ስልጤ ዞን ኮሚዩኒኬሽን - SILTIE ZONE COMMUNICATION
Статистика- Последний пост
- 31 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 402
- 1/48двое суток
- 460
- 1/72трое суток
- 496
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በሴቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የ2018 በጀት ዓመት የሴቶች ልማትና ንቅናቄ ሥራዎች አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለመምከር የተዘጋጀው ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ! (ወራቤ ፣ሐምሌ 24/2018)የስልጤ ዞን የሴቶችና ህፃናት መምሪያ "የሴቶች አቅምና ንቁ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላምና ብልፅግና!"በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የሴቶች ልማትና ንቅናቄ ሥራዎች አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ለመለየት የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የሴቶች ልማት ህብረት ስትሪንግ ኮሚቴ እና የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብረ ኃይል በዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በቀጣይ በሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ላይ የሚሰጡ ትኩረቶችን በስፋት ገምግመዋል። የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ረዳት የመግስት ተጠሪና የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሱነሞ ሴቶች በተለያዩ የልማት መስኮች እያሳዩ ያሉት ንቁ ተሳትፎ በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ መረጋጋት በሰላም እሴት ግንባታና በአጠቃላይ የዞኑ ልማት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑ ጠቅሷል። በኢኮኖሚ ዘርፍ ሴቶች በቡድን በመደራጀትና የገበያ ትስስር በመፍጠር እንደ ካሮትና ጎመን ያሉ የግብርና ምርቶችን እስከ አዲስ አበባ ድረስ በማቅረብ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆናቸው ገልዋል። የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም መጎልበት በቤተሰብ ውስጥ የነበሩ ግጭቶችን በመቀነስ ወደ ፍርድ ቤት የሚደርሱ የክርክር ጉዳዮችን እንዲቀንሱ አስተዋጽኦ ማድረጉም ጠቁሟል። በፖለቲካው ዘርፍም ሴቶች በዘንድሮው የምርጫ ሂደቶችና በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያላቸው ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱና ይበል የሚያስብል ስራ መሰራቱንም አንስተዋል። በማህበራዊ ዘርፍም ከጤና ጥበቃ፣ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መከላከልና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና ግንባታ ጋር ተያይዘው የተሰሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸው ገልፀዋል። ተቋማት ከታች እስከ ላይ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውና በዋናነትም ተቋማዊ ግድፈቶችን ማጥራት፣ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናቀቅ፣ እሴቶችን መጠበቅና ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገር እንዲሁም አሉታዊ አሰራሮችን መቀነስ ላይ በተገቢው መስራት ይጠበቃል ብለዋል። ሴቶች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአረንጓዴ አሻራ እና የትምህርት ስራዎችን ማጠናከር ላን ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል። የስልጤ ዞን የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ኸይሪያ ስርሞሎ በ2018 በጀት ዓመት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህፃናትን መብት ለማስጠበቅ አመርቂ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል። ሴቶች በቁጠባ፣ በህብረት ሥራ ማህበራት እና በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ያሳዩት ተሳትፎ የቤተሰብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ጨምረው ገልጿል። ሴቶች በአቅራቢያቸው መቆጠብና ብድር ማግኘት እንዲችሉ ሁሉም የልማት ህብረት አባላት የሆኑ ሴቶች የህብረት ስራ ማህበራት አባል መሆን እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥቶታል። የሴቶች ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ ማህበረሰቡ ይለወጣል ያሉት ወ/ሮ ኸይሪያ የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርና እና የፍትህ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ የሚያስችሉ የቴክኒክና የስትሪንግ ኮሚቴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሞዴል ቀበሌዎችን ማስፋፋት በአንድ ማዕከል የተቀናጀ አገልግሎት የሚሰጡ ሞዴል ቀበሌዎችንና ወረዳዎችን ቁጥር ማሳደግ ይገባል ብለዋል። "ሞዴል" የተባሉ አካባቢዎች ተሞክሮአቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉና በ2019 