One Love School Official
Статистика- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 212
- 1/48двое суток
- 1 388
- 1/72трое суток
- 1 498
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እቅዳችን ጋር እየደረስን ነው ።በርቱ፡የፔንት ትምህርት ቤት ጀግኖቻችን የትምህርት ጥራቱን ለማሳየት ለተማሪዎቻችን ይበጃሉ ብለን ያዘጋጀነዉን ከሌሎቹ ትምህርት ቤት በተለየ መንገድ ለማሳየት ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡ የፔንት ትምህርት ቤት ወላጆች ዝግጁ ናችሁ።የናንተ የወላጆች ድጋፍ ያስፈልገናል።
ውድ የPent School እና One Love KG ወላጆች፣ ከክፍያ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ለሁላችሁም ግልጽ ማሳሰቢያ እንሰጣለን። እባካችሁ ከዚህ በኋላ የትምህርት ክፍያ በምትፈጽሙበት ጊዜ በተማሪው የሚማርበት ትምህርት ቤት የባንክ አካውንት ብቻ ይጠቀሙ። One Love KG አካውንት የሚጠቀሙት የKG (መዋዕለ ሕፃናት) ተማሪዎች ወላጆች ብቻ ናቸው። ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች ግን የPent School የባንክ አካውንት ብቻ በመጠቀም ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ በአክብሮት እናሳስባለን። በተሳሳተ አካውንት የሚፈጸም ክፍያ የክፍያ ማረጋገጥና የተማሪ መረጃ ሂደትን ሊያዘገይ ስለሚችል፣ እባካችሁ ክፍያ ከመፈጸማችሁ በፊት ትክክለኛውን የባንክ አካውንት መጠቀማችሁን ያረጋግጡ። ስለ መልካም ትብብራችሁ እናመሰግናለን! Pent School Administration One Love KG Administration
ለክቡራን የOne Love School እና Pent School ወላጆች ውድ ወላጆቻችን፣ በመጀመሪያ ለትምህርት ቤታችን ላሳያችሁት እምነት፣ ድጋፍና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን። የልጆቻችሁ ትምህርት ለእኛ ሁልጊዜም ዋነኛ ቅድሚያችን ነው። እንደምታውቁት፣ One Love School (1–8) በቤት ኪራይ ሁኔታ ምክንያት በአሁኑ ቦታ ሥራውን መቀጠል አልቻለም። ሆኖም ይህ ማለት የትምህርት አገልግሎታችን ተቋርጧል ማለት አይደለም። ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በPent School ስም በተሻለ አቅም፣ በተሻለ አደረጃጀት እና በጠንካራ ራዕይ ሥራችንን እንቀጥላለን። በትምህርት መመሪያው መሠረት የትምህርት ቤት መዘጋትም ሆነ መከፈት ከአዲሱ የትምህርት ዘመን 2 ወይም 3 ወራት በፊት ለወላጆች ማሳወቅ ይገባል። በመሆኑም ይህን ማስታወቂያ አሁን በመስጠታችን ለልጆቻችሁ የሚሻለውን ውሳኔ ለመወሰን በቂ ጊዜ እንዲኖራችሁ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በመረጃ ብቻ እንዳትወስኑ እንጠይቃለን። ወደ ትምህርት ቤቱ በአካል ይምጡ፤ እየተከናወኑ ያሉትን የግንባታ፣ የማሻሻያ እና የአደረጃጀት ሥራዎች በዓይናችሁ ይመልከቱ፤ ከአስተዳደሩ ጋር ተወያዩ፤ የምታቀርቡትን ሀሳብ እና ጥቆማ ያካፍሉን። ገንቢ ሀሳቦቻችሁን አቅማችን በፈቀደ መጠን ለመተግበር ዝግጁ ነን። Pent School ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር ገብቷል። በትምህርት ጥራት፣ በዲሲፕሊን፣ በእንግሊዝኛ ትምህርት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመማሪያ ሥርዓት፣ በትራንስፖርት አገልግሎት እና በዘመናዊ የመማሪያ አካባቢ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል። ውድ ወላጆች፣ በዚህ የሽግግር ሂደት በቅርብ መከታተላችሁ፣ ጥያቄ መጠየቃችሁ እና ሀሳብ መስጠታችሁ የልጆቻችሁን የወደፊት ስኬት በጋራ ለመገንባት ያላችሁን ቁርጠኝነት ያሳያል። ስለዚህ ይህን ትብብር በቀጣይም እንዲቀጥል በአክብሮት እንጋብዛችኋለን። "One Love ታሪኩን በክብር አጠናቋል፤ Pent School ደግሞ የተሻለ የወደፊት ጉዞን በቁርጠኝነት ጀምሯል። ይህን አዲስ ጉዞ ከእናንተ ጋር በመሆን ለልጆቻችን የተሻለ ዕድል እንፈጥራለን።" ከአክብሮት ጋር፣ ውቢሸት ግርማው ዳኘው ባለቤትና መስራች Pent School / One Love KG
t.me/pent2019
🌟 ዋን ላቭ KG – የካ አባዶ ቅርንጫፍ 🌟 📢 የ2019 ዓ.ም. የተማሪዎች ምዝገባ ይጀምራል! 🗓 የምዝገባ መጀመሪያ ቀን: ሀምሌ 1 የሚመዘገቡ ክፍሎች 🎓 KG 1 • KG 2 • KG 3 💵 የክፍያ ዝርዝር - 📝 የምዝገባ ክፍያ፦ 850.85 ብር - 🏫 ወርሃዊ ክፍያ፦ 3,403.40 ብር 📋 ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ✔ የልደት ሰርተፍኬት ወይም እድሜ ማረጋገጫ ✔ 2 የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች ✔ የወላጅ/የአሳዳጊ መታወቂያ ቅጂ ✨ ልጅዎን ለወደፊቱ የሚያዘጋጅ ጥራት ያለው ትምህርት፣ አስተማማኝ እንክብካቤ እና ምቹ የመማሪያ አካባቢ በዋን ላቭ KG ያገኛሉ። 📌 ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እንኳን ደስ አላችሁ! ውድ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች፣ በትጋት፣ በትዕግስት እና በጽናት የሠራችሁበት ጉዞ ዛሬ ፍሬውን አፍርቷል። የፈተና ውጤታችሁ በመለቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ! የተሻለ ውጤት ላመጣችሁ እንኳን በደስታ አደረሳችሁ፤ ውጤታችሁ እንደጠበቃችሁት ላልሆነላችሁም ተስፋ አትቁረጡ። ይህ የመጨረሻ ሳይሆን ወደ ትልቅ ስኬት የሚወስድ አንድ እርምጃ ብቻ ነው። ለዚህ ስኬት አስተማሪዎቻችሁን፣ ወላጆቻችሁን እና ድጋፍ ያደረጉላችሁን ሁሉ አመስግኑ። መጪው የትምህርት ዘመን የበለጠ ስኬት፣ እውቀት እና ብሩህ ተስፋ ይዞላችሁ ይምጣ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Graduation ceremony of one love school
TOP 10
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи