Tikvah- university
Статистика- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Образование
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 390
- 1/48двое суток
- 1 592
- 1/72трое суток
- 1 718
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#JimmaUniversity የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ሥራ ጀምረዋል። አዲስ የተመደቡት ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር)፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲን ላለፋት ሰባት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ካገለግሉት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት የሥራ ርክክብ አድርገዋል። ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ላለፉት ሰባት ዓመታት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ማገልገላቸው ይታወቃል።
#ArsiUniversity አርሲ ዩኒቨርሲቲ የSTEM ፕሮግራም የክረምት ስልጠና ከፍተኛ ውጤት ላላቸው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እየሰጠ ነው፡፡ ሠልጣኞቹ በአሰላ ከተማ ከሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ስልጠናው ተማሪዎቹ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) እውቀታቸውን በማጎልበት የፈጠራ ክህሎታቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው ተብሏል።
#AssosaUniversity አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሦስቱም የክልሉ ዞኖች ለተውጣጡ ከ180 በላይ ተማሪዎች የክረምት የSTEM ማጠናከሪያ ትምህርት እየሠጠ ነው፡፡ ሠልጣኞቹ ከ9ኛ-11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ45 ቀናት የሚቆይ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በዩኒቨርሲቲው የSTEM ማዕከል በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፕሮግራሙ ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው በንድፈ ሐሳብ ያገኙትን ዕውቀት በዩኒቨርሲቲው ቤተ ሙከራዎች በተግባር እንዲያጠናክሩ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል፡፡
#የጤና_ሙያ_ፍቃድ_ፈተና የጤና ሙያ ፍቃድ ፈተና ለመውሰድ እየጠበቃችሁ የምትገኙ ምሩቃን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ ተብሏል። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የመውጫ ፈተና ያለፋችሁ እንዲሁም በድጋሜ የብቃት ምዘና (የሙያ ፍቃድ ፈተና) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ ጤና ባለሙያዎች፣ ለፈተናው ዝግጅት ለማድረግ የሚረዱና ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ የተከለሱ Information Booklets እና Practice Test Booklets ጤና ሚኒስቴር አቅርቧል (ከላይ የተያያዙትን ዚፕ ፋይሎች ይመልከቱ።) 🔔 የአመልካቾች የምዝገባ ጊዜ በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) matching ሥራ ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡ የmatching ሥራው በብቃት ላይ የተመሰረተና የERMP matching አልጎሪዝምን በመጠቀም የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡ Matching አጊኝተው ለሬዚደንሲ የተመደቡ ተማሪዎች ዝርዝር እንዲሁም የስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የማቺንግ ውጤትን ጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡ (ከላይ ተያይዟል) በማቺንግ ውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች ከመጋቢት 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የጥሪ መስመር 952 በሥራ ሰዓት ቅሬታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ በአካል ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው የቅሬታ ደረሰኝ 300 ብር በመክፈል መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ የፕሮግራም ወይም/እንዲሁም የተቋም ለውጥ ጥያቄ እንደማይቀበል አስረድቷል፡፡ ከሚያዝያ 07/2018 ዓ.ም በኋላ ማቺንግ ያገኙ የመጨረሻ እጩዎችን ዝርዝር የሬዚደንሲ ፕሮግራም ለሚሰጡ የሕክምና ትምህርት ቤቶች የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
#ETA በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የተላለፈባቸውን ውሳኔ ተግባራዊ ባላደረጉና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርተው በሚገኙ 52 ተቋማት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ባለሥልጣኑ ጠየቀ፡፡ ባለሥልጣኑ በቀን 16/07/2018 ዓ.ም ለሁሉም ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤቶች፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ለሁሉም ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮዎች፣ ለሁሉም ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ጽ/ቤቶች እና ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጽ/ቤቶች እንዲሁም ለሁሉም ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ በተቋማቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ባለመግባታቸው ምክንያት ከከፍተኛ ትምህርት ሴክተር እንዲወጡ የታዘዙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ተቋማቱ አራት ጊዜ በስልክ እንዲሁም አንድ ጊዜ በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ ጥሪ የቀረበላቸው ቢሆንም የሚጠበቅባቸውን መስፈርት እና ሒደት በማሟላት ከትምህርት ሴክተር ያልወጡ መሆኑን ደብዳቤው ያስረዳል፡፡ በመሆኑም "ተቋማቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ህጋዊነታቸው የተቋረጠ ሰለሆነ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርተው ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እንድታደርጉ እንዲሁም እስካሁን ያደረሱት ጉዳት ካለ በመፈተሽ አስፈላጊ የህግ እርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው" የተቋማቱን ስም ዝርዝር በማያያዝ ባለሥልጣኑ ጠይቋል፡፡ (የተቋማቱ ስም ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡) @tikvahuniversity
#AdigratUniversity ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 167 ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 16ቱ የሕክምና ዶክተሮች መሆናቸው ተገልጿል። የተቋሙ 12ኛ ዙር ተመራቂዎች 121 በመጀመሪያ ዲግሪ እና 46 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። @tikvahuniversity
ትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት በተገኘ ድጋፍ ያሳተማቸውን 23.9 ሚሊዮን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መፅሐፍት ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እያጓጓዘ ነው፡፡ በሀገሪቱ የሚታየውን የተማሪ መፅሐፍት አቅርቦት ችግር ለመፍታት 23.9 ሚሊዮን መፅሐፍት በማሳተም ወደ ሀገር ማስገባቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልፀዋል። መፅሐፍቱ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ ተጠናቀው በመግባት ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የሚሰራጩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መፅሐፍት ተደራሽነትን አንድ ለአንድ ለማድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ከተባባሪ አካላት ባገኘው ድጋፍ ተጨማሪ 40 ሚሊዮን የሚጠጉ መፅሐፍትን አሳትሞ ለክልሎች ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል። ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የታተሙ የ2ኛ ደረጃ መፅሐፍትን ለተማሪዎች አንድ ለአንድ እንዲደርስ ወደ ክልሎች ማሰራጨቱ ይታወሳል። #MoE
የፋይዳ መታወቂያ ያውጡ! ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎቻቸው በሙሉ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) እንዲያወጡ እያደረጉ ነው፡፡ ብሔራዊ መታወቂያው ለምዝገባ፣ ለፈተና እንዲሁም ለተለያዩ የግቢ ውስጥ አግልጋሎቶች ግዴታ እንደሚሆንም እየተገለፀ ነው፡፡ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ፣ ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ለመፈተን፣ የብቃት ምዘና ፈተና (Licensing Exam) ለመውሰድ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና (ESSLCE) ለመውሰድ ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት የግድ እንደሆነ በመንግሥት መገለፁ ይታወቃል፡፡
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለክርስትና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም የገና በዓል ይመኛል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙና በዓሉን ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ ለምታከብሩ ተማሪዎች መልካም በዓል እንመኛለን። Merry Ethiopian Christmas!! መልካም በዓል!!
