መጽሐፈ ስንክሳር
Статистикаበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመቱን ሙሉ የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት መታሰቢያቸው የሚታወስበት እና የተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚለቀቁበት ድረገጽ። ምስባክ፤ ማኅሌት እና ሌሎችን ለማግኘት👉 @Misbak_WeMahlet ዝማሬያትን ለማግኘት 👉 @Mezmur_ZeOrthodox21 🎯ለማግኘት ቻናላችንን ይጐብኙ። መወያያ 👉 @Mezgebe_Thewadho ለአስተያየት @Zethewahdobot
- Последний пост
- 17 июн. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 51
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://t.me/Misbak_WeMahlet/25449
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
††† እንኳን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† በዚሕች ቀን ለ40 ዓመታት በመላው ዓለም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት የተከፈቱበት ቀን ይታሠባል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:- ¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት ¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት ¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት ¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል:: ††† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :- ¤በመጸነሱ ተጸንሳ ¤በመወለዱ ተወልዳ ¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ ¤በጥምቀቱ ተጠምቃ ¤በትምሕርቱ ጸንታ ¤በደሙ ተቀድሳ ¤በትንሣኤው ከብራ ¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ ¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች:: ††† አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ200 ዓመታት እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ265 ዓ/ም የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም:: የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት (ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ) ዓለምን ለ2 ተካፍለው ክርስቲያኖችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ:: በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ ተሰጠ:: ለ40 ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ: አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ:: በአባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ ልንናገረው ከምንችለው በላይ ጭንቅና መከራ ደረሰ:: ነገር ግን ቅዱሳኑ ያን ሁሉ ችለው ጸኑ:: 47 ሚሊየን የሚያሕሉትን ደግሞ ሰይፍና እሳት በላቸው:: በዛ ዘመን አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት ከአሕጉር አሕጉር መሔድን ይጠይቅ ነበር:: ከዚሕ ሁሉ በኋላ ግን እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል" ሲል በ305 ዓ/ም ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ ከዓመታት በኋላ (በ313 ዓ/ም) ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ:: በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት (የደስታ ቀን)" ተብላ ትከበራለች:: ††† ቸሩ አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ይሠውርልን:: ከበረከቷም ያድለን:: ትውልዱ ደካሞች ነንና ከማንችለው ፈተናም ይጠብቀን:: ††† ሰኔ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 2.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት (ከታላላቆቹ ሶፍያዎች አንዷ ናት) 4.ቅዱሳት ሰማዕታት ደባሞንና ብስጣሞን (የቅድስት ሶፍያ ልጆች) 5.ቅዱስ አውሎጊስ ሰማዕት 6.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ::" ††† (መዝ. 121:1-9) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† 💚💛❤ @metsihafe_sinksar ❤💛💚 🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪 ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
без подписи
✝ሳሙኤል ነቢይ ወልዳ ለሐና፤ ወዕሌኒ ንግሥት ዘተረክበት በሲና፤ ሉክያኖስ ሰማዕት ጥዑመ ዝክር ወዜና፤ ወማኅበሩ ክቡራን ዘመርህዎ ፍና! 💚💛❤ @metsihafe_sinksar ❤💛💚 🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪 ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
без подписи
без подписи
