- Последний пост
- 29 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Messages in this channel will no longer be automatically deleted
Messages in this channel will be automatically deleted after 1 week
Channel name was changed to «.»
Channel photo removed
🩵🩵
… ያ አሂባ… እንደምን ናችሁ… የአሏህ ሰላም በእናንተ ላይ ይስፈን🩵 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባዘጋጀነው ፕሮግራም የጋዛ እንግዳ ጋብዘን ስለሱ በተወያንበት ፕሮግራም ላይ የቴሌግራሙ መተግበሪያ ባሳየን ማስጠንቀቂያ ተክትሎ ይህንን ቻናል የከፈትኩበትን አካውንት ሙሉ በሙሉ መክፈት በማይቻል መልኩ ban አድርጎታል… አሁን የምጠቀምበትም አካውንት የመዘጋት እድል ስላለው… በዚህም ምክንያት ቻናሉን መቆጣጠር ስለማይቻል… ሙናጃን ልናቆም ሆኗል…ያው መጀመሪያውኑ ቆማል እንዳትሉ እንጂ😄 በእነዚህ 4 አመታት ውስጥ የቁርዓን አንቀፆችን… ተጨባጭ ኢማን ነክ የሆኑ አጀንዳዎችን ፣ ተስፋ ሰጭ ምክሮችን ስለ ተበዳይ ሙስሊም ወገኖቻችን ሊኖረን የሚገባ ስሜትን እና… ስለ ሙስሊሟ ሴት አዳብ በተመለከተ ሲተላለፉ ቆይተዋል… ቻናሉ ለእኔ እራሴን መጀመሪያ የምመክርበት እና ሌሎችን የማስታውስበት የአጅር ምንጭ ሆኖ ቢሆንም እዚህ ጋር ላቆም ተገድጃለሁ። እናማ…… ሙናጃ ለእናንተ ምን ነበረች? ከእናንተ ጋር ያደረግነው ይህ ትንሽ ጉዞ በልባችሁ ውስጥ ምን ትዝታ እና ስሜት ጥሎ አልፏል? ይህ ቻናል ለእርስዎ ምን ማለት ነበር? اعزائي المتابعين، انا مضطرة لإغلاق القناة لظروف خارجية، استودعكم الله @Haaaala21 እስከ ነገ ምሽት 3:00 ድረስ የሚቆይ።
አላችሁ?
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ آمِنُوا كَمَا آمَنَ النَّاسُ قَالُوا أَنُؤْمِنُ كَمَا آمَنَ السُّفَهَاءُ ۗ أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ السُّفَهَاءُ وَلَٰكِن لَّا يَعْلَمُونَ ለነሱም «ሰዎቹ እንዳመኑ እመኑ» በተባሉ ጊዜ «ቂሎቹ እንዳመኑ እናምናለን?» ይላሉ፡፡ አዋጅ ንቁ እነርሱ ቂሎቹ እነርሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡ መናፍቃን አሁንም በኢማን ፣በተቅዋ እንዲሁም እውቀት ባላቸው ሰዎች ላይ እንዳሾፉ፣አሳንሰው እንዳዩ እና እንደተሳለቁ! በተለይም በአካዳሚክ ዘርፍ ላይ ከፍ ባሉ እና የማእረግ መጠሪያ ካላቸው ሊያሳንሱ ይችላሉ… በአለባበሳቸው… በዲን አቋማቸው… በኢማናቸው ላይ ሲሳለቁ ይስተዋላል… በእርግጥ እውቀትነቱ ወደ አኺራ እና ወደ አሏህ የማያመራ እውቀት… እውቀት አይደለም…
أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ الْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡ ይህ ሁሉ ሲጓዙ በጥንካሬ እና በወኔ አላማቸውን ሲያራምዱ ለምን የሚል ጠያቄ ይነሳል?? በግትርነት የሚጓዙት ከውስጣቸው የኢማን ስሜት እና ሸሪዓውን ከመከተል ስሜታቸው ስለበለጠባቸው ጥፋት ላይ መሆናቸው ስለማይታወቃቸው ነው… ሌላው ምልክታቸው ጥፋት ላይ እያሉ ልባቸው ውስጥ ስላለው በሽታ «ሸህዋ እና ሹብሃ» ስለማይታወቃቸው… በርትተው በአቋማቸው ሲጓዙ ይታያል…
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ قَالُوا إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡ መናፍቃን ሁሌም በማስተካከል ስም የተበላሸ ስራቸውን ያስፈፅማሉ…የዲኑን ማስረጃ አዛብተው ማህበረሰቡ ፊት በማቅረብ ስለ ፍትህ ፣ነፃነት እና ትክክለኛው መንገድ ያወራሉ… ከዛስ! ስለ ሀቅ እና እውነት ሰው ፊት እየተናገሩ እና እየተጣሩ…ከጀርባ ከእውነታው የራቀ ስራ እና አቋም ያራምዳሉ። ብዙዎቻችን ሚዲያ ላይ በማስተካከል ስም ጥሪ እያደረግን… በፕሮፋይላችን እየገለፅን ስራችን ጋር ይገጥም ይሁን?
ሱረቱል «በቀራ» ላይ ካለው ማስረጃ እናውጣጣ።
የመናፍቃን ምልክቶች ምንድን ናቸው? ከፊሉን እንግለፅ?
የሚገርም ቲላዋ… ይለያል አሏሁመ ባሪክ🩵
አሪፍ መክተባ ልጠቁማችሁ ሼር አድርጉት https://t.me/PDF90
مقيلي إذا زلت بي النعل عاثرا واسمح غفار واكرم واهب!
አሏህ ሆይ አስተካክለን… አቅርበን… መልካም መመለስን ወዳንተ መልሰን…
Minshawi🩵🏳
ربنا...ربنا... ربنا
. pinned «ይህንን ሁሉ ለመገንዘብና ለማንበብ ሞራሉ ከሌለህ፤ ስለ ዲኔ፣ ስለ ኢማሜ፣ ስለ ዓሊሜና ስለ ሙስሊሙ መብት የመቆርቆር መብት የለህም! ምክንያቱም አንተ በዚህ በተደራጀ መልኩ ቀስ በቀስ እየተገዘገዝክ ለመጠቃት ራስህን አመቻችተህ የተኛህ ነህና። ©Ahmedin jebel»
9ኛ) ሼህ አሊዩ መሀመድ አህመድ ፦ አጣዬ ከተማ- መጋቢት 10 ቀን 2013 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 በአጣዬ ከተማ የአንሷር መስጂድ ኢማም የነበሩት ሼህ አሊዩ መሀመድ አህመድ (ሌሎች ሃፊዝ ሼህ ዘይኑ በማለጥ የጠቀሱም አሉ) እለተ አርብ መጋቢት 10 ቀን 2013 ከምሽቱ በ2፡00 ላይ የኢሻ ሰላትን አሰግደው ከአራት ደረሶቻቸው ጋር ወደ ቤት በመመለስ ላይ ሳሉ በአማራ ክልል ልዩ ኃይል ተገደሉ። ይህ ግድያ አሰቃቂ ድርጊት በአካባቢው ለተቀሰቀሰው መጠነ-ሰፊ ቀውስ ዋነኛ መነሻ ሆኗል። የግድያውን ዜና ተከትሎ የኢማሙን አስክሬን ለማንሳት የሞከሩ የከተማው ነዋሪዎች እና ወደ ስፍራው የተሰባሰቡ የገጠር የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ተኩስ መክፈታቸው ግጭቱን ይበልጥ አባባሰው። ሂዩማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) በ2022 ዓለም አቀፍ ሪፖርቱ ላይ እንዳረጋገጠው፣ የጸጥታ አካላቱ በህዝቡ ላይ የወሰዱት የኃይል እርምጃ ውጥረቱን ወደ ታጠቀ የእርስ በርስ ጥቃት የለወጠው ሲሆን፣ ለቀናት በቀጠለው በዚህ አውዳሚ ግጭት ከተሞችና መንደሮች ወድመዋል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል፣ እንዲሁም ከ200,000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል። ሆኖም ይህ ሁሉ ጥፋት የደረሰ ቢሆንም፣ በወቅቱ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው የተዛባ ትርክት እውነተኛውን የግጭት መነሻ በመደብቅ፣ የሟቹን ኢማም ማንነት «አንድ ግለሰብ» በሚል በመደበቅ ጥቃቱ ሙሉ በሙሉ በ"ኦነግ ሸኔ" እንደተፈጸመ አስመስሎ በማቅረብ ሀቁን ለማድበስበስ የሞከረ ነበር። ሆኖም ግጭቱን ለማረጋጋት መከላከያ ከገባ በኋላ ጄነራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ መነሻው የኢማም መገደል መሆኑን በመግለጫቸው ላይ አንስተዋል። 10ኛ) ሼህ ኡመር ሀጂ ሀሰን፦ ሸዋ ሮቢት- መጋቢት 12 ቀን 2013 📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕 ሼህ ኡመር ሀጂ ሀሰን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጋንጋሃ ቀበሌ በተባለ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ የ40 ዓመት እድሜ ላይ ይገኙ የነበሩ ዓሊም ሲሆኑ በመጋቢት 12 ቀን 2013 በቀይ መስቀል አምቡላንስ በመጓዝ ላይ እያሉ በሸዋ ሮቢት ከተማ ውስጥ በአማራ ልዩ ሃይል አባላት እና የፋኖ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ከሌሎች ታካሚዎች ጋር በጥይትና በስለት ተደብድበው ተገድለዋል። ስለጉዳዩ «ዘ ሂዩማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ሆርን ኦፍ አፍሪካ» በአፕሪል 6 ቀን 2021 «Ethiopia: Appeal for Urgent Independent Investigation into Shewa Robit Massacre of March 21, 2021!» በሚል ባወጣው መግለጫ ላይ የሼህ ኡመርን ሞት ጠቅሷል። 11ኛ) ሼይኽ አሊይ ሀሰን፦በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰንበቴ ከተማ-ሚያዚያ 9 ቀን 2013 🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵🔵 በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ሰንበቴ ከተማ አስተዳደር የቢላል መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼይኽ አሊይ ሀሰን ሚያዚያ 9 ቀን 2013 መገደላቸውን የሃሩን ሚዲያ በአፕሪል 18 ቀን 2021 እንዲህ በማለት ዘግቦ ነበር፦ «በሰንበቴ ከተማ የቢላል መስጂድ ኢማም የሆኑት ሼይኽ አሊይ ሀሰን በትላንትናው ዕለት መገደላቸውን የሀሩን ምንጮች አሳውቀውናል። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን»። የሃሩን ሚዲያ የፌስቡክ ዘገባ በማንና እንዴት እንደተገደሉ የማያብራራ ሲሆን በኦሮምኛ ስለጉዳዩ የጻፉ ጥቂቶች ግን በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸው ጠቅሰው ነበር። ሌሎች የአይን እማኞች ደግሞ ገዳዮቹ የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ የልዩ ሃይል አባላት እንደሆኑ ገልጸው ኢማሙ በረመዳን ወር የመግሪብ ሶላትን አሰግደው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ፣ በመስጂዱ በር ላይ ህይወታቸው መቀጠፊን ጽፈዋል። ሃሩን ሚዲያም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በለጠፈው ተጨማሪ ጽሑፍ «ኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ቤተ-ክርስቲያናት ፣የግለሰቦች ቤቶች ፣የመንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቃት እንዳይደርስባቸው በሚል ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ስለመስጅድ ግን ምንም ያለው ነገር የለም። በነበረው ግጭት መስጅድ እንደተቃጠለ ኢማም እንደተገደለ እንኳን እየታወቀ ሙስሊሙ ላይ የሚደርስ በደል ግን እምብዛም ትኩረት ተሰጥቶት በመንግስት ደረጃ አልተገለፀም። የመስጅድ ኢማምን መገደል ስንዘግብ የተቃወማችሁ ሙስሊሞች መልዕክቱ ከማንም በላይ ለናንተ ነው። ቢያንስ ግራ በሚያጋባው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምንም ማለት ባንችል ከበደሎች መሀል የማናቸውም የሙስሊሞች በደል ተሸሽጎ እንዳይቀር በማሰብ ነው የደረሰንን የተጣራ መረጃ መሠረት አድርገን ዘገባውን የሰራነው። በየትኛውም አካባቢ የሚደርሱ የሙስሊሙ በደሎች አሁንም ወደፊትም ያሳስቡናል፤ እንደ ሚዲያ ዋነኛ የትኩረት አጀንዳዎቻችንም ናቸው። በዚህ ስራ ላይ ሁሉንም አካል ማስደሰት አይቻልም። የደረሰንን ከዚያም ያረጋገጥነውን መረጃ ግን ወደናንተው እናደርሳለን።» 12ኛ) ሼህ አዱላይ፦አፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ- 2013 መጨረሻ 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው የ80 ዓመት አዛውንት የነበሩት ሼህ አዱላይ የተገደሉት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት በ2013 መጨረሻ ወይም 2014 መግቢያ ላይ በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ ጎቢዶራ ከተማ ውስጥ በነበሩ የትግራይ ኃይሎች(ሕወሃት) ታጣቂዎች መስጂድ ውስጥ እንዳሉ ነበር በጥይት የተገደሉት። (Report on Violations of Human Rights and International Humanitarian Law in Afar and Amhara Regions of Ethiopia) 13ኛ) ሼህ ሰማን አደም፦ ሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ-ከሐምሌ 17 ቀን 2013 በኋላ ❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗ ከሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ል. ጀምሮ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የምትገኘውን የአደርቃይ ወረዳን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር። ሕወሓት በአካባቢው ላይ በቆዩባቸው ወራት ውስጥ በንጹሃን ዜጎች ላይ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና የታገቱ ግድያዎችን ፈጽመዋል። በዚህ የጥፋት ዘመቻ ከተገደሉ በርካታ ንጹሃን መካከል ዕድሜያቸው 54 ዓመት የነበሩት ታዋቂው የሃይማኖት አባት ሼህ ሰማን አደም አንዱ ነበሩ። የአማራ ማኅበር በአሜሪካ (AAA) ባጠናቀረው ሪፖርት መሠረት፥ ሼህ ሰማን አደም በሕወሓት ታጣቂዎች አማካኝነት በግፍ እንዲገደሉ የተደረገው በሃውዛ ቀበሌ ውስጥ ነበር። ይቀጥላል...