Reshad (ረሻድ)
СтатистикаWelcome to Reshad (ረሻድ) ! 📣 ቻናላችን ላይ ለማስተዋወቅ 📩 🚀 Promotion ➜ @reshreshad 📲 Download Android APK App from this links:https://ethioyt.pro.et ዩቱብ ቻናሌን ሰብስክራይብ ለማድረግ👇 https://youtu.be/Zz1AvCK7kk
- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 08:11
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Приложения
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 202
- 1/48двое суток
- 231
- 1/72трое суток
- 249
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Google Assistant ሊዘጋ ነው! ⭕ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት Google በብዙ ሚሊዮን አንድሮይድ ተጠቃሚዎች ለዓመታት ስንጠቀምበት የነበረውን Google Assistant ሙሉ በሙሉ ሊዘጋው መሆኑን ይፋ አድርጓል። በአዲሱ የGenerative AI Gemini እንደሚተካ ተገልጿል። ⭕አሁን ላይ በአንድሮይድ ስልኮች እና ስማርት device ላይ ዋናው የድምፅ ረዳት (Default Voice Assistant) ሆኖ የሚሰራው Gemini ነው። የGoogle Assistant ሞዴል አሁን ካለው የGenerative AI ቴክኖሎጂ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ ወደ Gemini እንዲሸጋገሩ ጉግል ግፊት እያደረገ ይገኛል። ኩባንያው አገልግሎቱን September 2026 ከአገልግሎት ውጪ እንደሚያደርገው 9to5Google ዘግቧል። ተጨማሪ ከፈለጉ 👍 ያድርጉ። @reshadapp
📱 የSamsung Account ጥቅሞችና አጠቃቀም የሳምሰንግ ስልክ ተጠቃሚ ሆናችሁ የSamsung Account ከሌላቹ የስልካችሁን ግማሽ አቅም እየተጠቀማቹ አይደለም ማለት ነው። ይህ አካውንት በሳምሰንግ ስልኮች፣ ታብሌቶች እና ቲቪዎች ላይ ያሉ ልዩ አገልግሎቶችን የምናገኝበት ቁልፍ ነው። 🌟 የSamsung Account ጥቅሞች ➡️Find My Mobile ስልክህ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ ያለበትን ቦታ ለማወቅ፣ በርቀት ለመቆለፍ ወይም በውስጡ ያሉ መረጃዎችን ለማጥፋት ይረዳል። ስልኩ ኦፍላይን (ከኢንተርኔት ውጭ) ቢሆን እንኳ የመፈለግ አቅም አለው። ➡️Samsung Cloud የስልክህን Contacts ፣ መልእክቶች፣ የጥሪ ታሪክ እና Settings Backup በማድረግ ይጠብቅልሃል። ስልክ ብትቀይር ወይም ፎርማት ብታደርግ በቀላሉ መመለስ ትችላለህ። ➡️Galaxy Store: ለሳምሰንግ ተብለው የተሰሩ ልዩ አፖችን፣ ጌሞችን እና የፎንት ዲዛይኖችን ለማውረድ የግድ አካውንቱ ያስፈልጋል። ➡️Samsung Pass: የተለያዩ ድረ-ገጾችና አፖች ፓስወርድን ከማስታወስ ይልቅ በጣት አሻራ ወይም በፊታችን ብቻ እንድንከፍት ይረዳናል። ➡️SmartThings: ቤታችን ውስጥ ያሉ ሌሎች የሳምሰንግ እቃዎችን (እንደ ቲቪ፣ ፍሪጅ፣ ወዘተ) በስልካችን ለመቆጣጠር ይረዳል። 🛠 የSamsung Account እንዴት ይከፈታል? አካውንት ለመክፈት ወደ ስልክህ Settings ግባ። ከላይ የሚገኘውን Samsung Account የሚለውን ተጫን (ወይም Accounts and backup > Manage accounts > Add account > Samsung account ውስጥ ግባ)። Create account የሚለውን መምረጥ ። @reshadapp
