መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
Статистика✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞ አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ @Mente8 ተጠቀሙ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 84
- 1/48двое суток
- 96
- 1/72трое суток
- 103
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️ 💁♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️ 👨🦱🧑🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️ ⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️ 🤵♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️ በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት 👇👇👇 @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel
⛪️📚🙏 1, እመጓ 2, ዝጎራ 3, መርበብት 4, ዴርቶጋዳ 5, ዮራቶራድ 6, ዣንቶዣራ 7,መጽሐፈ ሄኖክ 8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ 9, ፍኖተ አእምሮ 9, አዳም እና ጥበቡ 10, ዝክረ መስቀል 11, ሰይፈ ሥላሴ 12, ፍትሐ ነገስት 13, መጽሐፈ መነኮሳት 14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና 16, ህግጋተ ወንጌል 17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን 18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል 19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ 20, ግድለ ተክለሃይማኖት 21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ 22, የወጣቶች ህይወት 23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት 24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት 25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ 📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖 ✝ ይቀላቀሉን ✝
ይህ የቅዳሴ ተሰጥኦ መመለሻ እና የቅዳሴ ትምህረት ለምትማሩ ከጠቀማችሁ በሚል የተለጠፈ ነው። ግዕዝና አማርኛ ትርጉሙን የያዘ ነው። ቅዳሴ ስናስቀድስ ምን ያህሎቻችን የምንመልሰውን ተሰጥኦ ትርጉም አውቀን የምንመልሰው? እንዲሁም ተሰጥኦ መመለስ ሰለማንችል ከቅዳሴ የምንቀር በቤታችን በስራ ቦታ ብቻ ባለንበት በስልካችን ለማጥናት ይጠቅመናልና ተጠቀሙበት 🙏
📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? 📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ 📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ 📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ 📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ 📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን 📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው እና የሌሎችንም ........... የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻 👇👇👇 https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
🎉ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል የ 200 ብር ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ! የንኤስ_አንበሳ የተባለው ማን ነው ?
🗓⚪️#አንድ_ጥያቄ ●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው❓ ●✥
❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ” 🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅 📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ! 📜
#ትንሣኤሽን_ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ🙏 ✍ዔደን ታደሰ @Melikt_weg_gitim @Melikt_weg_gitim @Melikt_weg_gitim #Join_and_share
без подписи
ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት አድርገው መልእክት አስተላለፉ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፣ አሜን በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺህ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን አካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ አካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን አካላት ግንኙነት በአካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ አይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከአካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ አንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር አምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል። ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን አስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ አድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ አላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብር አዞናል ከቅዱሳን ፍጥረታት መካከል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም አብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብራት እዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በአጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢአታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት አውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር አባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ነው።
без подписи
አብርሃም በዚህ ምድር ቤት አልነበረውም፤ የሚኖረው በድንኳን ነበርና በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ ሥላሴ በሰው አምሳል ተገለጡለት፡፡ በግንባሩ ተደፍቶ የአምልኮት ስግደት ሰገደላቸው፤ በአክብሮትም ተቀበላቸው፡፡ ወደ ድንኳኑ እንዲገቡም ተማጸናቸው፡፡ አስተናገዳቸውም፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች የአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፤ ምክንያቱም ሥሉስ ቅዱስ በማኅፀኗ አድረዋልና ስለዚህ ማኅደረ ሥሉስ ቅዱስ ትባላለች፡፡ ሥላሴን በማኅፀኗ ተቀብላ በትሕትና አስተናግዳለችና፡፡ አብ አጸናት፣ ወልድ ተፀነሰባት፣ መንፈስ ቅዱስ ጋረዳት፡፡/ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ፤ ገጽ 30/፡፡ በአብርሃም ድንኳን አላፊ አግዳሚው ይመግብበት፣ ያርፍበት እንደ ነበረ ዅሉ በእመቤታችንም አማላጅነትም መንገደኞች ማረፍያ፤ እንግዶች መጠለያ፤ ስደተኞች ተስፋ ያገኛሉና፡፡ ከዅሉም በላይ የነፈስ የሥጋ መድኀኒት፤ የዘለዓለም ማረፍያ፤ እውነተኛ መብልና መጠጥ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እርሷ ናትና በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ ቀትር በኾነ ጊዜ ማለትም በስድስት ሰዓት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደ ገቡ ሁሉ፣ አምስት ሺሕ አምስት መቶው ዓመት ተፈጽሞ በስድስተኛው ሺሕ ዓመት እግዚአብሔር አብ ለአጽንዖ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፤ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመልበስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አድረዋልና እመቤታችን በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ እንደ ማጠቃለያ ሐምሌ ፯ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በአብርሃም ቤት ተገኝቶ አብርሃምና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሰረበት፤ ይስሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት ዕለት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን የተናገረበት ዕለት ከመኾኑ ሌላ የአብርሃምን ዘሩን እንደሚያበዛለትና አሕዛብ ሁሉ በእርሱ እንደሚከብሩ ማለትም ከአብርሃም ዘር በተገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ አሕዛብ እንደሚቀደሱ፤ ይህንን ምሥጢርም እግዚአብሔር ከወዳጁ ከአብርሃም እንደማይሠውር ቃል ኪዳን የገባበት ቀን ነው፡፡ በዓላት የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተደረገለትን የቸርነት ሥራ በማሰብ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎና ተአምራት በመስማትና በማሰማት የተደረገውን ድንቅ ነገር በመዘከር በደስታ የሚከበሩ ዕለታት ናቸው፡፡ “በቃለ አሜን ወበትፍስሕት ድምፁ እለ ይገብሩ በዓለ፡- በዓለ የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና የምስጋና ቃል አለው” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት /መዝ.፵፩፥፭/፡፡ ዛሬም ሀብት ንብረት ያለን ምእመናን በትሩፋት ሥራ በመሠማራት እንግዶችን በመቀበል፣ ለተራቡ በማብላት፣ በመመጽወት እና በመሳሰለው ተግባር ከኖርን ለተቸገሩ በመራራት፣ በቀና አስተሳሰብ ከተጓዝን እግዚአብሔር ይባርከናል፤ ይቀድሰናል፡፡ ሐምሌ ፯ ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ አብርሃምን የባረኩትና ልጅ እንደሚወልድ፣ መጻዒው ሕይወቱን የነገሩት ዕለት ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ቸርነታቸው፣ ፍቅራቸው እንዳይለየን እንማጸናለን፡፡ የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ ዋቤ መጻሕፍት ✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ✍️ ቅዳሴ ማርያም ✍️ መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ✍️ ዓምደ ሃይማኖት ✍️ ወላዲተ አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ✍️ መለከት መጽሔት
ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል (ሐምሌ ፯) በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!! መ/ር ጌታቸው በቀለ አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አብርሃም ቤት ገብተው አብርሃምን የባረኩበት፣ በቤቱም የተስተናገዱበት፣ ሣራ ይስሐቅን እንደምትወልድ ያበሠሩበት ዕለት ነው፤ ሐምሌ ፯ ቀን፡፡ ይህ የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ታሪኩን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርገን እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ሥላሴ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስት፤ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ “ሥላሴ” የሚለው ቃል ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲኾን ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ (፲፱፻፵፰)፡፡ መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡ ገጽ ፮፻፷፱/፡፡ በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በስም፣ በግብር፣ በአካል ሦስት ናቸው፡፡ የስም ሦስትነት፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ የግብር ሦስትነት፡- አብ አባት፣ ወልድ ልጅ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ፡፡ የአካል ሦስትነት፡- አብ የራሱ የሆነ ፍጹም ገጽ መልክ አለው፤ ወልድ የራሱ የሆነ ፍጹም ገጽ መልክ አለው፤ መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ ፍጹም ገጽ መልክ አለው፡፡ የእግዚአብሔር አንድነት በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣በመለኮት በፈቃድ በመሳሰሉት ሁሉ አንድ ነው፡፡ / መ/ር ብርሃኑ ጎበና (፲፱፻፹፭)፡፡ ዓምደ ሃይማኖት፡፡ ገጽ 40/፡፡ ሥላሴ “ቅድስት” ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት(እናት) ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ “ቅድስት ሥላሴ” እያልን እንጠራቸዋለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የወረደውን፣ የመጣ የሔደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ሰይጣን ለተንኮል አያርፍምና ይህንን መልካም ግብሩን ለማሰናክል አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ፤ የተጐዳ ሰው መስሎ ከጐዳና ቆሞ አብርሃም እንግዳ መቀበል እንደ ተወ፤ እርሱ ሊበላ ሊጠጣ ከቤቱ ቢሔድ ራሱን ፈንክቶ፣ ደሙን አፍሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ፣ ልብሱን ገፎ እንደ መለሰው ወደ አብርሃም ቤት ለሚሔዱ ሰዎች ይናገር ጀመር፡፡ በዚህ የተነሣም እንግዳ ወደ አብርሃም ቤት አይመጣም ነበር፡፡ አብርሃምም ማዕደ እግዚአብሔርን ያለ እንግዳ አልመገብም ብሎ ሦስት ቀን ሳይመገብ ጾሙን አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን ይህን ደግነቱን እግዚአብሔር ተመልክቶ በኦሪት ዘፍጥረት ፲፰፥፩-፲፱ ተጽፎ እንደምናገኘው በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በሦስት ሰዎች አምሳል አንድም በሥላሴ (በሦስትነት) በመምሬ አድባር