tgindex
Mereja🇪🇹 ታማኝ ኢትዮጵያዊ መረጃ 🇪🇹🇪🇹

Mereja🇪🇹 ታማኝ ኢትዮጵያዊ መረጃ 🇪🇹🇪🇹

Статистика

Te09

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
27
Всего постов
118
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
384
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
50
40 постов
Вовлечённость
13,0%
к подписчикам
Постов в день
3,9
всего 118
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
47
1/48двое суток
53
1/72трое суток
58

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ግብፅ በመካው ስምምነት ላይ እንዳትካተት ሳኡዲ አረቢያ ተቃውሞ ማቅረቧ ተዘገበ፡፡ ባለፈው ሳምንት ሳኡዲ አረቢያ፣ ቱርክና ፓኪስታን ‹‹የመካ ስምምነት›› የተሰኘ ወታደራዊ ስምምነት መፈፀማቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ስምምነት ውስጥ ግብፅ እንዳትካተት ሳኡዲአረቢያ ተቃውሞ ማሰማቷን ሚድል ኢስት አይ ዘግቧል፡፡ 3 ምንጮቹን በዋቢነት የጠቀሰው ዘገባው እንዳለው በስምምነቱ ውስጥ ግብፅ እንድትካተት ቱርክ ከፍተኛ ግፊት ማድረጓን ገልፆ ይሁን እንጂ የሳኡዲ ባለስልጣናት ‹‹ቢያንስ ለጊዜው መቀላቀል የለባትም›› የሚል አቋም ማንፀባረቃቸውን አስታውቋል፡፡ እንደዘገባው የሳኡዲ ተቃውሞ የመነጨው በሪያድና በካይሮ መካከል ያለው ውጥረት በመባባሱ የተነሳ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ፕሬዝደንት አል ሲሲ ስልጣን ከያዙ በኋላ ሳኡዲ አረቢያ ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን የጠቀሱት የጋዜጣው ምንጮች የካይሮ ኢኮኖሚ እንዲያገግም መጀመሪያ የሰጠችው 25 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር አውስተዋል፡፡ ነገር ግን ለዚህ ድጋፍ ተገቢነት ያለው ምላሽ ከካይሮ አለማግኘቷን ጠቅሰዋል፡፡ ሳኡዲ አረቢያ ለአመታት ከየም ሀውቲ ታጣቂዎች ጋር ባደረገችው ጦርነትና በኢራን ጦርነት ወቅትም ቢሆን ግብ የነበራት አቋም ‹‹አነስተኛና አስተማማኝ ያልሆነ›› በመሆኑን የገለፁት ምንጮቹ እንዲሁም ካይሮ በብዛት ለዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ የምታሳየው ‹‹መገዛት›› ሳኡዲዎችን እንዳስከፋ አስረድተዋል፡፡

  • ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞችን አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ በአዲስ አበባ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረጉ ተነገረ በከ5 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮን ጨምሮ ሌሎች ቅጣቶችን የሚያስከትለው ሴት መስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ለአሐዱ ሬድዮ አስታውቋል። በ2017 ዓ.ም. ህዳር ወር ላይ በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የወጣው ደንብ ቁጥር 178/2017፤ የደረት ክፍልን ያልሸፈነ ሸሚዝ፣ ከጉልበት በላይ የሆነ ጉርድ ቀሚስ እና ከጋብቻ ቀለበት ውጪ በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ጌጣጌጥ ማድረግን ይከለክላል። የማኅበሩ መስራች እና ስራ አስፈጻሚ አባል ናፍቆት ጌታሁን፤ "በአንዳንድ ተቋማት የመስተንግዶ ሰራተኞች እንዲለብሱ የሚገደዱት መለያ ልብስ (ዩኒፎርም) ከባህል ያፈነገጡ ነበሩ" ብለዋል። ይህንን ለማስተካከልም ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ደንቡ እንዲጸድቅ ግፊት አድርጓል። አሁን ላይ ደንቡ ጸድቆ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ ተግባራዊ ያልተደረባቸው ቦታዎች ካሉ ከመንግስት ክትትል በተጨማሪ ማኅበሩም አፈጻጸሙን እንደሚከታተል ተናግረዋል። መመሪያው ያልተገበሩ የማኅበሩ አባላት ሲገኙ ለአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ሪፖርት እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን የቀረበ ሪፖርት እንደሌለ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት በባር፣ በሬስቶራንት እና በሆቴሎች የሚለበሱ መለያ ልብሶች ጨዋነትን በጠበቀ መልኩ እንዲዘጋጁ እየተደረገ ነው ተብሏል።(አሐዱ ሬዲዮ)

