ድልድይ | Dildiy | Bridge
СтатистикаDILDIY Whispers of the soul. Echoes of the universe. Exploring consciousness, love, interconnectedness, and the mystery of existence through philosophy, mysticism & science. Every thought is a bridge. Every question is a path. Every soul is connected.
- Последний пост
- 17:14
- Последнее чтение
- 12:46
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 057
- 1/48двое суток
- 1 211
- 1/72трое суток
- 1 306
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
. . . ብዙ ሰዎች ገደብ አልባ ምርጫን 'ከነፃነት' ጋር፣ ልክ የሌለው ትኩረትን ደግሞ 'ከፍቅር' ጋር ያምታታሉ... በዚህም ምክንያት ከእጃቸው ላይ ያለውን በረከት በማይጨበጥ ቅዥት ሲያዘርፉ ይኖራሉ... . . . [የቆምንበትን ስንተው...] ሁሌም ቢሆን ካንተ ሚስት 'የምትበልጥ' ሴት በዚያ አለች... አንተ ግን የሁሏም አትሆንም... የትም ቢሆን ከባልሽ 'የሚሻሉ' ወንዶች ይኖራሉ... ሚስትነትሽን ግን አይጋሩም... እርግጥ ነው... 'የምትበልጥ' ወይም 'የሚሻል' የምንለው በስሜት ከባቢያችን ውስጥ የሚመላለሰውን ስሁት መስፈሪያ እንጂ አግባቢ መለኪያ አይደለም... መቼም እንደ መዝለቂያ ምክንያታችን ሁሉ መግቢያና መግባቢያ በራችንም ልዩ ልዩ ነው... ወንዶች - አካላዊ ውበት መግቢያችን፣ መላመድና መጣጣም መክረሚያችን ሊሆን ይችላል... ሆኖም ግን እኛ ካየነው ውበት 'የሚልቅ ውበት' ያላቸው ሌሎች ሴቶች በየትም አሉ... [በግንኙነት ውስጥ ግን ልባችን የሚዳረው ለአንዷ ብቻ ነው...] ሴቶች - ኢኮኖሚያዊ አቅም ማንኳኩያቸው፣ ቁምነገርና ብስለት መሻገሪያቸው ሊሆን ይችላል... ከሚያውቁት ወንድ የሚበልጥ ሃብት ያለው ወንድ ግን በየትም አለ... [በግንኙነት ውስጥ ግን የልብ አዳር የሚሰምረው አንዱ ጋ ብቻ ነው...] "A river gains its power not because it flows everywhere, but because it accepts its banks and moves toward its destination." አዎን... ሁሌም ቢሆን እጃችን ላይ ካለው 'የሚበልጥ' ነገር ከማዶም ከባሻገርም አለ... ልባችንን የሚያቀልጥ ግን ላይሆን ይችላል... የትም ቢሆን የምርጫ መስፈርታችንን የሚያስንቅ እልፍ አለ... ነፍሳችንን የሚዘልቅ ግን ላይሆን ይችላል... ውበት ይስብ ይሆናል - መሰረት የሚቆመው ግን ስብዕና ላይ ነው... ቅብጥብጥ ስሜት ግንኙነትን ሊያስጀምር ይችላል - የሚዘልቀው ግን ጥልቀት ላይ ነው... 'ቆንጆ' ሴት በዓይንህ ትገባለች፣ ትርጉም ያላቷ ግን ነፍስህን ትዘልቃለች... ብራም ወንድ ቀልብሽን ይወስዳል፣ የሚረዳሽ ግን ለግብሽ ያዋጣል... በነገራችን ላይ... ችግሩ ያለው 'የተሻለ' ማየታችን ላይ አይደለም - ማመናችን ውስጥ እንጂ... የሆነ ነገር 'የተሻለ ነው' ማለት የግድ ትርጉም የሚሰጥ ነው ማለት አይደለም... አንድ ሰው ከሚስቱ 'በላይ' ቆንጆ ሲያገኝ የበለጠ ዋጋ ያላት አገኘ ማለት እንዳልሆነው ሁሉ... ሌላም እውነት አለ... 'የተሻለ' ማየት እስከጀመርን ድረስ የቀደመውን 'አፍቅረናል' ማለት አንችልም... ዘግይቶ የሚረታን እስከመጣ ድረስ የቆየው ቦታ ይዞ ነበር አይባልም... ሁሌም 'የተሻለ' እስካለን ድረስ ፍለጋው በቅቶናል አያስብልም... ትርጉም ያለው ግንኙነት - የመምረጥ ብልሃትን ይፈልጋል... መምረጥ - ኁልቆ መሳፍርት አማራጮችን መተውን ይሻል... "Freedom means consciously choosing what deserves your devotion." Relationship - አስቦ የመምረጥ፣ መርጦም የመዝለቅ ጉዳይ ነው... ያም ሆኖ ግን ከበር ያላስተዋሉት እንከን ከቤት አይጎትትም ማለት አይቻልም... በዋዜማ ያልተገለጠ ጸባይ በማግስት አይፀኸይም ሊባል አይችልም... [አብሮነት በማትፈታው ቋጠሮ ቁርቋሬ ምቾት ማጣት አይደለም - ልታቻችል በምትችለው ክፍተት ላይ መሸካከም እንጂ...] ____ @bridgethoughts
⭐️ [[ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም...]] . . . ማሕበረሰባችን ውስጥ መተማመን ላልቷል... ታማኝነት በእጅጉ ሳስቷል... ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ይህ ዘመን ልዩ ቀለሙ በቃል አለመገኘት ነው... ለሕሊና ጀርባ መስጠት፣ ለስሜት ነውጥ ፊት ማሳየት፣ ቃልኪዳንን ማተናነስ፣ በየኩርባው ማነቀፍና ማንከስ ጉልህ ምልክቱ ነው... [ይህ ጉዳይ በተለይ በግንኙነት ውስጥ እጅግ ከባዱ ፈተና ይመስለኛል...] እርግጥ ነው - በሰዎች ዕለታዊ መስተጋብር ውስጥ ግንኙነትን እንደ ይዞታ የማሰብ አዝማሚያ መኖሩን መካድ አይቻልም... 'እከሊት የእንትና ናት'፣ 'እከሌ የእኔ ነው'፣ 'እርሷ የኔ ናት' እያልን ሰውነትን እንደ ቁስ ለመቁጠር መዳዳታችን እውቅ ነው... ጥንዶች ለየብቻ ሕይወት እንደሌላቸው ሁሉ የአንድ ሰው እስረኛ እንደሆኑ አድርገን እናስባለን... ይህ ግን ፍቅር አይደለም... ይልቅ እርሷ ሁሌም ነፃ ሆና እርሱን ትመርጣለች - ሌላ ምርጫ ባላት ጊዜም ቢሆን... እርሱ ሁሌም ነፃ ሆኖ እርሷን ይላል - ብዙ ሴቶች ዙሪያው ሳሉም ጭምር... [ልዩነቱ ግልጽ ነው...] ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም... የመተው ምርጫ እያለው ሁሌም በዚያ ያለ ሰው ግን እርሱ ፍቅርን ያውቃታል... [ይህ በእንዲህ እንዳለ - ይላል ራዲዮን...] ፍቅርን የሚያዘልቁት ከባዱን ዳገት መርጠው እንጂ ቀላሉን ቁልቁለት አቋርጠው አይደለም... ስለዚህ መታመን ጥንካሬን ይፈልጋል... ጽናትን ይፈልጋል... ምርጫ ነፃነት ቢሆንም ዳሩ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ለቃል ማደር ብርታትን ይጠይቃል... ሲታዩም ሳይታዩም ለአቋም መገዛት የሞራል ልዕልናን ይፈልጋል... እኔና እርሷ 'ሚጋራና 'ሚከለከለውን ካለየን... 'ሚገለጥ 'ሚሸፈነውን ካልመረጥን... በነ'ከሌ ድርሻና በራስ ሰው ድብቅ ላይ - ድንበር ካላኖርን ታማኝነት ውሉን ይስታል... ስብዕና ይተናነሳል... ያም ብቻ አይደለም፣ እኔ 'ጨዋ ነው ቀሚሷ' ለማለት ሳመነታ፣ እርሷ 'ልቡ የኔ ብቻ ናት' ለማለት ድፍረት ታጣለች... [ይሄኔ... ያልታሰረ ልብ ይዞ ጣትን በቀለበት የማሰር ልማድ ትርጉም ያጣል...] "... ማተብን ቢያጠብቁ - የአንጀት ፍቅር ሽረው በቁርባን ቢጋቡ - ቃልኪዳን ሸርሽረው ለአፍ ዓመል ካልሆነ - ማ'ላው ከምን ሊያስጥል በቀለበት ታስሮስ - ፍቅር ምን ሊቀጥል..." እንዲል ከያኒው እንደ ሰው ማሕበራዊ ተጋልጦ (Exposure) ቢኖረንም እንደ ቤተሰብ ደግሞ የማይነካ ግዛት አለን... ካርታ ባይኖረውም ቅሉ ቤተሰብ ሃገር ነው፣ የማይቆረስ ስስ ገላ - የሚከለል እውነት፣ የማይደራደሩበት ልዓላዊነት አለው... [ለቤት ከምንገልጠው ገጽ ላይ ገመና ባይኖረንም ለውጭ ከምንጋራው ላይ ግን ደስታና ሃዘናችንም ቁጥብ ነው...] ከገበያ ብንሸምትም የምናበስለውን የምናውቀው እኛ ነን... (የሸመትነውን ያወቀ ሁሉ የበላነውን መለየት የለበትም!)... ከአደባባይ ብንውልም አዳር የሁለታችን ብቻ ምስጢር ነው... (ያገኘን ሁሉ ልባችንን ማግኘት የለበትም)... [ከሳቅም ሸርፈው ይስቁታል፣ ከቃልም መርጠው ያወጉታል...] ለባልሽ ብቻ የምትስቂውን ሳቅ የምትስቂለት እስካለ ድረስ ታማኝነትሽ ከንቱ ነው... ለሚስትህ ብቻ በሚመጥን ቃል የምታወራት እስካለች ድረስ ሴሰኛነትህ ግልጽ ነው... ____ "Lust is a strong need. Love is not a need but a longing. When you love, you settle down – nothing more is needed." ~ Sadhguru _ @bridgethoughts
. . . ኢትዮጵያ ውስጥ የተሽከርካሪ ትርፍ መጫን የሚነገርህ ሲገለበጥ ብቻ ነው... ___ [አዎን - ይህ ሃሳብ ስለ ሕዝብ ማመላለሻ አይደለም] ___ @bridgethoughts
👍 ከመስበቅዎ በፊት... የተወረወረ ጦር የሚያውቀው አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው፤ ንግግር ግን መሄድን ብቻ ሳይሆን መመላለስንም ያውቃል... ሰሞኑን አንድ ፊልም እያየሁ ነበር… "Man of War" የተሰኘ የ 2026 የጦርነት ፊልም ነው… ፊልሙ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መሃል በቅጥረኛ ወታደሮች የታገተችን እንስት ለማዳን በጦርነት ቀውስ ውስጥ ወደምትገኘው ዩክሬን የተጓዘን አንድ ጡረተኛ የአሜሪካ ልዩ ኃይል (Special Forces) ወታደርን ጀብዱ ያትታል… ፊልሙ ሲጀምር - ቀደም ሲል በተሰማራባቸው የጦር ሜዳዎች የደከመውን፣ በከባድ የስነ-ልቦና ቀውስ (Trauma) ውስጥ የሚገኘውን እና ራሱን የማጥፋት ሃሳብ የሚታገለውን ሰው እናያለን... ይህ ሰው ጡረተኛው የባህር ኃይል ልዩ ተዋጊ (Navy SEAL) እና የ CIA ወኪል ማይክል ኮነር ሲሆን በአፓርታማው ውስጥ በከፍተኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ እንደተቀመጠ ይቀላቀለናል… ኮነር (በመዝገብ ስሙ LaMonica Garrett) ራሱን ለማጥፋት በሚዳዳበት ቅጽበት በዩክሬን ካርኪቭ በሚገኝ የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ረዳት ሰራተኛ ሆና ከምትሰራውና የማደጎ ልጁ ከሆነችው ራይሊ አስቸኳይ የቪዲዮ ጥሪ ይደርሰዋል…. የተጨነቀች ሴት ድምጽ፣ በፍርሃት የተዋጠች እንስት ፊት፣ በፈንጂዎች የምትናጥ ከተማ ድምጽ… "Mike, I'm in trouble. I need your help." "I'm still in Kharkiv." "I couldn't leave them, Mike. The Russians just crossed the border. They're bombing the city." ኮነር የሚወዳት ራይሊ፣ ኮኒየቭ በተባለ ጨካኝ የቅጥረኛ ጦር አዛዥ ታግታ ስትወሰድ በስልኩ ስክሪን ላይ እያየ ምንም ማድረግ ካለመቻል በሚፈጠር ሕመም ይጨሳል… ያ ከደቂቃዎች በፊት ራሱን ለማጥፋት ሲጣጣር የነበረ ሰው፣ ድንገት የመኖሪያ ምክንያትና የሕላዌ ትርጉም እንዳገኘ ሁሉ ከሚገኝበት ባርሴሎና ወደ ዩክሬን በድብቅ የመግባት ሃሳብ ወጥኖ በቀድሞ ወዳጆቹ አመቻችነት ጉዞ ይጀምራል… ከዚህ በኋላ ያለው ታሪክ ለተመልካች የሚተው ነው… ጦርነት የሚያመጣቸውን ሰቆቃዎች ሁሉ በፊልሙ ውስጥ ታያላችሁ… ስደት፣ መፈናቀል፣ አስገድዶ መደፈር፣ የሕፃናት - የእናቶችና የአዛውንቶች ሰቆቃ፣ የከተሞች መድቀቅ፣ የመሰረተ ልማት መውደም - ምኑ ቅጡ… . . . ዛሬ ስለዚህ ፊልም እንዳወራ የገፋፋኝ በታሪኩ ዋና ገጸ-ባሕሪ አማካይነት በፊልሙ መካከል ለዩክሬንያዊው መንገድ መሪ የተነገረ ሸንቋጭ ንግግር ነው… እንዲህ ይላል… “War is a monster that chews up everything in its path.” ~ Connor ደጋግሜ ሰማሁት... ____ አዎን... War is a monster... ጦርነት አውሬ ነው... መቼም ቢሆን አይጠረቃም... ለስግብግብነቱ ልክ፣ ለሆዱም እምብርት የለውም... ባለጠብመንጃውንም ሆነ ሰላማዊውን አኩል ይሰለቅጣል... ሕፃናት አድገው ሰው እንዳይሆኑ፣ ፍቅረኞች ተጋብተው ጎጆ እንዳይሰሩ፣ ሕልሞች ተወልደው እውን እንዳይሆኑ በአጭር ይቀጫል... War is a monster... የአበባ መስኮችን ወደ መቃብር፣ መኖሪያ ቤቶችን ወደ ፍርስራሽ፣ ታላላቅ ከተሞችን ወደ ትዝታነት እስኪቀየሩ ድረስ ያጋያቸዋል... ጦርነት ተስፋን ያገረጣል፣ የነገን ብርሃን ይነጥቃል፣ ሳቅና ጨዋታ በተመላለሰባቸው ቀዬዎች ላይ አስፈሪ ጭጭታን ትቶ ያልፋል... ጦርነት መቼም ቢሆን ሆዱን አሸንፎ አያውቅም... የሚበላው ነገር ሁሉ አልቆ ባዶነት ራሱ ባዶ እስኪቀር መቦጨቁንና መዋጡን አያቆምም… War is a monster... ለእርሱ ልዩ ልጅ፣ የተመረጠ ሕዝብ፣ ወይም ብቸኛ ተበዳይ የለም - ሁሉንም ያደቃል... አስቀድሞ ሥጋን - በመቀጠል እምነትን ይበላል... አስቀድሞ ሕንፃዎችን - በመቀጠል የጥሪት ባለቤትነትን ያፈርሳል... አስቀድሞ ታሪክን - ከዚያም ማንነትን ይበላል... ምድርን በቁስል የተሞላች፣ ነዋሪን በድንጋጤ የታወከ፣ የሞቱትንም በወዳጆቻቸው ልብ ውስጥ ባልተፈጸመ ሕልም ሜዳ እንደቀሩ ብኩኖች ይስላል... ስግብግብነቱ ለመሬት ወይም ለሥልጣን ሳይሆን፣ ሰው ያደረገንን መልካም ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው… War is a monster... የጦርነት አስፈሪው ነገር ገዳይነቱ ብቻ አይደለም የተስፋን ዕድልና የመጻኢ ሕይወትን ሙሉ በሙሉ ማጨለሙም እንጂ... በጦርነት የምትወድቅ እያንዳንዷ ነፍስ - ያልተጻፈ ግጥም፣ ያልተከፈተ መድኃኒት፣ ያልተወለደ ልጅ፣ ያልተጠናቀቀ ሙዚቃ፣ ያልተነገረ "እወድሃለሁ/እወድሻለሁ"፣ ያልተመሠረተ ወዳጅነት፣ ያልተተከለ ድንግል ጫካ፣ እና መቼም ቢሆን ሊመጣ የማይችል ጣፋጭ ትዝታዎችን ሁሉ ይዛ ትቀበራለች… የወግ ቀብር እንኳ አያውቃትም... . . . አውቃለሁ ለሃገሬ ይህ ሃቅ አይጠፋትም... የሆነችውን ሁሉ የሆነችው በጦር ወዳድ ልጆቿ ሰበብ ነው... ይህ ግን ጦርነትን ቤተኛዋ ከመሆን አላስቀረውም... መዝገብ ከሚያውቀው የ3 ሺህ ዓመት ዕድሜዋ እንኳ 9/10ኛው ገጽ የተያዘው በዚሁ አውሬ የውድመት ታሪክ ነው... 'ከባዕዳን' የጥይት አረርም ሆነ ከአብራኳ ክፋዮች ሳንጃ መሞሻለቅ እፎይ ብላ አታውቅም... ግን ዛሬም እዚያው ናት... ዛሬም ጎራዴ ከማርዘም፣ ሰይፍ ከመቆልመም አልወጣችም... ከሰማይ በራሪ እስከ ምድር ተሽከርካሪ ከማጠራቀም አልወጣችም... የጓዳዋን ችግር እንኳ በበጎ ቃል ሕብር መፍታት አልቻለችም... የልጆቿ እብሪት፣ መናናቅ እና ጥላቻ በባሩድ ሽታ እንጂ በንግግር ፋታ ሲረግብ ታይቶ አይታወቅም... [አንድ ላይ ብንሆንም ፈጽሞ አንድነት የለንም...] . . . ይህ በዓለም ዙሪያም የምናየው እብደት ነው... 'ሰልጥነናል፣ ዘመናዊ ሆነናል፣ ሰማያትን መርምረናል' ወዘተ የሚሉን እንኳ ሳይቀሩ ቋንቋቸው አረር ብቻ ነው... [እውነት ለመናገር የሰለጠነው አስተሳሰባችን አይደለም - ማሽኖቻችን ብቻ እንጂ...] እውነት ለመናገር የዚህ ትውልድና አስተሳሰቡ አካል መሆን በጭራሽ አያኮራም!!... ____ የሃገሬ ልጆች ግን እረፉ!!... ጦር የምትስሉት የመለያየት ተስፋ-ቢስ ምናባችሁ ከአንድ የሰው ልጅነታችሁ እውነት በላይ ገዝፎ ስለሚታያችሁ ነው... ግን አስታውሱ... 'ከጠላታችሁ' ሳንባ የሚወጣው አየር፣ እናንተን በህይወት የሚያቆየው ያው አየር ነው... 'ከጠላታችሁ' አካል የሚፈሰው ደም በእናንተም ውስጥ የሚፈሰው ያው ቀይ ወንዝ ነው... ጦርነት የሚጀምረው ሰውነታችሁ ሲደበዝዝ፣ መወገናችሁ ሲጎላና የሰውነት መልክ አጥታችሁ አውሬያዊነት ስትላበሱ ነው... እናም እረፉ - የጦር ክንዳችሁን እጠፉ!! ____ 🦢ሰላም በምድራችን ላይ ይስፈን!!🦢 ____ 📩 [ይህን መልዕክት የሰው ልጆችን ሰላም ለሚሹ ወዳጆችዎ አጋሩልኝ - አመሰግናለሁ] ____ @bridgethoughts
без подписи
ጨረርና ጸሐይ . . . ለህይወቴ ትርጉም የሚሰጣት አዲስ ነገር ለመሆን መባዘኔ አይደለም... ቀድሞውኑ የሆንኩትን ማንነቴን ማስታወሴ እንጂ… በየማለዳው የምነቃው በጸጥታና በድንቅ ስሜት ነው… ከዋክብትን የሚያንቀሳቅሰው፣ አበቦችን የሚያፈካውና ወንዞችን የሚያስጉዘው ያው ታላቅ ኃይል፣ በእኔም ውስጥ እንደሚተነፍስ በማሰብ… በየቀኑ የሚቀስቅሰኝ ብርታት በዚህ ጽንፈ ዓለም ውስጥ እንግዳ ወይንም ከህልውና ጋር ብቻዬን የምታገል ንጡል ነፍስ እንዳልሆንኩ ማወቄ ነው… እኔ የውቅያኖሱ ማዕበል አካል፣ የጽንፈ ዓለሙ ቅንብር ዜማ፣ የህላዌ ዛፍ አንድ ቅጠል ነኝ… ለዚህ ነው - በስራ፣ በምኞት፣ በስኬትና በውድቀት ጩኸት መካከል፣ ማንነትዋን በመዘንጋት ለምትንገላታዋ ነፍሴ ደጋግሜ እንዲህ የምላት፡ ‘እኔ የምልዓቱ አንድ ክፍል ነኝ - ሙሉውም የእኔ አካል ነው…’ ህይወትን ድል ለመንሳት፣ ከእሷ ለማምለጥ፣ ወይም ሙሉ በሙሉ ለመረዳት እዚህ አልተገኘሁም… እዚህ የመጣሁት በህልውና ውዝዋዜ ውስጥ በንቃት፣ በፍቅርና በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ብቻ ነው… አዎን... ከዋክብት ከኔ የራቁ ግዑዝ ነገሮች አይደሉም… እንጅላቶቼ እንጂ… ጽንፈ ዓለም ከውጪ ቆሞ የሚታዘበኝ ባዕድ አይደለም… በእኔ አይኖች በኩል ራሱን የሚመለከት ህያው እንጂ… ወንዞች በደሜ ውስጥ ይፈሳሉ… ምድር በሰውነቴ ውስጥ ትራመዳለች…. ስለዚህ ተግባሬ እጅግ ቀላል ነው… 👉 ህላዌ በጸጥታ ውስጥ ሲያወራ ለመስማት መንቃት… 👉 ራሴን በሌሎች ውስጥ አይቼ እስክመሰክር መውደድ… 👉 ህይወት ያለ ምንም ተቃውሞ በእኔ ውስጥ እንድትፈስ ራሴን ፍጹም ባዶ ማድረግ… 👉 እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከሚፈልቅበት ከዚያ ታላቅ ምልዓት ሳልለይ መኖር… . . . ግና እንደማንኛውም ሰው በየመሐሉ ይህን ተግባሬን እዘነጋለሁ... ወደ ንቃቴ ስመለስ ደግሞ መልሼ እንዲህ እላለሁ: ‘እኔ መንፈሳዊ ጉዞን በመለማመድ ላይ ያለሁ ተራ ሰው አይደለሁም… "እኔ" በሚባል አጭርና ውብ ቅጽበት ውስጥ ራሱን እያወቀና እያስተዋለ የሚገኝ ጽንፈ ዓለም እንጂ…’ ለዚህም ነው 'በህይወት ውስጥ የተለየ ግብና ዓላማ የለኝም - የተለየ ኃላፊነት እንጂ' የምለው… ✅ "የመነጠል" ከሚመስል የቅዠት እንቅልፍ መንቃት ብሎም በሁለንተና መልክ ለሚገለጠው ለዚያ ለ"አንዱ ህይወት" መታያ ሆኖ መኖር… ✅ ፀሐይ ለሁሉ እንደምትፈነጥቀው ሁሉ ያለስስት መውደድ… ✅ በአለቶች መሃል መንገዱን እንደሚፈልግ ወንዝ መፍሰስ… ብሎም... ቀድሞውኑ ወደቆምኩበት እውነተኛ ስፍራ መድረስ… ይህ ነው የኔ ኃላፊነት... . . . በአጭሩ… ለህይወቴ ትርጉም የሚሰጣት፣ ከህልውና የተለየሁ እንዳልሆንኩ ማስታወሴ ነው… በየቀኑ ብርታት የሚሆነኝ፣ ጋላክሲዎችን የሚያንቀሳቅሰው ያው ጥበብ በልቤ ውስጥ እንደሚመታ ማወቄ ነው… 'አንተ በውቅያኖስ ውስጥ ያለች አንዲት ጠብታ አይደለህም… ራሱን በጠብታ መልክ የሚገልጠው ያንኑ ውቅያኖስ ነህ እንጂ' እያልኩ ዘወትር ራሴን አሳስበዋለሁ… ከህይወት የተለየሁ እንዳልሆንኩ ማስታወሴ ደግሞ ለህይወቴ ትርጉም ይሰጣታል… ጋላክሲዎችን የሚያሽከረክረው፣ ውቅያኖሶችን የሚያናውጠውና ደኖችን የሚያለመልመው ያው እውቀት በልቤ በኩል እንደሚመታና በሳምባዎቼ በኩል እንደሚተነፍስ ማወቄ በየቀኑ ያበረታኛል… በዚህ ጽንፈ ዓለም ውስጥ - በስራ፣ በስኬትና በትግል መካከል እንደ ተራ የሚያልፍ እንግዳ እንዳልሆንኩ ማወቄ ያተጋኛል… እኔ - "እኔ" በሚባል ጊዜያዊ መልክ ራሱን እያወቀ ያለ ጽንፈ ዓለሙን ራሱን ነኝ… የእኔ ተግባር ሙሉ መሆን አይደለም… ይልቁንም ከቶውንም ቢሆን ከሙሉው ተለይቼ እንደማላውቅ ማስታወስ እንጂ… ❗️ ማዕበሉ ውቅያኖሱን ፍለጋ ህይወቱን ሙሉ ይባዝናል… በመጨረሻ ግን ቀድሞውኑ ውሃ እንደነበረ ይደርስበታል… . . . (ማስታወሻ: ይህ ጽሑፍ ለገጹ እንዲስማማ ከመሸራረፉ ውጪ ለአንዲት ወዳጄ የነፍስ ጥያቄ በውስጥ መስመር የተላከ ጨዋታ ነው) ____ @bridgethoughts
👀
የተስፋ ነገር... . . . "The mature person does not abandon hope for tomorrow, nor abandon responsibility for today." ተስፋ የአወሳሰድ ምጣኔው እንደማይታወቅ መድኃኒት ነው... እንደ ፈውስነቱ ሊያድንህ፣ እንደ dose ምጣኔው ሊያጠፋህ ይችላል... እርግጥ ነው ተስፋ ጠቃሚ ነገር ነው... ሕይወትን አጨልሞ ከመመልከት ይታደግሃል፣ ደስ በማያሰኙ ሁኔታዎች ውስጥ በጽናት እንድትቆም ያደርግሃል፣ ከማይመቹና ለጸጸት ከሚዳርጉ ውሳኔዎች ይጋርድሃል... ወዘተ፤ ተስፋ የሌለው ሰው ለራሱም ሆነ ለሌሎች አይጠቅምም... ለትውልድ አያስብም፣ ለስብዕናው አይጠነቀቅም፣ ርሕራሔና ፍቅር አያውቅም... በግልጽ ቋንቋ ተስፋ-ቢስ ሰው ጨካኝ ነው... "A person who has completely abandoned hope may lose the motivation to care, create, or protect." ስለዚህ የሰው ልጅ የተስፋ ነዳጅ ያስፈልገዋል... በሌላ በኩል ግን ተስፋ፣ ዓይኖችህን ከዛሬ ላይ አንስተህ ባልተጨበጠ 'ነግ' ላይ እንድትተክል የሚያደርግ አደንዛዥ ዕጽ ነው... እውን (Real) በሆነውና በምናባዊው (Imagined) ሁኔታ መሐል ያለውን ልዩነት ያፈርስብሃል... ነገ የተሻለ ግንኙነት እመሰርታለሁ፣ ነገ የተሻለ ስራ አገኛለሁ፣ ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል... ወዘተ እያልክ ተጨባጭ ከሆነው የዛሬ እውነታህ የሚፈነጥቁ የብርሃን ቅንጣቶችን ከማሳደግ ይልቅ በማይመጣ ነገ ውስጥ የሳልከውን የሚንቦገቦግ ዥረት እያሰብክ ዕድሎችህን እንድታመክን ሊያደርግህ ይችላል... ነገ ምን ውብ ዛፍ ቢሆን የዛሬ መደብ ላይ ከምትዘራው ዘር የለጠቀ እንጂ በተዓምራት የቆመ ሊሆን አይችልም... ለነገሩ ተስፋ ስለ ነገ ብቻ አይደለም - ስለ ዛሬም ነው... 'ነገ ምን እንደያዘ ባላውቅም ዛሬ መልካም ማድረግ አለብኝ' ብሎ ተስፋ ማድረግ አለ... ደግሞ እንደ Victor Frankl እጅግ አሰቃቂ ግፍና መከራ በሚወርድበት የናዚ ካምፕ ውስጥ ሆኖ እንኳ መኖርን የሚያስቀጥል የሕይወት ትርጉም ማግኘት አለ... ብርቱ ገበሬ የሚዘራት እያንዳንዷ ዘር ነገ ዛፍ ሆና ፍሬ እንደምትሰጠው ያምናል... አበው "ገበሬን የሚያህል አማኝ የለም" የሚሉትም ለዚሁ ነው... አፈር ላይ የጣላት ነቁጥ ጥሬ ለእልፍ ፍራፍሬ ምክንያት እንደምትሆን ያውቃል... በዚህም ምክንያት ዕለት ዕለት ለዘሯ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያደርጋል... 'የነግ ተስፋ' አሸንፎት ግን ድርስ አዝመራ ወይም ሙሉ ጎተራ፣ የደለበ ከብት ወይም የመና በረከት ቁጭ ብሎ አይጠብቅም... ነገሩን በመንፈሳዊ ዕሳቤ ውስጥ ካየነው፣ ገበሬው ችግኝ የሚተክለው እኔ እጠቀምበታለሁ ብሎ ብቻ ላይሆን ይችላል... እርሱ እንኳ ባይኖር ለሌሎች ጥላ እንዲሆን አስቦም ጭምር እንጂ... ___ ነገሩን ለማጠቃለል... ተስፋ ከዛሬ (ከተጨባጩ እውነት) እስካፋታህ ድረስ ጤናማ አይደለም - ይልቁንም ለቅዠት ይቀርባል... የነገ ውጤትህን አሁንህ ላይ እያየህ እንድትበረታ ሲያደርግ ግን ጉልበት ነው... ስለዚህ... ለሰው ልጅ የእውነታ ስርም፣ የምናብ ክንፍም ያስፈልገዋል... ክንፍ ያጣ ስር እስረኛ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ ስር የሌለው ክንፍም ቅዠታም ያደርጋል... ሁለቱን ማዛነቅ ግን ጥበብ ነው... መድኃኒትም ቢሆን በአወሳሰድ ምክንያት መርዝ ሊሆን ይችላልና!! ___ "Hope should not be a place where we hide from today. It should be the light that helps us walk through today." ____ @bridgethoughts
