tgindex
𝐁𝐞𝐧𝐚𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡

𝐁𝐞𝐧𝐚𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡

Статистика

ይህ ቻናል በወንድማችሁ ሁሰይን አል-በናን (አቡ ሱፍያን) የተከፈተ ሲሆን፣ ስለ ኮምፒውተር ትምህርቶችና ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎችንና እውቀቶችን የምናካፍልበት ቻናል ነው።

Последний пост
13 февр.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 514
−4 за 4 дн.
Сутки
−3
−0,20%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
4 285
19 постов
Вовлечённость
283,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 февр.1 26512иС AbuSufiyan_Albenan

    ❌ቴሌ ግራም ላይ መጠለፌን(ሀክ መደረጌን) እንደት ማወቅ እችላለሁ? 🌐እንድሁም ቴሌ ግራሜን እንዳይጠልፉብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? 📲በ ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን ~ ለሌሎችም ሊጠቅም ይችላል ሼር አድርጉላቸው! t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

  • The owner of this channel has been inactive for the last 17 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

  • 🏗ሙዘይን፡የግንባታ ህልምዎን ቀላል ለማድረግ አጋርዎ! • እየገነቡ ነው? እድሳትስ?  ሙዘይን የኮንስትራክሽን ዕቃ አቅራቢ ድርጅት ለግንባታ ፕሮጀክትዎ የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ዓይነት የግንባታ ቁሳቁሶች በአንድ ቦታ፣ በተመጣጣኝ ዋጋና ፈጣን አገልግሎት ያቀርብላችኋል።  በተለይም በቱርክ ማሽን የተመረቱ ጥራት ያላቸው ቡልኬቶችን ማቅረብ መለያችን ነው! •የ ቱርክ ቡልኬት፣ ሲሚንቶ፣ ማርብል፣ቴራዝ፣ ብረት፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የውስጥና የውጭ ማስጌጫ እቃዎች፣ እና ሌሎችም ለግንባታዎ፣ለእድሳትዎ፣አልፎ ተርፎም ለቤትዎ ዲዛይን የሚያስፈልጉዎትን ሁሉንም ነገር ከ ሙዘይኖች ጋር ያገኛሉ። | 📍የስራ ቦታ አድራሻ፦ 1ኛ-ሲዳም አዋሽ ከኖክ ማዳያው ገባ ብሎ፣ 2ኛ-ገላን ከተማ ከሶፉ ዑመር ፊት ለፊት 📞ይደውሉልን! +251910716296 +251921041742 | 💬ቴሌ ግራም ግሩፕ፦ @Muzeyn_PLC 📞የዋትስ አፕ ግሩፕ፦ https://chat.whatsapp.com/EYJezRcKq6t3cQ8ELZMcm4 Š የደንበኞቻችን እርካታ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው!

  • 21 июл. 2025 Đł.2 10018иС AbuSufiyan_Albenan

    ~ ዘመኑ የቴክኖሎጂ መሆኑን ደጋግሜ ብነግራችሁም፣ ይህን እውነት በወንድሜ በአብዱል ሀኪም ምሳሌ ልትረዱት ትችላላችሁ። ከሁለት አመት በፊት፣ በዚያን ጊዜ በ25,000 ብር እንኳን ባልሞላ ገንዘብ ሁለት ምርጥ የስራ ድረ-ገጾችን (job websites) ሰርቶልኝ ነበር። በዚያን ጊዜም ስራው አስደናቂ ነበር! ዛሬ ግን  ሁለት ሌላ አዳዲስ ድረ-ገጾችን እንድሰራለት ስንጠይቀው፣ በምክር እና በውይይት 150,000 ብር ለመክፈል ተስማምተናል። ይህ ገንዘብ ከፍ ያለ መስሎ ቢታይም፣ ለሱ እውቀትና ለስራው ጥራት ሲታይ እውነት ለመናገር ሲያንሰው ነው! ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ…አሁንም ቢሆን ሆነ ወደፊት፣ ትኩረታችሁን በቴክኖሎጂ እውቀት ላይ አድርጉ! በተለይም የሚከተሉትን ዘርፎች በሚገባ ተማሩባቸው፦ • የዌብ ዲቨሎ-ፕመንት (Web Development) • ግራፊክ ዲዛይን (Graphic Design) • ቪዲዮ ኤዲቲንግ (Video Editing) • ዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) እነዚህ ዘርፎች የወደፊቱ የስራ ገበያ መሰረቶች ናቸው። ጊዜና ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ በነዚህ ዘርፎች እውቀታችሁን አሳድጉ፤ ውጤቱ በእርግጥም የላቀ ይሆናል! =t.me/AbuSufiyan_Albenan

  • ምርጥ ቴሌግራም ቦቶች -①- • @filetobot ያልተገደበ cloud storage የምታገኙበት bot. • @DropmailBot ነፃ email adress የምታገኙበት (ለከባባድ ነገር ባትጠቀሙት እንመክራለን ለsocial midea ለመሳሰሉት) • @DrWebBot ማንኛውም ሰው ሊንክ ልኮላችሁ አልያም የተጠራጠራችሁት ሊንክ ካለ ለዚህ bot ላኩለት እና check ያደርግላችኋል። • @check_my_text_bot english ስትፅፉ spelling  ስህተት ካለ ያስተካክልላችኋል even if ለቻናላችሁ admin አርጋችሁት ስትፖስቱ ያስተካክልላችኋል። • @UTasksBot ልትሰሩ ያሰባችሁን እና የሰራችሁትን ስራዎች እዚሁ telegram ላይ manege ታረጉበታላችሁ ። • @WikipediaPDF_bot Wikipedia እዚሁ search አድርጋችሁ ማንበብ እና በ pdf ማውረድ የሚያስላችሁ bot. •@CopilotOfficialBot ትክክለኛው Microsoft copilot telegram bot. • @FontStylerBot የፃፋችሁለትን text በተለያዩ disign እና font ያደርግላችኋል።

  • 28 июн. 2025 Đł.16,4 тыс167

    💡 አስደሳች ዜና! ነፃ የዌብሳይት ዲቨሎፕመንት ስልጠና በቅርቡ ይጀምራል! 💻 የተካነ Web Developer መሆን ይፈልጋሉ?  በቴሌግራም ላይ ነፃ የ3 ወር ስልጠናችንን ይከታተሉ! HTML, CSS እና JAVASCRIPT ያካተተ ነው።  📅 ሰኔ 30/2017 ይጀምራል!  1️⃣ በዚህ https://t.me/hilal_web_dev የቴሌግራም ግሩፕ 3️⃣ ለሌሎች share በማድረግ ይተባበሩን 🚀  https://t.me/hilal_web_dev

  • 27 июн. 2025 Đł.2 1543иС riseuptech

    የክረምት ዕረፍትዎን እንዲሁ በከንቱ ማሳለፍ ይፈልጋሉ? ወይንስ ለልጅዎ የወደፊት ሕይወት ጠቃሚ ኢንቨስትመንት ማድረግ? እንግዲያውስ አፍታም አያመንቱ! Riseup Tech Solution ህይወትዎን ከፍ የሚያደርግ ልዩ እድል አዘጋጅቶላቹሀል! በዚህ ክረምት በቴክኖሎጂ ዓለም የራስዎን ታሪክ ይጻፉ! ጊዜዎን ወደ እውቀት ይቀይሩ! አሁን ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላይን ወይም በአካል፣ ምቹ በሆኑ ክፍሎቻችን ውስጥ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ስልጠናዎች ልጆቾን እና እራስዎን ያብቁ። ሴቶች በሴት መምህራን፣ ወንዶችም በወንድ መምህራን በነፃነት መማር ይችላሉ። የወደፊት ህይወትዎን በገበያ ተፈላጊ እውቀት ያንጹ! 💻 Fullstack (MERN) website development: የራስዎን ድረ-ገጽ መገንባት ይፈልጋሉ? እዚህ ይጀምሩ! 💻 Basic Computer Skill: ከኮምፒውተር ጋር ለመተዋወቅ ለሚፈልጉ ምርጥ መነሻ። 💻 Python: በዓለም ላይ ካሉ ተፈላጊ ቋንቋዎች አንዱን ይማሩ። 💻 Mobile app development: የራስዎን የሞባይል አፕሊኬሽን ይፍጠሩ! 📚 English & Arabic: የቋንቋ ችሎታዎን ያሳድጉ። ዛሬውኑ ይመዝገቡና ነገዎን አሁኑኑ ብሩህ ያድርጉ! https://riseuptechsolution.com/form.php አድራሻችን፦ ቤተል ከአደባባይ ወደ ዌራ ወረድ ብሎ ዳሽን ባንክ አጠገብ ያለው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ስልክ: +251907667777 ቴሌግራም: @riseuptechsolution | https://t.me/riseuptech ይህ ክረምት ከዚህ በፊት አይተነው የማናውቀውን የለውጥ በር የሚከፍትልዎ ወርቃማ እድል ነው! አያምልጥዎ!

  • Coding ለመማር የሚጠቅሙ የmobile መተግበሪያዎች ⚫ Mimo ጀማሪ ከሆናችሁ እና እንደ JavaScript, typescript, python ያሉ courses የምትማሩበት መተግበሪያ ነው። በተጨማሪም puzzle በመስራት practice ማድረግ ትችላላችሁ። ⚫ Enki የበርካታ programming language concept የምትማሩበት መተግበሪያ ነው። የተለያዩ ከጀማሪ እስከ Advanced የcoding challenges puzzle ጨምሮ አሉት። ⚫ Codecademy go Python, HTML/CSS, JavaScript, SQL እና የመሳሰሉትን እዚህ ላይ መማር ትችላላችሁ። እንዲሁም በርካታ videos እና articles ተካተውበታል። ⚫ encode web development እዛው እየሰራችሁ የምትማሩበት መተግበሪያ ነው። encode ጥራት ባላቸው content ይታወቃል። ⚫ Programming Hub የCoddingን ትንሽ concept ከተረዳችሁ ቡኋላ እዚህ ላይ ራሳችሁን challeng ማድረግ ትችላላችሁ። በተጨማሪም አንዳንድ የcoding courses አሉት። =t.me/Benan_Tech

  • 19 июн. 2025 Đł.2 04155иС Benan_Tech

    በነፃ ምርጥ ምርጥ ሎጎዎችን የምትሰሩበት ዌብ ሳይት ነው! https://www.zarla.com/free-logo-maker

  • 15 июн. 2025 Đł.2 16151иС AbuSufiyan_Albenan

    11 High Income Skills You Can Learn For Free Online (YouTube) 1. Copywriting 2. Photography 3. Video Editing 4. Proofreading 5. Transcription 6. Public Speaking 7. Digital Marketing 8. Web Development 9. Graphic Designing 10. Game Development 11. Software Development Learn for free 👇👇 A.  Learn copywriting 1. youtu.be/Pum2gV7N_9A 2. youtu.be/9qZcT9I8W4g 3. youtu.be/B13gAAcqrAc 4. youtu.be/UfCgUv8-HlI 5. youtu.be/LU4gHGdYDI0 B. Learn photography 1. youtu.be/yhAmMUi2NmM 2. youtu.be/LxO-6rlihSg 3. youtu.be/V7z7BAZdt2M C. Learn video editing 1. youtu.be/y7Ci_H9bYEk 2. youtu.be/oC3gXr1s_aU 3. youtu.be/ZQDGJn89uNk 4. youtu.be/MqwlW76sFCM D. Learn to proofread 1. youtu.be/Up3WZJn4OpQ 2. youtu.be/sNbi3h7Ucr0 3. youtu.be/pYb7p0DiVMI 4. youtu.be/14pgya2Xl8o E. Learn transcription 1. youtu.be/bltDLL6-CbQ 2. youtube.com/playlist?list=… F. Learn public speaking 1. youtu.be/i5mYphUoOCs 2. youtu.be/dHAbmoFHqgA 3. youtu.be/7tzentBmmUc 4. youtu.be/k8GvTgWtR7o G. Learn digital marketing 1. youtu.be/hiEb1m7CXH4 2. youtu.be/BjRmz6rO9SQ H. Learn web development 1. youtu.be/Q33KBiDriJY 2. youtu.be/zAfLvFHKUS0 I. Learn graphic designing 1. youtu.be/9QTCvayLhCA 2. youtu.be/k0EyAs9Q4NI J. Learn game development 1. youtu.be/wKNyTvImeqY 2. youtu.be/6luTavBJ3gw K. Learn software development 1. youtu.be/zOjov-2OZ0E 2. youtu.be/cYXkNOeKXQM L. Learn affiliate marketing 1. youtu.be/ZnKQlGpVWpE 2. youtu.be/ZjhZ7vCl3HQ 3. youtu.be/mzBHq9BK6i4 M.Learn dropshipping 1. youtu.be/fMt3kv1vc_A 2. youtu.be/rqGNDT_utao

