- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 30
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 31
- 1/48двое суток
- 35
- 1/72трое суток
- 38
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ለኡስታዝ አህመዲን! የእርሳቸው(የኢማም) እና የዘመኑን ሰው ልዩነቱን ምን ያህል እንደ አድማስ መስፋቱን፣ በዓይነ-ህሊናው ሲመለከተውና በልቦናው ሲያወዳድረው ጊዜ፣ በጣም ተራርቆ ቢታየውና ይህም ቢያሳስበው፤ የሐሰት ስሜትና ባዶ ጭንቀት ያስከተለው ውጥረት ሊመስለን አይገባም። ኢማም ሐጂ አ/ሃዲ በወቅቱ ተማሪ ናቸውና በጸሎታቸው ሰዓት: «ፈጣሪዬ ሆይ! የዕውቀት ብርሃኔን አስፋልኝ፣ ከሀብትም ለግሰህ ከጸጋህ አጎናፅፈኝ፣ ጀነትህንም ከአሁኑ አረጋግጥልኝ» በማለት መጠየቅ አላቃታቸውም ወይም አልጠፋቸውም ነበር። ይህን በዚያ በብሩህ አዕምሮው የተረዳውና ያስተነተነው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፤ ቢያስችለው ነበር የሚገርመው። ለዚያ ነው ውስጣዊ ስሜቱ ፈንቅሎ በመውጣት የሲቃ ድምጽ እያሰማ ሲተናነቀው የነበረው። 🔹ት/ቤቱ እስካሁን እነማንን አፈራ!? ይህ ብርሃን ት/ቤት ከተመሠረተበት ከ1974 ጀምሮ ለዘመናት ትውልድን ሲያንጽና ለከፍተኛ ደረጃ ሲያበቃ የኖረ ሲሆን ለአብነት ያህልም እነ ኢ/ር መሀመድ ጋግቾን(የዞኑን የከተማ ልማት መምሪያን የመሩ)፣ እነ ዶ/ር ረዲ ስርባሮን(Lecturer)፣ እነ አቶ ኸይሬ አብደላን(የቀድሞ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ እና የአሁኑ ዶክተር)፣ እነ አቶ ቀድሩ አብደላን(የቀድሞ የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ አማካሪ/ከአሁኑ ከክልሉ መሪዎች አንዱ)፣ አቶ አንዋር ዑመርን(የክልሉ ቁ 1 ግብር ከፋይ ባለሀብት)፣ አቶ ሐምዳላ ሹክሬን፣ እነ አቶ አብዱልባሲጥ ሐጂ ሀሚድንና ሌሎችንም ትላልቅ ምሁራንን፣ አመራሮችን፣ ባለሀብቶችንና ሌሎችንም ያፈራ ታሪካዊ ት/ቤት ለመሆን በቅቷልና ... :: ◆ይህ ታሪክ በናትራር መጽሐፍ በሰፊው በክፍል አንድ፣ በምዕራፍ 2 ላይ #ከ56_61 ድረስ በሚገኙት ገጾች ታሪኩ ሰፍሮ ይገኛል) ◆በምረቃ ፕሮግራሙ ዕለት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ያስተላለፈው ሙሉ መልዕክት ... 👉👇 https://www.facebook.com/share/v/1949pa9YJt/ ◆በሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርሙ ክስተቱ ከተገለጸባቸው ገጾች አንዱ ...👉👇 https://www.facebook.com/100007245575291/posts/4402713103313499/?app=fbl
