tgindex
በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ መንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ መንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Статистика

news and media website

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 044
+2 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,10%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
195
24 постов
Вовлечённость
18,7%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
102
1/48двое суток
116
1/72трое суток
126

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጅነት ለማላቀቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ ‎ ‎ሐምሌ 03/2018ዓ/ም ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን ‎ ‎የሳንኩራ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጅነት ለማላቀቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል ። ‎ ‎  ተቋሙ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅዶ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል ተጋላጭና ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን ከተረጂነት ማላቀቅ ነው፡፡ ‎ ‎ይህንን ተከትሎ ተቋሙ ከተለያዩ ቀበሌዎች ለተወጣጡ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የዶሮ ጫጩት ድጋፍ አደርጓል፡፡ ‎ ‎በድጋፍ መርሃ-ግብሩ የሳንኩራ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ ፣ የግብርና ተቋም የእንስሳት ዘርፍ ሀላፊና የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ጽ/ቤት ም/ል ሀላፊ ተገኝተዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎ ‎ ‎

  • የቅበት ከተማ  አስተዳደር ወጣቶች ክንፍ በሳንኩራ ወረዳ የድንበር ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት አከናወነ፡፡ ‎ ‎ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን ‎ ‎“በጎነት ለኢትዮጵየ ከፍታ'' ለወንድማማችነት፣ በወጣቶች ተሳትፎ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በሳንኩራ ወረዳ የድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አካሄዱ። ‎ ‎በዚህ የሰብዓዊ ድጋፍ መርሃ ግብር በሳንኩራ  ወረዳ ለሚገኙና ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ግንባታ ቁሳቁሶችና የምግብ ፍጆታ አስቤዛዎች አስረክበዋል። ‎ ‎ የተካሄደው የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴ ማኅበራዊ አንድነትን ፣ ወንድማማችነትንና ህዝባዊ መተሳሰብን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ‎ ‎ ድጋፉ ችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን ከመደገፍ ባሻገር በአካባቢዎች መካከል ያለውን የመደጋገፍና የመረዳዳት የጋራ ባህል የሚያጠናክር ነው፡፡። ‎ ‎በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሳንኩራ  ወረዳ  ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ፣ የቅበት ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ክንፍ ላከናወነው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል። ‎ ‎እንደነዚህ ያሉ ተግባራት በማህበረሰቡ መካከል የአንድነትና የወንድማማችነት መንፈስን በማጎልበት ረገድ የሚያበረክተው ፋይዳ የጎላ ስለመሆኑ ዋና አስተዳዳሪዋ ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ መሰል ሰብዓዊና ልማታዊ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም ወ/ሮ ተሚማ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎በሌላ በኩል የሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ስርበላ ከድር በጎነትና መተጋገዝ የማኅበረሰብ ጥንካሬ መሰረቶች መሆናቸውን በመግለጽ ፣ መሰል ድጋፎችን በቀጣይነት ለማከናወን የወጣቶች ክንፉ ቁርጠኛ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ‎ ‎በተመሳሳይ የቅበት ከተማ  አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ  ወጣት ፋርስ ከድር  በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ በአካባቢዎቹ መካከል ያለውን እህትማማችነትና ወንድማማችነት እንደሚያጠናክር ገልጸው፣ የበጎ ፈቃድ ባህል ተስፋፍቶ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ‎ ‎ይህ የድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተቸገሩ ወገኖች ላይ ተጨባጭ ለውጥ ከማምጣቱ ባሻገር፣ የወጣቶችን ማኅበራዊ ተሳትፎ በማሳደግ በመዋቅሮች መካከል ያለውን ህዝባዊ ትስስር አዲስ ምዕራፍ ላይ ያሸጋገረ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል። ‎ ‎ በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የወረዳው ዋና አስተዳደር  ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ  አብዱልፈታ ሰልማን ፣ የሳንኩራ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰላሞን ይልማ ፣ የሳንኩራ ወረዳና የቅበት ከተማ አስተዳደር የክንፍ ኃላፊዎች ፣የወጣት አደረጃጀት ፣ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶች የተለያዩ የአካባቢው ማኅበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎ ‎ ‎