ዛፍ ተገልጦለታል፡፡ አብርሃምም ሦስት ሰዎች ቆመው ባየ ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሮጠ፡፡ ወደ ምድርም ሰገደና “አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባርያህን አትለፈኝ?” ብሎ ተማጸነ፡፡ በመቀጠል አብርሃም “ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፡፡ ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፤ ልባችሁንም ደግፉ፡፡ ከዚያም በኋላ ትሔዳላችሁ፡፡ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና” ሲላቸው እነርሱም “እንዳልህ አድርግ” ብለውታል (ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ፣ ፬፥፴፪)፡፡ የኦሪት ዘፍጥረት አንድምታ ትርጓሜ እንደሚያስረዳው አብርሃም ሥላሴን “ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ ዕረፉ” ሲላቸው “ደክሞናልና አዝለህ አስገባን” አሉት፡፡ እርሱም እሺ ብሎ አንዱን አዝሎ ቢገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ (በአምላካዊ ጥበብ) ከቤቱ ገቡ፡፡ አብርሃምም ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ሔደና “ሦስት መሥፈሪያ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት፤ እርሷም እንዳዘዛት አደረገች፡፡ አብርሃምም ወይፈን አርዶ አወራርዶ አዘገጅቶላቸው ተመግበዋል፡፡ ከዚያም የታረደውና የተወራረደውም ወይፈንም ተነሥቶ በድንኳኑ ደጃፍ “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል” ብሎ እግዚአብሔርን አመስገኗል፡፡ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?›› አለው፡፡ አብርሃምም ከድንኳኑ ውስጥ እንዳለች ነገረው፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች›› ብሎ ለአብርሃም አበሠረው፡፡ ሣራ ይህንን ቃል በሰማች ጊዜ ባለቤቷም አርጅቶ፤ እርሷም የሴቶች ግዳጅ ትቷት ነበርና መውለዷን በመጠራጠሯ ሳቀች፡፡ እግዚአብሔርም ምሥጢሩን በአጽንዖት ለማስረዳትና አስረግጦ ለመንገር አብርሃምን ‹‹ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› አለው፡፡ ሣራም ስለፈራች ‹‹አልሳቅሁም›› አለች፡፡ እግዚአብሔርም መሳቋን እንዳወቀባት ከነገራት በኋላ በድጋሜ በዓመቱ ወደ አብርሃም ቤት እንደሚመጣና ሣራ ወንድ ልጅ (ይስሐቅን) እንደምትወልድ አብሥሯቸዋል፡፡ ከዚህ ትምህርት ብዙ ነገሮች እንማራለን፡፡ ለአብነትም ያህል የተወሰኑትን እንመልከት፡- አንድነትና ሦስትነት “በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባሪያህን አትለፈኝ?” የሚለው ኃይለ ቃል አንድነቱን፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ ብሎ ሦስትነታቸውን ምሥጢር ይገልጻል፡፡ ሣራ ዳቦ ያዘጋጀችበት ሦስቱ መሥፈሪያ የሦስትነቱ፤ ዳቦው አንድ መኾኑ ደግሞ የአንድነቱ ምሳሌ ነው፡፡ ሥላሴ አብርሃም ያዘጋጀውን እንስሳ ተመገቡ ተብሎ መነገሩም በሰው አምሳል ስለ ተገለጡና ለአብርሃም የበሉ መስለው ስለ ታዩት ነው እንጂ ለሥላሴ መብል መጠጥ አይስማማቸውም (አይነገርላቸውም)፡፡ ከዚህ በተለየ ምሥጢር ሥላሴ “ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?” ብለው ከጠየቁበት ኃይለ ቃል መካከል “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?” የሚለውን እመቤታችንን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ሲያበሥራት ‹‹ወንድ ሳላውቅ ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› /ሉቃ. ፩፥፴፯/ ብላ በጠየቀችው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ መናገሩ የእግዚአብሔር ቃል በዘመን ብዛት የማይለወጥ ሕያውና እውነተኛ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ የአብርሃም ድንኳን “በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት፡፡ ዐይኑንም አነሣና እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፡፡ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፡፡ ወደ ምድርም ሰገደ፡፡ እንዲህም አለ አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ” /ዘፍ.፲፰፥፲፭/፡፡
