tgindex
Riseup Tech
@riseuptechанглийский

Is placed in Addis Ababa it provides (MERN)Website Development, basic computer skill course, Language and other short term course.

Последний пост
13:56
Последнее чтение
00:23
Постов за неделю
12
Всего постов
46
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 812
−10 за 3 дн.
Сутки
−4
−0,14%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
769
40 постов
Вовлечённость
27,3%
к подписчикам
Постов в день
1,7
всего 46
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
281
1/48двое суток
322
1/72трое суток
347

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13:5623715

    Junior Developer ስትሆኑ እነዚህን 5 ስህተቶች አትስሩ Coding መማር ብቻ በቂ አይደለም። ብዙ Beginner Developers ተመሳሳይ ስህተቶችን ይደግማሉ። እነዚህን 5 ነገሮች ግን በተቻለ መጠን አስወግዱ፦ 1. Tutorial ብቻ መመልከት Video ማየት እውቀት ይሰጣል። ግን የምትማሩትን በProject ላይ ሳትተገብሩ እውቀቱ በቀላሉ ሊረሳ ይችላል። 2. Copy & Paste Coding ሌላ ሰው የጻፈውን Code መጠቀም ብቻ ከሆነ፣ ችግር ሲመጣ ለመፍታት ይከብዳል። 3. Project አለመስራት Todo App፣ Portfolio፣Stock Management፣ Dashboard ወይም Small Business Website ያሉ ነገሮችን ሞክሩ። 4. GitHub ችላ ማለት GitHub ኮድ ማስቀመጫ ብቻ አይደለም። የምትሰሩትን ፕሮጀክት እና የምትማሩበትን ሂደት ማሳያም ነው። 5. "ሁሉን ነገር እስካውቅ ድረስ አልጀምርም" ማለት እውነታው፣ ሁሉንም ነገር አታውቁም። Senior Developers እንኳን የማያውቁት ብዙ ነው። 💡 Learn → Build → Fail → Fix → Improve @riseuptech

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🚀 Prompting ≠ Context Engineering AI ላይ ጥሩ prompt መጻፍ ብቻ በቂ አይደለም። Prompting tells AI HOW to think. Context tells AI WHAT to know. ከAI የተሻለ መልስ ለማግኘት፣ perfect prompt ከመፈለግ ይልቅ ትክክለኛውን context, information, memory & data መስጠት ወሳኝ ነው። 👉 Better context = Better answers = Better AI systems. 💬 Which one do you think matters more: Prompting or Context? @riseuptech

  • 🔐 ኢሜይላችሁ ከምታስቡት በላይ አስፈላጊ ነው! ኢሜይል የምንጠቀመው መልዕክት ለመቀበል ብቻ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? እንደገና አስቡበት። ኢሜይላችሁ ብዙ ጊዜ የዲጂታል ህይወታችሁ ዋና ቁልፍ ነው። አንድ ሰው የኢሜይላችሁን መዳረሻ ካገኘ፣ የሚከተሉትን አካውንቶች የይለፍ ቃል መቀየር ይችላል፦ 📱 Social Media አካውንቶች 💳 Online Services ☁️ Cloud Storage 💼 የስራ አካውንቶች 🛒 Online Shopping አካውንቶች ስለዚህ ዛሬ 3 ደቂቃ ወስዳችሁ እነዚህን አረጋግጡ፦ 1️⃣ 2-Factor Authentication (2FA) አብሩ አንድ ሰው የይለፍ ቃላችሁን ቢያገኝም፣ ወደ አካውንታችሁ ለመግባት ተጨማሪ የማረጋገጫ ደረጃ ያስፈልገዋል። 2️⃣ ልዩ የይለፍ ቃል ተጠቀሙ ለኢሜይላችሁ እና ለሌሎች አካውንቶቻችሁ አንድ ዓይነት Password አትጠቀሙ። 3️⃣ በአካውንታችሁ የገቡ መሣሪያዎችን ያረጋግጡ የማታውቁት  Device ካገኛችሁ ከአካውንታችሁ  አስወግዱት (terminate session አድርጉ)። 💡 ዛሬ የምትወስዱት አንድ ትንሽ የደህንነት እርምጃ፣ ነገ ትልቅ ችግርን ሊከላከል ይችላል። ዲጂታል ደህንነታችሁን አንድ ችግር ከተፈጠረ በኋላ ማሰብ የለባችሁም። ከማስፈለጉ በፊት ጠብቁት። 🔒 @riseuptech

