"አንብቦተ መጻሕፍት ይመርሕ ለልብ ኀበ ተዘክሮተ እግዚአብሔር" ይህ የሰውን ልብ እግዚአብሔርን ወደ ማሰብ የሚመሩ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችና ትምህርቶች የሚቀርብበት መንፈሳዊ አውታር ነው። ሐዊ ፦ ጥበብ መንፈሳዊ ጥበብ ሥጋዊ የያዘ ማለት ነው። https://www.instagram.com/hawi_eotc_/ hawieotc@gmail.com
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 67
- 1/48двое суток
- 76
- 1/72трое суток
- 82
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
"በሳምንት ሁለት ጊዜ 14ቱን የጳውሎስ መልእክታትን አነባለሁ። ምንም እንኳን እንዲህ ባደርግም በቅዳሴ ጊዜ ከመልእክታቱ አንዲቷ ስትነበብ እንደ ቀጭን ፉጨት አሁንም ልቤን ትሰርቃለች።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ሐዊ
"ሊቀ ነብያት" የሚል መጠሪያ መዓርግ "እንደ ሊቀ ትጉሐን ፥ መልአከ እገሌ" ተብሎ ለአገልጋይ ሲሰጥ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? #በሕግ_አምላክ #ሐዊ
без подписи
ሕጻን ቂርቆስ ገድላተ ቂርቆስ ህዝብነ እንዘ በእሳት ይትዋነይ ኢይምሰልክሙ ሕጻነ የቂርቆስ ቤተሰብ ገድላት ሆይ ቂርቆስ እሳትን እየጨበጠ በእሳት ሲጫወት ልጅ አይመሰላችሁ ይላል አንዳንድ ልጆች ከእድሜያቸው በላይ ያስባሉ እንዲያውም ለትልልቅ ሰዎች አርአያ ይሆናሉ የሕጻኑ ቂርቆስ ታሪክም የሚያሰየው ይህን ነው በመከራው ሰዓት የሚፈላውን ውሃ የተዘጋጀው ሰይፍ የሚነደውን እሳት አይታ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ስታፈገፍግ ስትሸሽ ሕጻኑ ቂርቆስ እናቴ አንድ ጊዜ ጨክኚ አይዞሽ ዳግም አንሞትም እያለ ሲመክራት ሲያበረታታት እናያለን ቅድስት ኢየሉጣም ከዛሬ ጀምሮ አንተ አባቴ ነህ ስትል ታላቅነቱን መስክራለች በረከታቸው ይደርብን 🙏🙏🙏🙏🙏 ምንጭ ፦ ከአባ ገብረማርያም የ facebook ገጽ የተገኘ
ስለሁሉም ክብር ለእግዚአብሔር ደስ ብሎኛል በዚህ መንገድ በመምጣትህ ፥ በተረፈ ስሙት ታተርፉበታላችሁ ። እኔም ከባለቅኔው ተውሼ እንዲህ እላለሁ ኢየሱስ ዳዊት በኬብሮን ቤተ ክርስቲያን አንገሦ ለወንጌል ሰሎሞን ዘለጸላኢሁ አግኀሦ ። https://youtu.be/-MhfsbgslR4?si=UmoOGof6qZ3ftQyv
без подписи
+++ እንደ ሞት የበረታች ፍቅር +++ ወዳጄ ሆይ ሞትን በምን ትመልሰዋለህ? በጠበብት ምክር ወይስ በባለመድሃኒቶች መድሃኒት? በፍጽም "አንዱስ እንኳ ሊቃወመማት የሚችል የለም ። ፍቅርም እንዲሁ ናት ማንም የማይቃወማት ኃያል ናት ። እሳት ናት ግን እንደ ምድራዊ እሳት በውሃ ብዛት የማትጠፋ ናት።" በአብርሃም ዘንድ ያለች ፍቅረ እግዚአብሔር ዓይንን የተመሉ ኪሩቤል ያላዩትን አምላክ አሳየች ። ልዑል ሲሆኑ በድንኳን ይስተናገዱ ዘንድ ግድ አለች ። ከወዳጄ ከአብርሃም የምሰውረው ነገር አለን? አስባለች። ፍቅረ ማርያምስ ትለኝ እንደሆን የአባ ጊዮርጊስን ህይወት ተመልከት እልሃለው። በሊቁ ዘንድስ የሆነውስ ምንድነው? በርሱ ዘንድ ያለች ፍቅር የዓለም ንግሥትን ከሰማየ ሰማያት ጠራች ፥ ከዕውቀት ባዶ የሆነውን ማድጋ በምሥጢር ወይን መላች ፥ አፉን ለምሥጋና ሰውነቱን ለስግደት የበረታች አደረገች ። ዘመኑን እንደፈቃዷ ኖሮ ሳለ በዘመኑ ፍጻሜ "ኦ እግዝእትየ ረስይኒ ከመ እኩን ክርስቲያን / እመቤቴ ሆይ ክርስቲያን አድርጊኝ " እስኪል ድረስ አስደረሰች ። አይቷት ሳለ የሚናፍቃት ፥ አግኝቷት ሳለ ደግሞ ሊያገኝ የሚመኛት እስኪሆን ድረስ ደረሰ። ከልቡናው ቀላይ ውዳሴዋን አፈሰሰ ። ባሕረ ቀለሙ የብስ ብራናውን ቢያረጥበውም በልቡናው ያለ የፍቅሩን እሳት ግን ሊያበርደው አልቻለም ። ታድያ በድርሰቱ በመዝሙረ ድንግል ፍጻሜ ላይ እንዲህ አለ መኑ ይእቲ ዛቲ ትቤ ራእይ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ድኅረ ለያልይ በእንቲአኪ ማርያም ሙፃአ ፀሐይ ክነፈ ፍቅርኪ ክንፈ እሳት ውዑይ አጥፍኦታ ዘኢይክል ማይ ። ታድያ ከፍቅር የበረታ ምን አለ ወዳጄ? .................................................. ሐምሌ 07|2018 ዓመተ እግዚእ ሐዊ
ወገን የክብር ዲግሪ አለ እንዴ? ለነገሩ የክብር መጋቤ ሐዲስም ሰምተን የለ ! ነገሩ ጥያቄ ስለፈጠረብኝ ነው ፥ ውስጠ-ወይራውን የምታውቁ ሰዎች ካላችሁ ጻፉልኝ ። ........... ማጣቀሻ ፦ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምርቃት ተመልከቱ #ሐዊ
"ልሄድ ወደ ክርስቶስ እናፍቃለሁ " ፥ "ሩጫዬን ጨርሻለሁ" እኒህን ውብ ቃላት ከሁለቱ በላይ ሊናገር የሚችል ማን ይሆን? +++ "ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ዘጸዋዕኮሙ ለጳውሎስ ወለጴጥሮስ ጸውዓነ ውስተ ከብካብ ዘበሰማያት ።" #ሐዊ
"የ4 ዓመት የወንድሜ ልጅ ምስለ ፍቁር ወልዳ (ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ጋር) ያለችበትን ስዕል ስር ጸሎት አድርጋ ስትጨርስ ቀና ብላ ተመስጣ ካየቻት በኋላ አንቺም ታምሪያለሽ ልጅሽም ያምራል አለች ። " #ከማኅበራዊ_ገጽ_የተገኘ #ከሕጻናት_ዓለም #ሐዊ
ባለፈው ወደ ቤቴ ስሄድ አንድ ሰባኪ ፥ ሰው ታክሲ ለማግኘት ከሚኳትንበት ቦታ መሃል ቁሞ በዐቢይ ድምጽ "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።" ይላል የሰራዊት ጌታ ፥ ሰላምን ከፈለክ ጌታን ተቀበል .... እያለ ታንቡር በሚሰነጥቅ ጩኸት ይለፍፋል ። ታድያ ይህ ድምጽ በእጅጉን የረበሻቸው እናት "ምጽ ...እሱማ ብሎን ነበር አንተ ሰላምን ልትሰጠን አልቻልክም እንጂ" አሉት ንዴት በወለደው ድምጽ #በመንገዴ_ላይ #ሐዊ
+++ የፍቅርን ኃያልነት ተመልከቱ! +++ 'ልጅን የራስ ብቻ አድርጎ ከመያዝ ይልቅ ለሕይወቱ ቅድሚያ የሚሰጠውን “የእናትነት ፍቅር” ጥልቅ ተፈጥሮ አስተውሉ። ሰይፉ በተመዘዘ ጊዜ፣ በገዛ ክፋቷና በገዛ ሕፃኗ ሞት ዕውር የሆነችው ያቺ ሐሰተኛ እናት፦ «ለእኔም ለአንቺም አይሁን፣ ክፈሉት!» እያለች ጮኸች። የምቀኝነት ባሕርይ እንዲህ ነው። የራሱን ጥቅም አይሻም ፥ ነገር ግን በሌላው ሰው ደስታ መጥፋት ብቻ ሐሴት ያደርጋል። አንጀቷ ስለልጇ የታወከባት እውነተኛዋ እናት ግን፦ «ደኅነኛውን (ሕያውን) ሕፃን ለእሷ ስጧት እንጂ በምንም መንገድ አትግደሉት!» ስትል ጮኸች። እርሷ ልጁ ብቻ በሕይወት ይኑርላት እንጂ ወደ ሌላዋ እቅፍ ተላልፎ የመሰጠቱን ሐዘንና ማጣትን ትችለው ዘንድ መረጠች። ሰሎሞንም እውነተኛዋን ወላጅ የለየው በዚህ ነው፤ ይህም የምስክሮች ቃል በመስማት ሳይሆን፣ በተፈጥሮ ያለ በማይለወጥ ምስክርነትና መጥዎተ ርእስን ገንዘብ እስከሚያስደርግ ባለ ፍቅር ነው።' ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምንጭ፦ St. John Chrysostom, Homilies on Moral Reformation and Christian Charity #ሐዊ
የብርሃን ዓምድ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ሲነሳ እርሱን የማይጠቅስ ሊቅ ሲጠቀስ ያልሰማ ምእመን ማግኘት እጅግ በጣም ጭንቅ ነው፤ በተለይ ጉባኤ ዘርግተን ስናስተምር ስንማር ፣ ወደ መድረክ ስንወጣ “በስመ አብ” ብለን መናገር ከጀመረንበት ጊዜ ጀምሮ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን የስብከታች ጌጥ እርሱ ነው። ያለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የስብከት ውበት ይኑረዋል ብሎ ማሰብ አይቻልም፤ አንዳንድ ጊዜማ ሳናውቅ ደጋግመን የእርሱን ትምህርት ማንበብ፤ መጥቀስ ስንጀምር በእርሱ የአባትነት ፍቅር ራሳችን ተማርከን እናገኘዋለን። ይበልጥ በትምህርቱ ባወቅንው ቁጥር አብሮን እንዳለ ይሰማናል፤ ብቻ ምን ልበላችሁ? በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ከዋክብት የሚያበሩ ብዙ ሊቃውንት አሉ። ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለመግለጥ ስፈልግ ግን ቃላት ይሰንፉብኛል፤ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ!!! ስለ እርሱ የማውቀውን ትንሽ ልንገራችሁ። ✍️ለቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልፍ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንጌል ሰጥተውታል፤ በዲቁ መዓርግ ሳለ ብሉይ ኪዳን እና ሐዲስ ኪዳንን የተረጎመ ቤተክርስቲያን በትምህርቱ መዓዛ የጣፈጠችበት ዕንቁ አባት ነው። ✍️ስለ እመቤታችን ድንግልና ለንጉሡ አርቃድዮስ ሲያብራራ “የብኵር ልጇን እስክት ወልድ ዮሴፍ አላወቃትም ማለት ምን ማለት ነው? ” ብሎ ጠይቆት ሲያብራራ የዚህ ትርጓሜው « ክርስቶስ በእመቤታችንማኅፀን ሳለ በብርሌ (ብርጭቆ) ውስጥ ወይን ሲቀዱበት የወን መልክ ያሳያል፤ ውሃ ሲቀዱበት የውሃ መልክ ያሳያል። እመቤታችንም የክርስቶስ ኅብረ መልክዕ ሲለዋወጥ አብሮ የእርሷ መልክዕ ይለዋወጥ ስለነበረ ዮሴፍ እመቤታችን በአንድ ኅብረ መልክዕ አላወቃትም ነበር፤ ከአጠገቡ ተቀምጣ ሳለ “ማርያም” ብሎ ይጣራ ነበር፤ ጌታን ከወለድች በኋላ ግን መልኳ መቀያየር ስለ አቆመ በአንድ ዓይነት መልክ አውቋታልና ስለዚህ ነው» ብሎ ሲተርጎምለት በፊት ለፊታቸው ከግድግዳው ተሰቅላ የነበረችው የእመቤታችን ሥዕል “ሠናየ ተናገርከ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት፦ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት መልካም ተናገርክ ብላ ስመ ሥርጋዌ ሰጠችው ከዚያ ጀምሮ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተብሏል። ሐዲስ ዳንኤል የሚለውን ቅዱስ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ወንጌላዊው ሰጥውታል። የብርሃን ዓምድ የሚለውን መልአኩ ስጥቶታል፤ በአጠቃላይ አምስት ሰመ ሥርጋዌ አሉት፦ ✍️የብርሃን ዓምድ ✍️ሐዲስ ዳንኤል ✍️ዮሐንስ አፈ ወርቅ ✍️ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ✍️አፈ በረከት ለኢትዮጵያ ሊቃውንት የትርጓሜ ስልት ለአብነት ከሚጠቀሱ ሊቃውንት ቀዳሚውን ቦታ ይዞ የሚገኝ ፣“ዓይነ ንሥር ”ተብለው ከሚመደቡት ሊቃውንት አንዱ ነው፤ በእርሱ ጣዕመ ትምህርት አንክሮ ተደሞ ውስጥ የማይገባ፣ በስብከቱ ልቡ የማይነካ፣ እንኳን አማኝ የማያምን ሰው ለማግኘት ያስቸግራል።ግንቦት አሥራ ሁለት ዕረፍቱ ነው፤ በረከቱ ይደርብን። ✍️እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ!!! ናትናኤል ባዬ (የብሉይና የሐዲስ የሊቃውንት መምህር )
#ቀጠሮውን_ላከበረ_ሁሉ_የሊቁን_ማስታወሻ_ይዞ_ይሄዳል።
#ዘወትር_አንተን_ባሰብኩ_ቁጥር_ልቤ_በሐሴት_ይታወካል።
የኢትዮጵያ ፀሐይ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ማነው? ማኅሌታይ ነው ፥ መተርጉም ነው ፥ የቅኔ ፈጣሪ ነው ፥ መናኝ ነው ፥ በአጭር ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አምዷ(ምሰሶዋ) ነው ። #በረከቱ_ትደርብን።
#ሐዊ
ሚያዝያ 9/2018ዓ.ም ለ. ሥነ-መለኮት ትምሀርት ፈላጊዎች ተጨማሪ የትምህርትና የውይይት መርሐግብር (Additional Tutorial Class) ለመከታተል አስፈላጊ ቅድመ ተከተሎች፡- 1. የግል ፍላጎት 2. የምዝገባ ጊዜ እስከ ሚያዝያ 24/2018ዓ.ም 3. ሚያዝያ 25 ትምህርት ይጀምራል፡፡ 4. ሰዓትና ቀን በተማሪዎች አብላጫ ድምጽ (Poll) የሚወሰን ይሆንና በሳምንት ሁለት ጊዜ 5. የትምህርት ዓይነት: የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያ ክፍል (EOTC –I ) 6. ክፍያ፡ 200 ብር (ለአንድ የትምህርት ዓይነት) CBE - 1000088472447 Tele birr - 0901925530 ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ ደረሰኙን በሚቀጥለው User Name: @theo_study ይላኩት! ብዙዎቻችሁን እጅግ አመሠግናለሁ። በቅርቡ ክፍያ ፈጽማችሁ የላክችሁልኝን ወደ ግሩፕ አስገባችኋለሁ። ትምህርታችንም በተጠቀሰው ጊዜ ይጀምራል።
без подписи
ዛሬ የአቡኑ የልደት መታሰቢያ ስለሆነ በዚህች ቅኔ እንዘክራቸው። ቤተክርስቲያን እምነ ኢተአምሮ ለዘትትናገሮ ውሉዳ ፥ ቴዎፍሎስ አእምሮ ዚአሃ አኮኑ ተወስዳ። እናታችን ቤተክርስቲያን ለልጆቿ የምትናገረውን አታውቅም አእምሮዋ ቴዎፍሎስ ተነስቷታልና። ሰማዕተ ጽድቅ አቡነ ቴዎፍሎስ በረከቶ ትድረሰን። #ሐዊ