††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል ††† ††† እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) ያስተዳድሩ ጀመር:: በዘመኑ ደግሞ ማኅጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና:: ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በሦስት ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ : ማዕጠንቱን እያሸተተ : ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) ግን በበደል ላይ በደልን አበዙ:: ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ : እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት ሦስት ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከሰላሳ አራት ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ:: ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ : የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል : የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ (ሳዖል) እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው:: ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን (ሳዖልን) ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ:: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ : ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው:: ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ : ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው : አነገሠውም:: ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ (ቀንድ) አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ :- "ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል:: ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል:: ††† ቅዱስ ሉክያኖስ ††† ††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሉክያኖስ ይታሠባል:: በቀደመ ሕይወቱ ጣዖት አምላኪና አጣኝ የነበረው ቅዱሱ ማንም ሳያስተምረው ክርስቲያኖቹን በመመልከት ብቻ አምኗል:: የወቅቱ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው : ትጋታቸው : ጽናታቸውና ፍቅራቸው እንዲሁ ይስብ ነበር:: ከእነርሱ እምነት መውጣቱን የተመለከቱ ኢ-አማንያን አታልለው ሊመልሱት ሞከሩ:: እንቢ ቢላቸው በድንጋይ ጥርሱን አረገፉት:: ደሙን አፈሰሱ:: አሁንም በሃይማኖተ ክርስቶስ በመጽናቱ በዚሕ ቀን (ሰኔ 9) ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገድለውታል:: ††† የቅዱሳኑን በረከት አምላካቸው ያድለን:: ††† ሰኔ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ 2.ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ዮሐንስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . . " ††† (ዕብ. ፲፩፥፴፪) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† 💚💛❤ @metsihafe_sinksar ❤💛💚 🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪 ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
✝ተዝካረ በዓላ ለእመ አምላክ ገሊላዊት፤ ወቅዳሴ ቤታ ለድንግል ወለተ ዳዊት፤ ፲፻ወ፪ቱ ክቡራን ሰማዕታት፤ ወቅድስት ትምዳ እመ ርማኖስ ሰማዕት! ✝እንኳን አደረሰን ! 💚💛❤ @metsihafe_sinksar ❤💛💚 🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪 ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
без подписи
+<< #ወይን_ለማይጠጣ_ሕይወቱ_ምንድን_ነው? >>+ "ምንትኑ ሕይወቱ ለዘኢይሰቲ ወይነ" (ሲራክ. 34:26) =>#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን ወይንን (ጠላ: ቢራ . . .) ¤"አትጠጡ" ብላ አትከለክልም:: ¤ግን ደግሞ "ጠጡ" ብላም አታበረታታም:: ¤አልኮል መጠጦችን መጠቀም "ኃጢአት ነው" አትልም:: ¤ግን ደግሞ " . . . ካያያዝ ይቀደዳል" እንዲሉ አጠቃቀማችን ወደ ኃጢአት ሊወስደን ስለሚችል "ጥንቃቄን አድርጉ" ትለናለች:: +በዘመናችን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ (በተለይ ለክርስቲያኖች) 2 ፈተናዎች ይታያሉ:: 1.አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን (በተለይ ወጣቱና ጐልማሳው) አነሰም በዛም ጠጪ እየሆነ ነው:: (ልብ በሉልን "ይሰክራል" አላልኩም) 2.