  • 🎨 ዲዛይናችሁ ለምን “የሆነ ነገር ጎድሎታል” የሚመስል ይሆናል? የጥሩ ዲዛይነር ዲዛይን ማለት ብዙ ነገሮችን መጨመር አይደለም። ትክክለኛዎቹን ነገሮች በትክክል ማደራጀት ነው። 🎯ዲዛይናችሁን print ከማድረጋችሁ በፊት እራሳችሁን ይህንን ጠይቁ፦ 🎨 ቀለሞቼ ተመጣጣኝ ናቸው? 🔤 ፎንቶቼ ለማንበብ ቀላል ናቸው? 📐 ሁሉም ነገር በትክክል ተደራጅቷል? 👀 ዋናው መልዕክት በግልጽ ይታያል? 💡 አንዳንድ ጊዜ ዲዛይናችሁ የሚያሻሽለው አዲስ ነገር መጨመር ሳይሆን፣ አስፈላጊ ያልሆነውን ማስወገድ ነው። 🚀 በየቀኑ ተለማመዱ። 📈 በየፕሮጀክቱ ራሳችሁን አሻሽሉ። 🎨 የተሻለ ዲዛይነር ለመሆን መሞከራችሁን አታቁሙ! 💚 የCreative ጉዟችሁን ከRiseUp Tech ጋር ጀምሩ! 💬 ከእነዚህ የዲዛይን ስህተቶች የትኛው በብዛት ያጋጥማችኋል? በComment ንገሩን! 👇 @riseuptech

  • 💻 የመጀመሪያውን የ Developer Job ከማመልከታችሁ በፊት GitHubችሁን አረጋግጡ! GitHub ኮዳችሁን ለማስቀመጥ ብቻ የምትጠቀሙበት ቦታ አይደለም። ለRecruiter ደግሞ በእርግጥ ምን መገንባት እንደምትችሉ በፍጥነት የሚያይበት መንገድ ነው። ስለዚህ Job ለማመልከት ከመጀመራችሁ በፊት GitHubችሁን እነዚህን 5 ነገሮች እንዳሉት አረጋግጡ፦ 🛠 1.  2–4 ጥራት ያላቸው Projects 20 Projects ማድረግ አያስፈልጋችሁም ። ጥቂት ግን በጥሩ ሁኔታ የተሰሩ Projects ከብዙ ያልተጠናቀቁ Projects ይሻላሉ። 📝 2. ግልጽ README Files Projectችሁ ምን እንደሚሰራ፣ ምን Technologies እንደተጠቀማችሁ እና እንዴት ማስኬድ እንደሚቻል በግልጽ አስረዱ። 📸 3. Screenshot ወይም Demo የሠራችሁትን ነገር ኮዱን ሳያነቡ በቀላሉ እንዲረዱት ለማድረግ ይረዳችኋል። 🧹 4. ንጹህ እና የተደራጀ Code ጥሩ Naming፣ የተደራጁ Files እና ግልጽ Code...  ለምትሠሩት ነገር ምን ያህል ትኩረት እንዳላችሁ ያሳያል። 📈 5. የእድገት ማስረጃ GitHubችሁ... እየተማራችሁ፣ ራሳችሁን update እያደረጋችሁ እና በተግባር እየሠራችሁ እንደሆነ ማሳየት አለበት። 💡 አስታውሱ፦ GitHubችሁ የCode ማስቀመጫ ቦታ ብቻ አይደለም። መገንባት የምትችሉትን ነገር የሚያሳይ ታሪካችሁ ነው። Perfect Portfolio መኖር አያስፈልግም። እድገታችሁን የሚያሳይ Portfolio ብቻ ግን ያስፈልጋችኋል። 🚀👉 ዛሬ GitHubችሁን ተመልከቱ። መጀመሪያ ምን ማሻሻል ያስፈልጋችኋል?        @riseUptech