3. የታችኛው ዘመም ያለ አግድም እንጨት (የእግር መርገጫ - Suppedaneum) ይህ በስተግራው ከፍ፣ በስተቀኙ ደግሞ ዝቅ ብሎ የሚታየው ዘመም ያለ እንጨት የመስቀሉ እጅግ ጥልቅ ምሥጢር የሚገኝበት ክፍል ሲሆን ሁለት ዋና ዋና ትርጉሞች አሉት፡- የእግር ማረፊያ (መርገጫ)፦ በመጀመሪያ ደረጃ፣ የጌታችን ቅዱሳን እግሮች ተቸንክረው ያረፉበትን የእግር መርገጫ ሰሌዳ ያሳያል። የሁለቱ ወንበዴዎች እጣ ፈንታ (ሚዛን)፦ ይህ እንጨት እንደ "ፍትሃዊ ሚዛን" ያገለግላል። በክርስቶስ ቀኝና ግራ የተሰቀሉትን የሁለቱን ወንበዴዎች ፍጻሜ ያሳያል፡- ወደ ላይ ከፍ ያለው ጎን (በክርስቶስ ቀኝ ያለው)፦ በጌታ ቀኝ ተሰቅሎ፣ ንስሐ በመግባት “አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለቱንና “ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ” የሚለውን የምሕረት ቃል ሰምቶ ወደ ገነት የገባውን የድኃኑን (የቀኙን) ወንበዴ እጣ ፈንታ ያሳያል። ወደ ታች ዝቅ ያለው ጎን (በክርስቶስ ግራ ያለው)፦ በጌታ ግራ ተሰቅሎ፣ ጌታን ሲሳደብና ሲያፌዝ የነበረውን፣ ንስሐ ባለመግባቱ ምክንያት ወደ ሲኦል የወረደውን የግራውን ወንበዴ ፍጻሜ ያመለክታል። በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ምሳሌና ያለ ምሥጢር የሚሠራ ምንም ነገር የለም። ይህ መስቀል በቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ ሲቀመጥ፣ እያንዳንዱ አማኝ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመለከት የክርስቶስን ንግሥና (የላይኛው)፣ የክርስቶስን ቤዛነትና ፍቅር (መካከለኛው) እንዲሁም የንስሐን አስፈላጊነትና የዘላለም ፍርድን (የታችኛው) ሁል ጊዜ እንዲያስታውስና እንዲያስተውል ያደርገዋል። © Ayu prince
без подписи
🎯TP➽የብዙዋች ጥያቄ የሆነውን የሩሲያ ኦርቶዶክስ መስቀል መዋቅራዊ አካላት እና መንፈሳዊ ምሳሌያቸው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ዝም ብለው የተሰሩ ሳይሆኑ፣ እያንዳንዱ ቅርጽና ቀለም የራሱ የሆነ ጥልቅ ምሥጢርና ትምህርት አለው። ይህ መስቀል ሶስት አግድም እንጨቶች (ምሰሶዎች) ያሉት ሲሆን፣ ትርጓሜያቸውም እንደሚከተለው ነው፡- 1. የላይኛው አግድም እንጨት (ታብሌት / ጽሕፈት) ምሳሌነቱ፦ ይህ አጭር አግድም እንጨት አይሁድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ የቀረጹትን የክስ ማስታወቂያ (ታብሌት) ይወክላል። ምሥጢሩ፦ በሮማዊው ገዥ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ትእዛዝ “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” (በግሪክ INRI፣ በሩሲያኛ ЦС / ІНЦІ) የሚል ጽሕፈት ተጽፎበት የነበረውን ስፍራ ያመለክታል። ይህም ክርስቶስ የዓለም ሁሉ ንጉሥ መሆኑን በጠላቶቹ አንደበት ጭምር የተመሰከረበት መሆኑን ያስረዳል። 2. መካከለኛው አግድም እንጨት (ዋናው የምሰሶ አካል) ምሳሌነቱ፦ ይህ ረጅሙ አግድም እንጨት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን እጆች በምስማር የተቸነከሩበት ዋናው የመስቀል አካል ነው። ምሥጢሩ፦ ይህ እንጨት የክርስቶስን ሰፊ መለኮታዊ ፍቅር እና እጆቹን ዘርግቶ መላውን የሰው ልጅ ወደ እቅፉ የጠራበትን፣ ሰማይንና ምድርን፣ እንዲሁም የአይሁድንና የአሕዛብን ወገን በአንድነት ያስታረቀበትን የማዳን ሥራ ያሳያል።
ሌላው ቤተ ጉባኤው "የሕክምና መንደር" የሚያስገነባው የቅድመ ጋብቻ ትምህርት ለመስጠት የባለትዳሮች ደግሞ የልጅ አስተዳደግ ሥልጠና ለመስጠት እንዲሁም በሱስ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመንከባከብና እንደገና አዲስ ሰውነት እንዲያገኙ በማድረግ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችን በጎና ባለ አእምሮ ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር ተናግረዋል። ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን አክለውም "የሕክምና መንደሩ" ሀገር በቀል የሕክምና ማዕከል እንዲሁም የሕክምና ኮሌጅና የምርምር ማዕከል ያካተተ ይሆናልም ብለዋል። የሕክምና መንደሩ ወደ መሬት እንዲወርድ ለተባበሩት ሁሉ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ "የጉባኤ አምላክ ይጠብቅልን" ሲሉ አመስግነዋል። "የሕክምና መንደሩ" መሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ አቡነ ሚካኤል የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስካንዲቪያን እና የኖርዲክ አገራት አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ሓላፊዎች ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ካህናት አባቶች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሥራ ሓላፊዎች ተገኝተዋል።የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባ "የሕክምና መንደር" የመሰረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ። የገዳሙ ጉባኤ ቤት "ሰንፔር" ሲል ለሰየመው "የሕክምና መንደር" ግንባታ 30,000 ካሬ ቦታ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰኔ ፲፱-፳፲፰ ዓ.