  • Eye protection mode አሁን አሁን አብዛኞቻችን ስልካችን ላይ የምናሳልፈው የጊዜ መጠን እየጨመረ መጥቷል። ታዲያ እጃችን ላይ ያለው ስልክ  ምንም ያክል በርካታ ጥቅም ቢኖረውም የተለያዩ ጉዳቶች አሉት። የጤና ጉዳትም ስልክ ከሚያመጣቸው ጉዳቶች አንዱ ነው። ይህንን ጉዳት ለመቀነስ አንዳንድ የስልክ አምራች ድርጅቶች Eye protection mode የተሰኘ feature ካስተዋወቁ ሰነባብተዋል። Eye protection mode ከስልክ የሚለቀቀውን blue light ray በመቀነስ screen በምንጠቀምበት ጊዜ ምቾት እንዲሰማን የሚያደርግ እና አይናችን እንዳይጨናነቅ የሚያደርግ feature ነው። ይህ feature የአይን ጤናን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። Eye protection mode enable ለማድረግ notification bar ላይ በመሄድ Eye protection mode የሚለውን ማብራት አልያም ወደ Settings በመሄድ > Display > Eye protection mode የሚለውን turn on ማድረግ። ይሁን እንጂ እንደየ ስልኩ ስያሚውም ሊለያይ ይችላል። በቀን ስንት ሰዓት ስልካችሁ ላይ እንደምታሳልፉ comment ላይ አሳውቁን። t.me/Benan_Tech

  • ~ ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ላይ Sleep, Hibernate, Shutdown ልዩነታቸው ምንድን ነው? •ኮምፒውተርም እንደ ሰው ይደክማል፤ ጫና ሲበዛበትም ከተለመደው ፍጥነቱ ዘግይቶ መንቀራፈፍ ይጀምራል። በመሆኑም ስራችንን ከጨረስን በኋላ በተለያዩ መንገዶች ኮምፒውተራችን ማጥፋት ወይም ማሳረፍ ያስፈልጋል። •ኮምፒውተራችን ተርን ኦፍ፣ ስሊፕ አልያም ሀይበርኔት በማድረግ እረፍት እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን። ይሁን እንጂ የትኛው የተሻለ መንገድ ነው የሚለው የሚያከራክር ጉዳይ ነው። እናም ከዚህ በታች ሾለ ሶስቱ ኮምፒውተር ማሳረፊያ ዘዴዎች ጥቅሞች በዝርዝር እንመለከታለን። ◻️ስሊፕ • ላፕቶፕ ኮምፒውተራችን ስሊፕ ሞድ ላይ ስናደርገው ከራሙ በስተቀር ወደ ሁሉም የኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚሰራጨው ሀይል ይቋረጣል። የስሊፕ ሌላኛው ጥቅሙ ኮምፒውተራችን ከመዝጋታችን በፊት የተከፈቱ ስራዎችን ሴቭ ማድረጉ ነው። ከዚህም ባሻገር ያቆምነውን ሾል በፍጥነት ለመጀመር ይረዳል። ◻️ሸት ዳውን • ብዙዎቻችን ኮምፒውተራችን የምናጠፋው ሸት ዳውን የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሁሉም ነገር ይዘጋል  (ራንደም አክሰስ ሚሞሪ) ሚሞሪም ይጠፋል በአጠቃላይ ኮምፒውተሩ ምንም እንቅስቃሴ አይኖረውም። በሸት ዳውን የተዘጋ ኮምፒውተር ምንም ሀይል አይጠቀምም። ◻️ሀይበርኔት • ይህ አማራጭ ደግሞ በስሊፕ እና በሸት ዳውን መሀል የሚገኝ ነው። ሀይበርኔት ስናደርግ እያከናወንናቸው የነበሩ ስራዎች በራም ሳይሆን በኮምፒውተራችን ሀርድ ድራይቭ ላይ ይቀመጣሉ። ኮምፒውተራችን ስናስነሳም ሴቭ ሳናደርግ ትተናቸው የነበሩ ስራዎችን የምናገኛቸው ሲሆን ከስሊፕ አንፃር አነስተኛ ሀይል ይወስዳል። ኮምፒውተራችን ሀይል በመጨረስ ላይ ከሆነ ሀይበርኔት ተመራጭ ነው። =t.me/Benan_Tech

  • ~ቴሌግራም ላይ ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level 1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ። ይህን ለማስተካካል Settings - privacy and security - passcode 2. 2-step verification ተጠቀሙ። 2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው። Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት። ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ። 3. ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል። ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate secc ቀንሷቸው። 4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ። 5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ። 6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ። 7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ። 8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት። 9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ። Phone number - Nobody Last seen & online - My contacts Profile photos - My contacts Forwarded message - Nobody Calls - My contacts Group & channels - My contacts ~ t.me/Benan_Tech t.me/Benan_Tech

  • ስልክ ስንገዛ መጀመሪያ ማየት ያለብን ምንድነው!? ―መልሱ Processor ሲሆን፦ የስልክ Processor  ልክ እንደ ሰዉ አእምሮ  አድርጋቹ ማሰብ ትችላላችሁ።ስልኩ ላይ የምታደርጉት ማንኛውም ነገር የሚከናወነው በዚህ Processor አማካኝነት ነዉ። የተወሰኑትን እንመልከት :- ① Camera አንድ ስልክ አሪፍ Camera እንዲኖረዉ ከሚጠቀመዉ የ Camera Sensor በተጨማሪ ጥሩ Processor ሊኖረዉ ይገባል ይሄም የምታነሱት Photo እና የምትቀርፁት Video የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ያስችላል። ለምሳሌም:- -Low-light Performance -Faster Autofocus and Shutter Speed -Higher Resolution and Frame Rates -Video Stabilization -AI Features እነዚህ እና መሰል ነገሮችን በብቃት እንዲያከናውን ያስችላል። ② Battery አንድ ስልክ አሪፍ የሆነ የ Battery አጠቃቀም እንዲኖረው ጥሩ Processor ሊኖረዉ ይገባል ለምሳሌ ሁለት የተለያዩ ስልኮች ሁለቱም 5000mAh Battery Size ቢኖራቸውም Battery የሚጨርሱበት ፍጥነት ግን ሊለያይ ይችላል ይሄም የሚሆነው በ Processor የ Battery አጠቃቀም ነዉ። ጥሩ Processor ካለዉ ስልኩ ላይ ትልቅ ስራዎችን በምትሰሩ ሰአት ለምሳሌ Gaming ,multitasking ,እና መሰል ነገሮች ስታከናዉኑ የስልኩን Performance እና Battery አጠቃቀም Balance በማድረግ ሀይል እንዲቆጥብ ያስችለዋል። ③ Performance ሌላኛው Performance ሲሆን ይሄ በጣም ግልጽ የሆነ ነገር ነዉ ስልኩ ፈጣን እና የምታዙትን ነገሮችን በፍጥነት እንዲያከናውን ያለዉ Processor ቀልጣፋ መሆን ይኖሮበታል። Note! ስልክ ከመግዛታቹ በፊት መጀመሪያ እናንተ ምን አይነት የስልክ ተጠቃሚ እንደሆናቹ ማወቅ እና የምትገዙ ስልክ ከናንተ አጠቃቀም ጋር የሚሄድ መሆኑን ማወቅ አለባቹ። =t.me/Benan_Tech

  • йоС пОдписи

  • የ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል። ከላይ በጠቀስኩላችሁ አድራሻዎችም ከከፈት መልካም ነው። ሌላ ውጤት የምታዩበትንም መንገድ ይፋ ካደረገ ተከታተይ የማሳውቃችሁ ይሆናል።

  • ዛሬ ውጤት የምትጠብቁ የ12ኛ ክፍል የቻናላችን ቤተሰቦች አላችሁ!? በዚህ አጋጣሚ መልካም ዕድል ተመኝተናል። ነገር ግን ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በፀጋ ተቀብላችሁ በአዲስ አመት የወደፊት ህይወታችሁን አቅዳችሁ እንድትንቀሳቀሱ እንመክራለን። ጥሩ ውጤት ብታመጡ ደስ ይላል ግን ባታመጡም ህይወታችሁ እሱ ብቻ ነው ማለት አይደለም። ከጠነከራችሁ በዚህ ዘመን እራሳችሁን ልትለውጡባቸው የምትችሉባቸው በጣም ብዙ የስራ ዘርፎች አሉ። እድሜ ለቴክኖሎጂ!!! ስለዚህ አለፍን ብላችሁ ብዙ አትደሰቱ ዋናው ልፋት ገና ነው።  አላለፍንም ብላችሁም ብዙ አትከፋ ብዙ ዕድል ስላላችሁ። ስሜታችሁን በልክ አድርጉት። መልካም ዕድል!

  • 🎖የኮምፒውተር ሶፍትዌር ለማውረድ የሚጠቅሙ ምርጥ ድረገጾች፥ 1. getintopc.com ይህ ድረገጽ ትላልቅ ሳይዝ ያላቸውን ሶፍትዌሮች ለማውረድ ተመራጭ ነው። ለምሳሌ ያህል driver pack(11GB size) ከዚህ ድረገጽ ማውረድ ይቻላል። በተጨማሪም ዊንዶውስ 10,8.1,8,7, እና ማይክሮሶፍት ኦፊስ ማውረድ ይቻላል። 2. oceanofgames.com 3. filehippo.com 4. cnet.com 5. softonic.com 6. download.com 7. softpedia.com 8. Tucows.com 9. freewareFiles.com 10. majorGreeks.com 11. snapfiles.com 12. filecluster.com 13. geardownload.com 14. soft32.com 15. softonic.com 16. freewarehome.com 17. freedownloadcenter.com 18. opensourcemac.org 19. lo4d.co 20. fileEagle.com 21. P30download.com

  • ❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ ❶. #RAM (Random Access Memory) ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል:: (1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB  በላይ ራም ይኖራቸዋል:: ❷. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot) ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን:: ❸. #Heat_sinker ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም #Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰል ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል:: ❚.#Fan ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው:: ❺ #CPU #CPU ሾለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን:: #CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ሾል የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ሾል ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው:: ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው:: #CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም : ▫️1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ሾል ሁሉንም የኮምፒውተር ሾል መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው:: : ▫️2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል:: : ▫️3. #Regster ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው:: ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው:: ❻ #Port (ፓርት) : port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው:: መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መሾመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ሾል ያከናውናሉ:: የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው:: ❼ #Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል) power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው:: የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል:: ❽#ሞደም (Modem):- ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መሾመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው:: : ❞#ኪቦርድ Keybord:- መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን:: =t.me/Benan_Tech Benan Tech ❯❯❯

  • 30 авг. 2024 Đł.10,5 тыс26

    ~በነገራችን ላይ…እንግሊዘኛ ቋንቋ መማር በዛሬው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ይህን እንድትረዱ ጥቂት ምክንያቶችን ልጠቅስላችሁ፡ ① ዓለም አቀፍ ቋንቋ፦ እንግሊዘኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ቋንቋ ነው። በንግድ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት እና በመዝናኛ ዘርፎች ሁሉ እንግሊዘኛ በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። ② የሥራ እድል፦ እንግሊዘኛን መቆጣጠር የሥራ ገበያ ላይ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣችኋል። በብዙ ድርጅቶች ውስጥ እንግሊዘኛን መናገር መቻል የሥራ መስፈርት ነው። ③ ትምህርት፦ አብዛኛው የዓለም አቀፍ ትምህርት በእንግሊዘኛ ይሰጣል። በውጭ አገር ለመማር ወይም በዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ለመመዝገብ እንግሊዘኛን በደንብ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ④ መረጃ መድረስ፦በኢንተርኔት ላይ ያለው መረጃ አብዛኛው በእንግሊዘኛ ነው። እንግሊዘኛን መቆጣጠር ማለት በዓለም ላይ ካለው መረጃ ሁሉ ጋር በቀላሉ መገናኘት ማለት ነው። ⑤ ጉዞ እና ቱሪዝም፦በውጭ አገር በሚጓዙበት ጊዜ እንግሊዘኛን መናገር መቻል በጣም ጠቃሚ ነው። በብዙ አገሮች ውስጥ እንግሊዘኛ ሁለተኛ ቋንቋ ነው። ⑥ ግንኙነት፦እንግሊዘኛን መቆጣጠር ከተለያዩ አገሮች ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነት እንድትፈጥሩ ያስችላችኃል። በአጭሩ፣ እንግሊዘኛን መማር በዛሬው ዓለም ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። በአላህ ፍቃድ ይህ ቋንቋ የእናንተን የሥራ እድል፣ የትምህርት እድል እና የግል እድገት ያሻሽላል። ✏️[ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን] =t.me/Benan_Tech