tgindex
💙..ነጠብጣብ ✨🧩

💙..ነጠብጣብ ✨🧩

Статистика

✨ትዝታማ አለሽ የለኝም ብትይኝ እኔም አላምንሽም በህይወት መንገድ ላይ ተራምደሽ ሳታልፊ ዛሬ ላይ አልቆምሽም፨ ህይወት ያለ ታሪክ ቀን ያለ ጨለማ መች ቶሎ ይመሻል ሰዉ ስለሆንሽ ብቻ ለሰዉ ምታወጊዉ ቅፅበት ይኖርሻል፨ ትዝታ አለሽ?አዉጊኝ ትዝታ አለኝ!ላዉጋሽ ..እንዲህ ብናወራስ...ቅፅበታት እናዉጋ.. የልብ ንግግሮችም አይታጡም..ግቡ💙 ለአስተያየታችሁ @AnchinayehuGebrie

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 597
+5 Са 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
1 182
20 постов
Вовлечённость
45,5%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всогО 23
УпОПинаниК
3
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
424
1/48двое суток
485
1/72трое суток
524

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✨"ላግባሽ ያለሽ ላያገባሽ፤ከባልሽ ሆድ አትባባሽ"_የሕዝብ 👣

  • ለልጅዎ አስጠኝ ይፈልጋሉ። ለልጅዎ ከkg_12 ቤት ለቤት እንዲሁም በ online  የማስጠናት አገልግሎት እንሰጣለን። ☎️ 0934452215      0954096005 ይደውሉ። https://t.me/hopetuto

  • 11 авг.507194иС bridgethoughts

    ⭐️ [[ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም...]] . . . ማሕበረሰባችን ውስጥ መተማመን ላልቷል... ታማኝነት በእጅጉ ሳስቷል... ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ይህ ዘመን ልዩ ቀለሙ በቃል አለመገኘት ነው... ለሕሊና ጀርባ መስጠት፣ ለስሜት ነውጥ ፊት ማሳየት፣ ቃልኪዳንን ማተናነስ፣ በየኩርባው ማነቀፍና ማንከስ ጉልህ ምልክቱ ነው... [ይህ ጉዳይ በተለይ በግንኙነት ውስጥ እጅግ ከባዱ ፈተና ይመስለኛል...] እርግጥ ነው - በሰዎች ዕለታዊ መስተጋብር ውስጥ ግንኙነትን እንደ ይዞታ የማሰብ አዝማሚያ መኖሩን መካድ አይቻልም... 'እከሊት የእንትና ናት'፣ 'እከሌ የእኔ ነው'፣ 'እርሷ የኔ ናት' እያልን ሰውነትን እንደ ቁስ ለመቁጠር መዳዳታችን እውቅ ነው... ጥንዶች ለየብቻ ሕይወት እንደሌላቸው ሁሉ የአንድ ሰው እስረኛ እንደሆኑ አድርገን እናስባለን... ይህ ግን ፍቅር አይደለም... ይልቅ እርሷ ሁሌም ነፃ ሆና እርሱን ትመርጣለች - ሌላ ምርጫ ባላት ጊዜም ቢሆን... እርሱ ሁሌም ነፃ ሆኖ እርሷን ይላል - ብዙ ሴቶች ዙሪያው ሳሉም ጭምር... [ልዩነቱ ግልጽ ነው...] ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም... የመተው ምርጫ እያለው ሁሌም በዚያ ያለ ሰው ግን እርሱ ፍቅርን ያውቃታል... [ይህ በእንዲህ እንዳለ - ይላል ራዲዮን...] ፍቅርን የሚያዘልቁት ከባዱን ዳገት መርጠው እንጂ ቀላሉን ቁልቁለት አቋርጠው አይደለም... ስለዚህ መታመን ጥንካሬን ይፈልጋል... ጽናትን ይፈልጋል... ምርጫ ነፃነት ቢሆንም ዳሩ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ለቃል ማደር ብርታትን ይጠይቃል... ሲታዩም ሳይታዩም ለአቋም መገዛት የሞራል ልዕልናን ይፈልጋል...  እኔና እርሷ 'ሚጋራና 'ሚከለከለውን ካለየን... 'ሚገለጥ 'ሚሸፈነውን ካልመረጥን... በነ'ከሌ ድርሻና በራስ ሰው ድብቅ ላይ - ድንበር ካላኖርን ታማኝነት ውሉን ይስታል... ስብዕና ይተናነሳል... ያም ብቻ አይደለም፣ እኔ 'ጨዋ ነው ቀሚሷ' ለማለት ሳመነታ፣ እርሷ 'ልቡ የኔ ብቻ ናት' ለማለት ድፍረት ታጣለች...  [ይሄኔ... ያልታሰረ ልብ ይዞ ጣትን በቀለበት የማሰር ልማድ ትርጉም ያጣል...] "... ማተብን ቢያጠብቁ - የአንጀት ፍቅር ሽረው በቁርባን ቢጋቡ - ቃልኪዳን ሸርሽረው ለአፍ ዓመል ካልሆነ - ማ'ላው ከምን ሊያስጥል በቀለበት ታስሮስ - ፍቅር ምን ሊቀጥል..." እንዲል ከያኒው እንደ ሰው ማሕበራዊ ተጋልጦ (Exposure) ቢኖረንም እንደ ቤተሰብ ደግሞ የማይነካ ግዛት አለን... ካርታ ባይኖረውም ቅሉ ቤተሰብ ሃገር ነው፣ የማይቆረስ ስስ ገላ - የሚከለል እውነት፣ የማይደራደሩበት ልዓላዊነት አለው... [ለቤት ከምንገልጠው ገጽ ላይ ገመና ባይኖረንም ለውጭ ከምንጋራው ላይ ግን ደስታና ሃዘናችንም ቁጥብ ነው...] ከገበያ ብንሸምትም የምናበስለውን የምናውቀው እኛ ነን... (የሸመትነውን ያወቀ ሁሉ የበላነውን መለየት የለበትም!)... ከአደባባይ ብንውልም አዳር የሁለታችን ብቻ ምስጢር ነው... (ያገኘን ሁሉ ልባችንን ማግኘት የለበትም)... [ከሳቅም ሸርፈው ይስቁታል፣ ከቃልም መርጠው ያወጉታል...] ለባልሽ ብቻ የምትስቂውን ሳቅ የምትስቂለት እስካለ ድረስ ታማኝነትሽ ከንቱ ነው... ለሚስትህ ብቻ በሚመጥን ቃል የምታወራት እስካለች ድረስ ሴሰኛነትህ ግልጽ ነው... ____ "Lust is a strong need. Love is not a need but a longing. When you love, you settle down – nothing more is needed." ~ Sadhguru _ @bridgethoughts

  • 10 авг.47937иС justhoughtsss

    йоС пОдписи

  • ✨....come ...🪽 🌊Let's talk to each other through the soul.Saying things  secret to the eyes and ears. Let's smile like a rose garden Without lips and teeth. Let's converse through thoughts without tongues or lips. Let's tell all the secrets of the world untill the end without opening our mouth like devine intellect 🤍      🅡𝖚𝖒𝖎 https://t.me/yeesua_queen

  • https://t.me/yeesua_queen

  • Live stream finished (1 hour)

  • Live stream started

  • Live stream scheduled for Aug 9 at 17:30

  • 9 авг.2 52353

    ✨ክቡራን ቤተሰቦቻችን የዛሬ ማታ የመጽሐፍ ዳሰሳ ቀጠሯችን እንደተጠበቀ ነው! 📖ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? ደራሲ:- እሱባለው አበራ ንጉሴ 🕰 ከምሽቱ 02:30 ላይ #በነጠብጣብ ቻናል ላይ ኑ እናወጋለን!! https://t.me/yeesua_queen

  • 📖....ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? 🌻 https://t.me/yeesua_queen

  • 6 авг.3 059285

    ✨ወፌ ሰንብታ....🪽

  • 4 авг.1 3591313

    йоС пОдписи

  • 4 авг.1 33710

    ✨ጤና ይስጥልን ክቡራን ቤተሰቦቻችን!እንደምን ከርማችኋል?የህይወት መንገዷስ እንዴት ይዟችኋል? ይሄው  ዳግም በሌላ የመጽሐፍ ዳሰሳ ልንገናኝ ቀጠሮ ልንይዝ ነው! 📚 በዚህ ሳምንት ዳሰሳችን የእሱባለው አበራ ንጉሴን መጽሐፍ "ፀሃይ ከጨለማዬ ምን አለሽ"እንዳስሳለን። እሁድ ነሐሴ 03/12/2018 ዓ.ም እዚህ ቤት ማለትም #በነጠብጣብ_ቻናል ከምሽቱ 02:30 ይጠብቁን!! https://t.me/yeesua_queen

  • 4 авг.890166иС justhoughtsss

    በየወሩ የሚገናኙበት ቀን ሲደርስ መሄድ አስጠላት። አልመጣም ብላ text ልካላቸው ወደቁዘማዋ ተመለሰች። ትንሽ ቆይቶ የቀልፍ ድምፅ ሰማች እነሱ ናቸው አራቱም በየተራ ከሳሟት በኋላ በየሶፋው ላይ ተደረደሩ። "ቤዛ ሺቲ አምጪ ሜሪ ጋቢ አምጪ እኔ ሻይ አፈላለሁ ቤቲ ሶፋዎቹን አስተካክዪ" ብላ ማርካን ተነሳች "ማሪ..." አትድከሙ ልላቸው ነበር "አንቺ ዝም ብለሽ ቆዝሚ" ሁሉም የድርሻቸውን አምጥተው ተመቻችተው ተቀመጡ። እንፋሎቱ የሚፋጅ ሻይ ይዘው "ምን ልሁን ነው የምትዪው?" ቤዛ ፀጥታውን ሰበረች "ከዛ በፊት ይሄንን ለቅሶ ለቅሶ የሚል ነገር ቀይሪልኝ አስቴርንም ቢሆን ክፈቻት..." ማርካንን አቋርጣት "አይሆንም እንዳትቀይሩት Please" "ለምን?..." እኩል ደነገጡ "የቴዲ ታደሰ አድናቂ ነው እንዳትይኝ" በፍርሀት ሜሪ ጠየቀቺኝ ምላሼ ሲዘገይ አረጋገጡ "ምን ተባብለን ነበር? የቴዲ ታደሰ፣ የማዲንጎ እና የሚካኤል በላይነህን አድናቂዎች አይቻልም ብለን አልነበር?" "ተባብለን ነበር..." "ቆይ ምንድነው ችግሩ የቴዲ ታደሰ አድናቂ መሆኑ?" ቤቲ ይሄ ፍልስፍናችን sense አይሰጣትም "የአንድ ሰው personality ከሚያዳምጠው ዘፋኝ ጋር እንደሚገናኝ አታውቂም?" ማርካን እየተበሳጨች "ሆይ ሆይ የሚሰማ ሰው ቢሆን እኮ ችግር የለውም። ምክንያቱም ውል የለውም ንግግሩ ጥልቀት አይኖረው አድናቆቱ ውስጥሽ አይቀር ስንብቱም ያን ያህል ጉዳት አያደርስም። የቴዲ ታደሰ አድናቂ ግን..." ቤዛ ተቀበለቻት "የቴዲ ታደሰ አድናቂ ግን እንደ ቴዲ ማድነቅ ይችላል። ውበት እንዴት እንዴት እንደሚገለፅ ያውቃል እንዴት እንደሚሽሞነሞን ያውቃል ከውስጥ የማይወጣ አድናቆት ከፈለግሽ እኔ የለሁበትም። ከማድነቅ በላይ ደግሞ ለመሰበር ግድ የለውም። ተሯሩጦ ደህና ለመሆን አይሞክርም ከህመሙ ጋር መኖር ይችላል። ህመሙ አንቺን የሚያስታውስበት ብቸኛ መንገድ ከሆነ አይለቀውም እሹሩሩ ይለዋል። ታዲያ ከእንዲህ አይነቱ እንዴት ነው የምታግመው?" "አሄሄ እስኪ ድምፁን ከፍ አድርጊው አንቺ ደግሞ በደንብ ንገሪን ስለሱ" ማርካን ለሁሉም ሻይ ከፔርሙዙ እየጨመረች ሙሉ ቀን ስለሱ ሲወራ ዋለ... ✍ናኒ https://t.me/justhoughtsss https://t.me/justhoughtsss