ም መረከቡም ይታወቃል። "የሕክምና መንደሩ" የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ላይ እንደተገለፀው የሕክምና መንደሩ ዋና ዓላማ ለሁሉም የሰው ልጆች በምሕረት፡ እምነትን፣ ዘርንና ማንነትን ሳይለይ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚታዘንበት የምሕረት ማረፊያ እንዲሆንና ሁለንተናዊ ፈውስ ለመስጠት ነው ተብሏል። ከዚህ በመለስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራችን የነበራትን የጥበብ ታሪክ በዘመናዊ የምርምር ዐቅም ለማስቀጠል "የሕክምና መንደሩ" ከፍ ያለ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል። ሌላው ቤተ ጉባኤው "የሕክምና መንደር" የሚያስገነባው የቅድመ ጋብቻ ትምህርት ለመስጠት የባለትዳሮች ደግሞ የልጅ አስተዳደግ ሥልጠና ለመስጠት እንዲሁም በሱስ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመንከባከብና እንደገና አዲስ ሰውነት እንዲያገኙ በማድረግ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችን በጎና ባለ አእምሮ ትውልድ ለመፍጠር መሆኑን ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር ተናግረዋል። ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን አክለውም "የሕክምና መንደሩ" ሀገር በቀል የሕክምና ማዕከል እንዲሁም የሕክምና ኮሌጅና የምርምር ማዕከል ያካተተ ይሆናልም ብለዋል። የሕክምና መንደሩ ወደ መሬት እንዲወርድ ለተባበሩት ሁሉ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ "የጉባኤ አምላክ ይጠብቅልን" ሲሉ አመስግነዋል። "የሕክምና መንደሩ" መሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ አቡነ ሚካኤል የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስካንዲቪያን እና የኖርዲክ አገራት አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ሓላፊዎች ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ካህናት አባቶች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሥራ ሓላፊዎች ተገኝተዋል። የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
без подписи
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ትርጓሜ ምስክር ት/ቤት በባሕር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው "የሕክምና መንደር" የመሠረት ድንጋይ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተቀመጠ። ዘጋቢ ያረካል አድማሱ (#EOTCTV ሰኔ ፲፱ቀን ፳፲፰ ዓ.ም ባሕርዳር) የገዳሙ ጉባኤ ቤት "ሰንፔር" ሲል ለሰየመው "የሕክምና መንደር" ግንባታ 30,000 ካሬ ቦታ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሰኔ ፲፱ቀን ፳፲፰ ዓ.ም መረከቡም ይታወቃል። "የሕክምና መንደሩ" የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ላይ እንደተገለፀው የሕክምና መንደሩ ዋና ዓላማ ለሁሉም የሰው ልጆች በምሕረት፡ እምነትን፣ ዘርንና ማንነትን ሳይለይ፣ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚታዘንበት የምሕረት ማረፊያ እንዲሆንና ሁለንተናዊ ፈውስ ለመስጠት ነው ተብሏል። ከዚህ በመለስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራችን የነበራትን የጥበብ ታሪክ በዘመናዊ የምርምር ዐቅም ለማስቀጠል "የሕክምና መንደሩ" ከፍ ያለ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
#ልክ_እንዳንቺ_ማርያም የውድቀቴን መንገድ ሸርሽራ በመውደድ ያቀናችኝ ንግስት ... የሰጠችኝ ክብር አቤት አቤት ሲያምር ልክ እንዳንቺ ማርያም መኖር እንድጠላ መንፈሴን አድክሞ ማጣት አንቆኝ ሲዞር ክንዱን አፈርጥሞ የምሆነው ጠፍቶኝ ተንበርክኬ ሳዝን ሳትለኝ ደካማ ቀና አረገችኝ ቀንበሬን ተሸክማ! እምቅ የእንባ ጠል ጉንጬን ሲንጠለጠል ኅዘን በደቆሰው ልስልስ ስስ አንጀቷ ዕንባዬን ያበሰው አቤት ሲያምር ጣቷ ልክ እንዳንቺ ማርያም እኔነት እስካጣ ፍቅር ሸሽቶኝ በሮ ብቸኝነት ሚስማር ሲያደማኝ ቸንክሮ የማረገው ጠፍቶኝ ሞቴን እየናፈቅኩ ሳዘጋጅ መስቀሌን ትንፋሽ ለገሰችኝ ዳብሳ ሰንበር ቁስሌን የጅራፍ ሹል ትርትራት የልቤ ስውር ስብራት አድቅቆ ሲጥለኝ ... እንዲሆን ለነፍሷ ስሞ ሳቅ ያሳየኝ አቤት ሲያምር ጥርሷ ልክ እንዳንቺ ማርያም ስትችልበት ማዘን ስታውቅበት ማቀፍ ብሶት አስዘርግፎ በሰላም ማሳረፍ ልክ እንዳንቺ ማርያም ስትችልበት ጸሎት ስታውቅበት ማውራት ጨለማን ገርስሶ በፈገግታ ማብራት ልክ እንዳንቺ ማርያም ስትችልበት ማከም ስታውቅበት ማዳን ፍቅር በልብ ሰጥቶ መለገስ ማር ኪዳን ✍ኤልዳን @Melikt_weg_gitim @Melikt_weg_gitim @Melikt_weg_gitim #Join_and_share