የኤሌክትሪክ ሂሳብ ለመክፈል ሰልፍ መያዝ ቀረ በቀላሉ በቴሌብርይክፈሉ! 🛑 ከቤትዎ ሳይወጡ በቴሌብር (Telebirr) መተግበሪያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) ክፍያዎን በደቂቃዎች ውስጥ ይክፈሉ። ⚡️📱 አሁኑኑ ሊንኩን በመንካት ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ: 👉 https://youtu.be/h4AHZ2924ug @reshadapp
ዋትስአፕ አዲስ አፕዴት ለቋል! ከእንግዲህ ስልክ ቁጥርዎን ሳይሰጡ በዚህ አዲስ መንገድ መገናኘት ይቻላሉ። የራሳችሁን ዩዘር እንዴት እንደምትፈጥሩ በዝርዝር ለማየት ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፦ 👉 https://youtu.be/gvG5BFHsEIQ?si=TcknM9t6VB5lrBkL @reshadapp
Rumble ላይ እንዴት ነው ብር መስራት የምንችለው ? | ከዩቱብ በምን ይለያል ? | Rumble Tutorial For Beginners 🎥💰 ሠላም ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች! ዛሬ አዲስ እና ጠቃሚ ቪዲዮ ለቅቄያለሁ። ከዩቲዩብ ጎን ለጎን ወይም ሌላ ተጨማሪ የገቢ አማራጭ ለሚፈልጉ ሁሉ Rumble የተባለው መድረክ ትልቅ እድል አለው። በዚህ ቪዲዮ ውስጥ፦ ✅ Rumble ምንድን ነው? ✅ ከዩቲዩብ በምን ይለያል? ✅ እንዴት እንደ ጀማሪ ተጠቃሚ መሆን እንችላለን? የሚለውን በዝርዝር አይተናል። ቪዲዮውን ለመመልከት እና አብረን ለመጀመር ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ 👉 https://youtu.be/o8gD6ZEYdHk @reshadapp ማሳሰቢያ፡ ይህ የቪዲዮ ተከታታይ ክፍል 1 ነው፤ በቀጣይ ክፍሎች ደግሞ አካውንት አከፋፈት እና የክፍያ ስልቶችን እናያለን።
በኢትዮጵያ ሆናችሁ በዩቲዩብ ብር መስራት ለምትፈልጉ ሁሉ! 🇪🇹✨ ብዙዎቻችሁ ቻናላችሁ ላይ ገብታችሁ "Earn" የሚለውን ስትነኩ "Monetization is not available in your location" የሚል ማሳሰቢያ እየመጣባችሁ እንደተቸገራችሁ አውቃለሁ። ነገር ግን መፍትሄው በጣም ቀላል ነው! 📌 በቪዲዮው የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች (Timestamps): በኢትዮጵያ ሆነን የዩቲዩብ ብር አከፋፈልን ለማስተካከል ምን ማድረግ አለብን? የ "Monetization is not available in your location" ስህተት ለምን ይመጣል? በ YouTube Studio ላይ ሀገርን (Location) እንዴት መቀየር ይቻላል? ጠቃሚ የደህንነት ምክሮች 👇 አሁኑኑ ሊንኩን በመንካት ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ: 🔗 https://youtu.be/XL8Mnl7Ok0I @reshadapp
የ TikTok አካውንት ለጊዜው መዝጋት (Deactivate) ወይም በቋሚነት ለማጥፋት (Delete) ለማድራግ ! 🤔 የቲክቶክ አካውንታችንን Deactivate ካደረግን ምን ይሆናል? እንዴትስ በቋሚነት ማጥፋት እንችላለን ወይም Delete ስናደርግስ ዳታችን ሙሉ በሙሉ ይጠፋል? ሁሉንም ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በተግባር የሚያሳይ አጭርና ግልጽ ቪዲዮ ሰርቼላችኋለሁ። በተለይ አካውንታችሁን ሙሉ በሙሉ ከማጥፋታችሁ በፊት ማውረድ ያለባችሁን የዳታ ኮፒ (Data Download) አጠያየቅ ጭምር አካትቻለሁ። 👇 አሁኑኑ ሊንኩን በመንካት ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ: 🔗 https://youtu.be/XL8Mnl7Ok0I @reshadapp