  • 😎 https://t.me/yeesua_queen

  • ✨Let Them_Let me👸 https://t.me/yeesua_queen

  • 29 июл.1 304323

    ✨#ጴጥሮስ_ያቺን_ሰዓት 🦁 [ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን] አዬ! ምነው እመብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት? ምነው ቀኝሽን ረሳሻት? እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት? ልቦናሽን ታዞሪባት? ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት? አላንቺ እኮ ማንም የላት…. አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት ቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ …. እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን አንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃን ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡ አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ፣ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ … . አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ፣ የትብት ምግቤን ገድፌ ከእናቴ ማኅፀን አርፌ ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ ከወዟ ወዜን ቀፍፌ በሕፃ እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤ በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሸሽ በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ ለግልገሌ ካውሬ ከለል እማሳው ሥር ጎጆ መትከል ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል . ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ ….. ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት እመ ብርሃን እረሳሻት? ያቺን የልጅነት የምሥራች? የሕፃንነት ብሥራት የሣቅ የፍንደቃ ዘመን፣ የምኞት የተስፋ ብፅአት ያቺን የልጅነት እናት? አዛኚቱ እንዴት ብለሽ፣ ጥርሶችሽን ትነክሺባት? . ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ባገልግሎትሽ ስዋትት ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት እመጻሕፍት ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ ከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም ቅዳሴ እኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶ ቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦ መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞ በልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል ተሸልሞ እመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ በእሳት ታትሞ የመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣ አብሮኝ ታድሞ ሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶ ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ . ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ሆነሺኝ የእምነቴ ፋኖስ ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም፣ ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ ስሮጥ፣ በወንበሩ አኖርሺኝ፣ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ ታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ፣ ከምትሰጪኝ የፍርሃት ጦስ ምነው በረኝነት እድሜ፣ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስ የጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ፣ ወርዶ በጨለማ በርኖስ . ባክሽ እመ ብርሃን ይብቃሽ፣ ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ ጽናት ስጪኝ እንድካፈል፣ የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ፣ ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ፣ ከነደደችበት እቶን የሷን ሞት እኔ እንድሞታት፣ ገላዋ ገላዬ እንዲሆን፡፡ ….. አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ፡፡ . ሕፃን ሆኘ የእርግብ ጫጩት አንዳንዴ ርሃብ ሲያዳክማት ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፍ ግርጌ ሲጥላት እናቷ በርራ ደርሳላት በአክናፏ ሙቀት ተታቅፋት እፍ እያለች ግንባሯ ላይ ህይወት ስትተነፍስባት ወዲያው ነፍስ ትዘራለች ሽር-ብር-ትር እያለች ። ባክሽ አንችም አትራቂብኝ እመብርሃን እናቴ ትንፋሽሽን እፍ በይብኝ ፅናትሽን እፍ በይብኝ ፤ ወይም ይችን የሞት ጽዋ ፥ ጥላዋ ነፍሴን ካፈናት እንዳልጠጣት አሳልፊያት መራራ ክንፏን ገንጥለሽ ቀጠሮ ቃሏን ግደፊያት . አለዚያም ፅናትሽን ስጭኝ ልጠጣው ኪዳነ ውሉን የኔ ፈቃድ እምነትሽ ነው ያንች ፍቃድ ብቻ ይሁን ። እንደጳውሎስ እንድፀና ፣በፍርሃት ሳልታሰር ለየዕለቱ ሞት እንዳልሰንፍ የኪዳኔ ቃል እንዳይነጥፍ ቃልሽ በሕሊናየ ዲብ ፣ ኃይልሽ በሕዋሴ ይረፍ ። ፍርሃት ቢያረብብኝም አንች ካለሽኝ አልሰጋም ኩርምት እችልበት ፣ እሸሸግበት አይጠፋም የግማደ መስቀሌን ጉጥ እታገስበት አላጣም አለዚያማ ብቻየን ነኝ ፣ ኢትዮጵያም ያላንች የላት አንች አፅኝኝ እንድፀናላት ። አስርጭብኝ የእምነት ቀንጃ ፤ ለስጋቴ አጣማጅ አቻ ለጭንቀቴ መቀነቻ ።… . አዎን ብቻየን ነኝ ፈራሁ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ … ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን ፲፱፻፷፩ ዓ.ም https://t.me/yeesua_queen

  • йоС пОдписи

  • ✨እንኳን አደረሳችሁ...💙