tgindex
መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

Статистика

✟የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአቱን የጠበቀ በሰንበት ት/ቤቶች የሚዘመሩ መዝሙራትን ከነ ግጥም እና ዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉን @mezmurzhohte ☆ለማንኛውም ሐሳብ አስተያየት ጥያቄ ጥቆማ @kalzhohete እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን መዝ ፻፶፥፮

Последний пост
27 янв.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
am
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 594
+4 за 5 дн.
Сутки
−2
−0,06%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 639
21 постов
Вовлечённость
156,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • Channel photo updated

  • መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን pinned «ሰኔ ፳፩ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ‘ቤተ ክርስቲያን’ የሚለው ቃል አንዱ ዘይቤያዊ ትርጉሙ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ያመለክታል፡፡ ይኸውም የእግዚአብሔር ቤት፣ የክርስቲያኖች የጸሎት ቤት፣ የክርስቲያኖች መኖሪያ ማለት ነው፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም መሠረትነት የምትተከል፣ በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሜሮን የከበረች፣ ሥላሴ በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገኑባት፣ የክርስቶስ ሥጋዌ የሚነገርባት፣…»

  • መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን pinned «ሰኔ ፲፪ የቅዱስ ሚካኤል በዓል እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር። ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት በለጸጋ ጐረቤት ነበረው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት…»

  • Channel photo updated

  • 14 янв. 2025 г.11,5 тыс19

    ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡ ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን በማን ስም አጠመቀው? ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ ‹‹ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?›› ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡ ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቀው እጁን ለምን አልጫነበትም? - ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡ - መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል ጌታችን ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው? በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ. ፻፲፫፥፫/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቆላ. ፪፥፲፬/ ጌታችን ለምን በሌሊት ተጠመቀ? በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ. ፱፥፪ - አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡ - አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለምን ጌታ ከውኃ ከወጣ በኋላ ወረደ? ሀ. ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና ምክንያቱን ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየም ነበርና፡፡ ለ. ውኃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ አንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል፡፡ ሐ. ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ባሉ ነበርና ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፡፡ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!አሜን! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 👉@mezmurzhohte 👈 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

  • ፫፥፭ ላይ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› ብሎ እንደተናገረው ከውኃና ከመንፈስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት መንግሥተ ሰማያት የምንገባበት ኃጢአታችን የሚደመሰስበት ድኅነትን የምናገኝበት ዐቢይ ምሥጢር ነው፡፡ ጥምቀት በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ አምኖ ለሚፈጽመው ሰው ሁሉ ለኃጢአት መደምሰሻ ከሥላሴ የጸጋ ልጅነት ለመቀበልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የተሰጠ ልዩ የሕይወት መንገድ ነው፡፡ የጥምቀት አመጣጥ፡ የምሥጢረ ጥምቀት መስራች ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታችን ጥምቀት በፊት አይሁድ ለመንጻትና ለኃጢአት ሥርየት (ይቅርታ) የሚጠመቁት ጥምቀት ነበራቸው፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥባቸው የተቀደሱ ዕለታትና ቦታዎች ሁሉ ሰውነትንና ልብስን ማጠብ የእግዚአብሔር ቤት ማገልገያ የሆኑ ዕቃዎችን ሁሉ ማጠብ ማንጻት ሥርዓትና ልማድ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርም ፈቃድ ያለበት አሠራር ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከመቅረባቸውና ለተቀደሰው አገልግሎት ከመግባታቸው አስቀድመው እግሮቻቸውንና እጆቻቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው፡፡ ሰውነታቸውን ከአፍአዊ (ከውጫዊ) እድፍ በማጠብና ንጹሕ በማድረግ በባሕርይ ንጹሕና ቅዱስ በሆነው አምላክ ፊት ውስጣዊ ሕይወትን ንጹሕ አድርጎ የመቅረብን ሥርዓትና ምሥጢር የሚያመለክት ልማድ ነበር፡፡ ‹‹አሮንንና ልጆቹን ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ታቀርባቸዋለህ፤ በውኃም ታጥባቸዋለህ›› /ዘፀ. ፳፱፥፬/ ‹‹ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፣ በውኃም አጠባቸው፡፡›› /ዘሌ. ፰፥፮/ በብሉይ ኪዳን ዘመን የጥምቀት ምሳሌዎች፡ አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ መልከጼዴቅ መሄዱ የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ አብርሃም የምእመናን መልከጼዴቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ናቸው፡፡ /ዘፍ. ፲፬፥፲፯/ ኢዮብ በዮርዳኖስ ተጠምቆ ከደዌው ተፈውሷል፡፡ ይህም ምእመናን ተጠምቀው ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ የመፈወሳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ንዕማን ሶርያዊ ተጠምቆ ከለምጽ ድኗል፡፡ ፪ነገ. ፭፥፲፬ ይኸውም ምእመናን ተጠምቀው ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ የመዳናቸው ምሳሌ ነው፡፡ የኖኅ መርከብ የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ ዘፍ.፮፥፲፫ ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍሳት በውኃ የዳኑባትን መርከብ ሲሠራ በኖኅ ዘመን የእግዚአብሔር ትዕግሥት በዘገየ ጊዜ ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ሰበከላቸው፡፡ አሁንም እኛን በዚያው አምሳል በጥምቀት ያድነናል ሥጋን ከዕድፍ በመታጠብ አይደለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመነሣቱ በእግዚአብሔር እንድናምን መልካም ግብርን ያስተምረን ዘንድ ነው እንጂ፡፡›› /1ጴጥ. ፫፥፳/ እስራኤል በደመና ተጋርደው ቀይ ባሕርን መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ /ዘፀ. ፲፬፥፲፭/ ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹አባቶቻችን ሁሉ ደመና እንደ ጋረዳቸው ሁሉም በባሕር መካከል አልፈው እንደ ሄዱ ልታውቁ እወዳለሁ፡፡ ሁሉንም ሙሴ በደመናና በባሕር አጠመቃቸው›› /፩ቆሮ. ፲፥፩/ ለአብርሃም ሕግ ሆኖ የተሰጠው ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ አብርሃም ከአረጀ በኋላ ቢገረዝም ልጆቹ ግን በተወለዱ በስምንተኛው ቀን እንዲገረዙ እግዚአብሔር አዞ ነበር /ዘፍ. 17፥9/ ‹‹በሰው እጅ የአልተደረገ መገረዝን በእርሱ ሆናችሁ ተገረዛችሁ፡፡ በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችኋል በእርስዋም ከሙታን ለይቶ ባስነሣው በእግዚአብሔር ረዳትነትና በሃይማኖት ከእርሱ ጋር ተነሥታችኋል፡፡›› /ቆላ. ፪፥፲፩/ ጌታችን ለምን ተጠመቀ? ፩. ሚሥጢርን ለመግለጥ፡- ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ሚስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. ፫፥፲፮/ ፪. ትንቢቱን ለመፈፀም፡- በመዝ ፵፮/፸፯/፲፮ ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡ ፫. አርአያ ሊሆነን፡- ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ ፲፩፥፳፱/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. ፲፫፥፩-፲፯/ ፬. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡- አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ ፪፥፲፬ ጌታችን መች ተጠመቀ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ፶፭፴፩ ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር ፲፩ ቀን ከሌሊቱ በ፲ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፱ በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው ፴ ዓመት ከ፲፫ ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. ፫፥፳፫/ ጌታችን ስለምን በ፴ ዓመት ተጠመቀ? በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ፳ እና ፳፭ ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. ፬፥፫፤፩ዜና መዋ. ፳፫፥፳፬፤ 1ጢሞ.፫፥፮-፲/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ፴ ዓመቱ ነበር፡፡ ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ፴ ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ፴ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ፵ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡ ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. ፫፥፲፮/ ጌታችን በዮሐንስ እጅ ለምን ተጠመቀ?