📌 በPlay Store "የነፃ ኢንተርኔት" አፖች እውነታና ምስጢሩ! በብዛት የምናያቸው “የነፃ ኢንተርኔት እንሰጣለን” የሚሉ የቪፒኤን (VPN) መተግበሪያዎች እውነታ በአጭሩ፦ 1️⃣ ጥቅማቸው (Pros) ወጪ መቀነስ፦ ፓኬጅ መግዛት ለማይችሉ የተወሰነ አማራጭ ይሰጣሉ። የተዘጉ ገጾችን መክፈት፦ የተከለከሉ ሳይቶችን ለማግኘት ይረዳሉ። ግላዊነት፦ ታማኝ የሆኑት መረጃን ኢንክሪፕት ያደርጋሉ። 2️⃣ ጉዳታቸው (Cons) የመረጃ ስርቆት፦ የግል መረጃን ሰብስበው ለሶስተኛ ወገን የመሸጥ እድላቸው ሰፊ ነው። የቫይረስ ስጋት፦ ስልክን ለሰላይ ሶፍትዌሮች (Spyware) ሊያጋልጡ ይችላሉ። ደካማ ፍጥነት፦ ሰው ስለሚበዛበት ኔትወርካቸው ይቆራረጣል። ባትሪ ማዳከም፦ ከበስተጀርባ በመስራት ባትሪ በፍጥነት ይጨርሳሉ። 3️⃣ ምን ያተርፋሉ? "ለአገልግሎቱ ካልከፈልክ፣ ምርቱ አንተ ራስህ ነህ!" ገቢያቸው፦ በማስታወቂያ ጋጋታ፦ በአፑ ላይ በሚመጡ ማስታወቂያዎች ያገኛሉ። ዳታ በመሸጥ፦ የአጠቃቀም ልምድዎን ለድርጅቶች ይሸጣሉ። ወደ Premium በማሳደግ፦ በኋላ ላይ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገፋፋሉ። 💡 ምክር፦ ደህንነቱን ሳያረጋግጡ ማንኛውንም አፕ ስልክዎ ላይ አይጫኑ! 👉 @Reshadapp 👉 @reshadapp
የኮምፒውተራችሁ Drive C ሞልቶ ቦታ አጥሮባችኋል? ወይስ አንዳንድ ፎልደሮች አልከፍት ብለዋችኋል? 🖥⚠️ ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን ሲሞላ ወይም ፋይሎች Corrupt ሲሆኑ (ሲበላሹ) ሶፍትዌር ፍለጋ እንሮጣለን። ነገር ግን ምንም አይነት ሶፍትዌር ሳንጭን በዊንዶውስ ላይ ብቻ በሚገኙ 2 ሚስጥራዊ መንገዶች ኮምፒውተራችንን ማፅዳትና ማስተካከል እንችላለን! 🎯 በቪዲዮው ውስጥ የተካተቱት፦ ✅ Windows.old ማፅጃ፦ ብቻውን ከ 80GB እስከ 300GB+ በላይ የሚይዘውን አላስፈላጊ የድሮ ሲስተም ፋይል በቀላሉ ማጥፊያ ዘዴ (Clean up system files)። ✅ Error Checking፦ ፋይል ኮፒ ሲደረግ መብራት በመጥፋቱ ምክንያት የተበላሹ (Corrupt) የሆኑ ፋይሎችን መፍትሄ እና አልከፍት ያሉ ፎልደሮችን ማስተካከያ። @reshadapp አሁኑኑ ቪዲዮውን አይታችሁ የኮምፒውተራችሁን ፍጥነት እና ቦታ ጨምሩ! 👇 🎬 https://youtu.be/RSoW9Cml6EM 🎬 https://www.youtube.com/watch?v=RSoW9Cml6EM&feature=youtu.be
ሰላም ቤተሰቦች! 🙌 ቻናላችን 9,000 ተከታይ ደርሷል። ለምታሳዩኝ ድጋፍ፣ ለምትሰጡኝ አስተያየት እና አብራችሁኝ ስላላችሁ ከልብ አመሰግናለሁ። ወደ 10,000 ቤተሰብ ለመድረስ ጥቂት ነው የቀረን። አብራችሁኝ ሁኑ! @reshadapp
Claude AIን በኢትዮጵያ መጠቀም ለምትፈልጉ ሁሉ! 🔥 ብዙዎቻችሁ Claude AIን ለመጠቀም ስትሞክሩ የስልክ ቁጥር ጥያቄ እና የሀገር ገደብ አስቸግሯችኋል? አሁን መፍትሄው ተገኝቷል! ✅ ያለ ስልክ ቁጥር አካውንት መክፈት ✅ በVPN ብቻ መጠቀም የሚቻልበት መንገድ ✅ ደረጃ በደረጃ ዝርዝር መመሪያ @Reshadapp ቪድዮውን አሁኑኑ ይመልከቱ፦ 👇👇 https://youtu.be/5ci_oDf9KDk?si=-iQKuGy2_pyFValU https://www.youtube.com/watch?v=5ci_oDf9KDk?si
የዩቲዩብ ክፍያ ከጅማሬ እስከ ፍጻሜ፡ ማወቅ ያለባችሁ 9 ደረጃዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የቪዲዮ ይዘት ለምትሰሩ ወጣቶች የክፍያ ሂደቱን መረዳት ለስራችሁ ጥንካሬ ይሰጣል። ሂደቱ የሚከተለውን ይመስላል፦ * ደረጃ 1-4 (ጉዞው ከጎግል): ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ለጎግል ይከፍላሉ፣ ጎግል ደግሞ በዩቲዩብ በኩል የእናንተን ድርሻ በAdSense አካውንታችሁ ላይ ያስቀምጣል። * ደረጃ 5 (SWIFT): ይህ ዋናው ድልድይ ነው። ገንዘቡ ከአሜሪካ/ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣበት ኮድ ነው። * ደረጃ 6-7 (የሀገር ውስጥ ባንክ): ገንዘቡ ንግድ ባንክ (ወይም የመረጣችሁት ባንክ) ሲደርስ በብሄራዊ ባንክ ህግ መሰረት ምንዛሬው ይከናወናል። * ደረጃ 8-9 (IBD E እና የግል አካውንት): የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ክፍል (International Banking District) ሂደቱን ጨርሶ ወደ እናንተ ተራ የቁጠባ ሂሳብ ገቢ ያደርገዋል። ጠቃሚ ምክር፦ የAdSense መረጃችሁ እና የባንክ መረጃችሁ (Swift Code) በትክክል መገጣጠሙን ማረጋገጥ እንዳትረሱ! @Reshadapp 👍 @RESHADAPP