  • 11 авг.1 1331016

    💼 በአንድ Junior Developer ውስጥ Recruiters በእርግጥ ምን ይመለከታሉ? Recruiters ሁሉንም ነገር የሚያውቅ Developer እየፈለጉ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ❌ሁልጊዜ አይደለም! Junior Developer ስትሆኑ፣ Recruiters ብዙ ጊዜ የሚመለከቱት ከዚህ የበለጠ ተግባራዊ ነገር ነው፦ መገንባት፣ መማር እና ችግር መፍታት ትችላላችሁ? እነዚህ 5 ነገሮች እንድትለዩ ሊያደርጓችሁ ይችላሉ፦ 1️⃣ ትክክለኛ Projects > Certificates Certificate አንድ ኮርስ እንደጨረሳችሁ ያሳያል። አንድ Project ግን በእርግጥ ምን መስራት እንደምትችሉ ያሳያል። ቀላል ቢሆንም እንኳ አንድ ነገርን ስሩ/ገንቡ፦ 🌐 Website 📱 Small App 🤖 AI-powered Tool 📊 Data Dashboard 2️⃣ የተደራጀ GitHub Profile GitHub የኮድ አሰራራችሁን እና የምትማሩበትን መንገድ ሊያሳይ ይችላል። ጥሩ Projects ምረጡ፣ አደራጁዋቸው፣ ግልጽ README ጻፉ። እና እባካችሁ… Projects ሁሉንም “final-final-v2” ብላችሁ አትሰይሙ። 😅 3️⃣ Problem-Solving Skill ሁልጊዜ መልሱን ማወቅ አይጠበቅባችሁም። እና ይሄ ችግር አይደለም። አስፈላጊው ችግሩን፦ → መረዳት → ወደ ትናንሽ ክፍሎች መክፈል → መረጃ መፈለግ → Solutions መሞከር → ከስህተቶች መማር መቻላችሁ ነው። 4️⃣ Communication በቴክኒክ ጥሩ መሆን ብቻ በቂ አይደለም። የገነባችሁትን Project በቀላል ቋንቋ ማስረዳትም መቻል አለባችሁ። Projects ስታስረዱ ይህንን መዋቅር ሞክሩ፦ “ይህን Project የገነባሁት ___ ምክንያት ነው። ትልቁ ችግር የነበረው ___ ነው። የፈታሁትም ___ በመጠቀም ነው። ተጨማሪ ጊዜ ቢኖረኝ ___ አደርግ ነበር።” 5️⃣ የመማር ፍላጎት Technology ሁልጊዜ እየተቀየረ ነው። Junior Developer ስትሆኑ ሁሉንም ነገር ማወቅ አያስፈልጋችሁም። የማታውቁት ነገር ሲያጋጥማችሁ፣ እንዴት መማር እንዳለባችሁ ማወቃችሁ ነው አስፈላጊው። 💡 ግባችሁ Senior Developer መስሎ መታየት አይደለም። ግባችሁ ለመማር፣ ለማደግ እና የተሻለ Developer ለመሆን ዝግጁ የሆነ Junior Developer መሆናችሁን ማሳየት ነው። 🚀 Build. Learn. Improve. Repeat. @riseuptech

  • ዋናው ቁርጠኛ መሆን ነው!

  • 8 авг.957101

    “አይ፣ አመሰግናለሁ፤ AI እጠቀማለሁ!” 😁🤖 Really AI እኛን ይተካናል? ይተካኛል ብለህ ከመጨነቅ፣ ከAI ጋር አብረህ ለማደግ ዝግጁ ነኝ? ብለህ ራስህን ጠይቅ። AI የሰው ልጅ አቅም መጨረሻ አይደለም፤ አቅማችንን ወደ አዲስ ደረጃ የሚያሻግር መሳሪያ እንጂ። AI ስለሚያስብ አንተ ማሰብን አትተው። AI ከአንተ ጋር ስለሚሰራ፣ የበለጠ በሰፊው ማሰብ ጀምር። መሳሪያውን(Tool) ተጠቀም። ሰብአዊነትህን ግን ጠብቅ። 😊 የወደፊቱ ዓለም AIን በሚፈሩ ሰዎች ሳይሆን፣ ከAI ጋር አብረው መነሳትን በሚማሩ ሰዎች ነው የሚገነባው። @riseuptech

