tgindex
Werabe City Government Communication Affairs Office

Werabe City Government Communication Affairs Office

Статистика

Werabe Communication Social Media Links👇 @ https://m.facebook.com/Werabecommunication @ https://twitter.com/Werabecommu @https://www.werabecity.com

Последний пост
17:54
Последнее чтение
13:14
Постов за неделю
35
Всего постов
50
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 957
+3 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
426
40 постов
Вовлечённость
14,4%
к подписчикам
Постов в день
5,0
всего 50
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
339
1/48двое суток
388
1/72трое суток
419

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 17:542833

    በወራቤ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የፀጥታ ተግባራት እና ዘላቂ ሰላምን ይበልጥ ማፅናት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከከተማው የፖሊስ አባላት ጋር የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1343546554656921/?app=fbl

  • ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ ጉዞ ስልማ 3 የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት! የስልጤ ልማት ማህበር የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ  የ2018 በጀት ዓመት የጉዞ ስልማ 3 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን በማስመልከት  ለልማት ማህበሩ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ወዳጆች በአጠቃላይ ለስልጤ ህዝብ  ጥሪና መልዕክት አስተላልፈዋል። አቶ ዘይኔ ቢልካ በመልዕክታቸው የስልጤ ልማት ማህበር  የስልጤን ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ከመንግስት ጋር በመሆን ለማረጋገጥና የስልጤን ህዝብ ባህልና ዕሴት እንዲሁም ቋንቋ ለማሳደግ በሚል የተቋቋመ መሆኑን በማስታወስ ልማት ማህበሩ የተመሰረተበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ሰፋፊና ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶችና ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በዚህም በባህልና ቋንቋ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት  ውጤታማ የሆኑ ዘመን  የማይሽራቸው ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል። በቅርቡ የተደረገውን 12ኛ ጠቅላላ ጉባዔ መነሻ በማድረግ የተጀመረው ዓለም ዓቀፍ የተድባበሎት ቻሌንጅ ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር የህዝቡን የጋራ አንድነትና ህብረት፣ የጋራ እሳቤና ጥረት፣ የመደጋገፍ ዕሴት ጎልቶ የወጣበት እንደነበረም ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው አስታውሰዋል፡፡ በዚህም ዓለም ዐቀፉን የድባበሎት ቻሌንጅ በገንዘብ በዕውቀት ሲደግፉና ሲያስተባብሩ ለነበሩ ሁሉ በስልጤ ልማት ማህበርና በስልጤ ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህን የአንድነትና የጋራ ዕሳቤ እንዲያጎለብት በሚል በየዓመቱ የሚከናወነው የጉዞ ስልማ መርሃ ግብር፣ በዘንድሮ ዓመት "ጉዞ ስልማ 3" በሚል ስያሜ በላንፉሮ ወረዳ እና በጦራ ከተማ አስተዳደር  የጋራ አዘጋጅነት በላንፉሮ ገባባ ቀበሌ በጡፋ ሀይቅ ዳርቻ የፊታችን እሁድ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወን የቦርዱ ሰብሳቢና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ዘይኔ ቢልካ ተናግረዋል። የጉዞ ስልማ ዕሳቤ ችግኝ የመትከል ፕሮግራም ብቻ አለመሆኑን በመግለጽ የእርስ በርስ መተሳሰባችንን፣ አንድነታችንን፣ ትብብራችንን እና ለልማታችን ያለንን የጋራ ራዕይ የምናሳይበት መድረክ ነው ብለዋል። አቶ ዘይኔ አያይዘው እንዳነሱት ዛሬ አንድ ችግኝ በጋራ ስንተክል፣ ነገ የምንጠብቀው የተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን፣ የአንድነት፣ የትብብር እና የመልካም ትውልድ ዘር እየዘራን ነው። በመጨረሻም የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ክቡር አቶ ዘይኔ የስልጤ ልማት ማህበር አባላት፣ ደጋፊዎች፣ ወዳጆች እና የልማት አጋሮች በሙሉ፣ በዚህ የጋራ ተስፋና የአንድነት ጉዞ ላይ በአካል ተገኝተው ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ በአክብሮት ጥሪያቸውን አቅርበዋል ። አንድ ሆነን ተስፋን እንትከል፤ በጋራ እንልማ!! ጉዞ ስልማ ከአረንጓዴ ልማት ባሻገር !!                           አቶ ዘይኔ ቢልካ የስልጤ ልማት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ! ነሐሴ 8 ቀን 2018