  • ለፈጣን የከተሜነት ዕድገት መስፋፋት በአንድ አከባቢ የሚኖር የንግድ እንቅስቃሴ ወሳኝነት እንዳለው ተገለፀ ‎ ‎ነሀሴ 3 /2018 ዓም ሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ የበርጮ ቀበሌ ጥንስስ ከተማን ዕድገት በማፋጠን የአከባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የገበያ ቀን ማብሰሪያ መርሃ-ግብር  ተካሄደ፡፡ ‎ ‎ገበያ ለአንድ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገትና የህዝብ ለህዝብ መስተጋብር ፣ የኢኮኖሚ ልውውጥ እንዲኖር ፣ አምራች አርሶ ደሮችን በቅርበት የገበያ ትስስር መፍጠር እንዲችሉ የሚያስችል ነው ፡፡ ‎ ‎በዚህም መሰረት የበርጮ ቀበሌ ጥንስስ ከተማን ዕድገት በማፋጠን የአከባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የገበያ ቀን ማብሰሪያ መርሃ-ግብር በበርጮ ቀበሌ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎መርሃ-ግብሩን አስመልክቶ የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀያቱ ኑሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ‎ ‎ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ለአንድ አከባቢ ለፈጣን የከተሜነት ዕድገት በቋሚነት የሚካሄድ የንግድ እንቅስቃሴ መኖር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ ‎ ‎የበርጮ ጥንስስ ከተማ ፈጣን እንቅስቃሴ የሚታይባት ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪዋ የገበያው መመስረት የአከባቢውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር በአጭር ጊዜ ፈጣን የንግድ ማዕከል መሆን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‎ ‎የበርጮ ቀበሌ ጥንስስ ከተማ የቀበያ ቀን በየሳምንቱ ዕሁድ ቀን እንደሚቆም ዋና አስተዳዳሪዋ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎በዕለቱም ለገበያ የቀረቡ የተለያዩ ምርቶችን በፕሮግራሙ በታደሙ እንግዶች ተጎብኝቷል፡፡ ‎ ‎በመርሃ-ግብሩ የወረዳው አስተባባሪ አካላትና አመራሮች ፣ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎ ‎ ‎

  • ‎ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያዩ መስኮች ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ ‎ ‎ነሀሴ 2 /2018 ዓም ሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎ከስልጤ ዞን የተወጣጡ የክረምት በጎ ቴክኒክ ኮሚቴ በዘንድሮ የክረምት ወራት ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያዩ መስኮች ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡ ‎ ‎ ለወገን ችግር ቀድሞ መድረስ ፣ የተራበውን ማጉረስ ፣ የታረዘውን ማልበስ ፣ የታመመውን መንከባከብ ፣ የተቸገረውን መርዳትና ያዘነውን ማፅናናት ፍፁም! እርካታ የሚያጎናፅፉ ሰብአዊ እሴቶች ናቸው፡፡ ‎ ‎ታዳ እኚህ ሰብዓዊ እሴቶች ከሚገለፁባቸው አንዱ የበጎ ፈቃድ ስራ ሲሆን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሰፊው ማህበረሰብ ልማትና እድገት እንዲሁም ለሀገር ሰላምና ደህንነት ሲባል ዜጎች ጊዚያቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን እንዲሁም ገንዘባቸውን አስተባብረው ተግባራዊ የሚያደርጉት ዘመናዊ የድጋፍ አሰጣጥ መንገድ ነው፡፡ ‎ ‎ከስልጤ ዞን ተወጣጥተው በሳንኩራ ወረዳ የተገኙ የክረምት በጎ ቴክኒክ ኮሚቴ  ፤ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮነሚያዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ እንዲችል በ18 ዘርፎች ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የበጎ ስራዎች በተገቢው አደረጃደትና ዕቅድ እየተመሩ ስለመሆናቸው በተለያዩ ቀበሌዎች በመዟዟር ክትትልና ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ‎ ‎የክረምት በጎ ቴክኒክ ኮሚቴው በተለያዩ ቀበሌዎች ተዟዙረው በመስክ ካረጉት ምልከታ መነሻ የወረዳ አስተባባሪና ባለድርሻ አመራር አካላት በተገኙበት የመስክ ግብረ-መልስ በማቅረብ በታዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ‎ ‎ቴክኒክ ኮሚቴው ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያዩ መስኮች ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በየዘርፉ የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎ ‎ ‎

  • በሳንኩራ ወረዳ በሚገኙ ሁሉም ብልጽግና ሕብረቶች ደረጃ "ከምርጫ ማግስት ጠንከራ ፓርቲ ፣ ለጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ህብረት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት የፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ ተካሄደ ነሐሴ 1/2018 የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች በሚገኙ ብልጽግና ሕብረቶች ደረጃ "ከምርጫ ማግስት ጠንከራ ፓርቲ ፣ ለጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ሕብረቶች የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዓ/ም የፈጻሚ ማዘጋጃ እቅድ ግምገማ መድረክ ተካሂዷል። በወረዳው በሚገኙ የብልጽግና ሕብረቶች ደረጃ በተካሄደው የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የፈጻሚ ማዘጋጃ እቅድ ግምገማ መድረክ ላይ ያለፈውን በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት ስራዎች አፈፃፀም በጥንካሬና በጉደለት በዝርዝር በማቅረብ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን የቀጣይ እቅድ ቀርቦ ተገምግሟል። በመድረኩ ባለፈው በጀት ዓመት በተሻለ ሁኔታ የተፈፀሙ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል በጉደለት የተለዩትን የቀጣይ እቅድ አድርጎ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ጠንካራ ግምገማ በማካሄድ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል። በመጨረሻም በአፈፃፀም ግምገማና ፈፃሚ ማዘጋጃ መድረኩ ላይ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ መፈጸም ለቻሉ ብልጽግና ሕብረቶች፣የብልጽግና ቤተሰብና አባላት ማበረታቻ ሰርተፊኬት በመስጠት ተጠናቋል። ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 🌍 ቴሌግራም፦ https://t.me/+7_qexDRrC-Q2ODhk 🌍 ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/SWCTCAffairs 🌍 ዩቲዩብ፦https://www.youtube.com/@sankuratube 🌍 ቲዊተር:-https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 🌍 ኢንስታግራም:-https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA 🌍 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu 🌍 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎

  • ‎የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ አቅም የሚፈጠር ስለመሆኑ ተገለፀ ‎ ‎ሐምሌ 30/2018 ሳንኩራ ኮሚኒኬሽን ‎ ‎"በምርጫ ማግስት ጠንከራ ፓርቲ ፣ ለጠንካራ መንግስት " በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሲያካሂዱ የቆየው የ2018 ዓ.ም ዕቅደ አፈጻጸም እና የ2019 የፈጻሚ ማዘጋጃ የማጠቃለያ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡ ‎ ‎የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ባካሄደው መድረክ በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃሃፊ አቶ ስርበላ ከድር የ2018 ወጣቶች ክንፍ ታቅደው የተሰሩ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ‎ ‎በሌላም በኩል በወጣቶች ዕሴት ግንባታ ዙሪያ የተዘጋጀ የስልጠና ሰነድ በሳንኩራ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሱነሞ በኩል ቀርቦ ለወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ‎ ‎በቀረበው የስልጠና ሰነድና ሪፖርት ዙሪያ ከወጣቶች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ ‎ ‎የውይይት መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲና ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙበሽር ከይረዲንና በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃሃፊ አቶ ስርበላ ከድር የተመራ ነው፡፡ ‎ ‎በመድረኩ የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እንዲመጣ አቅም የሚፈጠር በመሆኑ እንደ ወረዳ እየተሰሩ ባሉ ሁሉ አቀፍ ተግባራት ወጣቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል ተብሏል፡፡ ‎ ‎በመድረኩ መጨረሻ የ2019 ዕቅድ የግብ ስምምነት በወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት እና በቀበሌ ወጣቶች ክንፍ የተደረገ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ ለቻሉ ወጣቶች የሰርፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎

  • ‌‎"በጎነት ለህትማማችነት በሴቶች ተሳትፎ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ተካሄደ ‎ ‎ሐምሌ 30/2018 ሳንኩራ ኮሚኒኬሽን ‎ ‎በስልጤ ዞን የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ "በጎነት ለህትማማችነት በሴቶች ተሳትፎ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር በሳንኩራ ወረዳ አካሂደዋል፡፡ ‎ ‎የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሰፊው ማህበረሰብ ልማትና እድገት እንዲሁም ለሀገር ሰላምና ደህንነት ሲባል ዜጎች ጊዚያቸውን ፣ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን አስተባብረው ተግባራዊ የሚያደርጉት ዘመናዊ የድጋፍ አሰጣጥ መንገድ ነው። ‎ ‎በጎነት የድንበር ወሰን የማይገድበው የመደጋገፍ ዕሴት መሆኑን ተከትሎ የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ በሳንኩራ ወረዳ በመገኘት ለአቅመ-ደካማ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ግንባታ የክዳን ቆርቆሮና ምንጣፍ ድጋፍ በማድረግ የግንባታ ስራ አስጀምረዋል፡፡ ‎ ‎በሌላም በኩል ከተለያዩ ቀበሌዎች ለተውጣጡ ድጋፍ ለሚሹ አቅመ-ደካሞች የዱቄትና ዘይት ድጋፍ ያደረጉት በጎ ፈቃደኞቹ ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም ለህጻናት ደግሞ የደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ‎ ‎በወረዳው የተገኙት የቅበት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ በወረዳው ረግዲና ቆሬ ቀበሌ በመንገድ ዳር የኮሪደር ልማት የለሙ የሙዝ ኢንሼቲቮችን የጎበኙ ሲሆን በዕለቱም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ከወረዳው አስተደዳዳሪና ሌሎች አመራር አካላት ጋር በመሆን አካሂደዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎

  • ሁሉ አቀፍ የልማት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ ‎ ‎ ሐምሌ 28/2018 ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን ‎ ‎ በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት "በምርጫ ማግስት ጠንከራ ፓርቲ ፣ ለጠንካራ መንግስት " በሚል መሪ ቃል ሲያካሂድ የቆየው የ2018 ዓ.ም የፓርቲ ስራዎች ዕቅደ አፈጻጸም ማጠቃለያና የፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ ተጠናቋል፡፡ ‎ ‎የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፤ በባለፈው በጀት ዓመት ውጤታማ አደረጃጀቶችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተጠቅሞ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በላቀ ቁርጠኝነት በመፈጸም ረገድ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና በአሰራር ሂደት በየመዋቅሩ የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም በበጀት ዓመቱ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን መስራትን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ‎ ‎በመድረኩ ለሁሉም ቀበሌዎችና ህብረቶች የወረደ የ2018 ግብረ-መልስ በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዘይኔ አህመድ እና  ‎በፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስርጎታ ደርፈታ ደግሞ የ2018 የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ሰነዶችን መነሻ ያደረገ ግምገማ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎በየደረጃው ተወጣጥተው በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ፤ በየደረጃው የተስተዋሉ ጉድለቶችን ለማረምና የማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ‎ ‎ የግምገማ መድረኩ በሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ‎ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ እና የሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ ሰልማን የተመራ ነው፡፡ ‎ ‎በመድረኩ በትምህርት ፣ በጤና እና በግብርና ዘርፍ ፣ በመንገድ  ፣ በስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በውሃ ፣ በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ እንዲሁም በቀበሌ ደረጃ በመሰራት ላይ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ገምግሟል ፡ ‎ ‎ መንግስት የዜጎችን ሁለንተዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ  በማህበራዊና ኢኮነሚያዊ የልማት ዘርፎችን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ሁሉ አቀፍ የልማት ስራዎችን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራና ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገ ስለመሆኑ ተገልጿል ፡፡ ‎ ‎ የዜጎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው ለመመለስ ፣ የኑሮ ውድነት ጫናንና ለመቀነስ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን የማሳደግና የማዘመን ስራዎች በቁርጠኝነት መሰራት ስለመቻላቸውም በመድረኩ ተገልጿል ፡፡ ‎ ‎በየደረጃው የሚገኙ አደረጃጀቶች ዕቅድንን መሰረት ባደረገ መልኩ በሁሉም የልማት መስኮች የበኩላቸውን ሚና ማበርከት እንዲችሉ ትኩረት አድርጎ ከመስራት አንጻር የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም የሚገባ ስለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን የአደረጃጀቶችን ሚና በውል በመገንዘብ ተግባራትን በአደረጃጀት እየገመገሙ በዕቅድ መምራት አስፈላጊ እንደሆነም በመድረኩ በትኩረት ተቀምጧል፡፡ ‎ ‎በሁሉም ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና በአሰራር ሂደት የተስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ስለመሆኑ መድረኩ አመላክቷል ፡፡ ‎ ‎በመድረኩ በበጀት ዓመቱ ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጀ የግብ ስምምነት ሰነድ ፊርማ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎በመጨረሻም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ ለቻሉ  ቀበሌዎችና መሰረታዊ ድርጅቶች የዕውቅናና የሰርተፊኬት እንዲሁም የወንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎ ‎ ‎

  • ‎ዛፍ መትከል ለዛሬ ብቻ የሚጠቅም ተግባር ሳይሆን  ለመጪው ትውልድ የሚተው ዘላቂ አሻራ ስለመሆኑ ተገለፀ ‎ ‎ሐምሌ 27/2018 ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን ‎ ‎በስልጤ ዞን ሳራንኩራ ወረዳ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በወረዳው ጀጀቢቾ ለምለም ቀበሌ የ2018 የአረንጓዴ ልማት አሻራ መርሃ-ግብር የችግኝ ተከላ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎በመርሃ-ግብሩ የእንኳነ ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሳንኩራ ወረዳ ም/ል አስተዳዳሪና የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሀባ ሳሊያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የአየር ንብረትን በመቋቋም ምቹ ከባቢያዊ ስነ-ምህዳርን በማስተካከል ረገድ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸውን ችግኞች እንደ ወረዳ በየዓመቱ በመትከል ምቹ ከባቢን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ‎ ‎አእንደ ወረዳ የተተከሉ ችግኞቸ እየተለዋወጠ የመጣውን የአየር ንብረትና የአከባቢ የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት እንዲሻሻል ፣ እየተስፋፋ የመጣውን በረሃማነት መከላከል እንዲቻል እንዲሁም ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት በማሳደግ አከባቢን ለኑሮና ለሥራ ምቹ ማድረግ ስለማስቻሉ አቶ ሙሀባ ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎ለነገው ትውልድ አሻራችንን ለማስቀመጥ በሚካሂደው  ወረዳዊ የአንድ ጀምበር የማስጀመሪያ የችግኝ ተከላ ከ1መቶ 14 ሺ በላይ የደን ፣ የፍራፍሬና የቡና ችግኞች  ይተከላሉ ሲሉ ም/ል አስተዳዳሪው አያይዘው ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎ወረዳዊ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩን ያስጀመሩት የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱ የችግኝ ተከላ ፕሮግራሞች ፤ በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ የመጣውን አጠቃላይ የደን ሽፋን ለማስተካከል እንዲሁም ዘላቂነት ያለው ሀገራዊ ልማት መረጋገጥ እንዲችል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከት መቻሉን ገልጸዋል፡ ‎ ‎ በባለፉት ስምንት አመታት እንደ ወረዳ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ከ20 ሚሊየን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን የገለፁት ወ/ሮ ተሚማ በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከተላ  የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸውን የቡናና አቡካዶ ፣ የደን እንዲሁም የመኖ ችግኞችን ጨምሮ 5ሚሊየን 9መቶ ሺ ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል ፡ ‎ ‎ዛፍ መትከል ለዛሬ ብቻ የሚጠቅም ተግባር ሳይሆን ፤  ለመጪው ትውልድ የምንተወው ዘላቂ አሻራ መሆኑን የገለፁት አስተዳዳሪዋ የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ የሕይወት፣ የልማት ፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የወደፊት ተስፋ ምልክት መሆኑን አስድተዋል፡፡ ‎ ‎ ዋና አስተዳዳሪዋ አያይዘው የተራቆቱ ፣ የተጋጋጡና የተቦረቦሩ መሬቶችን እንዲያገግሙ ማድረግ የሚያሰችሉ ችግኞችን በመትከል የተመቻቸ መሬትና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ተፈጥሮ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁላችንም ሀላፊነትና ግዴታ መሆኑን መረዳትና ለተግባራዊነቱ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም  አሳስበዋል፡፡ ‎ ‎በመርሃ-ግብሩ የወረዳ አስተባባሪ አካላት ፣ የዞን ደጋፊ አመራር ፣ የክልል የATI አተባባሪና ባለሙያ ፣ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ፣ የቢሮና የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች እንዲሁም የጀጀቢቾ ለምለም ቀበሌ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን በተዘጋጁ ቦታዎችና በATI በሚገነባው የአግሪ-ቢዝነስ ኩባንያ ተቋም የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች ተከላ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎ ‎ ‎ ‎ ‎

  • "የሴቶች አቅምና ንቁ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላምና ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ‎ ‎ ሐምሌ 26/2018 ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን ‎ ‎የሳንኩራ ወረዳ  ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት  "የሴቶች አቅምና ንቁ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላምና ብልፅግና!"በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የሴቶች ልማትና ንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መሰረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል። ‎ ‎በመድረኩ የሴቶች ልማት ህብረት ስትሪንግ ኮሚቴ እና የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብረ ኃይል በዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በቀጣይ በሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ላይ የሚሰጡ ትኩረቶችን በስፋት ገምግመዋል። ‎ ‎መድረኩን የመሩትየሳንኩራ ወረዳ  ብልፅግና ፓርቲ ረዳት የመግስት ተጠሪና የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስርጎታ ደርፈታ  ሴቶች በተለያዩ የልማት መስኮች እያሳዩ ያሉት ንቁ ተሳትፎ በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ መረጋጋት በሰላም እሴት ግንባታና በአጠቃላይ የወረዳዉ  ልማት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑ ጠቅሷል። ‎ ‎በኢኮኖሚ ዘርፍ ሴቶች በቡድን በመደራጀትና የገበያ ትስስር በመፍጠር እንደ ካሮትና ጎመን ያሉ የግብርና ምርቶችን እስከ አዲስ አበባ ድረስ በማቅረብ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ መሆናቸው አቶ ስርጎታ ገልፀዋል። ‎ ‎የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም መጎልበት በቤተሰብ ውስጥ የነበሩ ግጭቶችን በመቀነስ ወደ ፍርድ ቤት የሚደርሱ የክርክር ጉዳዮችን እንዲቀንሱ አስተዋጽኦ ማድረጉም ስለመቻሉም ሀላፊው ጠቁመዋል። ‎ ‎አቶ ስርጎታ አያይዘውም በፖለቲካው ዘርፍም ሴቶች በዘንድሮው የምርጫ ሂደቶችና በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያላቸው ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱና ይበል የሚያስብል ስራ መሰራቱንም አንስተዋል። ‎ ‎በማህበራዊ ዘርፍም ከጤና ጥበቃ፣ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መከላከልና የማህበረሰብ ንቃተ ህሊና ግንባታ ጋር ተያይዘው የተሰሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተመላክቷል። ‎ ‎ተቋማት ከታች እስከ ላይ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውና በዋናነትም ተቋማዊ ግድፈቶችን ማጥራት፣ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናቀቅ፣ እሴቶችን መጠበቅና ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገር እንዲሁም አሉታዊ አሰራሮችን መቀነስ ላይ በተገቢው መስራት ይጠበቃል ብለዋል። ‎ ‎ሴቶች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአረንጓዴ አሻራ እና የትምህርት ስራዎችን ማጠናከር ላን ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል። ‎ ‎የሳንኩራ ወረዳ  ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ፀፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘይንያ ሸ/አደም በ2018 በጀት ዓመት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህፃናትን መብት ለማስጠበቅ አመርቂ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል። ‎ ‎ሴቶች በቁጠባ፣ በህብረት ሥራ ማህበራት እና በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ያሳዩት ተሳትፎ የቤተሰብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ሀላፊዋ ጨምረው ገልጿል። ‎ ‎ሴቶች በአቅራቢያቸው መቆጠብና ብድር ማግኘት እንዲችሉ ሁሉም የልማት ህብረት አባላት የሆኑ ሴቶች የህብረት ስራ ማህበራት አባል መሆን እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥቶታል። ‎ ‎የሴቶች ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ ማህበረሰቡ ይለወጣል ያሉት ወ/ሮ ዘይንያ  የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርና እና የፍትህ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ የሚያስችሉ የቴክኒክና የስትሪንግ ኮሚቴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል። ‎ ‎ሞዴል ቀበሌዎችን ማስፋፋት በአንድ ማዕከል የተቀናጀ አገልግሎት የሚሰጡ ሞዴል ቀበሌዎችንና ወረዳዎችን ቁጥር ማሳደግ ይገባል ብለዋል። ‎ ‎"ሞዴል" የተባሉ አካባቢዎች ተሞክሮአቸውን ለሌሎች እንዲያካፍሉና በ2019 የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም አካል በቁርጠኝነት እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል። ‎ ‎በሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማጠናከር በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የሴቶች ልማት ቡድንና የንቅናቄ ስራዎችን የሚያሳይ አጠቃላይ የአፈፃፀም ሪፖርት በፅ/ቤቱ በለሙያ  በአቶ መሀመድ አወል  ቀርቧል። ‎ ‎ሪፖርቱ በዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የተመዘገቡ ውጤቶች ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸውን የስራ አቅጣጫዎች ላይ አቶ መሀመድ አወል በዝርዝር አቅርበው ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል። ‎ ‎የሴቶችን የኢኮኖሚ የፖለቲካና የማህበራዊ ተሳትፎ ይበልጥ ለማጠናከር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠልና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሁሉም የአመራር አካላት በቅንጅትና በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል። ‎ ‎በመጨረሻም የወረዳዉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ፅ/ቤት  በ2019 በጀት አመት በሚሰሩ የዘርፉ ተግባራት በትኩረት መመራት ፤እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎

  • የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በማስፋትና የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ ‎ ‎ሐምሌ 25/2018 ዓ/ም ሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎የሳንኩራ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በማስፋትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትትራንስፎርመርን ጨምሮ 4 ሚሊን 5መቶ ሺ ብር በሆነ የህብረተሰብ ተሳትፎ ወጪ የቆሬ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን ማህበርን ከጄነሬተር በተጨማሪ ወደ መብራት መቀየር የሚያስችል የትራንስፎርመር ሰቀላ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ ‎ ‎ተቋሙ በየደረጃው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራይገኛል ፡ ‎ ‎ይህንን ተከትሎ ተቋሙ የቆሬ  የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳንቴሽን ማህበር ከጀኔሬተር በተጨማሪ በመብራት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በተገኘ በጀት ከ4 ሚሊየን 5መቶ ሺብር በላይ ወጪ የ2 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ ፣ የ50 ፖል ተካለ ፣100 KVA ትራንስፎርመር ግዥ እና አስፈለግ የሆኑ ቁሰቁስ እንዲሟላ በማድረግ በዛሬው ዕለት የወረዳ አስተባባሪ በተገኙበት የትራንስፎርመር   ሰቀላ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎ የቆሬ ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በዘላቂነት ለማስፋት የውሃ ማህበሩን ከጄኔሬተር በተጨማሪ በመብራት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ከህብረተሰቡ በተደረገ ውይይት አስፈላጊው፡በጀት ተዘጋጅቶ ትራንስፎርመርን ጨምሮ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ግዢ በመፈጸም የማብራት ዝርጋታ ስራ በማጠናቀ ትራንስፎርመር የመስቀል ስራ በዛሬው ዕለት ተሰርቷል። ‎ ‎ ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎

  • ከ3መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የመድኃኒት ግዢ በመፈጸም ለጤና ጣቢያዎች ስርጭት ስለመደረጉ ተገለፀ ‎ ‎ሐምሌ 24/2018 የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዕድሜያቸው ከ 2-5 አመት ለሆናቸው 10ሺ 5መቶ ህፃናት እና ለ 3ሺ 5መቶ  ነፍሰጡር እናቶች ተደራሽ መሆን የሚችሉ  የአልቤን- ዳዞልና አሞክሳሲሊን መድኃኒቶችን ከ3መቶ ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ ግዢ በመፈጸም ለጤና ኬላዎች አሰራጭቷል፡፡ ‎ ‎ተቋሙ የአንጀት ጥገኛ ትላትል መከላከያ መድሃኒት (Albendazole እና በጤና ጣቢያ እና ጤና ኬላ የሚታከሙ ህፃናት አገልግሎት የሚውሉ (Amoxacilin )መድኃኒቶችን ግዢ በመፈጸም ነው ያሰራጨው፡፡ ‎ ‎በመርሃ-ግብሩ የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ መዴና የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አርጋ ከድር እንዲሁም ም/ል ኃላፊ አቶ ኢክማ ኑሪ ተገኝተው ለጤና ጣቢያዎች መድኃኒቶችን አስረክበዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎

  • ወቅታዊ ልማታዊ ስራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በመፈጸም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ ‎ ‎ሐምሌ 24/2018 የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ በተያዘው የበጀት ዓመት የማህበረሰቡን ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ ወቅታዊ ተግባራትን መነሻ ያደረገ የግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በዛሬው ዕለት የተካሄደው የግምገማ መድረክ ፤ በወረዳ ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ወቅታዊ ተግባራት አጠቃላይ አፈጻጸም ምን ይሚመስላል የሚለውን በማየት የአፈጻጸም ጉድለት የተስተዋለባቸው መዋቅሮች ከጉድለታቸው መውጣት እንዲችሉ በማስቻል በየዘርፉ ታቅደው እየተሰሩ ያሉ ወረዳዊ ተግባራትን ውጤታማ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ‎ ‎በመድረኩ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ የግብርና ልማት ስራዎች ፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ፣ በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በትምህርት ፣ የግብዓት ስርጭት ፣ በጤና በመከላከያ ምልመላ ፣ በዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ እንዲሁም ሌሎች በየቀበሌው እየተሰሩ የሚገኙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ወቅታዊ ተግባራት የአተገባበር ሂደትና ዝርዝር አፈጻጸሞች በየተቋሙ የስራ ሀላፊዎች እንዲቀርብ ተደርጎ የቀረበውን ሪፖርት መነሻ ያደረገ ግምገማ ተካሂዷል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ወረዳዊ ተግባራትን ለመገምገም የተካሄደውን የግምገማ መድረክ በስልጤ ዞን ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መሀመድ ፈጌሳ ‎በሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ እና በሳንኩራ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ ሰልማን የተመራ ነው፡፡ ‎ ‎አሁን ላይ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ የግብርና ልማት ስራዎች በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ልመናን በማስቀረት ከተረጂነት ለመውጣት የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ወደ ስራ መገባቱ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን አርሶ አደሩ በሁሉም ዘርፍ የጀመራቸውን የግብርና ልማት ተግባራት አጠናክሮ በማስቀጠል ለምርትና ምርታማነት መጨመር እየተደረገ ያለውን ጥረት በተሳካ መልኩ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተብራርቷል፡፡ ‎ ‎የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮነሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በንቅናቄ ተጀምሮ በ17 ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ የክረምት ወራት የበጎ ስራዎች ላይም እየተስተዋሉ ያሉ ጉድለቶች መገምገም የቻለው መድረኩ አቅመ-ደካማና ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች በመተግበር ላይ የሚገኙ የበጎ ተግባራትን በላቀ ቁርጠኝነት መፈጸም እንደሚገባ በአጽንኦት አስቀምጧል፡፡ ‎ ‎በሌላም በኩል በትምህርት ፣ በጤና እና በግብዓት ስርጭት ፣ በመከላከያ ምልመላ ፣ በዲጅታል መታወቂያ በስራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም በቀበሌ ደረጃ በመሰራት ላይ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ወቅታዊ ተግባራት ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ የገመገመው መድረኩ በሁሉም ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና በአሰራር ሂደት የተስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ መሆኑን አመላክቷል ፡፡ ‎ ‎በየደረጃው የሚገኙ አደረጃጀቶች ዕቅን መሰረት ባደረገ መልኩ በሁሉም የልማት መስኮች የበኩላቸውን ሚና ማበርከት እንዲችሉ ትኩረት አድርጎ ከመስራት አንጻር የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ ማረም የሚገባ ስለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን የአደረጃጀቶችን ሚና በውል በመገንዘብ ተግባራትን በአደረጃጀት እየገመገሙ መምራት አስፈላጊ ስለመሆኑም በመድረኩ በትኩረት ተቀምጧል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ዘላቂና ሁሉ አቀፍ ልማታዊ ለውጦች መመዝገብ እንዲችሉ በሀላፊነት መስራት እንደሚገባ በመድረኩ ማጠቃለያ ተመላክቷል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ተግባራትን ለመገምገም በተካሄደው መድረክ ፣ የወረዳ አመራር አካላት ፣ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ‎ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎

  • የስልጤ ዞን ኢንቨስትመንት ልማት መምሪያ የድጋፍና የኢንስፔክሽን ቡድን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙሪያ የመስክ ምልከታ አካሄዱ ‎ ‎ሐምሌ 23/2018ዓ/ም ሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎የስልጤ ዞን ኢንቨስትመንት ልማት መምሪያ የድጋፍና የኢንስፔክሽን ቡድን በሳንኩራ ወረዳ ረግዲና ማዞሪያ ከተማ በባለሀብቶች በአገልግሎትና በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ በማካሄድ አፈጻጸምን ገምግመዋል፡፡ ‎ ‎በከተማው መሬት ወስደው ግንባታ ያልጀመሩና ጀምረው ያቋረጡ ፣አጥረው ያስቀመጡ እንዲሁም በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በማምረት የዘርፉን ውጤታማነት ማሳደግ በሚችሉበት አግባብ ድጋፍ ያደረጉት የኢንስፔክሽን ቡድኑ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በማያለሙ ኢንቨስተሮች ላይ ህጋዊ እርምጃዎች የሚወሰድ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ‎ ‎በድጋፍና ክትትል ፕሮግራሙ የስልጤ ዞን ኢንቨስትመንት መምሪያ የድጋፍና ክትትል ቡድን ፣ የሳንኩራ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ እና የሳንኩራ ወረዳ ከተማና ቤቶች ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የረግዲና ማዞሪያ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ ሀላፊ ተገኝተዋል። ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎ ‎

  • በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአረጋዊያንና ለአቅመ ደካሞች ለተሰሩ የቤት ግንባታዎች የሚውል የቆርቆሮ ድጋፍ ተደረገ ‎ ‎ሐምሌ 23/2018ዓ/ም ሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎የሳንኩራ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚሰራውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ‎ ‎ተቋሙ በዛሬው ዕለትም በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተገነቡ ላሉ የአረጋዊያንና የአቅመ ደካማ የመኖሪያ ቤቶች የቤት ክዳን ቆርቆሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ‎ ‎ በድጋፍ ፕሮግራሙ በሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ‎ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘይኔ አህመድና የሳንኩራ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙደስር አማን ተገኝተው ድጋፉን ለግለሰቦች አስረክበዋል ፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎

  • የሳንኩራ ወረዳ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስፈፃሚ ሴክተር መስሪያቤቶች የ12 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት ግመገማ መነሻ በየዘርፉ በመሆን በየደረጃው በተሰሩ ተግባራት ዙሪያ የመስክ ምልከታ አካሄዱ ‎ ‎ሐምሌ 23/2018ዓ/ም ሳንኩራ ኮሙኒኬሽን ‎ ‎የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎች በ2018 በጀት ዓመት ታቅደው የተከናወኑ የ12 ወራት ዝርዝር የአፈጻጸም ተግባራትን መነሻ በማድረግ የአስፈጻሚ መስሪያቤቶችን ሪፖርት ሲገመግም ቆይቶ በዛሬው ዕለት , በተለያዩ ቀበሌዎች በመዟዟር የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡ ‎ ‎ ቋሚ ኮሚቴዎች ባካሄዱት የመስክ ምልከታ ፤ በጀጀቢቾ ሰያቶ ቀበሌ የወጣቶች ማዘውተሪያ ስፍራና በፌደራል ውሃ ሚንስትር መስሪያ ቤት ተቆፍሮ የወጣ ውሃና የመስኖ ልማት፣ በጀጀቢቾ ሰያቶ ቀበሌ የተሰራ የ17 ኪ/ሜ የመንገድ ዝርጋታ ኢንሼቲፍ ስራ ፣ በጀጀቢቾ ለምለም እየተሰራ ያለ የኮሪደር ልማት እና በጉርባዬ እንጃሞ አገልግሎት የጀመረው የድልድይ ግንባታና በገተም ጉርባዬ የፖሊስ ማዕከልን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ‎ ‎በዕለቱም በጀጀቢቾ ለምለም ቀበሌ የኮሪደር ልማት መሬት የችግኝ ተከላ አካሂዷል፡፡ ‎ ‎ ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎

  • ‎"በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል  የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል ‎ ‎ሐምሌ፣22/2018 ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን ‎ ‎ በሳንኩራ ወረዳ ወጣቶች እና የሴቶች ክንፍ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት በተለያዩ መስኮች አጠናክረው አስቀጥለዋል፡፡ ‎ ‎ማህበራቱ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ለማድረግ እንዲረዳ የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ገበያን ምክንያት በማድረግ ገቢ የማሰባሰብ ስራ አካሂደዋል፡፡ ‎ ‎የሳንኩራ ወረዳ የወጣት እና የሴት አደረጃጀቶች በጋር በመቀናጀት ፣ ስራ አስፈፃሚዎች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማስተባበር ለወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ተግባር አከናውነዋል። ‎ ‎የቁሳቁስ ማሰባሰብ መርሃ-ግብር በክረምት ወራት የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና በሌሎች አካባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው። ‎ ‎በማሰባሰብ ሂደቱ ላይ የተሳተፉት የስራ አስፈፃሚዎች ፣ በጎ ፈቃድ ወጣቶችና የአደረጃጀት መሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ‎ ‎ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇 ‎ ‎📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs ‎ ‎📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/ ‎ ‎📌 የቴሌግራም Link፦ ‎https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk ‎ ‎📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu ‎ ‎📌 ዩቲዩብ፦ ‎https://www.youtube.com/@sankuratube ‎ ‎📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA ‎ ‎📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19 ‎