  • Graphic Design ደግሞ 🏠 ከቤት ግንባታ ጋር በደንብ ይመሳሰላል። እንዴት መሰላችሁ፦ 🏗 Layout = Floor Plan ቤት ከመገንባቱ በፊት የክፍሎቹ አቀማመጥ እቅድ እንደሚወጣው ሁሉ፣ Graphic Design ውስጥም Layout እያንዳንዱ ነገር የት እንደሚቀመጥ ይወሰናል። ግንባታው ካለቀ በኋላ የቤቱ ቀለም ለሰዎች የሚማርክ፣ ጊዜውን ያማከለ ዘመናዊ እንደሚደረገው Design ውስጥም Colors የሰውን ትኩረት ይስባሉ። 🔤 Typography = Signboard ቤቱ ምንም ያህል ያመረ ቢሆን የቤቱ ቁጥር/መግቢያው ግልፅ ካልሆነ እንግዶች እንደሚሳሳቱ ሁሉ፣ Design ውስጥም Typography መልእክቱ በቀላሉ እንዲነበብና ሰዎችን እንዲመራ ያደርጋል። 📏 Spacing = Room Space ዕቃዎችን በጣም ተጣብቀው ካስቀመጣችኋቸው ክፍሉ ይጨናነቃል። Design ውስጥም በቂ ክፍተት (Whitespace) መተው ንጹህ እና ፕሮፌሽናል መልክ ይሰጣል። 🖼 Images & Icons = Furniture ሶፋ/መጅሊስ፣ ጠረጴዛ እና ሌሎች የቤት ዕቃዎች ቤቱን እንደሚያሳምሩ፣ Images እና Icons ደግሞ Designን የበለጠ ማራኪ ያደርጉታል። ስለዚህ Graphic Design ማለት ቀለም መጨመር ብቻ አይደለም። ሰዎች በቀላሉ እንዲያዩ፣ እንዲረዱ እና እንዲማረኩ መረጃን በሥርዓት ማቅረብ ነው። @riseuptech

  • 6 авг.1 580312

    🍽 Coding ከRestaurant ጋር ምን ግንኙነት አለው?🤔 በመጀመሪያ ስናየው ምንም የማይገናኝ ሊመስል ይችላል። ግን አንድ Website እንዴት እንደሚሰራ በRestaurant ምሳሌ ብንመለከት በጣም ቀላል ይሆናል። የምትወዱትን ሬስቶራንት 🍽  አስቡ... 👨‍🍳 Backend የሬስቶራንቱ ኩሽና ነው። ከዓይን ውጭ ያለው ሁሉም ስራ እዚያ ይሰራል፤ ምግብ ይዘጋጃል። በተመሳሳይ ሁኔታ በዌብ አፕሊኬሽን ውስጥ Backend መረጃን ያስተናግዳል፣ ሎጂኩን ያከናውናል እና ሁሉንም ከጀርባ ያስተዳድራል። 🧑‍🍽 Frontend ደግሞ የመመገቢያው ቦታ ነው። ደንበኛው የሚያየውና የሚጠቀምበት ሁሉ እዚህ ነው። በድረ-ገጽ ወይም በሞባይል መተግበሪያ ውስጥ የምታዩት ገጾች እና ዲዛይኖች ሁሉ Frontend ናቸው። 🧑‍💼 API ደግሞ አስተናጋጁ (Waiter) ነው። ትዕዛዛችሁን ከጠረጴዛ ወደ ኩሽና ያደርሳል፣ ከዚያም የተዘጋጀውን ምግብ መልሶ ያመጣል። በፕሮግራሚንግም API በFrontend እና Backend መካከል ጥያቄ (Request) እና መልስ (Response) ያስተላልፋል። 📋 API Endpoints የምግብ ዝርዝር (Menu) ናቸው። በሜኑው ላይ ያለ እያንዳንዱ አማራጭ አንድ አገልግሎትን ይወክላል። ለምሳሌ፦ 🛍 ምርቶችን ማየት (View Products) 🔐 መግባት (Sign In) 🛒 ትዕዛዝ መስጠት (Place an Order) 👤 ፕሮፋይልን ማስተካከል (Update Your Profile) 📦 Database የማከማቻ ክፍል ነው። በሬስቶራንት ውስጥ እቃዎችና ግብዓቶች እንደሚቀመጡበት ማከማቻ፣ Database ደግሞ የተጠቃሚዎችን መረጃ፣ የምርቶችን መረጃ፣ ትዕዛዞችን እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያከማቻል። 💡 ምግብ ሲያዝዙ የሚካሄደው ሂደት ሁሉ በተመሳሳይ በዌብሳይት ይከናወናል፦👇 Frontend ➜ API ➜ Backend ➜ Database ➜ Backend ➜ API ➜ Frontend ይህ ብዙ ዘመናዊ ድረ-ገጾችና የሞባይል መተግበሪያዎች የሚሰሩበት መንገድ ነው! 💚 በRiseUp Tech ውስብስብ የቴክኖሎጂ ሀሳቦችን ከዕለታዊ ህይወት ምሳሌዎች ጋር በማያያዝ ለሁሉም ቀላል እና ግልጽ እናደርጋለን። 🚀 እንደዚህ ያሉ ቀላል፣ ተግባራዊ እና ለጀማሪዎች ተስማሚ የኮዲንግ ትምህርቶችን ለማግኘት RiseUp Techን ይከተሉ! 💬 ቀጣዩን በዕለታዊ ህይወት ምሳሌ እንድናብራራው የምትፈልጉት የቴክኖሎጂ ርዕስ ምንድን ነው? በኮመንት አጋሩን! 👇 @riseuptech