እጅግ በሚያስቀይም መንገድ ለመጠጣት ጥቅሶች ከቅዱስ መጽሐፍ ሲጠቀሱ እየሰማን ነው:: +በተለይ "#ወይን_ያስተፌስሕ_ልበ_ሰብእ" (መዝ. 103:15) ከእኛው አልፎ በዘፈንና በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያዎች ላይ ሲጠቀስ ስንሰማ አንጀታችን ካላረረ የቁም ሙት ሆነናል ማለት ነው:: +አሕዛብ ከመጽሐፋቸው አንዲት ዘለላ ብትነካ ሃገሪቱን በተቃውሞ እንደሚንጧት እናውቃለን:: ¤እኛ ግን #የሊቀ_ሰማዕታት ስም የቢራ ማሻሻጫ ሲሆን: #ቅዱስ_ቃሉ ለአልኮል መጠጥ ሲጠቀስ: #በአባቶቻችን_ካህናትና_ጻድቃን ላይ በፌዘኞች (ኮሜዲያን ነን ባዮች) ሲቀለድ: ማንም ባለጌ በተቀደሰች ሃይማኖታችን ላይ አፉን ሲከፍት ምንም አይመስለንም:: (አንቀላፍተናላ!!!) =>ወደ ጉዳዬ ልመለስና የወይንን ነገር እንጨዋወት:: "የትውልዱ ክፋቱ ኃጢአት መሥራቱ አይደለም:: ይልቁኑ ኃጢአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስመሰሉ እንጂ" ብለውኛል የኔታ ክንፈ ገብርኤል:: (በቀኝ ያቁማቸውና!!!) +ዛሬ በሃገሪቱ የሚገኘውን ጠጪ (ካልጠጣ የሚሞት የሚመስለው) በመቶኛ/በ% ቢሰላ አብዛኛው (ምናልባት እስከ 90 % ) ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ባይ ነው:: +ታዲያ ይህ ጥራዝ ነጣቂ ትውልድ ለምን ስትሉት "ዳዊት እንዲህ አለ: ሐዋርያው ቅ/ዻውሎስ እንዲህ አከለ . . ." ይላል:: << ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ስለ ወይን መጠጣት የሚናገሩ ቃላት ትርጉም እንደሚባለው ነው?? #ለመሆኑ_ቅዱስ_መጽሐፍ_ጠጪነትን_ያበረታታል?? አምላካችን እግዚአብሔርስ ወደዚህች ምድር ያመጣን ለዚሁ ግብር ነው?? (ሎቱ ስብሐት!!!) >> +ቅዱስ ቃሉን ለገዛ ፈቃድ መተርጐም ፍጹም ኃጢአት ነው:: (2ዼጥ. 1:20) ስለዚህም "ወይን" የሚሉ ቃላት ምንድን ናቸው? ወደሚለው እንመለስ:: +በመጀመሪያ ግን #ብርሃነ_ዓለም: #ዓዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ) #ቅዱስ_ዻውሎስ ለደቀ መዝሙሩ #ቅ/ጢሞቴዎስ ስለ ምን "ውሃ ብቻ አትጠጣ:: ጥቂት ወይን ጨምር" አለው ቢሉ:- 1.ወይን በዘመኑ ለሆድ በሽተኞች ፍቱን መድኃኒት ስለ ነበር ነው:: (ቃሉም የሚለው ስለ ሆድህ ህመም ነው(1ጢሞ. 5:23)) ቅዱሱ ከገድል የተነሳ ሆዱ ፍጹም ሕመምተኛ ነበርና:: 2.ወይን መጠጣት በልኩ (ጥቂት) የሆነ እንደሆን አካልን ያለመልማል:: ልቡናን ያረጋጋል:: ግን በጊዜው: በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ነው:: +#ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ ግን "ወይን" ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው በርካታ መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ:: እነዚህን መነሻ ርዕስ ባደረግነው: በቃለ ሲራክ ተመርኩዘን እንመልከታቸው:: =>ነቢዩ "#ወይን_ለማይጠጣ_ምን_ሕይወት_አለው?" ይላል:: 1.ወይን=(#ምስጢረ_ሥላሴ) ¤"ምስጢረ ሥላሴን ላላመነ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ይለናል:: የእግዚአብሔርን አንድነት: ሦስትነት ሳያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወት የለምና:: (ዮሐ. 1:12, 3:17, ማቴ. 28:19) +ምስጢረ ሥላሴ በወይን መመሰሉን #አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው "አብ ጉንደ ወይን: ወልድ ጉንደ ወይን ወመንፈስ ቅዱስ ጉንደ ወይን . . ." ሲል ነግሮናል:: 2.ወይን=#ክርስቶስ (#ምሥጢረ ሥጋዌ) ¤በወልድ (ክርስቶስ) ያላመነ የዘለዓለም ሕይወት የለውም:: (ዮሐ. 3:36) ስለዚህ ነገር ጌታችን ራሱን የወይን ግንድ: አባቱን ተካይ አድርጐ ሲጠራ እንሰማዋለን:: "#አነ_ውእቱ_ጉንደ_ወይን=እኔ የወይን ግንድ ነኝ" እንዲል:: (ዮሐ. 15:1) +መዳን የሚቻለውም መድኅን ክርስቶስን "#አምላክ_ወልደ_አምላክ: #ወልደ_አብ_ወልደ_ማርያም: #ሥግው_ቃል" ብሎ ማመን ሲቻል ነው:: 3.ወይን=#ድንግል_ማርያም (#ነገረ_ማርያም) ¤ጌታን ወይን ካልን ድንግል ማርያምን #ሐረገ_ወይን: #አጸደ_ወይን ልንላት ግድ ይለናል:: (እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ) +መዳንን የሚሻ ሁሉ እመቤታችን ማርያምን #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን: #ዘለዓለማዊ_ድንግልናዋን: ፍጹም ሞገስ ያላት #አማላጅ መሆኗን: #ቅድስናዋንና #ክብሯን ሊያምን ግድ ይለዋል:: (መዝ. 44:9, 86:5, ኢሳ. 1:9, 7:14, ሕዝ. 44:1) 4.ወይን=#ቅዱሳን (#ነገረ_ቅዱሳን) ¤መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን የወይን ግንድ ብሎ አልቀረም:: ወዳጆቹን #ወአንትሙሂ_አዕጹቂሁ=እናንተ የወይኑ ቅርንጫፎች ናችሁ" ይላቸዋል:: (ዮሐ. 15:5) +ስለዚህም በቅዱሳን #ክብር: #አማላጅነት: #ፈራጅነትና #የጸጋ_አማልክትነት ልናምን ግድ ይለናል:: (ዘጸ. 7:1, መዝ. 81:1, ማቴ19:28) 5.ወይን=#ሥጋ_ወደሙ (#ምስጢረ_ቁርባን) ¤#እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ቸር ልጇን የጠየቀችው ስለጊዜአዊው መጠጥ ቢመስልም ምስጢሩ ግን ለዘለዓለማዊው መጠጥ (ክቡር ደሙ) ነው:: (ዮሐ. 2:1) +ለዚያም "#ወይንኬ_አልቦሙ=ወይንኮ የላቸውም" ስትለው: "ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ=እናቴ ሆይ! በቀራንዮ አንባ ሥጋና ደሜን የምሰጥበት ጊዜየ ገና ነው" ሲል የመለሰላት:: +ወንጌል ደግሞ እንዲህ ይላል:: "የክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም::" (ዮሐ. 6:53) ¤የወይን ትርጉም ይቀጥላል . . . ለእኛ ግን እዚህ ላይ ይብቃን:: +ቅዱሱ #ነቢይ_ሲራክ "ወይን ለማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ሲል በአንክሮ የጠየቀው ስለዚህ ነው:: ¤በወይን በተመሰሉ #በሥላሴ: #በምስጢረ_ሥጋዌ: #በነገረ_ማርያምና #ነገረ_ቅዱሳን ሳያምኑ: ከወይኑ ግንድ ክርስቶስ ጐን በፈሰሰ #ማየ_ገቦ ሳይጠመቁና #ከቁርባኑ ሳይሳተፉ ሕይወት የለምና:: =>ቸር አምላከ ቅዱሳን የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: << ወስብሐት ለእግዚአብሔር >> 💚💛❤ @metsihafe_sinksar ❤💛💚 🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪 ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи