tgindex
#TeddyAfroFans Officialወደፍቅር

#TeddyAfroFans Officialወደፍቅር

Статистика

እንኳን ወደዚህ ግዙፍ ወደ ሆነው ''ወደ ፍቅር . . .'' ቻናል በደህና መጡ ይህ ቻናል በቴዲ አፍሮ ወዳጅ ቤተሰቦች የተመሰረተ ሲሆን ባለቤትነቱም በቴዲ አፍሮ #Teddy_Afro እውቅና ባለው ''ወደ ፍቅር . . . ''ማህበር አባላትና መስራቾች ነው ፡፡ ፍቅር ያሸንፍል !!

Последний пост
15 июл.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
454
0 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
238
21 постов
Вовлечённость
52,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በክብረ በዓላችን ላይ ድምቀት የሆነችን ልዩ እንግዳችን ቴዲ «የመጀመሪያ ችሎታዬን አይታ መንገዱን የጠረገችልኝ፣ የሙያ እናቴ» ብሎ የሚጠራት፤ እጅግ የሚወዳት እና የሚያከብራት፤ለኛም ለ«ወደፍቅር» ማህበር የቅርብ ቤተሰባችን የሆነችው፤ተወዳጇ አርቲስት Adanech Weldgebriel (አዲ) በተገኘችበት ሰብሰብ ብለን በደስታ አክብረነዋል። 🎂 ውድ ቴዲ...ላበረከትከው ታላቅ የኪነጥበብ መሥዋዕትነት፣ ላሳየኸው ፍጹም ታማኝነትና ለሀገርህ ላለህ ቅንነት ምስጋናችን ወሰን የለውም💚💛❤️🙏 ታላቁ የጥበብ ሰው _የኢትዮጵያ የምንግዜም ውድ ልጅ ሆይ! ፈጣሪ ረጅም እድሜ፣ ጤና እና ሰላምን ይስጥህ። ወደፊትም በጥበብህ ብርሃን ሀገራችንን ፍቅርና ሰላም እንድታበስርልን እንመኛለን። በ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ የልደት በዓልህ ላይ፡ጤናህ እንዲበዛ፣ እድሜህ እንዲረዝም፣የፈጠራ አቅምህ ይበልጥ እንዲለመልም እንመኛለን። «የወደፍቅር» ማህበር አባላት ሁሌም እንወድሃለን እናከብርሃለን🙏 🎈🎈 መልካም 50ኛ ዓመት የልደት በዓል! 🎈🎈 ልዩ ምስጋና 👇 #ለመዝገበስጋቤት (ቦሌ) #Fraisie_cafe_and_restaurant

  • የልብ ትርታችን ለሆነው፣ የኢትዮጵያዊነት እና የፍቅር ተምሳሌት ለሆነው ለተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ የልደት በዓል ላይ #ወደፍቅር ማህበራችን ልደቱን በፍቅር እና በበጎ ተግባር አክብሯል። 💖 ዋዜማ በ Sele Enat Mahiber (ሰኞ ሐምሌ 6 / 2018 ዓ.ም) ፍቅር በተግባር ሲገለጥ ውበት አለው! ማህበራችን ሁሌም እንደሚያደርገው የንጉሱን ልደት ምክንያት በማድረግ፣ በዋዜማው ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን «ስለእናት የህፃናት ማሳደጊያ በጎ አድራጎት ድርጅት» በመገኘት ከነገ የሀገር ተረካቢ ህፃናት ጋር ደስ የሚል የከሰዓት ቆይታ አድርገናል። የፍቅር ማዕድ፡ ከህፃናቱ ጋር አብረን በመሆን ምሳ አብልተናል። የልደት ኬክ፡ ከእነዚህ ንፁሃን የኢትዮጵያ ልጆች ጋር በመሆን የቴዲን 50ኛ ዓመት የልደት ኬክ በታላቅ ደስታ ቆርሰናል። 👉ማህበራችን ላለፉት ተከታታይ ዓመታት በዚህ ተቋም ውስጥ ይሄንን የበጎ አድራጎት ስራ ሲያከናውን ቆይቷል። በተለይ ከእኛ እጅግ ፍቅር እና እንክብካቤ ለሚሹት ለእነዚህ ህፃናት ድጋፍ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ስለዚህ ማንኛውም ሰው ይህንን ተቋም በመጎብኘት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በታላቅ አክብሮት እንጋብዛለን። 🎉 ማክሰኞ ሐምሌ 7 / 2018 የምንግዜም የኢትዮጵያ ውድ ልጅ ቴዎድሮስ ካሳሁን የልደት በዓልን የማህበሩ አባላት እና ወዳጆች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አክብረነዋል።

  • እኛ የወደ ፍቅር ማህበር አባላት፣ ያንተን የፍቅር መንገድ እንደ መርህ እንወስደዋለን። በጥበብህ የዘራኸው የፍቅር፣ የይቅርታና የአንድነት ዘር ዛሬም በብዙ ሚሊዮኖች ልብ ውስጥ እያደገ ፣እየተስፋፋ ያልተረዱህም እየገባቸው ይገኛል። ላበረከትከው ታላቅ የኪነጥበብ መሥዋዕትነት፣ ላሳየኸው ፍጹም ታማኝነትና ለሀገርህ ላለህ ቅንነት ምስጋናችን ወሰን የለውም💚💛❤️🙏 ታላቁ የጥበብ ሰው _የኢትዮጵያ የምንግዜም ውድ ልጅ ሆይ! ፈጣሪ ረጅም እድሜ፣ ጤና እና ሰላምን ይስጥህ። ወደፊትም በጥበብህ ብርሃን ሀገራችንን ፍቅርና ሰላም እንድታበስርልን እንመኛለን። #መልካም_50ኛ_ዓመት_የልደት_በዓል! ኢትዮጵያ በጥበብህ፣ አንተም በሕዝብህ ልብ ውስጥ ለዘላለም ትኖራላችሁ❗️ "ፍቅር ያሸንፋል!" #ከወደ_ፍቅር_ማህበር Teddy Afro Fans ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም

  • የፍቅር፣ የአንድነትና የጽናት ተምሳሌት ለሆነው ለሙዚቃችን ንጉሥ! ክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን Teddy Afro ዛሬ #ሐምሌ_7 ቀን የሀገራችንን ሰማይ በታላቅ የጥበብ ድምፅ ካደመቁትና የኢትዮጵያዊነትን ማማ በክብር ካቆሙት ታላላቅ የጥበብ ሰዎች መካከል ቀዳሚው እና አንዱ የሆንኸው አንተ፣ ወርቃማውን 50ኛ ዓመት የልደት በዓልህን ስታከብር፣ እኛ የወደ ፍቅር ማህበር አባላትና መላው ወገንህ በታላቅ አክብሮትና ኩራት «እንኳን ተወለድክልን!» እንልሃለን። ያንተ የ50 ዓመታት የሕይወት ጉዞና የእድሜህን ግማሽ ያህሉ የጥበብ አበርክቶ ተራ የሙዚቃ ታሪክ ሳይሆን፤ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አንድነት፣ ለፍቅርና ፣ ለሰላም ፣ ለጽናት የተከፈለ ታላቅ መሥዋዕትነት ነው። ከጎጥ በላይ የቆመው የኢትዮጵያዊነት አርማ❗️ ብዙዎች በከፋቸው ጊዜ በብሔርና በጎጥ ጥላ ሥር ተወሽቀው የመከፋፈልን መርዝ ሲረጩ፣ አንተ ግን «ኢትዮጵያዊነት» የሚለውን ታላቅ ስም እንደ ደማቅ አክሊል ደፍተህ፣ ያለ ምንም የዘር ልዩነት ለአንድነትና ለፍቅር ዘመርክ። ዘረኝነት በገነገነበትና አጥር በተበጀበት ዘመን፣ አጥር አፍራሽና ድልድይ ሰሪ አቀራራቢ ሆነህ በታማኝነት ለሀገርህ ቆምክ። 🎙️ ለታፈነው ሕዝብ ቀዳሚው ድምፅ❗️ ሁሉም ድምፁን አጥፍቶ በፍርሃት በዝምታ በተገዛበት ሰዓት፣ አንተ ግን ለተጨቆኑት፣ ለታፈኑትና ፍትሕ ለተራቡት ወገኖችህ ቀዳሚ ድምፅ ሆንክ። በየጊዜው በሚፈራረቁ መንግሥታት ያረፈብህን ጫና፣ ግፍና እስራት በጽናት ተቋቁመህ፣ ዋጋ ከፍለህም ቢሆን ከሕዝብ ጎን ከመቆም መቼም ቢሆን ወደኋላ አላፈገፈግክም። ይህ ጽናትህ ነው ዛሬም ድረስ በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም እንድትጻፍና የምንግዜም ውድ የሕዝብ ልጅ እንድትሆን ያደረገህ።

