tgindex
FOR መረጃ Abeni News

FOR መረጃ Abeni News

Статистика

የስፖርት የፖለቲካ የተለያዩ ዜናዎችንና መረጃዎችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ።

Последний пост
24 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
149
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
367
−2 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
40
40 постов
Вовлечённость
10,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 149
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋርኛ ቋንቋ ያዘጋጀው "ማንነትና ራስን በራስ ማስተዳደር" ላይ መሠረት ያደረገው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክን ሙሉውን ለማየት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። https://youtu.be/vlItjNo-3DM?si=aCHuX3XzOfVznd_l

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋርኛ ቋንቋ ያዘጋጀው "ማንነትና ራስን በራስ ማስተዳደር" ላይ መሠረት ያደረገው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ። ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ላይ ከምሽቱ 2:30 ላይ ይጠብቁን።/ https://web.facebook.com/share/v/1G1PQHfkne/

  • видео или голосовое, без подписи

  • " ወደ ሀገራችሁ ተመልሳችሁ አመልክቱ " - አሜሪካ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የመኖሪያ ፈቃድ የሚጠይቁ ስደተኞች በመጀመሪያ ከአሜሪካ እንዲወጡ ሊያስገድድ ነው። የአሜሪካ የኢሚግሬሽን አገልግሎት መስሪያ ቤት (USCIS) በሀገሪቱ ውስጥ ሆኖ የመኖሪያ ፍቃድ (ግሪን ካርድ) የማግኛ ሂደትን የሚገድብ እና አመልካቾች ከሀገር ወጥተው እንዲያመለክቱ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። ይህ ውሳኔ ጊዜያዊ ቪዛ ይዘው በአሜሪካ የሚገኙ ግለሰቦች የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻቸውን ከሀገሪቱ ወጥተው በሀገራቸው ወይም በሌላ ሶስተኛ ሀገር በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ወይም ቆንስላዎች በኩል እንዲያመለክቱ የሚያያስገድድ ነው። - የቪዛ ሕግ መጣስ፣ - የቆይታ ጊዜ ማራዘም፣ - ያለፈቃድ መስራት እና ማጭበርበር ደግሞ እጅግ ጥብቅ ምርመራና ቅጣት ያስከትላል ነው የተባለው። በፊት ያለውን ሁኔታ በመቀየር በአሜሪካ ውስጥ ሆኖ የነዋሪነት ሁኔታን ማስተካከል ፍፁም መብት ሳይሆን እንደ ሁኔታው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ነበር ብሏል። ተቋሙ ፤ " ከአሁን ጀምሮ በአሜሪካ በጊዜያዊነት ያለ እና ግሪን ካርድ የሚፈልግ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ከተለዩ ልዩ ሁኔታዎች በስተቀር ለማመልከት ወደ ትውልድ ሀገሩ መመለስ አለበት " ሲል ገልጿል። ምንም እንኳ መመሪያው ለባለ ሁለትዮሽ ፍላጎት / Dual Intent/ ቪዛዎች መጠነኛ ልዩ ሁኔታዎችን ቢያስቀምጥም ሙሉ ዋስትና እንደማይሰጥ በግልጽ አስታውቋል። መመሪያው እንደ ተማሪዎች፣ ቱሪስቶች እና ሌሎች ጊዜያዊ ቪዛ የያዙ ሰዎችን እንዲሁም በህጋዊ መንገድ ገብተው የቪዛ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ጨምሮ በአሜሪካ ዜግነት ባላቸው የትዳር አጋሮቻቸው ወይም አሰሪዎቻቸው አማካኝነት በሚቀርቡ ስፖንሰርሺፖች ግሪን ካርድ ለማግኘት ከመሞከራቸው በፊት አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሊያስገድድ ይችላል። መረጃው የሲቢኤስ ኒውስ ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • ኬንያ ከነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ ወደ 100 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪኖች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ወሰነች። ከሰሞኑን በኬንያ የሀገሪቱ መንግስት የነዳጅ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው እንዲሁም የትራንስፖርት ስራ ማቆም አድማ መደረጉ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ መግለጫ ሰጥተው ነበር። ሩቶ፥ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭት ሳቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅ ቀውስ በኬንያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን ገልጸዋል። መንግሥት ቀደም ሲል የነዳጅ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም VATን ከ16 በመቶ ወደ 8 በመቶ ዝቅ ማድረጉን ገልጸው በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ የታክስ ቅናሽ ማድረግ የመንግሥትን የገቢ ምንጭ በእጅጉ ስለሚጎዳና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ተግባራዊ ሊሆን እንደማይችል ገልጸዋል። " በመንግሥት በኩል የሚደረገው የዋጋ ማስተካከያ ገደብ አለው ነው " ያሉት። ምንም እንኳን ተጨማሪ የታክስ ቅናሽ ባይኖርም መንግሥት በሚቀጥለው ወር በሚደረገው የዋጋ ክለሳ የናፍጣ ዋጋን በ10 የኬንያ ሺሊንግ ለመቀነስ እንደወሰነ  አስታውቀዋል። መንግስታቸው፥ በነዳጅ ዋጋ ንረት ሳቢያ ለተፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ጫና የፔትሮሊየም ፈንድንና የታክስ ቅነሳን በመጠቀም ከ28 ቢሊዮን ሺሊንግ በላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አመልክተው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ወደ ኢ-ሞቢሊቲ (E-mobility) ትኩረት ማዞር እንደሚገባ ገልጸዋል። በዚህ መሰረት ለዘላቂ መፍትሄ የሚውሉ የመጀመሪያ 100 ሺ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት ፣ የትራንስፖርት ዘርፉን ለመደገፍ የሚያስችሉ አዳዲስ የሕግ ማዕቀፎችንና የብድር እፎይታዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ገልጸዋል። የኬንያ መንግሥት 3,000 (ሶስት ሺህ) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደህንነትና አስተዳደር አገልግሎት ማዘዙ ተሰምቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • #ምርጫ2018 በሙሰኛ ባለሥልጣናት እና ፖለቲከኞች ላይ "የሞት ቅጣት" እንዲደነገግ የሚል አጀንዳ ይዘው የቀረቡት እጩ ! ⚫ " የሕዝብ ሀብት ዘረፋ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ መታየት ጀምሯል ! " በሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ኮልፌ ቀራንዮ የምርጫ ክልል 24ን ወክለው በግል እጩነት ለሕ/ተ/ም/ቤት የቀረቡት ጠበቃና የሕግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ፤ ለከባድ የሙስና ወንጀል የሞት ቅጣት እንዲደነገግ የሚጠይቅ አጀንዳ ይዘው መቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ጠበቃ ወንድሙ በፖለቲካው መድረክ ለመሳተፍ የወሰኑበት ዋና ምክንያት፣ ፖለቲካው ሙሉ በሙሉ ለሕግ የበላይነት ተገዥ እንዲሆንና መንግስት የሚያወጣቸው ሕጎች ፖለቲከኞችን በሚመጥን መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል። ​በተለይም ሀገሪቱን እያመሰ ያለውን የሙስና ወንጀል ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት እጩው፤ በሙስናና በሕዝብ ሀብት ዝርፊያ የተሳተፉ የመንግስት ባለሥልጣናትን፣ ፖለቲከኞችንና ሌሎች ግለሰቦችን በሞት የሚያስቀጣ ሕግ እንዲወጣ አቋም ይዘዋል። ጠበቃ ወንድሙ አቋማቸውን ለማስረዳት እንደ ቻይና እና ጃፓን ያሉ ሀገራት የሞት ቅጣትን ለሙስና ወንጀል እንደሚጠቀሙበት ያነሱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የህዝብ ሃብት ዘረፋ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ መታየት መጀመሩን በመተቸት ይህንን ለመግታት የሞት ቅጣት መፍትሔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ጠበቃው ከዚህ አጀንዳቸው በተጨማሪ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39 (1) " በማንኛውም ጊዜ እስከ መገንጠል " የሚለው እንዲሰረዝ ፤ እንዲሁም የቤተሰብ ሕግ ትዳርን በሚያከብር መልኩ እንዲሻሻል ለማድረግ እንደሚታገሉ አመልክተዋል። ​ተመራጭ ከሆኑ በምርጫ ክልላቸው ቋሚ ቢሮ በመክፈት በሳምንት አንድ ቀን የዜጎችን ጥያቄ በቀጥታ እንደሚቀበሉ ቃል የገቡት አቶ ወንድሙ ፤ ቀደም ሲል በሙያቸው ከ600 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ነፃ የጥብቅና አገልግሎት መስጠታቸውን አስታውሰዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • " ከ5 ሺህ በላይ ምዕመናን እና በግቢው የሚማሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት መንገድ ነው የተዘጋው " - ቤተክርስቲያኗ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሙዱላ ከተማ የምትገነው መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ላለፉት 40 ዓመታት ስትጠቀምበት የነበረው የመግቢያና መውጫ መንገድ በግለሰብ ግንባታ መዘጋቱን ተከትሎ የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ አቶ አዳነ አዋኖ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅርበዋል። አቶ አዳነ እንደሚሉት፥ ቤተክርስቲያኗ በአራቱም አቅጣጫ እንዲያዋስናት ተደርጎ በተሰራው የከተማው መሠረታዊ ፕላን መሰረት ለዓመታት አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች። ይሁን እንጂ ማዘጋጃ ቤቱ ባወጣው አዲስ መዋቅራዊ ፕላን መንገዱ መዝጋቱን እንዲሁም ቤተክርስቲያኗን ሳያማክር ቦታውን ለግለሰብ መስጠቱን በማመልከት ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይከራከራሉ። ከ5 ሺህ በላይ ምዕመናን እና በግቢው የሚማሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት ይህ መንገድ መዘጋቱ ለከፍተኛ ችግር እንደዳረጋቸውና የቤተክርስቲያኗ አቤቱታ ከ2017 ዓ.ም. ታህሳስ ወር ጀምሮ ለሚመለከታቸው አካላት ቢቀርብም " ይታገሱ ይከፈታል " ከሚል ምላሽ ውጪ መፍትሄ እንዳልተገኘላቸው አስረድተዋል። ሰብሳቢው በጉዳዩ ላይ ማስረጃ የሚሆኑ ደብዳቤዎች እንዳሏቸውና ጉዳዩ ለረጅም ጊዜ መፍትሔ ሳይበጅለት መቆየቱን ተናግረዋል። አሉን ያሉትንም ሰነዶችም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን ይዞ የሙዱላ ከተማ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ገዳሞን ጠይቋል። አቶ ሀብታሙ ፥ ቦታው ቀደም ሲልም የግለሰቡ ይዞታ እንደነበርና በአዲሱ ፕላን መሰረት መንገዱ መዘጋቱን አብራርተዋል። ይሁን እንጂ ማዘጋጃ ቤቱ የግንባታ እገዳ መጣሉን በመግለጽ፣ ሁኔታዎች እስኪጠሩ ድረስ በቦታው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደማይደረግ ገልጸዋል። ሥራ አስኪያጁ አክለውም " ጫና የሌለበትና እንደ ከተማ አስተዳደርም ሆነ እንደ ልዩ ወረዳ ችግሩን ለመፍታት እየሰራን ነው " በማለት፣ ሁለቱንም አካላት ለማስታረቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ አቶ አዳነ ማዘጋጃ ቤቱ " እገዳ ጥለናል" ቢልም፣ እስካሁን የደረሳቸው ምንም ዓይነት የተጻፈ የእገዳ ደብዳቤ እንደሌለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • #Bloomberg የብሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ (BMIA) ከአዲስ አበባ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ያሰለጥናቸውን 101 የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ባለሙያዎችን አስመርቋል። ተመራቂዎቹ ከሚዲያ፣ ፋይናንስ፣ ኮሙኒኬሽንና ቴሌኮም ዘርፎች የተውጣጡ ሲሆን 30 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው። የአዲስ አበባ ፕሬዜዳንት ​ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ፥ ስልጠናው በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑንና አመልክተዋል። ፕሮግራሙ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመው " ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና ለዴሞክራሲ ስርዓት መሰረት ነው " ብለዋል። ተመራቂዎች ውስብስብ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን ለዜጎች፣ ለባለሀብቶችና ለፖሊሲ አውጪዎች ግልጽ በሆነ መንገድ ተርጉመው ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ፥ የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ከፖለቲካ ዘገባ በተለየ መልኩ ጥንቃቄ የሚፈልግና በቁጥር ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። " በፖለቲካ ውስጥ የፈለጉትን ማለት ይቻላል ሁለት ሲደመር ሁለት አምስት ወይም ሰባት ሊሆን ይችላል በፋይናንስ ዘገባ ግን ሁለት ሲደመር ሁለት የግድ አራት መሆን አለበት " ብለዋል። ሀገሪቱ ወደ ካፒታል ገበያና ዲጂታል ንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት መረጃ የባለሀብቶች መተማመኛ መሆኑን በመግለጽ፣ ባለሙያዎቹ እውቀታቸውን በሃላፊነትና በድፍረት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። ዩኒቨርሲቲዎቹ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መረጃን በማቀናጀት ረገድ ያለውን ሚና በመረዳት ተመራቂዎች ቴክኖሎጂውን ለፋይናንስ ዘገባ ጥራት እንዲጠቀሙበት መክረዋል። የፋይናንስ ዘገባ ስልጠናውን ሲከታተሉ በቆዩ ሙያተኞች የተዘጋጀ " The Business Side " የተሰኘ መጽሄት ይፋ ተደርጓል 👉 https://thebusinessside.concepthub.net/ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • #ምርጫ2018 በሙሰኛ ባለሥልጣናት እና ፖለቲከኞች ላይ "የሞት ቅጣት" እንዲደነገግ የሚል አጀንዳ ይዘው የቀረቡት እጩ ! ⚫ " የሕዝብ ሀብት ዘረፋ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ መታየት ጀምሯል ! " በሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ኮልፌ ቀራንዮ የምርጫ ክልል 24ን ወክለው በግል እጩነት ለሕ/ተ/ም/ቤት የቀረቡት ጠበቃና የሕግ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ፤ ለከባድ የሙስና ወንጀል የሞት ቅጣት እንዲደነገግ የሚጠይቅ አጀንዳ ይዘው መቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ጠበቃ ወንድሙ በፖለቲካው መድረክ ለመሳተፍ የወሰኑበት ዋና ምክንያት፣ ፖለቲካው ሙሉ በሙሉ ለሕግ የበላይነት ተገዥ እንዲሆንና መንግስት የሚያወጣቸው ሕጎች ፖለቲከኞችን በሚመጥን መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል። ​በተለይም ሀገሪቱን እያመሰ ያለውን የሙስና ወንጀል ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት እጩው፤ በሙስናና በሕዝብ ሀብት ዝርፊያ የተሳተፉ የመንግስት ባለሥልጣናትን፣ ፖለቲከኞችንና ሌሎች ግለሰቦችን በሞት የሚያስቀጣ ሕግ እንዲወጣ አቋም ይዘዋል። ጠበቃ ወንድሙ አቋማቸውን ለማስረዳት እንደ ቻይና እና ጃፓን ያሉ ሀገራት የሞት ቅጣትን ለሙስና ወንጀል እንደሚጠቀሙበት ያነሱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የህዝብ ሃብት ዘረፋ እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ መታየት መጀመሩን በመተቸት ይህንን ለመግታት የሞት ቅጣት መፍትሔ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ጠበቃው ከዚህ አጀንዳቸው በተጨማሪ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39(1) " እስከ መገንጠል " የሚለው ድንጋጌ እንዲሰረዝ፣ እንዲሁም የቤተሰብ ሕግ ትዳርን በሚያከብር መልኩ እንዲሻሻል ማድረግ በማኒፌስቷቸው የተካተቱ መሆኑን አመልክተዋል። ​ተመራጭ ከሆኑ በምርጫ ክልላቸው ቋሚ ቢሮ በመክፈት በሳምንት አንድ ቀን የዜጎችን ጥያቄ በቀጥታ እንደሚቀበሉ ቃል የገቡት አቶ ወንድሙ ፤ ቀደም ሲል በሙያቸው ከ600 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ነፃ የጥብቅና አገልግሎት መስጠታቸውን አስታውሰዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ያዘጋጀው "ማንነትና ራስን በራስ ማስተዳደር" ላይ መሠረት ያደረገው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክን ሙሉውን ለማየት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። https://youtu.be/YYoXszCvkdM?si=jBCkQw-3ESyEerm4

  • видео или голосовое, без подписи

FOR መረጃ Abeni News — tgindex