  • видео или голосовое, без подписи

  • ከወራቤ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የተላለፈ መልዕክት! ​የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች ጽሕፈት ቤት ለ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ፣ የመምህራን ሪፖርት እና የመማር ማስተማር መደበኛ ትምህርት መጀመሪያ ቀናትን አስመልክቶ የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል። ​📝 1. የተማሪዎች ምዝገባ መረጃ፦ ​📅 የምዝገባ ጊዜ፦ ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም ​📍 ቦታ፦ በሁሉም ትምህርት ቤቶች። ​👥 የሚመዘገቡት፦ ​የቅድመ-አንደኛ (አፀደ ሕፃናት)፦ ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 6 ዓመት የሆኑ ሕፃናት ​ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል፦ ሁሉም ተማሪዎች ​የተቀናጀ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ተሳታፊዎች ​📌 ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦ ​አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎች፡ ​የፋይዳ (Fayda) መታወቂያ ወይም የፋይዳ ካርድ ቁጥር። ​ለወላጆችና አሳዳጊዎች የተላለፈ ጥሪ፦ ልጆቻችሁን በወቅቱ በማስመዝገብ የወላጅነትና የአሳዳጊነት ድርሻችሁን እንድትወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን። ​👨‍🏫 2. የመምህራንና ሠራተኞች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ​በ2018 ዓ.ም በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች ስታስተምሩና ስታገለግሉ የነበራችሁ መምህራን እና ሠራተኞች በሙሉ፦ ​📅 ከነሐሴ 07/2018 ዓ.ም ጀምሮ በየተመደባችሁበት ትምህርት ቤት በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት የምታደርጉ ይሆናል። ​🎒 3. መደበኛ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን፦ ​📅 መስከረም 04/2019 ዓ.ም ​ሁሉም ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት በተመዘገባችሁበት ትምህርት ቤት በተጠቀሰው ቀን ትምህርት የምትጀምሩ መሆኑን እናሳስባለን። ​"ትምህርት ለትውልድ፤ ለተሻለ ነገ!" ​የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 8ቱም ቡድኖች መግባባት ላይ ደረሱ በ8 የአጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲመካከሩ የቆዩት የሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ቡድኖች መግባባት ላይ ደርሰዋል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡ ቀደም ሲል በሰላም ግንባታ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በሙስናና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በመንግስት አደረጃጀት እና የፖለቲካ ስርዓት ሲመካከሩ የቆዩት ቡድኖች መግባባት ላይ እንደደረሱ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡ በዛሬው ዕለትም በሀገር ግንባታ፣ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብት እንዲሁም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ቀሪዎቹ አራት ቡድኖች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡(ኤፍኤምሲ) ነሐሴ 7፣ 2018 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

  • የወራቤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ በጀመረባቸው የተለያዩ ተቋማት ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መንገድ በመስጠት የተገልጋዩን ዘርፈ ብዙ እንግልት አስቀርቷል ሲሉ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኑ ማህሙድ ገለጹ! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1341795194832057/?app=fbl

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • በየዘርፉ እየተከናወነ ያለው የ2018 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል! ነሐሴ 7፣ 2018 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን] በወራቤ ከተማ አስተዳደር በልዩ ልዩ የስራ መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገው የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በተለያዩ አካባቢዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በየዘርፉም የሚበረታታ ስራ እየተሰራ ይገኛል። እየተከናወኑ ከሚገኙ ሰብዓዊና ማህበራዊ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በመከናወን ላይ ነው። በዚሁ መሰረትም በከተማ አስተዳደሩ የአልከሶ 01 ቀበሌ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች "አንዲት ጠብታ ደም ለህወት ዋጋ አላት" በሚል እሳቤ ደም በመለገስ የወገን አለኝታነታቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ። በደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ የአመራር አካላት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል። (መረጃውን ያገኘነው ከወራቤ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ነው)

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

Werabe City Government Communication Affairs Office — tgindex