  • የንጉሱ Teddy Afro 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ልደት ዋዜማ ላይ ነን። ብዙዎች መናገር በፈሩበት፣ እውነት በጠፋበትና ህዝብ በከበደው ጊዜ ሁሉ ቴዲ የህዝብ እንባና ህመም በጥበቡ ድምፅ ሲሆን ኖሯል። ስለ እውነት እና ስለ ሀገር ፍቅር የከፈለው ዋጋ፣ የደረሰበት መገፋት እና ፈተና ሁሌም በታሪክ ሲታወስ ይኖራል። ቴዲ ማለት የጥበብ ጋሻ፣ የህዝብ ወገን ነው። ፈተናዎች እና ማዕበሎች ቢበዙም፣ እርሱ ግን ሳይናወጥ የሀገሩን ክብር እና የሕዝቡን ፍቅር ከፍ አድርጎ ይዟል። ዕድሜ እና ጤና ለአንደበተ ርቱዕው ድምፃችን! መልካም የ50ኛ ዓመት የልደት በዓል፣ ንጉሥ! 👑✨ #TeddyAfro #TeddyAt50 #Ethiopia #PeaceAndLove #Legend

  • 🎉 የንጉሱ 50ኛ ዓመት የልደት በዓል በደመቀ ሁኔታ ይከበራል! 🎉 የኪነ-ጥበባችን ፈርጥ የኢትዮጵያ የምንግዜም ውድ ልጅ የ Teddy Afroን 50ኛ ዓመት የልደት በዓል በታላቅ ድምቀት ለማክበር፣ ሁላችንም ይህንን ምስል የፕሮፋይል ፎቶ በማድረግ አጋርነታችንን እና ፍቅራችንን እናሳይ።

  • Channel photo updated

  • የኢትዮጵያ ውድ ልጅ የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን Teddy Afro 50ኛ ዓመት የልደት በዓል ዋዜማ ላይ እንገኛለን ወዳጆቹ ፣ አድናቂዎቹ ፣ እንዲሁም የተለያዩ ድርጅቶች የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን እየላኩልን ይገኛሉ ። እኛም የሚላኩት መልዕክቶች ብዙ ቢሆንም በተቻለ አቅም ለእናንተ ለማድረስ እየሞከርን ነው። አሁን ደግሞ Dj @Nathan ከዱባይ ሙሉ ነገ ምሽት በ Etete production YouTube የሚለቀቅ ለንጉሱ መልካም ምኞቱን እና ፍቅሩን አክብሮቱን የገለፀበት አዲስ ነጠላ ዜማ ይጠብቁ ቅንጫቢ ሙዚቃውን ከታች ጋበዝናቹ👇

  • የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ፣ የተወዳጁና የተከበረው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ( Teddy Afro ) የ50ኛ ዓመት ወርቃማ የልደት በዓልን አስመልክቶ፤ ለምትወዱት አርቲስት ያላችሁን አክብሮት፣ ፍቅርና መልካም ምኞት የምታስተላልፉበት ታላቅ ዕድል! የንጉሱን ልደት በደመቀ ሁኔታ ለማክበር፤ ወዳጆቹ፣ አድናቂዎቹ እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ያዘጋጃችሁትን ደረጃውን የጠበቀ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፣ ከንጉሡ ፎቶ እና ጥራቱን ከጠበቀ ግራፊክስ ዲዛይን ጋር በውስጥ መስመር ብትልኩልን፣ መልዕክታችሁ ለሰፊው ሕዝብና ለአርቲስቱ እንዲደርስ ገጻችን Teddy Afro Fans በደስታ ለማስተላለፍ ዝግጁ መሆኑን እንገልጻለን። #SisayGuzay #አዲስዓይንሚዲያ_AddisAyenMedia

