ስብሐተ ነግህ ዘደብረ ኢዮር
Статистикаበኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአ/አ ሐገረ ሥብከት የቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ስብሐተ ነግህ ሰ/ት/ቤት የቴሌግራም ቻናል ነው፡፡ የስብሐተ ነግህ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 13
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 125
- 1/48двое суток
- 143
- 1/72трое суток
- 154
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🌟 ታላቅ የበጎ አድራጎት ጉዞ 🌟 ውድ የቡድን አባላት፣ በመጪው የበጎ አድራጎት ጉዞአችን ለህፃናቱ የምናበረክታቸውን የእርዳታ ጥቅሎች እንደሚከተለው አዘጋጅተናል፦ 🎁 ጥቅል 1 • 2 የገላ ሳሙና • 1 ሶፍት 🎁 ጥቅል 2 • 1 የጥርስ ብሩሽ • 1 የጥርስ ሳሙና 🎁 ጥቅል 3 • 1 ሞዴስ • 1 ፓስታ 🕒 የመነሻ ሰዓት፦ 3:00 ሰዓት ‼️ቦታው ሩቅ ስለሆነ ሁላችንም ቀድመን በመገኘት የጉዞውን ሂደት በሰዓቱ እንድንጀምር እንጠይቃለን። 📍 የጉብኝት ቦታ፦ ዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና በጎ አድራጎት መርጃ ማዕከል ከሽሮሜዳ ከፍ ብሎ፣ ቁስቋም ማርያም አካባቢ። በቆይታችንም ከህፃናቱ ጋር ጊዜ የምናሳልፍ ሲሆን፣ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት አስደሳችና የማይረሳ ጊዜ እንድናሳልፍ እንሰራለን። ከሁሉም በላይ፣ አንድ ትንሽ አስተዋፅኦ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። ለበለጠ መረጃ @Betiejonie. +251929350110 @Hela5015 +251977154551 ✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችንጎ ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል የቴሌግራም ቻናል የፌስቡክ ገጽ የኢንስታግራምፀ ገጽ የቲክቶክ ገጽ #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ #በጎአድራጎት #ጉዞ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ https://youtube.com/@snegih የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/sbhatenegh የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sibhate.negeh የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/snegih/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@snegih #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ https://youtube.com/@snegih የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/sbhatenegh የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sibhate.negeh የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/snegih/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@snegih #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/50tpdzacS0I?si=pIf_zfCusghKFmSJ ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ ✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ https://youtube.com/@snegih የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/sbhatenegh የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sibhate.negeh የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/snegih/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@snegih #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ
እንኳን አደረሳቹሁ ! ጾመ ፍልሰታ #ጾመ_ፍልሰታ ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው። እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው። ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው። ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል። ✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ https://youtube.com/@snegih የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/sbhatenegh የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sibhate.negeh የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/snegih/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@snegih #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ
видео или голосовое, без подписи
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
видео или голосовое, без подписи
✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ https://youtube.com/@snegih የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/sbhatenegh የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sibhate.negeh የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/snegih/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@snegih #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ
▎የ2018 ዓ.ም. የማጠቃለያ ፈተና እንዴት ተፈፀመ ??? በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አዘጋጅነት እየተተገበረ ባለው የትምህርት ሥርዓት መሠረት፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም. የ4ኛ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና በተወሰነው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዛሬ፣ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተካሂዷል። በዚህ ዓመት በመላ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ20,000 በላይ ተማሪዎች በምዘናው እንደተሳፉ ተገምቷል። በእኛ ሰንበት ትምህርት ቤት፣ በቤቴል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ስብሐተ ነግህ ሰንበት ትምህርት ቤት፣ የ8ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች በዚህ የማጠቃለያ ፈተና ተሳትፈዋል። በአጠቃላይ፦ • የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች፦ 40 ተማሪዎች • የ10ኛ ክፍል ተፈታኞች:- 120 በላይ በተማሪዎች • ጠቅላላ ተፈታኞች፦ ከ160 በላይ ተፈታኞች በአካልና በኦንላይን ተፈትነዋል። ፈተናው በተያዘለት ሰዓት ተጀምሮ በሰላምና በስኬት ተካሂዷል። ተማሪዎችም በሠዐታቸዉ ተገኝተው ፈተናቸውን በጥሩ ሁኔታ ወስደዋል። በፈተናው ሂደት ላይ የተስተዋለ ከፍተኛ ችግር ያልነበረ ሲሆን፣ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በመሆኑም የፈተናውን ሂደት ላስተባበሩ አካላት፣ ለመምህራን፣ ለፈተና ተቆጣጣሪዎች፣ ለተማሪዎች እና ለወላጆች ላደረጉት ትብብርና ድጋፍ ምስጋና እናቀርባለን። ✨✨✨ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ✨✨✨ 🛖በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ! የዩቲዩብ ቻናል፡ https://youtube.com/@snegih የቴሌግራም ቻናል፡ https://t.me/sbhatenegh የፌስቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sibhate.negeh የኢንስታግራም ገጽ፡ https://www.instagram.com/snegih/ የቲክቶክ ገጽ፡ https://www.tiktok.com/@snegih #ስብሐተ_ነግህ_ሚዲያ