  • ነገር ግን Ctrl + Z ህይወት ላይ አይሠራም!!! @riseuptech

  • Just b/c it's hard doesn't mean it's impossible. The only way to fail is to stop trying. @riseuptech

  • 2 авг.1 13893из bintt_jemal

    ትንሽ መዘግየት ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል! አስተውላቹ ከሆነ በህይወታችን ትልልቅ እድሎችን የሚያባክኑብን ትልልቅ መሰናክሎች ሳይሆኑ፣ በየቀኑ የምንሰራቸው ትናንሽ የ"ነገ" ቀጠሮዎች ናቸው። ነገ እጀምራለሁ... እያልን የተውነው አዲስ ኮርስ፣ የሰነፍነው ኮዲንግ፣ ሳናናግረው የቀረነው ድርጅት... ዛሬ የእኛ እቅዶች ነበሩ፤ ነገ ግን የሌላ ሰው ስኬቶች ሆነው ስናያቸው የቁጭት ዋጋ እንከፍላለን! ዛሬ አነስተኛዋን እርምጃ ወስደን መስራት ካልጀመርን፣ ነገ የሚጠብቀን የቁጭት ዋጋ በጣም ውድ ነው።  የሀገራችን ሰው "የማያቋርጥ ጠብታ አለት ያጎደጉዳል" እንዲል፤ ትልልቅ ስኬቶች የሚገነቡት በየቀኑ በሚደረጉ ትናንሽ ጥረቶች እንጂ በነገ የተደራጀ ቀጠሮ አይደለም።😊 @bintt_jemal

  • 2 авг.1 1576

    ብዙዎቻችሁ በውስጥ መስመር (Inbox) እንዲሁም በኮመንት "ዲዛይኑ አሪፍ ነው፡ ግን ፅሁፉ ላይ ስህተት አለ" ብላችናል፤ በጥልቀት አይታችሁ ላነሳችሁልን አስተያየት እጅግ በጣም እናመሰግናለን! 😁 ልጆች አይደሉ በሂደት... ያስተካክላሉ! ገና እየተለማመዱ ስለሆነ ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ ዲዛይኑ ላይ በማድረጋቸው ለፅሁፉ ያን ያህል ትኩረት አልሰጡትም። እኛም የነሱን ጥረትና ተነሳሽነት ለማበረታታት ስንል የሰሩትን ምንም ሳንነካ ነው ያቀረብንላችሁ።

  • 1 авг.1 187

    видео или голосовое, без подписи

Riseup Tech — tgindex