  • የሀገር ፍቅር መግለጫው "ኢትዮጵያ" አልበም በዓለም አቀፉ Billboard World Albums ሰንጠረዥ ላይ 1ኛ ደረጃ በመያዝ የሀገራችንን ስም በአለም አደባባይ ያስጠራ ድንቅ ስራ ነው። 10 ቀናት ብቻ ቀሩ! 🌍📈

  • Teddy Afro በሙዚቃዎቹ ታሪካችንን በኩራት እንድንዘክር ብቻ ሳይሆን የታሪክ መዝገብ ገልጠን እንድንመረምር አድርጎናል። ከአፄ ቴዎድሮስ ፅናት እስከ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት፣ ከአፄ ምኒልክ የጥቁር ህዝብ ኩራት እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ዲፕሎማሲያዊ ግርማ፣ እንዲሁም እንደ ጀግናው በላይ ዘለቀ ያሉ የሀገር ፍቅር ተምሳሌቶችን በዜማዎቹ ህያው አድርጓቸዋል። አድዋን፣ ሰማዕታቱንና የጥንት ስልጣኔያችንን በልባችን ያሰረፀ ድንቅ የታሪክ መዝገብ ነው! የቀደሙት አባቶቻችንና እናቶቻችን ለሀገር የከፈሉትን ዋጋ ሁሌም እንድናስታውስና በማንነታችን እንድንኮራ ስላደረገን ይህን ታላቅ የጥበብ ፈርጥ እናመሰግነዋለን። ጥቁር ህዝብ ለአለም ያሳየውን የነጻነት አርዓያነት በዜማ ያነገሰውን ውድ ልጃችንን እናከብራለን! የሁላችንም ስስት ለሆነው ለኪነጥበብ ፈርጡ ቴዎድሮስ ካሳሁን የወርቅ ኢዮቤልዩ 50ኛ ዓመት ልደት በዓል 13 ቀናት ብቻ ቀሩ! 📜👑🦁 #ቴዲአፍሮ50 #የታሪክማስታወሻ #አቦጊዳ #ጥቁርሰው #ያስተሰርያል #ኢትዮጵያ #ኢቶሪካ #አድዋ #ኢትዮጵያ

  • "ፍቅር ያሸንፋል" የሚለውን ታላቅ መርህ በሙዚቃው የሰበከ፣ በዜማዎቹ ልቦችን ያገናኘ የሰላም 🕊️❤️ አምባሳደር! Teddy Afro ለኢትዮጵያ ጥበብ ያበረከተው አስተዋፅኦ በታሪክ ማህደር ሁሌም ህያው ነው። መልካም የልደት ዋዜማ ለጥበቡ ንጉሥ! 🎂🎈 #TeddyAfro #TeddyAfro50 #Ethiorica #EthiopianMusic #LoveWins #TeddyAfroGoldenJubilee #ፍቅርያሸንፋል

  • ለታላቁ የኪነጥበብ ሰው 50ኛ ዓመት ልደት #20 ቀናት ቀሩት! ሙዚቃን ከዜማ በላይ አድርጎ፣ የሀገር ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን በልባችን የዘራው ታላቁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ( Teddy Afro ) 50ኛ ዓመት የልደት ወርቅ ኢዮቤልዩን ለማክበር ጥቂት ቀናት ቀሩት። ላለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት በኪነጥበብ ስራዎቹ የሀገር ቁስልን የፈወሰ፣ ፍቅርን የሰበከና ሁላችንንም በአንድ ጥላ ስር ያሰባሰበ የዘመናችን የሙዚቃ ንጉስ! የቴዲ አፍሮ ስራዎች ለእናንተ ምን ትርጉም አላቸው? 🎶 የእናንተ ተወዳጅ የመጀመሪያ የቴዲ አፍሮ አልበም የቱ ነው? #TeddyAfroAt50 #GoldenJubilee #LegisOfMusic #TeddyAfro

  • ከኪነ-ጥበብ ፈርጡ ቴዲ አፍሮ ጋር የነበረ የላቀ የሥራ ዘመን፦አቶ አዲስ ገሰሰ ከ10 ዓመታት በላይ ከተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ጋር በማኔጀርነትና በፕሮዲውሰርነት የነበራቸው የሥራ ትስስር የኢትዮጵያን ዘመናዊ የሙዚቃ ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ነበር። ይህ የረጅም ጊዜ የሥራ ትብብር የሙዚቃ አስተዳደርን ሥርዓት ያስደገፈ፣ የአርቲስቱን እምቅ አቅም ለዓለም ያሳየ እና በሁለቱ መካከል ከሥራ ባሻገር የጸና ወንድማማችነትና ፍቅር የሰፈነበት እንደነበር ማህበራችን በታላቅ አክብሮት ያስታውሰዋል። እሳቸው ለጥበብ ሰዎች ብርታት፣ ለታዋቂዋ ድምጻዊት ጂጂ የዓለም አቀፍ መድረክ መከፈት ምክንያት የሆኑ እና ሁልጊዜም በትሕትናቸውና በበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸው የሚታወቁ ታላቅ መሪ ነበሩ። በ "One Love Africa Foundation" በኩል በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የነበራቸው ሰፊ ራዕይ ለሀገራቸውና ለወገኖቻቸው የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅር ማሳያ ነው። በዚህ አስቸጋሪና መሪር የሀዘን ወቅት፣ ማህበራችን «ወደ ፍቅር» ለአቶ አዲስ ገሰሰ መላው ቤተሰቦች፣ ለወንድማቸው ለሙዚቀኛ ዘለቀ ገሰሰ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለአርቲስት ቴዲ አፍሮ እንዲሁም ለጥበብ ቤተሰቦች በሙሉ ከልብ የመነጨ መጽናናትን ይመኛል። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!🙏 ሥራቸውና በጎ አሻራቸው ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል። 🕯🕯🕯🕯 ከአክብሮት ጋር «ወደ ፍቅር» ማህበር አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  • видео или голосовое, без подписи

  • ከ «ወደ ፍቅር» ማህበር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ ሰኔ 12 /2018 ዓ.ም (June 19, 2026) በታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ ህልፈተ ህይወት የተሰማን ጥልቅ ሀዘን መግለጫ ለአቶ አዲስ ገሰሰ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና ለመላው የጥበብ አፍቃሪያን በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ታላቅና የማይረሳ አሻራ ያሳረፉት ወንድማችን፣ ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ (አዲሱ) በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስንሰማ በ«ወደ ፍቅር» ማህበራችን ስም የተሰማን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ ቃላት ያጥሩናል። አቶ አዲስ ገሰሰ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጥበብ በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ካቆሙ ጥቂት የዘርፉ ባለውለታዎች መካከል ቀዳሚው ነበሩ። ከዳሎል ባንድ ስኬት ጀምሮ የዓለም አቀፉን የሬጌ ንጉስ የቦብ ማርሊን ቤተሰቦች (ሪታ ማርሊ እና ዚጊ ማርሊ) በቅርብ በማማከርና በማስተዳደር፣ እንዲሁም ታሪካዊውን የ "Africa Unite" ኮንሰርት በአዲስ አበባ አዘጋጅተው ያሳዩት ድንቅ ብቃት ዘላቂ ታሪካችን ነው።

  • https://youtu.be/-hgSIlnNrE8?si=XNM0q8ZJtHYw9slZ

  • የአንጋፋና ወጣት የጥበብ ሰዎችን የሕይወትና የጥበብ ጉዞ ባማረ ቤተሰባዊ ጨዋታ የሚያስኮመኩመን በተወዳጇ አርቲስት Adanech Weldgebriel ተዘጋጅቶ የሚቀርበው «አዲ ጠብታ» የ YouTube Channel አዳዲስ ዝግጅቶችን ይዞ መቅረቡን እንደቀጠለ ነው ። የዚህ ሳምንት እንግዳ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ጉዞ ላይ የሚያጠነጥነውን «ወደ ፍቅር ጉዞ» የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ደራሲ ቢኒያም አቡራ ነው። ይህንን ልዩ ቆይታ እንዳያመልጥዎት አሁኑኑ ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ፤ ቻናሉን ሰብስክራይብ፣ ላይክ እና ሼር በማድረግ ጥበብን ይደግፉ! 👉 ለመመልከት፡ [ https://youtube.com/channel/UCokKz4vkpWCpBgZphID0lZQ?si=gsUrxq-VEy0W7wvN ] #AdiTebta #TeddyAfro #EthiopianArt #SubscribeNow Teddy Afro Amleset Muchie @topfans Teddy Afro Fans Zerihun Teznanu Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

  • ቴዲ አፍሮን እንጠብቅ👉 ጥበብን፣ ነፃነትን እና ሰብአዊ ክብርን እንደግፍ❗️🛡️✨ #ሙዚቃ የነፍስ ድምፅ ነው፤ ጥበብ ደግሞ መታፈን የለባትም። የተከበረው የሙዚቃው ንጉስ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ያለውን የመግለጽ ነፃነት እና ሰብአዊ ክብሩን ለመጠበቅ ሁላችንም አጋርነታችንን እናሳይ። ይህንን ፒቲሽን በመፈረም ከምንጊዜውም በላይ ከምንወደው አርቲስት ጎን መቆማችንን እናረጋግጥ። አንድነታችን ኃይላችን ነው! ✊🏾 ፒቲሽኑን እዚህ ይሙሉ 👇 Protect Teddy Afro👉 Defend Art, Freedom, and Human Dignity❗️ 🛡️✨ #Music is the voice of the soul, and art should never be silenced. Stand with the legendary King Of Music Tewodros Kassahun (Teddy Afro) as we champion the right to creative expression and human dignity. Show your solidarity by signing this petition. Let’s prove that we stand stronger together behind our beloved artist! ✊🏾 Fill out the petition here 👇 https://www.change.org/p/protect-teddy-afro-defend-art-freedom-and-human-dignity?recruiter=34793693&recruited_by_id=1b445f70-1673-0130-c9c6-3c764e044346&utm_source=share_petition&utm_campaign=psf_combo_share_initial&utm_term=share_petition&utm_medium=copylink&utm_content=cl_sharecopy_491212874_en-US%3A7&share_id=GRNBKhkCKC&fbclid=IwVERDUARgZq5leHRuA2FlbQIxMQBzcnRjBmFwcF9pZAo2NjI4NTY4Mzc5AAEe5xkFX2_jED2AkL2y4vTPFNhtNbIv7Y7RrsIvxFzh5fgXgTxK-h6Tz1bjKtk_aem_uTc07rcMJMK7xwY_SJ0rhA

  • ለ Teddy Afro አድናቂዎች እንዲሁም Teddy Afro Fans Page ተከታዮች በሙሉ! 📢 በተወዳጁ ተከባሪው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ስም እና ምስል እየተጠቀሙ የውሸት (Fake) የዩቲዩብ ቻናሎችን በመክፈት አድናቂዎችን ለማታለል የሚሞክሩ አካላት በዝተዋል ብዙዎችም በነዚህ Fake YouTube ቻናሎች እየተሸወዱ ይገኛሉ ። ⚡️የእርስዎ ድጋፍ አሁን ያስፈልገናል! ✅️የቴዲ አፍሮ ብቸኛው እና ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል ይህ ብቻ ነው፡ ዛሬውኑ ይከተሉን፡ 👇 https://youtube.com/@teddyafroofficial?si=9ikv8HnMWB2JWA1g 🔰 ከዚህ ውጪ በስሙ የተከፈቱ ሌሎች ቻናሎችን ካዩ፣ እባክዎን በዩቲዩብ ላይ "Report" ያድርጓቸው። ⚡️እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል⁉️ 👉 ወደ ቻናሉ ይሂዱ። 👉የ "About" ወይም የ "Channels" ክፍል ላይ የሚገኘውን የሶስት ነጥብ (⋮) ምልክት ይጫኑ። 👉 "Report user" የሚለውን ይምረጡ። 👉በመቀጠል "Impersonation" (አርቲስቱን እየመሰለ ያለ Fake Account ) የሚለውን በመምረጥ ሪፖርት ያድርጉ። ✅️ማሳሰቢያ፦ በሌሎች ስም የሚከፈቱ የዩቲዩብ ቻናሎች የአርቲስቱን ኦፊሴላዊ የቪዲዮ ምንጭ አይወክሉም። እባክዎን ትክክለኛውን ቻናል በመከተል ጥራት ያለው መረጃ እና ስራዎችን 👉የጥበብ ባለቤቶችን እና የቅጂ መብትን እንጠብቅ! #TeddyAfro #OfficialChannel #ReportFakeAccounts @topfans Amleset Muchie Adanech Weldgebriel Zerihun Teznanu Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ #ወደፍቅር

#TeddyAfroFans Officialወደፍቅር — tgindex