  • ከተራ እና የጥምቀት በዓል ከተራ ከተራ ማለት "ከበበ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡ በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር ፲ ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን ዓለም መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ውኃ የሚከተርበት ቦታ " ባሕረ ጥምቀት (ጥምቀተ ባሕር)" (የታቦት ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር ፲፩ ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡ ሥርዐተ ከተራ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.፫፥፫/ እንዲል፡፡የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጎን፤ መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ ሕዝቡም "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ" እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኛ) “ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥምቃት፤ በፍሥሓ ወበሰላም" (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተደርጎ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹አንሺዎች›› ይባላሉ፡፡ የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት (ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ) ፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ ፯-፱ ሰዓት ነው፡፡ በከተራ ዕለት የሚከናወኑ ድርጊቶች ምሳሌነት አላቸው እነዚሁም፤ #ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ #ታቦቱን አክብሮ ይዞ የሚሄደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ምሳሌ #ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ ምሳሌ #ታቦታቱን አጅበው የሚሄዱት ምዕመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌ #ታቦታቱ በከተራ ዕለት ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸው መድኀኔዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተራውን ሲጠብቅ አድሮ መጠመቁን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡››ማቴ፡ ፫፥፲፫ #ጥምቀቱ የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡፡ ጥምቀት ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል፡፡ ቃሉ በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መጥለቅ ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን (ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ሜሮን፣ ምሥጢረ ቁርባን፣ ምሥጢረ ንስሐ፣ ምሥጢረ ክህነት፣ ምሥጢረ ተክሊል፣ ምሥጢረ ቀንዲል) አንዱና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በዮሐ.

  • መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን pinned «የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ልደት ማለት ምን ማለት ነው? ልደት ብዙ ምሥጢር ይለበት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ከማኅፀን መወለድ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም፣ ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት፣ መኖር፣ መፀነስ፣ መወለድ፣ ከእናት ኾድ ወደ ብርሃን መውጣት፣ መገኘት፣ ተገልጾ መታየት ነው፡፡ የጌታችን ልደት ከሌላው በምን ይለያል? ሰው ሁሉ በአባትና በእናት…»

  • መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን pinned «የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ልደት ማለት ምን ማለት ነው? ልደት ብዙ ምሥጢር ይለበት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ከማኅፀን መወለድ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም፣ ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት፣ መኖር፣ መፀነስ፣ መወለድ፣ ከእናት ኾድ ወደ ብርሃን መውጣት፣ መገኘት፣ ተገልጾ መታየት ነው፡፡ የጌታችን ልደት ከሌላው በምን ይለያል? ሰው ሁሉ በአባትና በእናት…»

  • без подписи

  • без подписи

  • ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም (፪ ) ዘይሁዳ በቤተልሔም አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ (፪ )  በቤተልሔም ትርጉም ፡ ኢየሱስ የይሁዳ ክፍል በምትሆን በቤተልሔም ተወለደ ያን ጊዜ የጢሮስ ቆነጃጅት ሰገዱለት 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 👉@mezmurzhohte 👈 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи