New Leaf Fertility Center
СтатистикаExtraordinary Fertility Care in Ethiopia
- Последний пост
- 13 апр.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🤰 እርግዝና እና የአካል ብቃት፡ መሰረታዊ መመሪያ በእርግዝና ወቅት እንቅስቃሴ ማድረግ ለእናቲቱም ሆነ ለፅንሱ ጤንነት ወሳኝ ነው። ስፖርት ሲጀምሩ እነዚህን 3 ነጥቦች ያስታውሱ፡ - የ150 ደቂቃ ህግ፦ በሳምንት 150 ደቂቃ (ወይም በቀን 30 ደቂቃ) እንደ እርምጃ ያሉ የካርዲዮ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ለልብ ጤንነትና ለቀላል ምጥ ይረዳል። - አሰራርን ማስተካከል (Foundation)፦ ክብደት ከመጨመርዎ በፊት እንቅስቃሴውን በትክክለኛ አኳኋን መስራት መልመድ አለብዎት። መጀመሪያ በሰውነትዎ ክብደት ብቻ አቀማመጥዎን ማስተካከል ከጉዳት ይከላከልልዎታል። ደረጃ በደረጃ ማሳደግ፦ በመጀመሪያው ወር ፋውንዴሽን ላይ ከሰራን በኋላ፣ እንደ እናቷ ጥንካሬ መጠን እንቅስቃሴዎቹን እያሳደግን እንሄዳለን። ባጭሩ፦ ካርዲዮ እና የጥንካሬ ስልጠናን (Strength Training) በትክክለኛ ፎርም በማጣመር ጤናማ የእርግዝና ጊዜ ማሳለፍ ይቻላል። ⚠️ ማሳሰቢያ፡ ማንኛውንም ስልጠና ከመጀመርዎ በፊት ሃኪምዎን ያማክሩ። #PregnancyFitness #PrenatalHealth #SafeWorkout #EthiopiaHealth
PCOS እና እርግዝና፦ ማወቅ ያለብን 5 ወሳኝ ነጥቦች 🌸 • መድኃኒት፦ የወር አበባን ለማስተካከል ብቻ የወሊድ መቆጣጠሪያን ለረጅም ጊዜ ከመውሰድ ይልቅ፣ እርግዝናን የሚያፋጥኑ አማራጮችን ከመካንነት ስፔሻሊስት ጋር መምከር። • ክትትል፦ የእንቁላል ማሳደጊያ መድኃኒቶችን ያለ አልትራሳውንድ ክትትል ፈጽሞ አለመውሰድ። • ለውጥ፦ አንድ ዓይነት ህክምና ከ4-5 ጊዜ በላይ ሞክረው ለውጥ ካልመጣ፣ ወደ ስፔሻሊስት ዘንድ በመሄድ አማራጭ መፈለግ። • ምርመራ፦ ከPCOS በተጨማሪ የማህጸን ቱቦ እና የወንድ ዘር ፍሬ ምርመራዎችን አስቀድሞ ማጠናቀቅ። • ተስፋ ሳይቆርጡ ክትትል ማድረግ ከተቻለ ማርገዝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የማይቻል አይደለም። #PCOS #Fertility #WomensHealth #Ethiopia #NewLifeInfertility
📢 በኒው ሊፍ (New Leaf) የመካንነት ህክምና ማዕከል የቀረበ ዘመናዊ የPCOS ህክምና በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ የ PCOS ህክምና ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ ይገኛል። በ ኒው ሊፍ (New Leaf) የመካንነት ህክምና ማዕከል እነዚህን ዘመናዊና አዳዲስ የህክምና ዘዴዎች ስራ ላይ በማዋል በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገብን እንገኛለን። ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ፣ በዚህ አዲስ የህክምና መንገድ፦ * በPCOS ምክንያት እርግዝና ለዘገየባቸው፣ * የወር አበባ መዛባት ላጋጠማቸው፣ * እንዲሁም በተለያዩ የሆርሞን መዛባት ችግሮች ለተቸገሩ ሴቶች ህክምና ስንሰጥ ቆይተናል። የህክምናው ልዩ ባህሪያት ይህ አዲስ የህክምና አቀራረብ ከቀድሞው የሚለየው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡- 1. ቀላል እና ምቹ መሆኑ፦ ህክምናው በአብዛኛው ያለምንም ውስብስብ ሂደት፣ በታዘዙ ክኒኖች (Medications) ብቻ የሚከናወን በመሆኑ ለታካሚዎች እጅግ ምቹ ነው። 2. ከፍተኛ ውጤታማነት፦ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ አስገራሚ የሆኑ ውጤቶችን እያየንበት እንገኛለን። በተለይም እርግዝና ለዘገየባቸው ወገኖቻችን ተስፋ ሰጪና ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል። በPCOS ዙሪያ ለሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች ወይም የህክምና ምክር ለማግኘት ማእከላችንን መጎብኘት እንደሚችሉ በደስታ እንገልጻለን። ኒው ሊፍ (New Leaf) የመካንነት ህክምና ማዕከል - ለተሟላ የቤተሰብ ደስታ! #NewLeafFertility #PCOS #WomensHealth #FertilityJourney #InfertilityTreatment #EthiopiaHealth #HormonalBalance
ስለ IVF እውነታው 😱 IVF ሲባል ብዙ ሰዎች በላብራቶሪ ውስጥ ሰው የሚሰራ ሂደት ይመስላቸዋል። ይህ ግን በጣም የተሳሳተ አመለካከት ነው። አንዲት ሴት በየወሩ በተፈጥሮ ከአስር እስከ አስራ አምስት እንቁላሎችን ታመርታለች። እነዚህ እንቁላሎች ያድጋሉ፣ ይለቀቃሉ። ነገር ግን እንደ ማህጸን ትቦ መዘጋት ባሉ ምክንያቶች የወንዱ ዘር እና የእንቁላል ግንኙነት ሳይፈጠር ቀርቶ እርግዝና ካልተከሰተ፣ እነዛ እንቁላሎች በሙሉ ይሞታሉ። የ IVF ሚና በተፈጥሮ ሊጠፉ እና ሊባክኑ ያሉትን እነዛን እንቁላሎች በመድሃኒት በማሳደግ ለፅንስ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ባጭሩ IVF ተፈጥሮአዊውን ሂደት በመደገፍ ሊባክኑ ለነበሩ የህይወት ዘሮች እድል የሚሰጥ የህክምና ጥበብ ነው።
New Leaf Fertility Center pinned a photo
PCOS እና መካንነት፡ መፍትሄውና የምርመራ መንገዶች PCOS መኖሩን እንዴት ማወቅ ይቻላል? * የአልትራሳውንድ ምርመራ፦ በማህፀን አካባቢ የሚደረግ ምርመራ የእንቁላል ክምችትን (Follicles) ለማየት። * የወር አበባ መዛባት፦ የወር አበባ መምጫ ጊዜ መዛባት፣ መቆራረጥ ወይም በብዛት መፍሰስ። * የሆርሞን ምርመራ፦ የደም ምርመራ በማድረግ የወንድ ሆርሞን (Androgens) መጠንን ማረጋገጥ። * አካላዊ ምልክቶች፦ ያልተለመደ የፊት ወይም የሰውነት ፀጉር እድገት፣ የፊት ብጉር እና የክብደት መጨመር። መፍትሄዎቹ ምንድን ናቸው? * የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ፦ ጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሆርሞን መዛባትን ለማስተካከል ትልቅ ሚና አላቸው። * የህክምና ክትትል፦ እንቁላል እንዲመረጥ የሚያደርጉ (Ovulation induction) መድኃኒቶች እና የሆርሞን ማስተካከያ ህክምናዎች። * ቀጣይነት ያለው ክትትል፦ ተስፋ ሳይቆርጡ የባለሙያ ምክርን መከተል። መልእክታችን፦ PCOS ስላለባችሁ ብቻ ልጅ መውለድ አትችሉም ማለት አይደለም። በዘመናዊ ሕክምና እና በጥንቃቄ የታገዘ ክትትል ልጅ ወልዶ መሳም ይቻላል። ተስፋ አትቁረጡ፤ መፍትሄው በምርመራ ይጀምራል! #WomensHealth #PCOS #Fertility #ReproductiveHealth #Ethiopia #HealthEducation
ከIVF ባሻገር ለመካንነት መፍትሔ የሚሆኑ አማራጮች! ልጅ ለመውለድ ለሚቸገሩ ወገኖች ሁሉ መፍትሔው "IVF" ብቻ እንደሆነ ተደርጎ የሚወሰደው የተሳሳተ ግንዛቤ ሊታረም ይገባል። ወደ ሕክምና ከሚመጡ 100 ጥንዶች መካከል IVF የሚያስፈልጋቸው 10 በመቶ የሚሆኑትን ብቻ ነው። ቀሪዎቹ 90 በመቶ የሚሆኑት ታካሚዎች በሚከተሉት ቀላል የሕክምና መንገዶች ውጤታማ መሆን ይችላሉ፦ - የምክር አገልግሎት (Counseling)፦ ስለ ተዋልዶ ጤና እና ስለ ትክክለኛው የጊዜ አጠቃቀም ግንዛቤ በመፍጠር። - ቀላል መድኃኒቶች፦ የእንቁላል እድገትን የሚያነቃቁ መድኃኒቶችን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ። - IUI (Intrauterine Insemination)፦ የወንድ ዘርን በማዘጋጀት በቀጥታ ወደ ማኅጸን በማስገባት የሚደረግ ቀላል ሕክምና። የእኛ ዓላማ ለእያንዳንዱ ታካሚ እንደ አስፈላጊነቱ፣ ቀላሉንና ተመጣጣኙን የሕክምና አማራጭ በማስቀደም ውጤታማ እንዲሆኑ መርዳት ነው። #FertilityCare #IVF #IUI #ReproductiveHealth #WomenHealth #Ethiopia #HealthAwareness
PCOS እና ተያያዥ ጉዳዮች 🥚 በተፈጥሮ PCOS የሌላቸው ሴቶች፡ የወር አበባ ከመጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በመቁጠር፣ እንቁላል ብዙውን ጊዜ ከ10ኛው እስከ 18ኛው ቀን ባለው ጊዜ አድጎ ይለቀቃል። PCOS ያለባቸው ሴቶች ላይ ያለው ልዩነት: 🥚 እንቁላል ልቀት: መቼ እንደሚለቀቅ መተንበይ አስቸጋሪ ነው (ዘግይቶ ሊሆን ወይም ላይለቀቅ ይችላል)፤ ይህ እርግዝናን ያዘገያል። 🩸የወር አበባ መዛባት: እንቁላል ባለማደጉ ኢስትሮጂን ስለማይመነጭ የማህፀን ግድግዳ አይዘጋጅም ይህም ማለት የወር አበባ ላያዩ ይችላሉ። እንቁላል ባለመለቀቁ ፕሮጄስትሮን ስለማይኖር የወር አበባ ሊዛባ ይችላል። ⚠️ የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እውነታዎች: ክብደት: ሁሉም PCOS ያለባቸው ሴቶች ውፍረት አይኖራቸውም (ብዙዎቹ ቀጭን ሊሆኑ ይችላሉ)። ተጓዳኝ ችግሮች: ሁሉም ሴቶች ላይ የስኳር በሽታ ወይም ሌሎች ተጨማሪ የጤና ችግሮች አይታዩም። 🗝️ ቁልፍ መፍትሔ: የPCOS ችግሮች በአብዛኛው የሚፈቱት የአኗኗር ዘይቤን (Lifestyle) (በአመጋገብ እና እንቅስቃሴ) በማስተካከል ነው።