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም አካል በቁርጠኝነት እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል። በሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማጠናከር በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የሴቶች ልማት ቡድንና የንቅናቄ ስራዎችን የሚያሳይ አጠቃላይ የአፈፃፀም ሪፖርት በመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ መህዲያ ሀምዳላ ቀርቧል። ሪፖርቱ በዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የተመዘገቡ ውጤቶች ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸውን የስራ አቅጣጫዎች ላይ ወ/ሮ መህዲያ በዝርዝር አቅርበው ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል። የሴቶችን የኢኮኖሚ የፖለቲካና የማህበራዊ ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠልና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሁሉም የአመራር አካላት በቅንጅትና በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል። በመጨረሻም የዞኑ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ በ2019 በጀት አመት በሚሰሩ የዘርፉ ተግባራት ላይ ከዞን ከሚመለከታቸው መዋቅሮች ጋር የግብ ስምምነት በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ተግባራትን አቀናጅቶ በመምራት የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል! :- ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ወራቤ ሐምሌ 23/2018 ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን ተግባራትን በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ በመምራት የዞኑን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ገለፁ። ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት የዞኑን የካቢኔ አባላት ያካተተ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በማዋቀር ለተመደቡት አመራሮች የቀጣይ ስራዎችን አቅጣጫ የሚያስይዝ ጠንካራ ኦሬንቴሽን በሰጡበት ወቅት ነው። በመድረኩ ላይ በዋናነት ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል የመጀመሪያው ከተረጂነት ወደ ሉዓላዊነት የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይ ሲሆን በምግብ ዋስትና እና በምርት እድገት እራስን መቻል ሙሉ የሀገር ሉዓላዊነትን እንደሚያረጋግጥ የገለፁት ኃላፊዋ ማህበረሰቡን ከእርዳታ ጠባቂነት አውጥቶ አምራችና ምርታማ ወደ ሚያደርጉ አሰራሮች መቀየር ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልፀዋል። ክብርት ወ/ሮ ነኢማ አክለውም ከእርዳታ ጥገኝነት በመውጣትና የራስን አቅም ለመገንባት ትኩረት በማድረግ ማህበረሰቡ በውስጡ ያለውን እምቅ አቅም፣ የተፈጥሮ ፀጋዎች እና የሰው ኃይል በአግባቡ በመጠቀም በራሱ የሚቆምበትን መንገድ አጠናክሮ መሄድ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ይህንንም ለማሳካት በሁሉም የልማት መስኮች አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችንና የውስጥ ሀብት የማንቀሳቀስ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራትን አጠናክሮ መሄድ እንደሚያስፈልግ ያነሱት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ በክረምቱ ወቅት የሚከናወኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የበጎ ፈቃድ ስራዎች በሁሉም የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። ክብርት ነኢማ አክለውም አቅመ ደካሞችን ከመደገፍ እስከ አረንጓዴ አሻራ ድረስ ያሉት ተግባራት በእኩል ትኩረት ሊመሩ እንደሚገባም አሳስቧል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምልመላ እና የኤልኒኖ ክስተት ተፅዕኖዎችን መቋቋም ላይ አመራሩ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባውም ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር ገልፀዋል። የሀገርን ሰላምና ደኅንነት የሚያስጠብቅ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የዞኑ ማኅበረሰብ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲያበረክት የማስተባበር ሥራ ይሠራል ያሉት ኃላፊዋ በተመሳሳይ መልኩ የአየር ንብረት ለውጥ ያመጣውን የኤልኒኖ ክስተት ተፅዕኖ ለመቋቋም እና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅትና የመፍትሔ ሥራዎችን አጠናክሮ መሄድ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በመጨረሻም የተዋቀረው የድጋፍና ክትትል ቲም ወደ ተመደበበት መዋቅር በመውረድ እነዚህን አምስት ዋና ዋና አጀንዳዎች መሬት የማውረድ፣ አመራሩንና ህዝቡን የማስተባበር እንዲሁም የተግባር ውጤታማነትን የመከታተል ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዳለበት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር አሳስበዋል።የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи