tgindex
Ministry of Mines- Ethiopia

Ministry of Mines- Ethiopia

Статистика

ይህ የማዕድን ሚኒስቴር ትክክለኛ የTelegram Channel ነው።

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
et
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 554
−1 за 3 дн.
Сутки
+1
+0,06%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
440
29 постов
Вовлечённость
28,3%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
214
1/48двое суток
245
1/72трое суток
264

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በድንጋይ ከሰል ምርት ጥራትና አቅርቦት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ( ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) ከድንጋይ ከሰል አምራች ማህበራትና ከድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካዎች ተወካዮች ጋር በድንጋይ ከሰል ምርት ጥራት፣ አቅርቦትና የገበያ ሰንሰለት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ምርት ጥራትን ማሻሻል፣ የማጠቢያ ፋብሪካዎችን የማጠብ አቅም ማጠናከር እንዲሁም ከምርት እስከ ገበያ ያለውን ሰንሰለት በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገልጿል። በተጨማሪም በዘርፉ እየተስተዋሉ ያሉ የምርት ጥራት፣ የአቅርቦት፣ የማጠቢያ አቅምና የገበያ ትስስር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል።የድንጋይ ከሰል ለኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ካላቸው ማዕድናት መካከል ተጠቃሽ ሲሆን በተለይም ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች የኃይል ምንጭ በመሆን ለሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ዕድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ምርትና አቅርቦትን ማሳደግም በኢንዱስትሪው የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ወጪ በማስቀረት አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካዎች ያላቸውን አቅም በሙሉ ተጠቅመው ማምረት እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።ፋብሪካዎቹ ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው ሲሸጋገሩ፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የታጠበ የድንጋይ ከሰል ፍላጎታቸውን በሀገር ውስጥ ምርት ለማሟላት የሚያስችል አቅም ይፈጠራል። ይህም የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል የአቅርቦት አቅምን በማሳደግ፣ የምርት ጥራትን በማሻሻልና የኢንዱስትሪውን የግብዓት ፍላጎት በሀገር ውስጥ በመሸፈን የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት፣ የውጭ ምንዛሬ  ማዳንና የማዕድን ዘርፉን የኢኮኖሚ አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል።   ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_ ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/ Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8 Email: info@mom.gov.et

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • https://youtu.be/_hR6L4Nz63c?si=8QMHSj9U7hdv3H3T

  • የዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ  ግምገማ ተካሄደ። (ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እና  የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2018 አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት የዘርፍ ዕቅድ ተገመገመ፡፡ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ  የማዕድን ዘርፍ ከአምስቱ የሀገሪቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ ባለፉት ዓመታት የዘርፉ ዕድገት በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን አመላክተዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉንም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ማውጣት የጀመረችበት በተጠናቀቀው በጀት አመት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የተፈጥሮ ጋዙ በአሁኑ ወቅት ለትላልቅ የሴራሚክ ፋብሪካዎች በግብዓትነት እየዋለ እንደሚገኝና ወደፊትም ለትራንስፖርት፣ ለማዳበሪያ ምርትና ለኃይል ማመንጫነት እንደሚውል አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ የማዳበሪያና የብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ሥራ መጀመራቸውን ተናግረው፤ እንደ ፖታሽ ያሉ ስትራቴጂካዊ ማዕድናትን ወደ ምርት ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ በክልሎች በአነስተኛ ደረጃ ላሉ የማዕድን ሥራዎች ፈቃድ እንዲሰጡ ሥልጣን መውረዱ ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል። የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድም በ2018 በጀት የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን በማስቀጠል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በመድረኩ ተቀምጠዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን ትዊተር፦ https://twitter.com/MinistryofMine_ ድረ ገጽ፦ www.mom.gov.et ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/ Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8 Email: info@mom.gov.et

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

Ministry of Mines- Ethiopia — tgindex