💜 ስለ (PCOS) ማወቅ ያለብዎት! PCOS (Polycystic Ovary Syndrome) በወሊድ ዕድሜ ላይ ባሉ ሴቶች ላይ የተለመደ የሆርሞን መዛባት ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሴቶችን የሚጎዳ ቢሆንም፣ ብዙውን ጊዜ ግንዛቤው ዝቅተኛ ነው። የፒሲኦኤስ 3 ቁልፍ ምልክቶች፦ • መደበኛ ያልሆነ የወር አበባ መዛባት ወይም መቅረት. • ከመጠን በላይ የ Androgen(የወንድ ሆርሞን) መጠን መጨመር (የፀጉር መጨመር፣ ብጉር). • በእንቁላል ከረጢት (Ovaries) ላይ የቋጠሮ (cyst) መፈጠር. ለምን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል? PCOS ለመካንነት፣ ለስኳር በሽታ እና ለሌሎች የጤና ችግሮች ተጋላጭነትን ሊጨምር ይችላል። መፍትሄው ምንድነው? ትክክለኛ ምርመራ እና በባለሙያ የሚሰጥ ህክምና ወሳኝ ነው። ይህም የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ (ጤናማ አመጋገብ እና ስፖርት) እና አስፈላጊ ከሆነ መድሃኒት ያካትታል። 👉 ሴቶች ሁሉ የሰውነታቸውን ለውጥ እንዲከታተሉ እና ምልክት ካዩ የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ እናበረታታለን። ስለ PCOS ግልጽ ውይይት በማድረግ ግንዛቤን እናሳድግ! #PCOS #ሴቶችጤና #Hormone #ጤና #ግንዛቤ
💛 ለ(PCOS) ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች የሚመከር PCOS (Polycystic Ovary Syndrome) የአካል እና የአእምሮ ጤናን የሚፈታተን የረጅም ጊዜ ችግር ነው። ይህንን ሁኔታ በብቃት ለመቋቋም፣ ከሕክምና ባለፈ እንደ መፍትሄ ወይም ምክር የምንሰጠው ወሳኝ ነገር የተደራጀ ማኅበረሰብ መመሥረት ነው። ይህ ማኅበረሰብ የሚሰጣቸው ዋና ዋና ጥቅሞች፦ 1. ስነልቦናዊ እና ስሜታዊ ድጋፍ • ልምዶችን መጋራት፡ የብቸኝነት ስሜትን በማስወገድ እና በሌሎች ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ባሉ ሰዎች መረዳትን በማግኘት የአእምሮ ጤናን (Mental Health) መጠበቅ። • መበረታታት፡ ጭንቀትን ለመቀነስ የሚያስችሉ መንገዶችን በጋራ መፈለግ። 2. ትክክለኛ መረጃና እውቀት ማግኘት • እውቀት መለዋወጥ፡ ስለ ተለያዩ የPCOS አስተዳደር ዘዴዎች (ለምሳሌ፡ የአመጋገብ ስልቶች፣ ተስማሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች) እና አዲስ መረጃዎችን መጋራት። • የባለሙያ ምክር፡ ከPCOS ጋር በተያያዘ ልምድ ያላቸውን ዶክተሮች፣ የስነ-ምግብ ባለሙያዎች እና ስፔሻሊስቶች ምክር በቀላሉ ማግኘት። 3. ተነሳሽነትና የጤናማነት ተጠያቂነት • ሃላፊነት መጋራት፡ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን በተከታታይ ለመጠበቅ አንዳችን የሌላችንን ተነሳሽነት በማጠናከር እና ተጠያቂነትን በመፍጠር መደጋገፍ። • በጋራ ማደግ፡ ወደፊት ተስፋ የሚያስቆርጡ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ፣ በጋራ በመቆም እና በመደጋገፍ ተስፋን መመለስ። በማኅበረሰብ ውስጥ መሆን የሕክምናውን ሂደት ቀላል ከማድረጉም በላይ፣ በራስ የመተማመን ስሜትን በመጨመር የPCOS ተፅዕኖ ይቀንሰዋል። #PCOS #CommunitySupport #ጤና #የሴቶችጤና #አእምሮጤና #Ethiopia