  • #Sudan #NationalDialogue የሱዳን ጦር አዛዥ ለብሔራዊ ምክክር ይፋ ያልተደረገ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ። የሱዳን ጦር አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን፣ በሀገሪቱ የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ ብሔራዊ ምክክር ለማካሄድ ከፖለቲካ እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮችና ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር ይፋ ያልተደረገ ውይይት ማድረጋቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። በውይይቱ የተሳተፉ ወገኖች ለብሔራዊ ምክክር የሚያመች ሁኔታ ለመፍጠር በተወሰኑ ተግባራዊ እርምጃዎች መስማማታቸው ተገልጿል። ከእነዚህም መካከል በፖለቲካ ተቃዋሚዎች ላይ የሚደረጉ የሚዲያ ዘመቻዎችን ማቆም እና በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ የተመሰረቱ የሞት ቅጣት ሊያስከትሉ የሚችሉ ክሶችን ማቋረጥ ይገኙበታል። በተለይም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የሚመራው የሱዳን ፖለቲካ ጥምረት አባላትን ጨምሮ በበርካታ የፖለቲካ ተዋናዮች ላይ ክሶች መቅረባቸው ተጠቅሷል። ክሶቹም ከጦርነት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች፣ ጦርነትን ማነሳሳት እና ሕገ መንግሥቱን ማፍረስ የሚሉ ክሶችን ያካትታሉ። ለብሔራዊ ምክክር ከተለያዩ ወገኖች የተውጣጡ፣ በሰፊው ተቀባይነት ያላቸው ገለልተኛ ሰዎችን ያካተተ የዝግጅት ኮሚቴ እንዲቋቋም በውይይቱ ተስማምተዋል። ኮሚቴው የምክክሩን ተሳታፊዎች፣ አጀንዳ፣ ቦታና ጊዜ እንዲሁም የቀጠናውና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችን የመጋበዝ ሂደት እንደሚወስን ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም አል-ቡርሃን ከፖለቲካ ቡድኖች መሪዎች፣ ከባህላዊ መሪዎች፣ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከአካዳሚ ምሁራን ፣ ከተለያዩ ባለሙያዎች እና ከተቃውሞ ኮሚቴዎች ተወካዮች ጋር ስብሰባዎች ማድረጋቸው ተጠቁሟል። ዓላማውም ብሔራዊ መግባባትን ማጠናከርና ሁሉም የሚስማማበት ብሔራዊ ፕሮጀክት ላይ መድረስ መሆኑ ተገልጿል። በሌላ በኩል፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ ኢጋድ እና የአረብ ሊግን ያካተተው  ቡድን በሱዳን የፖለቲካ ውይይት ለማስጀመር እየሰራ ቢሆንም፣ በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ባሉ ልዩነቶች ምክንያት እስካሁን ተጨባጭ ስምምነት ማምጣት አልቻለም። በተለይም በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ውይይት በሱዳን የፖለቲካ ቡድኖች መካከል ባለው አለመግባባት ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱ ተዘግቧል። የሱዳን ብሔራዊ ምክክርን ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ ያለው የሱዳን ጦር እና ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) የሚያደርጉት ጦርነት ሦስተኛ ዓመቱን በያዘበት ወቅት ሲሆን፣ የታቀደው ብሔራዊ ምክክር ጦርነቱን ለማስቆምና ወደ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመሸጋገር ዋነኛ የፖለቲካ መድረክ ይሆናል ወይስ አዲስ የፖለቲካ መካረር ይፈጥራል የሚለው ጉዳይ ይጠበቃል። መረጃው የአልጀዚራ ነው።

  • የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሱዳን ጦር በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች የድሮን ጥቃት ፈፀመ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በምህጻሩ (RSF) የሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱምን ጨምሮ የሱዳን ጦር በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ ከተሞች ላይ ዛሬ በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቃት አድርሷል። የዓይን ምስክሮችና የጦር ምንጮች እንዳሉት የዛሬው ጥቃት ለወራት ከተፈጸሙት ጥቃቶች በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው። ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ኻርቱምን ፣ በኮርዶፋን የምትገኘው ኤል ኦቤይድ እና የሰሜን ሱዳን ከተሞችን አትባራን እና ኤል ዳመርን ብዛት ባለቸው ድሮኖች መደብደቡን የሱዳን ጦር ምንጭ ተናግረዋል። የሱዳን ጦር የፈጥኖ ደራሹን ኃይል አስወጥቶ መልሶ የያዛት እና ከዚህ ቀደምም የድሮን ጥቃቶች ዒላማ የሆነችው ካርቱም ለወራት አንፃራዊ መረጋጋት ሰፍኖባት ነበር። በኻርቱም ጥቃቱ የደረሰው ከማለዳው 11 ሰዓት ላይ እንደነበር በወቅቱም ከኦምዱርማን በስተሰሜን በሚገኘው ዋዲ ሴይዲና ከተባለው የሱዳን ጦር ሰፈር በኩል ደግሞ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳይሎች ድምጽ መሰማቱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

  • የአሜሪካ ሴኔት ለ32 የአፍሪካ ሀገራት የሚሰጠውን የአጎዋ የንግድ ፕሮግራም ለማራዘም ወሰነ የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት የአፍሪካ የእድገትና የዕድል ስምምነትን ለሁለት ዓመታት እንዲራዘም ያጸደቀ ሲሆን፤ ይህም ብቁ ከሆኑ ሀገራት የሚገቡ ከ1 ሺህ 8መቶ በላይ ምርቶች እስከ ታህሳስ 2028 ድረስ ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲገቡ ያስችላል። ለ25 ዓመታት የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ ግንኙነት መሰረት ሆኖ የቆየው አጎዋ፤ አሜሪካ 32 ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጡ መኪናዎችን፣ ልብሶችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ከቀረጥ ነፃ እንድትገዛ ዕድል ሰጥቷል። አሁን ያለው ስምምነት በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሊያበቃ የነበረ በመሆኑ፤ ይህ ማራዘሚያ በአሜሪካ የኤክስፖርት ንግድ ላይ ለሚደገፉ የአፍሪካ የንግድ ተቋማት ትልቅ እፎይታ ሆኗል። ለማራዘሚያው መሳካት ድጋፍ ያደረጉት የአሜሪካው ሴናተር ራፋኤል ዋርኖክ፤‹‹ይህ ውሳኔ የዕለት ተዕለት ዕቃዎችን ዋጋ ከመቀነሱም በላይ፤ የዓለም አቀፍ አጋሮቻችንን ኢኮኖሚ በማረጋጋት የሀገራችንን ብሄራዊ ደህንነት ያሻሽላል›› ብለዋል።

  • ከሰሜን ኮሪያ የተተኮሰው ሚሳኤል የቀጣናውን ውጥረት አናግቷል   አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ሊያካሂዱት ካዘጋጁት ግዙፍ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ሰሜን ኮሪያ ሌላ አዲስ የባሊስቲክ ሚሳኤል በማስወንጨፍ ቀጣናውን አስበርግጋለች።  የደቡብ ኮሪያ እና የጃፓን ወታደራዊ ባለስልጣናት እንደገለፁት፤ ውጥረት በነገሰበት የኮሪያ አካባቢ የተደረገው ይህ ድርጊት አዲስ የፖለቲካ እና የደህንነት ስጋት ደቅኗል።   የፒዮንግያንግ አስተዳደር ሚሳኤሉን የተኮሰው ከምስራቃዊ የወንሳን የባህር ዳርቻ ሲሆን፤ የጦር መሳሪያው በምስራቅ ባህር (የጃፓን ባህር) ላይ ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ተጉዞ አርፏል።    ይህ ድርጊት አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ "ኡልቺ ፍሪደም ሺልድ" የተሰኘውን አመታዊ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመጀመር በሚዘጋጁበት ወቅት መከናወኑ ድንገተኛ እንዳልሆነ ይነገራል።  ሰሜን ኮሪያ እነዚህን የጋራ ልምምዶች ሀገሬን ለመወረር የሚደረጉ ማደናገሪያዎች ናቸው በማለት አጥብቃ የምትቃወም ሲሆን፤ የአሁኑ ማስወንጨፍም ለዋሽንግተን እና ለሴኡል የተላከ ግልፅ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

  • ትራምፕ ፊፋ ኢንፋንቲኖን ከኃላፊነቱ ካነሳ ትልቅ ስህተት እንደሚሰራ አስጠነቀቁ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊፋን ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖን ሰኞ ዕለት የደገፉ ሲሆን፣ የእግር ኳስ የበላይ አካሉ እሳቸውን ከቦታቸው ካነሳ ትልቅ ስህተት እንደሚሰራ አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስራ ቦታ የፍቅር ግንኙነት ፈጽመዋል በሚል በተነሳባቸው ውንጀላ እና በከሸፈ የግል ኢንቨስትመንት ዕቅድ ምክንያት በጠንካራ ትችት ውስጥ በሚገኙት የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ላይ ያላቸውን ድጋፍ ሰኞ ዕለት ገልጸዋል። ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ ፊፋ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖን ለመተካት የሚያስብ ከሆነ ትልቅ ስህተት ይሰራል ብለዋል። ጣሊያናዊ-ስዊዘርላንዳዊውን ህግ አዋቂ ድንቅ ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን እስካሁን ከተካሄዱት ሁሉ በአራት እጥፍ የበለጠ ስኬታማ የሆነውን ዓለም ዋንጫ መርተዋል ሲሉ አክለዋል። እሱ ከሄደ፣ ድርጅቱ ዳግመኛ እንደዚህ ስኬታማ ወይም አትራፊ ሊሆን አይችልም። ትራምፕ ለኢንፋንቲኖ የሰጡት ድጋፍ፣ ከካናዳ እግር ኳስ ማህበር እንዲሁም ከመካከለኛው አሜሪካ እና ከካሪቢያን እግር ኳስ ድርጅቶች ጋር በመሆን የፊፋን መሪ የነቀፈ መግለጫ ካወጣው የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቋም ጋር ይጋጫል። በመጪው መጋቢት ወር ለድጋሚ ምርጫ የሚቀርቡት ኢንፋንቲኖ የተሰነዘሩባቸውን የጥፋተኝነት ውንጀላዎች አስተባብለዋል። ፊፋ በበኩሉ ውጥረት ውስጥ የሚገኙትን ፕሬዚዳንቱን የደገፈ ሲሆን፣ የተሰነዘረባቸውን ትችትም ተቋሙን ለማዳከም በአንዳንዶች በኩል የሚደረግ የተቀናጀ ጥረት ሲል ጠርቶታል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ የበላይ አካል (ኮንሜቦል) ጨምሮ ሌሎች የእግር ኳስ ድርጅቶች ኢንፋንቲኖን በመደገፍ ረገድ የትራምፕን አቋም ይጋራሉ።

  • የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በስፔስኤክስ አክሲዮን ዕድገት ምክንያት ዳግም ከ800 ቢሊዮን ዶላር በላይ አለፈ የስፔስኤክስ አክሲዮን በ15.8 በመቶ ማሻቀቡን ተከትሎ የኩባንያው የገበያ ዋጋ 1.75 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህንን ተከትሎም የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ 817 ቢሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም በፎርብስ መጽሔት 823.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል። የቅርብ ጊዜው የገበያ ንቅናቄ የመጣው ኩባንያው ካስመዘገበው ጠንካራ የሩብ ዓመት የገቢ አፈጻጸም በኋላ ሲሆን፣ የኩባንያው ገቢ ከታሰበው በላይ በመጨመር 7.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የኦፕሬቲንግ ኪሳራውም ወደ 541 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማለት ችሏል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት (AI) መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የ18.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ቢያደርግም፣ የባለሀብቶች እምነት ከፍተኛ ሆኖ ቀጥሏል። የስታርሊንክ ሳላይት ኢንተርኔት ገቢ በ66 በመቶ አድጎ 4.29 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የክላውድ እና ኤአይ ክፍል ገቢ ደግሞ የ247 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል። ስፔስኤክስ እጅግ ፈጣን ዕድገት በማሳየት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በታህሳስ ወር ዓመታዊ ገቢውን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና እስከ 2030 ድረስ ደግሞ 1 ትሪሊዮን ዶላር ገቢ ለማስመዝገብ ግብ ማስቀመጡ ተመላክቷል።

  • ሶስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ! 🔴 ቡድኑ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ 7 የቡድኑ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሉም 🔴 የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ብቻ ሳትሆን በርካቶች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማም ሆና ተመዝግባለች ✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት) በአሜሪካ ኦሪገን ዩጂን ሲካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች 21ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቁ ይታወሳል። ወደ ውድድሩ ስፍራ የተጓዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣3 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳሊያ ማግኘቷም ይታወቃል። ከወደ ኦሪገን ከደቂቃዎች በፊት የደረሠን አስደንጓጭ ዜና ለሻምፒዮናው ከተጓዙት የልዑኳን ቡድን አባላት መካከል ሰባቱ ፖሬትላንድ ላይ መኮብለላቸው ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን በአሁን ሠዓት ከፖርትላንድ ተነስቶ ወደ ቺካጎ አየር ማረፊያ እየተጓዘ ሲሆን እነዚሁ ሰባቱ የቡድኑ አባላት ከልዑኳን ቡድኑ ተለይተው መቅረታቸውን ነው ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ያረጋገጠችው። እንደ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ከሄዱት አራት አሠልጣኞች ሶስቱ ከቡድኑ ጋር ባለመመለሳቸው በአሁን ሠዓት ወደ ኢትዮጵያ በመገስገስ ላይ በሚገኘው አውሮፕላን ውስጥ አንድ አሠልጣኝ ማለትም አሠልጣኝ መሠረት  ብቻ እንደሚገኝ ነው ምንጮቻችን የገለፁልን። አትሌቶቻችን በተመለከተ አራት አትሌቶች እንደኮበለሉ የገለፁልን የመረጃ ምንጮቻችን በወኪንግ፣በ800፣በ5ሺ እና በ3ሺ መሠናክል ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ከቡድኑ ጋር አብረው እንዳልተመለሱና እንደኮበለሉ ነው የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው የገለፁልን። የአትሌቶቹና የአሠልጣኞቹ ሙሉ ስም የደረሳት ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ለቤተሠቦቻቸውና ለደህንነታቸው ስትል የሁሉንም ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥባለች። የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ቤቻ ሳትሆን በርካታ አትሌቶች፣አሠልጣኞችና  አመራሮች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማ ሆና ተመዝግባለች።