#ጥቆማ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS) በጅማ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡ ብሪቲሽ ካውንስል ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና የካቲት 28/2018 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የአመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ጀምሯል። ኦንላይን ይመዝገቡ 👇 🔗 ieltsregistration.britishcouncil.org የመመዝገቢያ ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ "IELTS Academic" የሚለውን ይምረጡ፣ "Choose Country/Territory" ከሚለው ስር "Ethiopia" የሚለውን ይጫኑ፣ Jimma የሚለውን የመፈተኛ ቦታ ይምረጡ፣ 7 March 2026 የሚለውን የፈተና ቀን ይምረጡ፣ "Search for Tests" የሚለውን ከመረጡ በኋላ የሚመጡ የፈተና አማራጮችን በማየት "Book Test" የሚለውን ይምረጡ። የኦንላይን ቅፁን በመሙላት አስፈላጊ የግል መረጃዎች፣ የኢሜል አድራሻ እና ሰነዶችን በማስገባት ምዝገባዎን ያጠናቅቁ። ለተጨማሪ መረጃ፦ 0911769560
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈት የስርዓተ ትምህርት የውስጥ ግምገማ አካሒዷል። ፕሮግራሙ በዘርፉ በሀገሪቱ ያለውን የባለሙያ ፍላጎት የሚያሟላ እና ብሔራዊ ስትራቴጂክ ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑ ተገልጿል። ስርዓተ ትምህርቱን የበለጠ ለማዳበርና ፕሮግራሙን ለማስጀመር የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች በግምገማ አውደ ጥናቱ ቀርበዋል።
የጋዜጠኝነት ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች፣ የሚዲያ እና የጋዜጠኝነት ዓይነቶች 👉 የዜና አሰራር እና የቃለመጠይቅ አደራረግ 👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት፣ የማስታወቂያ አሰራር እና የዶክመንተሪ ዝግጅት 👉 የሞባይል እና የዩቲዩብ ጋዜጠኝነት አካቷል፡፡ ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AAU #GAT በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ የተመዘገባችሁና ነገ ሰኞ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም የሚሰጠው የፈተና መርሐግብር ውስጥ ያልተካተታችሁ አመልካቾች መኖራችሁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። እነዚህ አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ 👇 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSc1WoR6gikog5SrwKseX--ocSicMM2-SMTAopi4viYvZBl0QA/viewform?usp=header በመጠቀም የምታገኙትን ቅፅ በፍጥነት እንድትሞሉ ተጠይቋል። ⤴️ የእነዚህ አመልካቾች ፈተና ሰኞ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ከሰዓት እንደሚሰጥ ተገልጿል። ጥያቄ ያላችሁ አመልካቾች በፎረም ህንፃ 4ኛ ወለል በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል እስከ ረፋዱ 5:00 ሪፖርት ማድረግ ይኖርባችኋል። ለፈተናው ምዝገባ ያደረጉበትን የቅበላ ቲኬት እና የቴሌብር ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርብዎታል።
የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 AutoCAD, Revit, እና 3D Max ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ 👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕ የሚሰጥ ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
без подписи
без подписи
без подписи
#AAU #GAT በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ የተመዘገባችሁ አመልካቾች፣ ፈተናው ሰኞ ታህሳስ 27/2018 በጠዋት እና ከሰዓት ፈረቃ ይሰጣል። ከላይ የተያያዘው መርሐግብር ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ምዝገባ ያደረጉ አመልካቾችን ዝርዝር የያዘ ነው። ማየት የተሳናቸው አመልካቾች በሙሉ ዋናው ግቢ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ላብ 1 ፈተናው እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡ በስህተት ሌላ የመፈተኛ ክፍል ተመድበው ከሆነ በቀጥታ ለአካል ጉዳተኞች ማዕከል በዕለቱ ሪፖርት ያድርጉ ተብሏል፡፡ (የተፈታኞች ኮድ፣ ስም ዝርዝር እና የመፈተኛ ቦታ ዝርዝር መርሐግብር ከታች ተያይዟል፡፡)
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው። ዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ተማሪዎችን በሁለቱ ካምፓሶቹ ማለትም በአዳያኣ ግቢ እና በሀሴደላ ግቢ በመቀበል ላይ ይገኛል።