በመካንነት ህክምና ላይ ከሚሰጡት መድሀኒቶች እና ህክምናዎች በተጨማሪ ምን ምን እናድርግ? እሱም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ነው፡፡ 1. የተመጣጠነ ምግብን መመገብ :- * አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን በየቀኑ በብዛት ይመገቡ። * ጥራጥሬዎችና ሙሉ እህሎች (እንደ አጃ፣ ቡኒ ሩዝ) ያላቸውን ፋይበርና ንጥረ ነገር ይጠቀሙ። * ጤናማ የቅባት ምንጮች (እንደ አቮካዶ፣ ለውዝ፣ የዓሳ ዘይት) አዘውትረው ይውሰዱ። * ከመጠን ያለፈ ስብ (saturated fat) ያላቸውን፣ የተጠበሱ ምግቦችንና ስኳር የበዛባቸው መጠጦችን ይቀንሱ ወይም ያስወግዱ። 2. ጎጂ ልማዶችን ማስወገድ ጤናዎን ከሚጎዱ ከሱስ ነክ ነገሮች ሙሉ በሙሉ መራቅ ወሳኝ ነው። * አልኮልንና ሲጋራን ጨምሮ አደንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም ይቆጠቡ። እነዚህ የመራቢያ አካል ሴሎችን ይጎዳሉ፣ የመፀነስን አጋጣሚ ይቀንሳሉ እንዲሁም ሌሎች የጤና እክሎችን ያመጣሉ። * የሰውነት ክብደትን በመቆጣጠር፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እና በቂ እንቅልፍ በማግኘት ሰውነትዎን ያጠናክሩ። ለ በለጠ መረጃ እና የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ኒው ሊፍ የመካንነት እና ስነ-ተዋልዶ ማዕከላችንን ይጐብኙ። አድራሻችን፡ አዲስ አበባ፣ ብስራት ገብርኤል፣ ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት።
የወንድ የዘር ፍሬዎ ላይ ችግር እንዳለብዎ እንዴት ማወቅ ይችላሉ? አንዳንድ የተለመዱ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ፡- • "አንድ ወንድ ግንኙነት ላይ ጥሩ ከሆነ ችግር የለበትም" • "አንድ ወንድ ጥሩ ካልሆነ ደግሞ ችግር አለበት ልጅ መውለድ አይችልም." እነዚህ በከፊል እውነት ቢሆኑም ግን እውነታውን አይናገሩም፡- • ጥሩ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የመራባትን ዋስትና አይሰጥም ምክንያቱም መካንነት የሚወሰነው ከግንኙነት ባለፈ በብዙ ባዮሎጂያዊ እና የአኗኗር ዘይቤዎች ላይ ነው። • ደካማ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የመካንነት ችግሮችን ሊያመለክት ይችላል ግን ሁልጊዜ አይደለም በተጨማሪም ብቸኛ ማሳያ አይደለም ስለዚህ ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ምንድን ነው? በትክክለኛ የወንድ የዘር ፍሬ ምርመራ የወንድ የዘር ፈሳሽ ናሙና ከተሰጠ በኋላ በአጉሊ መነፅር እንመለከተዋለን:: ከዛም በነዚህ ቁልፍ መለኪያዎች እንገመግማለን- የወንድ የዘር ብዛት፣ ምን ያህል በጥሩ ሁኔታ እንደሚንቀሳቀሱ፣ እና ሞርፎሎጂ (የወንድ የዘር ፍሬ ቅርፅ)። እነዚህ አንድ ሰው የመራባት አቅም እንዳለው እና እንደሌለው ይነግሩናል! አንድ በጣም መረሳት የሌለበት ደግሞ የምተነትነውም የሚመረምረውም ማን ነው? በወንድ የዘር ፈሳሽ ተፈጥሮ በቂ ስልጠና ከሌለው ወይም የወንድ የወሊድ መለኪያዎች ምርመራው ስፔሻላይዝድ ባልሆነ ላብራቶሪ ውስጥ ከሆነ የተካሄደው የተሳሳተ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ! ስለዚህ በኒውሊፍ የአንድሮሎጂ ቡድናችን እንዲሁም ኢምብርዮሎጂስቶቻችን ምርመራዎቹ ይካሄዳሉ ትክክለኛ ውጤቶችንም ያገኛሉ:: በተጨማሪም ማን ትንታኔውን እንዳደረገ በትክክል ማወቅ ያስችሎታል። የወንድ የዘር ፍሬዎ ጤና ደህና ነው ወይ ብለው እያሰቡ ከሆነ፣ ሙሉ ግምገማ በማድረግም በማማከርም ለማገዝ ኒው ሊፍ የመካንነት ማዕከል ሁሌም ዝግጁ ነን።
የወሊድ መቆጣጠርያ እውነት መካንነትን ያመጣል? 🤔 ብዙ ጊዜ ከምንጠየቃቸው ጥያቄዎች አንዱ ነው........ ጽንስን ለተወሰነ ጊዜ ለማዘግየት የምንጠቀምባቸው ክኒኖች መሃን ያደርጋሉ ብለን ስናስብ ማወቅ ያለብን፤ ለምሳሌ: • ፅንስ መከላከያ ክኒን ምትጠቀም አንድ ሴት ካቆመች በ 1-3 ወር ማርገዝ ትችላለች። • በክንድ ስር የሚቀበር መከላከያ (Implants) ወይም ሉፕ (IUD) ልክ እንደወጣ ማርገዝ ይችላሉ • በመርፌ መልክ የሚወስዱት ደግሞ ብዙ ጊዜ ከ6-12 ወራትን ሊወስድ ይችላል ነገር ግን፣ አንድ ሴት መከላከያ መጠቀም አቁማ ጽንስ ሊፈጠር ካልቻለ ከዚህ በፊት ወልዳ የምታቅ ቢሆንም ጥንዶቹ ሙሉ የመካንነት ምርመራ ማድረግ ይኖርባችዋል! ለእርግዝና መዘግየት የተለያየ ምክንያት ሊኖር ስለሚችል ቀድሞ ምክንያቱን ማወቁ በጊዜው መፍትሄ እንዲያገኝ ይረዳል። 💚በኒው ሊፍ የመካንነት ማዕከል በጊዜው መታከም እንዲሁም የተረጋገጠ መረጃ ለጤናማ እና ደስተኛ የወላጅነት ጉዞ ቁልፍ ናቸው የምንለው ለዚህ ነው!
ስለ መካንነት ማውራት አሁንም ለምን ከባድ ሆነ?💚 መካንነት የግል ሚስጥር ብለን ከምንይዛቸው ጉዞዎች መሃል አንዱ ነው፤ ልክ ሲወራ ደግሞ ማሸማቀቅ እንዲሁም ማግለልን ይታያል። ይህም የህክምና ባለሙያዎችን ስራ የበለጠ ከባድ ያደርገዋል! በተዘዋዋሪም ታካሚን ይጎዳል። በኒውሊፍ ወላጅ የመሆን ጉዞ ክብር፣ርህራሄ፣ እንዲሁም ከልብ መረዳትን በእያንዳንድዋ ደረጃ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን! ለዚህም ነው እያንዳንዱን ታካምያችንን በርህራሄ እና እንክብካቤ የምናክመው። በማያሸማቅቅ ውይይት ታካሚ የሚፈልገውን ጥያቄ ወይንም ያሳሰበው ጉዳይ እንዲያማክረን በኛ ተቋም እናበረታታለን፤ እያንዳንዳችን በዚህ መሰረት ካልተረዳዳን ይህ ችግር ዘላቂ ይሆናል። ተስፋ መዝራት እያንዳንዱ ታካሚ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ከማድረግም አልፎ ህብረተሰባችንን ያስተምራል! የህክምናው ባህሪ ጊዜ የሚፈልግ ብዙ ትእግስትን ፍቅርን መረዳትን የሚሻ ስለሆነ ማህበረሰባችን ይህን እንዲረዳ አደራ እንላለን፡፡ #FertilityCare #BreakingTheStigma #HealthcareWithCompassion
ሰላም ጤና ይስጥልን በዚህ ሳምንት ከዛሬ ጀምሮ ለምትጠይቁን የመካንነት ጥያቄዎች ሁሉ የቴሌግራም ግሩፓችን ላይ በመጠየቅ ቀጣይ ሳምንት የTiktok ገጻችን ላይ በሚኖረን Live Session ሀኪሞቻችን የሚመልሱ ስለሆነ ካሁኑ መጠየቅ እንዳይረሱ! በተጨማሪም እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ Follow ያድርጉን። NewLeaf Fertility Center እናመሰግናለን
መካንነት የጥንዶች የጋራ ችግር ነው, የአንዱ ወገን አይደለም! ጥንዶች ሊታከሙ ሲመጡ ብዙዎች መካንነት የሴቶች ችግር እንዲሆነ ይጠብቃሉ። ህብረተሰቡ ብዙ ጊዜ ሴቶችን ያገለለ እና ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ይወቅሳቸዋል። ነገር ግን የሕክምና እውነታ የተለየ ታሪክ ይናገራል! አንዳንድ ጊዜ ምርመራው ምንም ዓይነት የወንድ የዘር ፍሬ አለመኖሩን ያሳያል:: ይህ በሚሆንበት ጊዜ የሴቲቱ እንቁላል ምንም ያህል ጤናማ ቢሆን, ፅንስ ሊከሰት አይችልም:: ወላጅ መሆን የጋራ ጉዞ ነው። ኃላፊነቱ በወንዶች እና በሴቶች መካከል እኩል ነው! ኒውሊፍ በሴቶች ላይ ብቻ ሸክሙን የሚጭነውን ጎጂ መገለልን ማቋረጥ እንፈልጋለን። ጥንዶችን በማስተማር እና በማበረታታት, ውይይቱን ቀላል በማድረግ እና ለእያንዳንዱ ታካሚ ተስፋ, ክብር እና ርህራሄን በማሳየት ለውጥ ማምጣት እንችላለን:: የመካንነት ፈተናዎች የሴቶች ሸክም አይደሉም፣ የወንዶችም ብቻ አይደሉም። እነዚህ ጥንዶች አንድ ላይ የሚያጋጥሟቸው ጉዞዎች ናቸው:: ልምድ ባለው ሀኪም ድጋፍ እና ህክምና መፍትሄዎች ይገኛሉ!💚 ህብረተሰቡ መውለድን እንደ አንድ ወገን ሸክም ሳይሆን የጋራ ጉዞ አድርጎ እንዲረዳ አደራ እንላለን ፡፡ ህብረተሰቡ መውለድን እንደ አንድ ወገን ሸክም ሳይሆን የጋራ ጉዞ አድርጎ መመልከቱን እንዴት እናስተምር? #FertilityAwareness #SharedJourney #NewLeafFertility
ሶስት ልጆች! በአንድ IVF! እዚሁ በቤታቸው! ይህ የአንድ አስደማሚ ታካምያችን ታሪክ ነው, በNewLeaf Fertility Center:: ለአመታ በመካንነት ከተሰቃዩ በኋላ... ዶክተሮች IVF እንደሚያስፈልጋቸው አማከሯቸው, ለመታከም ግን ውጪ ነው የምንሄደው አሉ:: ከመሄዳቸው በፊት ግን ከኃላፊ ነርሳችን ጋር ተገናኝተው ነበር ካስረዳቻቸው በኋላም እዚሁ ኢትዮጵያ IVF ለመሞከር ተስማሙ! ውጤቱ? ቆንጅዬ ወንድ ልጅ 💙 በኋላም የተቀመጡ ፅንሶች በመመለስ ያለተጨማሪ IVF በወንድ እና ሴት መንታ ተባረኩ💙💖 በአጠቃላይ 3 ልጆች ከ 1 IVF ሕክምና🙏🏼 በ ኒው ሊፍ! ከደስታቸውም በላይ, ከዚህ ታሪክ አገር ውስጥ መታከም ካሉት ጥቅሞች የምንማረው ጥቂቶቹ: ✅ ውጪ የመታከም ወጪ እንደ ሆቴል, ትራንስፖርት ትኬት (Plane ticket), ምግብ...ያሉትን መቀነስ ✅ በለመድነው ቋንቋ, ባህል, ቤተሰብ ጋር ሆነን መታከም ✅ ከፍተኛ ጥራቱን የጠበቀ IVF አገልግሎት ከኢትዮጵያ ሳይወጡ አንዳንዴ የምንፈልገው መፍትሄ ከምናስበው በላይ ቅርብ ነው💚
በወንዱ የዘር ፈሳሽ ውስጥ ምንም አይነት የወንድ የዘር ፍሬ አልተገኘም! በመአከላችን ከታከሙ ጥንዶች ታሪክ አንዱን እናጋራችሁ። የቅድመ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት የባል የዘር ፈሳሽ ውጤት 'አዞስፐርሚያ' እንደሆነ ታወቀ። ይህ ማለት ፈሳሽ ቢኖርም ዘር ግን የለውም፡፡መድሃኒት ቢወስድም ምንም ለውጥ አላመጣም። ስለዚህ ወደ ቀጣዩ ህክምና አለፍን TESE በተሰኘው መለስተኛ የቀዶ ህክምና በዘር ፈሬዎቹ ላይ ተደረገ ፡፡ከዛም ላይ የተገኘው ናሙና ውስጥ ዘር ተገኘቶ መቀዝቀዘ ቻለ፡፡በመቀጠልም የባለቤቱን እንቁላሎችን በመድሐኒት በማሳደግ ከሰበሰብን በኃላ በላብራቶሪ ውስጥ ሁለቱም ባለሙያዎች አገናኟቸው፡፡ ከዚያም 11 ፅንሶችን ማደግ ችለው ከነሱም ውስጥ 2ፅነስ ወደ ማህፀኗ ተመለሱ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በተደረገው የደም እና የአልትራሳውንድ ምርመራ ላይ አስደሳች ዜና ሰሙ ። ዛሬ እነሱ የአንድ ቆንጆ ወንድ ልጅ ወላጆች ናቸው። የተቀሩት ፅንሶች ደግሞ ለወደፊቱ ጊዜ አቀዝቅዘን አስቀመጥንላቸው። *ኑ የወላጅነት ህልሞን ከኛ ጋር እውን ያድርጉ፡፡ የስራ ሰዓታችን ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 2:00 - 6፡30 ከሰዓት 7፡30 - 11:00 ቅዳሜ ከጠዋት 2:00 - ከሰዓት 8:00 ከታች ባሉት ስልኮች ይደውሉልን +251 945484848 /+251946484848 አድራሻችን : አዲስ አበባ ብስራት ገብርኤል ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት
🌿 ከ PCOS እስከ እርግዝና፡ የተስፋ ጉዞ 🌿 አንዲት የ32 ዓመት ሴት ለሁለት ተከታታይ አመታት እርግዝና ከዘገየባት በኃላ ነበር ወደ ተቋማችን የመጣችው ። ፈተናዎቿ የተለዩ አልነበሩም፡- ● የወር አበባዋ ይዛባል 2-4 ወር ይቆያል ● የክብደት መጨመር እና የፊት ፀጉር ማብቀል ለታካሚያችን በመጀመሪያ እርግዝና እንደሌለ ካረጋገጥን በኃላ ከሁኔታዋ ጋር የተጣጣመ የህክምና እቅድ በጥንቃቄ ነድፈን፡- ✔️ በመጀመሪያ Primolut የተሰኘውን መድሀኒት በመጠቀም የወር አበባን እዲመጣ ተደረገ ✔️ የእንቁላል እድገትን ለማነቃቃት ደግሞ Letrozole መድሀኒትን ተጠቀምን ✔️ የእቁላሉን እድገትን በማህፀን በኩል በሚገባ የአልትራሳውንድ ክትትል አደረግን ✔️ ያደገ እቁላል እንዳገኘን HCG መርፌ በመስጠት እንቁላሉ እንዲለቀቅ አገረግን ልክ ከሶስት ሳምንታት በኋላ በተፈጥሮ መፀነስ ችላለች።🎉 የPCOS ታካሚዋች በትክክለኛው ምርመራ, ህክምና እና እንክብካቤ ማግኘት ከቻሉ ማርገዝ ይቻላሉ! ከPCOS ጋር እየታገልሽ ከሆነ ብቻሽን አይደለሽም! ወደ እናትነት ጉዞሽ ከእኛ ጋር እያንዳንዷን እርምጃ አብረን እንጓዛለን።
Happy World IVF Day እያልን ከNewLeaf Fertility Center ነፃ የማማከር አገልግሎት ይዘን መጥተናል 🎉 #WorldIVFDay