☪️ በ«ናትራር» መጽሐፍ የምረቃ ዕለት(ሐምሌ 12/2018 በዓድዋ 00) መድረኩ ላይ ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ሲቃ እንዲተናነቀው ያስገደደው ጉዳይ ምን ነበር⁉️ {የትምህርት ቤት መሥራቹ ተማሪ!} ታሪክ❗️ ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ በዘመኑ(ከ1960-1972) በደረሳነት እና በመደበኛ የዲን ትምህርት ተማሪነታቸው ወቅት፣ በሱዳንና በስ/ዓረቢያ ሀገራት ላይ የተመለከቷቸው መስጂዶች፣ መድረሳዎችና ተቋማት(Institutions) ሀገር ቤት ላይ ከሚያውቋቸው የሣር ቤት መድረሳዎች(ሐሪማዎች/ኸልዋዎች) እና መስጂዶች ጋር ልዩነታቸው እጅግ የተራራቀ መሆኑ ይገርማቸውም ያሳዝናቸውም ነበር። ኢማም በትውልድ ቀዬአቸውም ሆነ በመላው ሀገራቸው ላይ አንድም ዘመኑን የዋጀ ዲናዊ ተቋም አለመኖሩ እየታወሳቸው፤ በዚያ የልጅነት አዕምሯቸው ውስጥ ከአባት እጦት፣ ከእናት ናፍቆትና ከአብሮ-አደጎች ትዝታ በልጦባቸው ያሳስባቸው ነበር። …በዘመኑ ከጭንቀታቸው መገላገያ የሚሆናቸውን መፍትሔ ፈለጉና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በየወሩ እያዋጡ በአደራ መልክ ማስቀመጥና ማጠራቀም ጀመሩ። ከ2 ዓመታት በኋላ ግን ያስቀመጡባቸው አንድ/ሁለት ሰዎች፤ ገንዘቡን አጥፍተውባቸው እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል ...። የዛሬው ኢማም/ሐጂ፣ የዚያኔው የ9ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩት አብዱልሃዲ፣ ብሩ መጥፋቱን በተረዱበት ምሽት: ❝ረሱል/መልዕክተኛው ﷺ ግመላቸው ቦታውን መርጣው ራሳቸው ባሠሩትና «መስጂደል-ቁባ/ጉልላት» በመባል በሚታወቀው አጠገብ፣ ጀግናው ባለታሪክ ሠላሀዲን አል-አዩቢ ድሮ ወቅፍ ያደረገው የተምር ዛፍ ፊት ለፊት፤ መናፈሻ ነገር ነበረ። እዚያ ላይ ሆኜ ያ አላህ! ለአንድ መስጂድ/መድረሳ አይደለም፣ በየቦታው እንዳስገነባ ለምን አታደርገኝም!? ብዬ አምርሬ በማልቀስ ለመንኩት፤ ...❞ እያሉ ባለፈው ሐምሌ 12/2018 ላይ በዓድዋ 00 ሙዚየም ውስጥ በሚገኝ አዳራሽ ላይ በተመረቀው «ናትራር» መጽሐፍ ያብራራሉ። ኢማም: ❝... በደርሱ/በጥናቱ የቀራሁትን ከዚያም በፊት ሱዳን ላይም አንድ ሁለቴ ዱዓዬ ሰምሮ ያየሁትን ነገር(እንዲሁም በስልጤነት ትግሉም ዘመን) አላሁ ተዓላ እንደገና በማግስቱ ጠዋት በተግባር ያሳየኝ ጀመር:: … ጠዋት የተከሰተው ነገር ያስገርማል! ...❞ ሲሉም በአድናቆት እየገለጹ ይቀጥላሉ ●●●(ቀሪውን ከመጽሐፉ ታገኙታላችሁ ●●●) በአጭሩ 2 የዓረብ ተወላጆች 1,500 ሪያል አምጥተውላቸው፣ እራሳቸውና ጓደኞቻቸው 2,500 ሪያል አዋጥተው፣ በድምሩም 4,000 ሪያል ይዘውና በዘመኑ ትንሽ ትሻል በነበረችውና አማካይ ቦታ የሆነችው «ዳሎቻ ከተማ» ናትና እዚያ ሄደን መድረሳ እንመሥርት ተባብለው መምጣታቸውን፤ ሪያሉንም ኢትዮጵያ ላይ በ12,000 ብር መንዝረው ወደ ዳሎቻ በማቅናት። ሐጂ ሀሚድ ሁሴንን አግኝተው፣ ስለ ዓላማቸውና ስለያዙት ገንዘብ በመንገር ከተወያዩ በኋላ፤ ገንዘቡ ለሀጂ ሀሚድ ከፍተኛ ዓቅም ሆኗቸው መሬቱን ህጋዊ ማድረግ ከመቻላቸውም በላይ ከመስጂዱ ወጥቶ/ተለይቶ በ1974 ላይ «መድረሰተ-ኑር(ብርሃን ት/ቤት» ተብሎ መመሥረቱን ታሪኩ በዝርዝር ያስረዳል። 