ቴሌግረም ቻናሌን ሞኒታይዝ አደረገልኝ ይከፍላል? | ስንትስ ከፈለኝ? Telegram Monetization Payment Proof ------------------ Please share the channel with your friends 🔥 :) ------------------ @reshadapp 🙏 ♡ㅤ ❍ㅤ ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ -------------------------- ▶️▶️ቪድዮውን ለማየት👇👇 https://youtu.be/8Q_zzTlZgVA https://www.youtube.com/watch?v=8Q_zzTlZgVA
ዩቲዩብ ቻናላችሁ እንዳይዘጋ ሊታወቁ የሚገቡ 8 አደገኛ ስህተቶች NEVER Do These 8 Things On YouTube in 2026 (Amharic) ------------------ Please share the channel with your friends 🔥 :) ------------------ @reshadapp 🙏 ♡ㅤ ❍ㅤ ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ -------------------------- 👇👇ቪድዮውን ለማየት👇👇 https://youtu.be/zQjm8_7kzpkq https://www.youtube.com/watch?v=zQjm8_7kzpkq
Eid Mubarak 🎆 🔹 https://t.me/reshadapp ❤️🔥 🔺 https://t.me/reshadapp 💙
የፋይዳ (Fayda) ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ካርዳችሁን በ telebirr SuperApp እንዴት በቀላሉ ማዘዝ (Order) ማድረግ እንደምትችሉ እናያለን።የፋይዳ (Fayda) ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ካርዳችሁን በ telebirr SuperApp እንዴት በቀላሉ ማዘዝ (Order) ማድረግ እንደምትችሉ እናያለን። ------------------ Please share the channel with your friends 🔥 :) ------------------ @reshadapp 🙏 ♡ㅤ ❍ㅤ ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ -------------------------- 👇👇ቪድዮውን ለማየት👇👇 https://youtu.be/SVzqRwHzr-Y?si https://www.youtube.com/watch?v=SVzqRwHzr-Y?si
ጎግል ከ1.75 ሚሊዮን በላይ የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙ አደገኛ መተግበሪያዎችን ከፕሌይ ስቶር አገደ ጎግል እ.ኤ.አ. በ2025 ባደረገው የደህንነት ግምገማ፤ የተጠቃሚዎችን መረጃ ያለአግባብ ለመውሰድ የሞከሩና የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙ ከ1.75 ሚሊዮን በላይ መተግበሪያዎችን ከፕሌይ ስቶር (Google Play) ማስወገዱን አስታውቋል። ከእነዚህ መተግበሪያዎች መካከል ከ255,000 በላይ የሚሆኑት የግል መረጃዎችን ለመስረቅ በመሞከራቸው የታገዱ መሆናቸውን ኩባንያው ገልጿል። ጎግል አደገኛ መተግበሪያዎችን በፍጥነት ለመለየት የሰው ሰራሽ አስተዝህሮ (Generative AI) ቴክኖሎጂን መጠቀም መጀመሩን በዚሁ ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን፤ ከኦፊሴላዊው የፕሌይ ስቶር ውጭ የወረዱ (Sideloaded) 27 ሚሊዮን አደገኛ መተግበሪያዎች (Malicious Apps) በጎግል የደህንነት ሲስተም መለየታቸውንም ይፋ አድርጓል። ⛔ከአደገኛ ሶፍትዌሮች ራሳችንን ለመጠበቅ ምን እናድርግ? 👉ታማኝ ምንጮችን ብቻ ይጠቀሙ፦ መተግበሪያዎችን ከታወቁና ይፋዊ ከሆኑ የ-App Store መድረኮች ብቻ ይጫኑ። 👉የመተግበሪያ ፈቃዶችን (Permissions) ይፈትሹ፦ አንድ መተግበሪያ ከሚሰጠው አገልግሎት ውጭ የግል መረጃዎችን (እንደ ካሜራ፣ ስልክ ቁጥሮች ወይም ጋለሪ) እንዲያገኝ ሲጠይቅ በጥንቃቄ ይመርምሩ። 👉የስልክዎን ሶፍትዌር ያዘምኑ፦ እንደ "አንድሮይድ 16" ያሉ አዳዲስ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች የላቀ የደህንነት ጥበቃ ስለሚሰጡ ስልክዎን ሁልጊዜ በማዘመን (Update በማድረግ) ይጠቀሙ። @reshadapp @reshadapp
YouTube Tax Info for Ethiopia 🇪🇹 | Avoid 30% Withholding Important things Ethiopian creators should understand የ YouTube እና Google AdSense የታክስ መረጃ አስፈላጊ ነውን ? ይህ ቪዲዮ የትምህርት እና መረጃ ዓላማ ያለው ሲሆን የታክስ መረጃ ለምን እንደሚጠየቅ እና ታክስ ባትሞሉ ምን ሊከሰት ይችላል፣ ------------------ Please share the channel with your friends 🔥 :) ------------------ @reshadapp 🙏 ♡ㅤ ❍ㅤ ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ -------------------------- ይህ ቪዲዮ ለትምህርት እና ለመረጃ ብቻ የተዘጋጀ ነው። 👇👇ቪድዮውን ለማየት👇👇 https://youtu.be/hLUfKhGCGMc https://www.youtube.com/watch?v=hLUfKhGCGMc
🚨 YouTube መጀመር ፈልገው ግን ከየት እንደሚጀምሩ አያውቁም? ይህ YouTube Channel ከዜሮ 2026 eBook የሚያስፈልግዎትን ሁሉ በአንድ የያዘ የPdf መፅሃፍ ነው። ከChannel መክፈት እስከ ገቢ ማግኘት ድረስ በቀላሉ ያስተምሮታል። 📘 አሁኑኑ ይግዙ👇 Download Now 🔥 🌟 @reshadapp @reshadapp
ማይክሮሶፍት የየካቲት ወር ለዊንዶዉስ ምርቶቹ የደህንነት ማሻሻያ አቀረበ ማይክሮሶፍት ኩባንያ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳይበር ወንጀለኞች ጥቃት እየተፈጸመባቸው ያሉ ስድስት ቀደም ብለው ያልታወቁ አደገኛ የደህንነት ክፍተቶችን (Zero-day Vulnerabilities) ማግኘቱንና እነዚህን ክፍተቶች የሚደፍኑ የሶፍትዌር ማሻሻያዎችን #Updates) መልቀቁን አስታውቋል። የመረጃ መንታፊዎች #Hackers የተጠቃሚዎችን ኮምፒውተር ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር፣ መረጃ ለመስረቅ ወይም ሲስተሞችን ለማቋረጥ የሚጠቀሙባቸው እነዚህ ክፍተቶች በሚከተሉት መንገዶች ሊከሰቱ ይችላሉ፦ 1️⃣ ለማይክሮሶፍት ዎርድ #MS_Word ተጠቃሚዎች፦ አጠራጣሪ የሆኑ የዎርድ ፋይሎች በኢሜይል ወይም በቴሌግራም ሲላኩልዎ በፍጹም አይክፈቱ! አጥቂዎች ተጠቃሚው ፋይሉን ሲከፍት ብቻ ኮምፒውተሩን በቀጥታ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችሉ ስልቶችን ጥቅም ላይ ማዋላቸው ተለይቷል። 2️⃣ አሳሳች ሊንኮች #Malicious_Links)፦ በዊንዶውስ ሲስተም ላይ ያሉ የደህንነት ማስጠንቀቂያዎችን ሰብረው የሚገቡ ሊንኮች ተገኝተዋል። ስለሆነም "ይህን ይጫኑ" የሚሉ አጠራጣሪ መልዕክቶችን ከመክፈት ይቆጠቡ። 3️⃣ ለባንክና ለንግድ ተቋማት፦ የኤስ.ኤ.ፒ (SAP) የንግድ ሶፍትዌር የምትጠቀሙ ተቋማት ፣ የደንበኞቻችሁ መረጃ ለጥቃት እንዳይጋለጥ በአስቸኳይ ሲስተሞቻችሁን እንድታዘምኑ (Update እንድታደርጉ) ይመከራል። @reshadapp @reshadapp