  • ግልገል በለስ‼️ በጋራ ግልገል በለስ ከተማን ለመቆጣጠር ሞክረዋል - የመተከል ዞን አስተዳደር‼️ የመተከል ዞን አስተዳደር የፋኖ ሀይሎችና የጉሙዝ ሀይሎች ግልገል በለስ ከተማን ዛሬ ማለትም ነሐሴ 5/2018 ከንጋቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ ለመቆጣጠር ሞክረው እንደነበረ ገለፀ። የዞኑ አስተዳደር ይሄ ኦፕሬሽን እንዳልተሳካና ከተማውም ወደ ቀድሞ ሰላሙ መመለሱን አስታውቋል። በከተማዋ ዋና መንገድ መድፍ ጭምር ሲንቀሳቀስ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ የገለፁ ሲሆን ጠዋት አካባቢ በከተማ መናኸሪያ ውስጥ ፈንጂ በማፈንዳት በርካታ ተሳፋሪዎች እንደተጎዱ እና እንዲሁም 10 ሰዎች እንደሞቱ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። ተጎጂዎች ፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀውልናል።

  • ኢራን የመካ ስምምነት የቀጣናውን ከአሜሪካ መራቅ የሚያሳይ ነው አለች፡፡ ኢራን በሳዑዲ ዓረብያ፣ በፓኪስታን እና በቱርክ መካከል የተፈረመው የሶስትዮሽ የመከላከያ ስምምነት አገራት ስለ አሜሪካ ያላቸውን አመለካከት መለወጡንና በራሳቸው የደኅንነት መዋቅር ላይ መተማመናቸውን የሚያሳይ ነው ስትል ገልጻለች። ቴህራን አክላም ስምምነቱን እንደ ስጋት ለመመልከት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለ አስታውቃለች። ቱርኪ ቱደይ እንደዘገበው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ ይህንን አስተያየት የሰጡት ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ቃል አቀባዩ አሜሪካን በማመላከት “ደኅንነት ከሐሰተኛ ደላሎች የሚገዛ ሸቀጥ አለመሆኑን” የቀጣናው ሀገራት ተገንዝበዋል ብለዋል። እስማኤል አክለውም ኢራን ከሳዑዲ ዓረብያ፣ ከፓኪስታን እና ከቱርክ ጋር ያላትን “ጥልቅ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እና የሥልጣኔ ቁርኝት” በመጥቀስ ስምምነቱ በቴህራን ላይ ያነጣጠረ ነው ብሎ ለማሰብ “ምንም ምክንያት የለም” ብለዋል።

  • የትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ 11 አዳዲስ የሙያ ትምህርት ዓይነቶችን ይፋ አደረገ ​የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር የሚተገበሩ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ፣ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ መመሪያ አስተላለፈ። ​አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ «የሙያና ቴክኖሎጂ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜ ጋር በተመጣጠነ መልኩ ይሰጣል» በሚለው አቅጣጫ መሠረት፣ በ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ እየተደረገ ይገኛል። በተጨማሪም በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በ12 የሙያ ዓይነቶች ትምህርት እየተሰጠ እንደሆነ ተገልጿል። ​ሚኒስቴሩ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሚተገበሩት 11 ተጨማሪ የሙያ ዓይነቶች የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ-ትምህርቶችን፣ እንዲሁም የ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችንና የመምህራን መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል። ​ለዚሁ ትግበራ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፦ 👉​ዝርዝር ዕቅድና በጀት በመያዝ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤትና በተማሪዎች ደረጃ እንዲያስመርጡ፣ 👉​የሙያ መምህራንን እንዲቀጥሩና እንዲያሰለጥኑ፣ 👉​የመማሪያና ማስተማሪያ ግብዓቶችን እንዲያሟሉ፣ ​የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠንና የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ​የአዲሶቹ 11 የሙያ ዓይነቶች ዝርዝር፦ 👉​ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ 👉​አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ 👉​አልባሳት ቴክኖሎጂ 👉​ሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ​ቧንቧ ሥራ 👉​ሶፍትዌር ማበልጸግ 👉​ሰብል አመራረት 👉​ጤና ክብካቤ አገልግሎት 👉​ሆቴል አገልግሎት 👉​ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት 👉​ምግብ ዝግጅት

Mereja🇪🇹 ታማኝ ኢትዮጵያዊ መረጃ 🇪🇹🇪🇹 — tgindex