🔷 ወደ ጉዳዬ ስገባ ፦ የ«ናትራር» መጽሐፍን የአርትኦት፣ የኤዲቲንግና የማማከር ሥራውን በነጻ ያገለገለው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል! በመጽሐፉ ምረቃ ዕለት፣ ከዳሎቻው ኑር መድረሳ(ብርሃን ት/ቤት) ምሥረታ ጋር የተያያዘው ታሪክ፤ ስሜቱን ረብሾት እንደነበረ ይታወሳል። የባለታሪኩ የኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ልባዊ የወገንና የሀገር የተቋማት እጥረትን የመሸፈንና የመሠረተ-ልማት ጉድለትን የማሟላት ፍላጎታቸው እንዲሁም ጥረታቸው አስገርሞት እንደነበር አስተውያለሁኝ በግንኙነታችን ወቅት። ኢማም! ለግላቸው ሳይሆን ለወገናቸው ብለው እያለቀሱ አላህን የተማጸኑበት ጉዳይ፣ ኡስታዙ በጥልቅ ግንዛቤው እና አስተውሎቱ አጥንቶት ነበረና እጅግ ቢገረም አያስደንቅም። እጅግ በተመስጦ አንብቦ የአርትኦት ተግባሩን ከፈጸመውና edit ካደረገው እንዲሁም እጅግ ከለፋበትና ካማከረው የ«ናትራር» መጽሐፍ ገጾች በደንብ መርምሮ ዐውቆት ነበር። በምረቃ ዕለቱ ደግሞ በእራሳቸው ፊት፣ ሕዝብ በተሰበሰበበት መድረክ ላይ እርሳቸውን(ኢማምን) ዓይነት ሰው ለኡማው የመሻቱ ጉጉት፣ የንጹህ ዱዓቸው ተቀባይነትና ስምረት፤ ከጊዜው ግለኝነትና ራስ ወዳድነት ጋር አነጻጽሮት ሚዛን አልደፋ ሲለው፣ የሕዝቡ የኔነትና የባለቤትነት እንዲሁም የአቃፊነትና የአንድነት ስሜት እየጎደለና እየወረደ እፊቱ ድቅን እያለበት፣ አውዱም አላስችል ቢለው ጊዜ ራሱን መቆጣጠር ተሳነውና ሲቃ ሲተናነቀው፣ እልህ እና ቁጭት ወኔውን ሲፈታተነው በዓይናችን በብረቱ ከፊት ለፊቱ ቁጭ ብለን ተመለከትን። ኢማም! በዚህ ግለኝነት በበዛበት ዘመን፤ አንድ በህይወት ያሉ ኢማም በዚህ ልክ ለኡመቱ ለመሥራት ሐሳብ አመንጭተው፣ ገንዘብ አዋጥተው ለማሰባሰብ ጥረት አደረጉ። ቢሆንም ባንድ/ሁለት ባልደረቦቻቸው አማካኝነት ባጋጠማቸው የአማና ገንዘብ መጥፋት ምክንያት፡ ❝ለምንና እንዴት!?❞ እያሉ፤ በዚያ ውድቅት ለሊት አብዛኛውን የምሽቱን ክፍል እየተከራከሩ አሳለፉ። ቀጥሎም የእንቅልፍ እጦቱ፣ ድካምና ዝለቱ ሳይበግራቸው ሁሉን አድራጊና ፈጣሪ ወደሆነው ጌታቸው፣ ፊታቸውን አዙረውና እጆቻቸውን አንስተው እንደለመኑት፤ ኡስታዝ አህመዲን በደንብ ያስታውሳል ...። ...(ምን እያሉ❓) ❝... ያ አላህ! እኔ የሳር መስጂድ(ኸልዋ) እና መድረሳ ወይም ጎጆ ቤት እንጂ ምንም በሌለበት ሀገራችን ላይ በጣም ብዙ መስጂድንና መድረሳን(ዲናዊ ተቋማትን) መሥራትን እየለመንኩህ፤ እንዴት አንዷን እንኳን እንዳሳካ መልካም ፈቃድህን ከለከልከኝ!? እኔ አሁንም በአንተ ተስፋ አልቆርጥም። በርካታ ዲናዊና ዓለማዊ ልማት ለሀገሬ/ለወገኔ ያስፈልገዋልና ይህንን ለማሳካት ነው የምማጸንህ‼️❞ ... ብለው መጸለያቸውን፤ ከዚያም ከአንድ መቶ በላይ መሳጂዶችንና መድረሳዎችን ማሠራታቸውን በተጨባጭ ማረጋገጥ ችሏልና “ሁላችንም ምናለ እንደ እርሳቸው በሆን!?” ብሎ ቢያልም አይፈረድበትም። ኢማም ሐጂ አ/ሃዲ እንደዚያ አዝነውና ተክዘው፣ ቅስማቸው ተሠብሮ እያለቀሱ ጌታቸውን የጠየቁበትን ዱዓንና ታሪኩን የሚያስታውሰው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ በምረቃው መድረክ ስለ ክስተቱ በሚያወሳበት ቅጽበት፤ ... የኢማም ጸሎታቸው ሰምሮ በትክክልም ከዘመናት በኋላ ስኬታማ የተቋማት ምሥረታንና የግንባታ ሥራን ከማከናወናቸው ጋር በተጨማሪም ይህን የመሰለ አስተማሪ ታሪክ ተሟልቶና ተሠንዶ፤ በዚያ ሁኔታ ላይ ደግሞ በታሪኩ ፈላጊዎችና አንባቢዎች አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለምርቃት የመብቃቱ ነገር ተደማምሮበት አላስችል ቢለው ሰውኛ ባህሪ መሠለኝ እንደ እኔ። ኡስታዝ አህመዲን ጀበል «ረበል-ዓለሚንን» ከልባችን ከለመነው፣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ መሆኑን በኃይማኖታዊ ትምህርቱም ሆነ በልምዱ የሚያውቀውን ነገር ነው መቸም። እና በተግባር ከኢማም ታሪክ አረጋግጦ ቢገረምና ከዲኑም ሆነ ከሚናፍቀውና ሰላም ከሌለው የዱንያ ህይወት፤ ሁለት-ያጣ የሆነው የዘመኑ ሰው ቢያዓጅበውና ቢያስለቅሰው እኮ ተዓምር ወይም ትንግርት አይደለም አዙሮ-መመልከቻ አንገት ባለቤት ለሆነ ፍጡር።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ህዝብ ቆሞ ያስመረቀው ድንቅ መፅሐፍ… ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል። 🔗 https://youtu.be/AcVGdp3GCis 🔗 #ኸሚስ_ምሽት #ኢማም_ሐጂ_አብዱልሃዲ ★ ★ ★ Ethio Sat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
видео или голосовое, без подписи
ዛሬም በተወዳጁ የኸሚስ ምሽት ፕሮግራማችን ከቀደመው ሳምንት ያሳደርነውን ሃሳብና በጅሕልና የሚተገበርን የዒባዳ ሥራ አሳዛኝ ፍፃሜ ከአዳዲስ ጉዳዮች ጋር ይዘን በሰዓታችን እንቀርባለን። የጉዞ ማስታወሻቸውን በረጋ አንደበት ሲያጋሩን የቆዩት እንግዳችን ኢማም ሐጅ አብዱልሐዲ ሸይኽ አህመድ ደግሞ ከረጅም ዓመታት መለያየት በኋላ ከወላጅ እናታቸው ጋር ለመገናኘት የነበራቸው ጉጉት በምን መልኩ ፍፃሜውን እንዳገኘ እያወጉንና፤ በወራቤ ከተማ አመሰራረትና በተለያዩ የኸይር ተግባራት ላይ የነበራቸውን ደማቅ ተሳትፎ እያስታወሱን ከኛ ጋር ይቆያሉ። ለይሉ ጁምዓ ነው! ፕሮግራሙ ደግሞ ተወዳጁ ኸሚስ ምሽት!! እንደሁልጊዜውም በዚክርና በሰለዋት ድምቅ ያለ ለይል ይሁንላችሁ። ምሽት ከ02:30 ጀምሮ በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን! #ኸሚስ_ምሽት #ለይሉ_ጁምዓ_ነው #የሸይኻችን_ሰዓት #ከመዲና_ሰማይ_ስር #ሸይኻችን #ሐጂ_አብዱልሃዲ ★ ★ ★ Ethio Sat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ!
