidusan💛 ❤️ @mahiberekidusan❤️
ወበዛቲ ዕለት ሐምሌ ፭ “ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ” “ክበር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር፤ (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ. ፻፲፭/ ፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15) “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።” ማቴ.፲፫፡፲፩ እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታቱ ለቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት ቀን በዓላቸው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ አሜን። ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኰኩሐ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ ስምዖን ነው። ዮሐ.፩፡፵፭ (1፥45)፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል። እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መነኸርያ በነበረችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡ ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ይተዳደር የነበረው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ነበር። ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗለ። ማቴ. ፬፡፲፱ (4:19) ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን ዕዳ በዕዳ ከተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋያ ነውና ሮምን ደርቦ ሰርቶታል። በሮምም ፳፭ (25) አስተምሯል። ከዚያ በፊ ግን በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣በቀጳዶያና በቢታኒያ አስተምራል። በትምህርቱም ጣቢታ ከሞት አስነስቷል። ሐዋ. ፱፡፴፪-፴፬ (9፡32¬-34) ያስተማራቸው ምዕመናም ከሃማኖታቸው እንዳይወጡ ፪ (2) መዕክታትን ጽፎላቸዋል። ንጉሱ ኔሮን ቄሳር ጣኦት አምላኪ ነበርና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር። ለጣዖትም እንዲሰግድ ባስገደደው ጊዜ ለጣኦ አልሰግድም በማለቱ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት። አይሁድ ሲጣሉት ወደ ጌታ ቢያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር። ይዞ ዳግም ቢሰቅሉትም ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው። በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅሎታል። ሥጋውን ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንቦ እንዳይፈርስ በማረ በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @mahiberekidusan💚 💛 @mahiberekidusan💛 ❤️ @mahiberekidusan❤️
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም፣ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ለቅዱሳን 72ቱ አርድእት (ዛሬ ኹሉም ይታሠባሉ)፣ ለቅዱስ ሳቁኤል ሊቀ መላእክት፣ ለቅድስት መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ሚስት)፣ ለቅዱሳን ዘደብረ ዓሣ እንዲኹም ለቅዱሳት አንዕስት (ዴውርስ: ቃርያ: አቅባማ: አቅረባንያና አክስቲያና-የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮች) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 "ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!" ዳግመኛም ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ፣ ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ እንዲኹም ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ) ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ @mahiberekidusan 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)፣ ለቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)፣ ለአባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ) እንዲኹም ለቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ (ከ36ቱ ቅዱሳት አንዕስት-የአልዓዛር እህቶች) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 "ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!" ዳግመኛም ዛሬ ሰኔ 30 ቀን ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)፣ አባ ሣሉሲ ክቡር፣ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት እንዲኹም ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ @mahiberekidusan 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ፣ ለቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ፣ ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፣ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት) እንዲኹም ለአባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 "ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!" ዳግመኛም ዛሬ ሰኔ 21 ቀን አበው ጎርጎርዮሳት፣ አባ ምዕመነ ድንግል፣ አባ ዓምደ ሥላሴ፣ አባ አሮን ሶርያዊ፣ አባ መርትያኖስ እንዲኹም አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ @mahiberekidusan 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንዲኹም ለቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ዕረፍቱ) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 "ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!" ዳግመኛም ዛሬ ሰኔ 20 ቀን ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)፣ ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር፣ ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ፣ ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)፣ አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና እንዲኹም ቅድስት ሳድዥ የዋሒት ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ @mahiberekidusan 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
видео или голосовое, без подписи