የ5000 ሪያል የስራ ዕድል ትቼ ኢትዮጵያ የመጣሁበት ምክንያት… ሙሉ ፕሮግራሙን የዩትዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል። 🔗 https://youtu.be/lWxHPFbs-XQ 🔗 #ኸሚስ_ምሽት #ኢማም_ሐጂ_አብዱልሃዲ ★ ★ ★ Ethio Sat | 11545 | H | 45000 #ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
https://www.facebook.com/share/1EamMHbVbP/ በታሪክ ሂደት ውስጥ ስልጤ “በስልጤነቱ” ካገኛቸው ዕድሎችም ሆነ ከገጠሙት የዘመን ፈተናዎች በላይ “እስላም” በመሆኑ እና እስላምኛውን ጠብቆ ለማቆየት የከፈለው ዋጋ ወደር የለውም። ለአሁኑ ማንነቱ መደላደልም ሆነ ለደረሰበት ፈተና ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ይኸው ሃይማኖታዊ ማንነቱ ነው። ስልጤነት ትናንት የነበረ ዛሬም ያለና ነገም የሚኖር የማንነት ማዕቀፍ ቢሆንም ማህበረሰቡን በአንድ ጥላ ለመሰብሰብ የቻሉ መሠረቶችን ብንፈልግ መጀመሪያ የምናገኘው ታላቁን የእስልምና እምነት ነው። ከባህልና ከቋንቋ በላይ ከተለያዩ ጎሳዎች የተወጣጡ አባቶችን በአንድ ላይ ያሰባሰበው ወጥ የሆነ ስነ ልቦናና የደም ትስስር የፈጠረላቸው ዋነኛው ምሶሶ ይኸው ኢስላመኝነቱ ነው። ይህ የጋራ እሴት ከመልጋ እስከ አዘርነት ያሉ ቀደምት የሀገር ሽማግሌዎችን በአንድነት አምጥቶ “በኢስላምኛ” ተወያይተውና መክረው “ስልጤ” በሚል ስያሜ ለማቆም እንዲወስኑ አድርጓቸዋል። እንጂማ ተስማምተው ከቀደመው የሐዲያ ሱልጣኔት ጋር የነበራቸውን ታሪካዊ ቁርኝት መነሻ አድርገው “ሐዲያ” ቢሉት የሚቀረው “ኢስላመኝነቱን” ሊተካ የሚችል የጋራ ታሪክ፣ ያንን ስነ ልቦናዊና የደም ትስስር የሚገልፅ ወጥ የሆነ የጋራ ስያሜ ብቻ ነበር። ቀደምት “የእስላምኛ” ቋንቋ ተናጋሪ ስልጤዎች በየወቅቱ ይነሱ የነበሩ ወራሪዎችን ለመመከትና እስላማዊ ማንነታቸውን ጠብቀው ለማቆየት ከፍተኛ መሥዋዕትነት ከፍለዋል። ይህ የጋራ መሥዋዕትነትና ገድል በሌላው ማህበረሰብ ዘንድ ዕውቅና ሳይቸረው ረጅም ዘመናትን ያሳለፈ ቢሆንም አሁን ግን ይህ ታሪክ እየጎመራና የንቃት ዘመኑ ላህ እየደረሰ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች ይታያሉ። ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነው ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል “የናትራር” መፅሐፍ ምርቃት ላይ ያደረገው ታሪካዊ ንግግር ሲሆን ኡስታዝ በንግግሩ ወቅት “የወደፊቱ የስልጤነት ትግል ምን መልክ መያዝ እንዳለበት በጋራ መመካከር ያስፈልጋል” በማለት ወቅታዊና ስልታዊ ጥሪ አስተላልፏል። ይህ የኡስታዝ ጥሪ ትልቅ መነሻ መልዕክት ሲሆን ስልጤ ኢስላመኝነቱ ከሰጠው ዕድል ይልቅ ያመጣበት የፖለቲካና የማህበራዊ ፈተና እንደሚበዛ ማሰብ ብልህነት በመሆኑ ዛሬ ላይ ተቀምጠን በጋራ መመካከር ያሉትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አማራጮች በሚገባ ፈትሸን ያንን የታሪክ ፈተና ወደፊት ወደሚጠቅም ዕድል እንዴት እንቀይረው ብለን በሰፊው መወያየትም የብስለት ነው። Ezedin Baba
"አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት ነው" ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በስልጥኛ “ሀደ በሎኒ በላም ቢዮኒ ሀደም ኢላኒ፣ ሀደ በሆኒ ቀለም ቢዮኒ ሀደም ኢሎኒ” በሚል የዘወትር መፈክራቸው ይታወቃሉ። (አንድ ካልሆን ብዙም ብንሆን ምንም አናደርግም አንድ ከሆንን ትንሽም ብንሆን ምንም አንሆንም) ማለታቸው ነው። ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የተወለዱት በአሁኑ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ መንዞ ፈጠን ቀበሌ በ1954 ሲሆን የተለያዩ ሀይማኖታዊ እውቀቶች በሀገር ውስጥና በተለያዩ የዓለም ሀገራት በመዘዋወር ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የሸሪዓ (ሀይማኖታዊ) ትምህርቶችን ተምረው በስኬት አጠናቀዋል። ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ በተለያዩ አካባቢያዊ፣ ሀገራዊና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ሲሳተፉ፣ ሲደግፉ እና ሲያገለግሉ በመቆየት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አባልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን ህዝባቸውን በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በየሄዱበት ሁሉ የአንድነት ስብከት መልዕክቶችን በማስተላለፍ የሚታወቁት ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ በዋናነት ስለ አንድነት አስፈላጊነትና የመለያየትን ጎጂነት በኃላፊነት ያስተጋባሉ። የአንድነት ናፋቂ ሰው በመባል የሚታወቁት ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ "አንድነትን" የሚሰብክ ታዋቂ የስልጥኛ ቋንቋ አባበል (መፈክር) አላቸው ። «ሀደ በሎኒ በላም ቢዮኒ ሀደም ኢላኒ፣ ሀደ በሆኒ ቀለም ቢዮኒ ሀደም ኢሎኒ» የአማርኛ ትርጓሜውም ፦ አንድ ካልሆን ብዙም ብንሆን ምንም አናደርግም፤ አንድ ከሆንን ትንሽም ብንሆን ምንም አንሆንም ሲሆን ይህንንም አባባላቸውን በሰዎች መካከል አለመግባባት ሲኖር፣ የተጣሉ ሰዎችን ለማግባባት፣ ለማቀራረብና ለማስታረቅ እንዲሁም የአንድነት ኃይል ለማስረዳት ደጋግመው የሚጠቀሙበት፣ ታዋቂነትን ያተረፈ አባባላቸው (መፈክር) ሆኗል። ሰዎች ሲጣሉ አልወድምና ለማስታረቅ የማላደርገው ጥረት የለም የሚሉት ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ልዩነቶች ሲፈጠሩ በማወያየት፣ በማግባባትና በማቀራረብ አንድነትን መፍጠር ሲቻል በመለያየትና በጥላቻ ውጤት እንደማይመጣ የሚታወቅ ሲሆን ዋነኛው ጉዳቱ ደግሞ ለጠላት ጥቃት፣ ሽንቁር በር መክፈቱ መሆኑን ይገልፃሉ። "አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት" መሆኑን የሚናገሩት ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን፤ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት፣ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር እና ዘላቂ ሰላምን ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ይናገራሉ። ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ስለአንድነትና ጠቀሜታው፣ ሕብረት ከሌለ የሚያስከትለውን ጉዳት ከመግለጽና ከመስበክ ባለፈ፤ ልዩነቶች ሲፈጠሩ ሁልጊዜ “እባካችሁ! በትንሽ በትልቁ አንጣላ” እያሉ ከመማጸን በተጨማሪ በመደማመጥ፣ በመከባበር እና በመተማመን ሀገር ይገነባል ቂም-በቀል፣ ቁርሾና ጥላቻ ሲኖር ደግሞ ድህነትና ኋላቀርነት ይነግሳል ይላሉ። “ሀገር ካለ ዲን (እምነት) አለ፣ ዲን ካለ ኢማን (እውቀት) አለ፣ ኢማን (እውቀት) ካለ ደግሞ ጀነት (ገነት) አለ እያሉ የሀገርን ታላቅነት የሚገልፁት ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ፥ ችግሮች ሲፈጠሩና ውድቀት በሚከሰትበት ጊዜ: “እኔም ብሆን ልሳሳት/ላጠፋ እችል ነበር” ብሎ ኡዝር (ምክንያት) በመስጠት አንድነትን መጠበቅ ሲገባ፤ ወደ ኩርፊያ፣ ማማረርና አላህ የማይፈቀደውን ክፉ መነጋገር ከተጀመረ፤ መጣላት ይመጣና ከዚያም መራራቅ ይከተላል:: መግባባት ከሌለና ልዩነት እየሰፋ ከመጣ ደግሞ ለሌላ ጥቃት በር የመክፈት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ማስተዋል እንደሚገባ ይመክራሉ። በየሶሻል ሚዲያው የባለ-ታሪኮችን ስም ማጥፋትና ክብር መንካት፣ ሰዎችን ባልተረጋገጠ ጉዳይ መዝለፍና ማዋረድ ተገቢ አለመሆኑን ይገልፃሉ። ሌላው ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ የሥራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ ያላቸው አቋም ጠንካራ ሲሆን “ዓሳ አትስጠው፣ ዓሳ ማውጫ ስጠው” በሚለው ንግግራቸው ለተቸገረ ሰው ዓሳ አውጥተህ ልትሰጠው ትችላለህ፣ ለጊዜው ረሃቡን ሊያስታግስ ቢችልም ጥገኛ ያደርገዋል፤ ነገር ግን ዓሳ ማውጫ ገዝተህ ብትሰጠው ነፃ ታወጣዋለህ›› የሚሉት ሐጂ አብዱልሃዲ በተለይም ልማቱ በሚከናወንበት አካባቢ ላሉ ነዋሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጥ በማድረግ የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጠር በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ ከዚህም በተጓዳኝ ኢማም ሐጅ አብዱልሃዲ የስልጤ ማህበረሰብ ለ10 ዓመታት ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ያደረገው ሰላማዊ የማንነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ካበረከቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ በስልጤ ዞን የልማት ስራዎች ላይ ፈር ቀዳጅ በመሆን በሆቴል፣ በግብርና በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ተሰማርተው ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል። ከዚህ ባሻገር የእስልምና ዲን (ትምህርት) በስፋት እንዲዳረስ በሀገሪቱ በበርካታ አካባቢዎች መስጂዶች እንዲገነቡ፣ መድረሻዎች እንዲቋቋሙ እና የጎዳና ሕፃናትን በመሰብሰብ መጠለያ፣ ትምህርት፣ ሥነ ምግባር እና ተስፋ እንዲያገኙ ከማድረግ ጎን-ለጎን የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ለብዙዎች በአርዓያነት የሚጠቀስ ተግባር ያከናውናሉ። ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የትብብር ጥሪ ላይም ቀድመው በመድረስና በመለገስ የሚታወቁ ሲሆን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ይሳተፋሉ። ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ በተለያዩ አካባቢያዊ፣ ሀገራዊና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ሲሳተፉ፣ ሲደግፉ እና ሲያገለግሉ በመቆየት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በስልጤ ባህልና ታሪክ ውስጥ ለማህበረሰባቸው መልካም በመሥራት፣ ከጠላት በመከላከልና ደህንነትን በማረጋገጥ፣ መብትን በማስከበርና ሌሎችንም ገድሎችን ለፈጸሙ ታላላቅ ሰዎች ከሚሰጡ በርካታ የማዕረግ ስሞች መከከል አንዱ የሆነውን የ"ኢማም"ነት ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን የህይወት ታሪካቸው እና በስልጤ ህዝብ የማንነት ትግል እንዲሁም በሀገር ሁለንተናዊ ልማት ላይ ያላቸውን አበርክቶ የሚዳስስ መጽሀፍ ተዘጋጅቶላቸዋል። አንድነት የማንኛውም ሕዝብ እና ማህበረሰብ ትልቁ ጉልበት ነው፤ በተናጥል የሚከሰቱ ችግሮች በአንድነት ሲጋፈጡ መፍትሔ ያገኛሉ፤ የተዋሃዱ ሕዝቦች ታላላቅ ድሎችን አስመዝግበዋል፤ ስለዚህ የእድገታችን፣ የሰላማችን እና የስኬታችን መሠረት አንድነት ነው። እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ልብ ለልብ ተግባብተን ስንሠራ የማይፈታ ችግር አይኖርም፤ የማይወጣ ተራራ አይኖርም፤ የማይደረስበት ስኬትም አይኖርም ይላሉ ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን። ዘጋቢ: ሙጂብ ጁሀር - ከሆሳዕና ጣቢያችን
видео или голосовое, без подписи
https://youtu.be/dFKpGOfoJjc?si=nrjYPy668AjBiFPJ