When we have lived with a problem for a long time, the first thing that exposes the problem may appear to be the cause of the problem. . . . እንደምታውቀው ጥርሱን ሳይፍቅ/ ሳይቦርሽ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሰው የአፉ ጠረን እንደሚያስቀይም ለመረዳት ሩቅ ነው... እንዲህ ዓይነት ሰው ለተወሰኑ ቀናት የጥርስ ሳሙና መጠቀም ቢጀምርና መልሶ ቢተዉ እንኳ የአፉን ሽታ በተለየ መንገድ ለማስተዋል ዕድል ስለሚያገኝ 'በምን ምክንያት ነው ይህ ሽታ የተፈጠረብኝ?' ብሎ መጠየቁ አይቀርም... ሁኔታው በቅርብ ከጀመረው የጥርስ መቦረሽ ጉዳይ ጋር ስለሚያያዝበት ወደ አዕምሮው ቶሎ የሚመጣለት ድምዳሜ ‘የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል’ የሚል ነው… ስለምን?... ነገሩ ወዲህ ነው... ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት የአፉን መጥፎ ጠረን ተላምዶት ስለቆየ ‘አፍህ ይሸታል’ ቢሉት እንኳ አይሰማም ነበር… ወይም ደግሞ እንደ ችግር ለመቀበል ይከብደው ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳትና መለየት ስለሚጀምር፣ ሽታውን እንደ አዲስ ክስተት ወስዶ ሰበቡ 'አዲሱ እንግዳ ነው' በሚል የጥርስ ሳሙናን ለማውገዝ አንደኛ ይሆናል… "Sometimes the thing that disturbs your comfort is the thing that restores your clarity." በአጭሩ... እንከን ጠቋሚው ከእንከን በሚጸዳበት ወቅት የነበረውን አጋርነት አይረዳም… — ይሄ አዲስ ዕውቀት አይደለም... አፍንጫ ሊቆርጥ በሚደርስ መጥፎ ጠረን የተቀላቀልከው መጸዳጃ ቤት እንኳ ትንሽ ስትቆይበት 'ሽታ የለም' አስብሎ ሊያስክድህ ይችላል... መላመድ ክፉ አባዜ ነው... __ የሆነስ ሆነና... ጠረን እንድትለይ የረዱህን ‘ብሩሾች’ ስንቴ ‘አፍ ያሸታሉ’ ብለህ ጣልክ?… ስንቴስ ከእድፍ ያላቀቁህን ሳሙናዎች 'ጥርስ ያሳድፋሉ' ብለህ አወገዝክ?... ስንቴ ወደ ቀደመ ሽታህ ለመመለስ ተንደረደርክ?… ስንቴስ ለልማድ አጎበደድክ?... __ ተገንዝቦት (Awareness) ሁሌም ጅምሩ አስደሳች ነው ብዬ ልሞግትህ አልደፍርም... ምክንያቱም የተገንዝቦት የመጀመሪያ ግብ ልናይ የማንሻቸውን ነገሮች ማስተዋወቅ ነውና... በምሳሌ ብናየው... የመስታወት ግብር የቆዳህን ሽብሽብ መፍጠር አይደለም - ገልጦ ማሳየት እንጂ፣ የላምባዲና ድርሻ አቧራ መውለድ አይደለም - መጠቆም እንጂ፣ የመምህር ግቡ ድንቁርናን መስጠት አይደለም - ዕውቀት የሚያሻውን ክፍተት መጠቆም እንጂ፣ አዎን እነዚህን ማየት አያስደስት ይሆናል... ጥያቄው ግን 'ጉድለትን ሳያውቁት እንዴት ይሞሉታል?' የሚለው ነው... ___ ብዙ የሚፈትኑን ነገሮች እርግጥም እየረዱን ይሆናል... ቀጥተኛ መምህራን፣ ሕመም የተሞሉ ልምምዶች፣ ለመቀበል የከበደን ሃቅ፣ ምቾት የነሳን የወዳጅ አስተያየት... ብዙ ነገሮች፤ ነገሩን ከኢጎ ሳንጸዳ ካየነው "ለምንድነው ሰላም የሚነሱኝ?" ያስብለናል... በለውጥ ውስጥ ሆነን ስንረዳው ግን "አስቀድሜ ላየው ያልቻልኩትን ችግር እንድገነዘብ ስላደረግኸኝ አመሰግናለሁ" ለማለት እንደፍራለን... ___ "The first enemy of transformation is not the problem itself; it is our attachment to what has become familiar. We often reject the hand that cleanses us because cleanliness makes us aware of the dirt we had learned to ignore." ___ የመዳን መጀመሪያ ስለ ቁስልህ ጠንቅቆ ማወቅ ነው!!... ___ @bridgethoughts
. . . ታክሲ ውስጥ ነኝ... ኋላ ወንበር ላይ ቁጭ ብያለሁ... ክ/ሃገር ለመሄድ ነው ወደ አውቶብስ ተራ የሚወስዱኝን ጎማዎች የምከተለው... አጠገቤ አንድ ጎልማሳ ተቀምጧል... በተሽከርካሪ መጓዝ ምቾት የሚነሳኝ ዓይነት ሰው ስለሆንኩ በመዳረሻዬ ላይ እንጂ በመጓጓዣዬ ሁነት ብዙ አልመሰጥም... በዚህ ምክንያት ወሬ አልሰማም - ወይም ሲያወሩኝ አልወድም... ሰውየው ግን ጆሮ እንዳለኝ እንጂ ሁኔታ መርጬ እንደምገለገለው አያውቅም... ስናወጋ እንደቆየን ሁሉ ከመሐል ጀምሮ ማውራት ጀመረ... ምናልባት በውስጡ የሚመላለሰው ሃሳብ ከአፉ ድንገት አፈትልኮ ሊሆን ይችላል... ሆኖም ቀልቤን መግዛት አልተሳነውም... ብርቱ ቃል ያሸንፈኛል - ደካማ ጎኔ ነው... [ቀጥሎ የምታነቡዋቸው መስመሮች ክልበ-ቢስ ልቤ የተንጠባጠቡ የማላውቀው መንገደኛ ተብሰልስሎቶች ናቸው...] . . . "... እኔ እርሷን የምወድበት አቅም፣ እርሷ ገንዘብን ከምታመልክበት ጉልበት ጋር ሲነፃጸር መቶ እጥፍ ያንስ ነበር... እናም ተውኳት!!... መውደዴን ሳይሆን ፍለጋዎቼን ተውኩ... ማፍቀሬ ላይ ሳይሆን መከተሌ ላይ አመጽኩ... አውቃለሁ ፍቅርን የሚስተካከል ሐብት እንደሌለ... አውቃለሁ መውደዴን ገንዘብ እንደማያክለው... ይህ ግን ለኔ እንጂ ለእርሷ የሚዋጥ አይደለም... እውነት ለመናገር ገንዘብ ፍለጋ መሄድ እችል ነበር... በሃቅ ወይ በረቂቅ ሐብት ማካበት እችል ነበር - ሆኖም ምርጫዬ አላደረኩትም... ፍቅሯን በማጣት ላይ ፈርጄ ግን አልነበረም - ራሴን አጥቼ እርሷን ባገኝ እርባን የለውም ብዬ እንጂ... ቀልቧን እንጂ ልቧን ለማግኘት ዋስትና አይደለም ብዬ እንጂ... ደግሞስ... በገንዘብ ያገኙት ልብ በገንዘብ እንዳይሄድ መቋጠሪያው ምንድነው?... ባለኝ እንጂ በሆንኩት ላይ ያልቆመ አብሮነት ጽናት ምኑ ነው?... አዎን... የማይጠረቃን የንዋይ ጥንወት በመውደድ እጆች ማስካድ አይቻልም... ገንዘብ እያሳዩ የሚስቧት ሴት አጥንት እያሳዩ ከሚጎትቱት ቡችላ በምን ትለያለች?... ስለዚህ... ተውኳት!!..." . . . ___ "ወራጅ አለ" ድንገት ጮኸ... ሁላችንም ደነገጥን... ሰውዬው ድንገቴ ነገር ነው... በተለመደው የተግባቦትና የንግግር ደንቦች አይዳኝም... ይህ ግን የአድማጭ ጆሮ ከመማረክ አላገደውም... ከልቤ አሳዘነኝ... ተውኳት ሲል የማይተው ተቆጣጥሮት ቢሆንስ?... እንደ ታክሲው 'ወራጅ አለ' ያላለው የሆነ ዓይነት ነገር ተጣብቶት ቢሆንስ?... ___ መንገደኛው በየራሱ መንገድ የጎልማሳውን ጉዳይ ይበልት ገባ... እኔ ወዲህ በ Buddha ቃል ተወስጄ ነበር... "Anger will never disappear so long as thoughts of resentment are cherished in the mind" ___ @bridgethoughts
📌 . . . በውዳሴ ወቅት የምታሳየው ፈንጠዝያ፣ በወቀሳ ጊዜ ለመሰበር ያለህን ፍጥነት አመልካች ነው... ለሙገሳ ፈጥኖ እጅ የሚሰጥ ሰው በውግዘት ወቅት በፍጥነት ይፈራርሳል... ብልህ ሰው ግን ሲያሞግሱት በዝምታ ያልፋል - ከቁምነገር አይጽፈውም... ሲያወግዙትም አንዳች ሳይረበሽ ጸንቶ ይጓዛል - በግሉ አይወስደውም... ዓለሚቱን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ ሰውንም ከእጁ መዳፍ በላይ በማንበብ ስለሚራቀቅ እያንዳንዱ አጋጣሚ በቀላሉ አሻራውን የሚያትምበት የመንገድ ላይ ሸራ ከመሆን ነፃ ወጥቷል... ስለምን ቢሉ... ብልህ መሆን ማለት "ይህም ያልፋል!!" ይሉትን ብሂል መገንዘብ ነውና... ___ The moment you are disturbed by insult or pleased by praise, you are still slave ~ Osho ___ @bridgethoughts
_ የቤቲ ሼርን አልበም ሰምተን ስናበቃ የምጋብዛትን ሙዚቃ ርዕስ ጠየቀችኝ... ብዙ ጊዜ አዲስ አልበም ሲወጣ ተመሳሳይ ልማድ አለን... "አካልዬ" አልኳት... እውነቴን ነበር፣ እርሷን እያሰብኩ ነው ያደመጥኩት... ዝም አለችኝ... "ያንቺስ ግብዣ ምንድነው?" ድርሻዬን ጠየቅሁዋት "ቻው ቻው" አለችኝ... በተራዬ ዝም አልኩ... __ ጊዜና የሰው ልጅ እንደ ሙዚቃ አልበም ናቸው... ውስጣቸው መንታ ስሜት ባላቸው 'ስልቶች' የታጨቀ ስለሆነ መቼ የቱን "ሙዚቃቸውን" እንደሚጋብዙህ አታውቅም... ___ @bridgethoughts
. . . "ይህን ነገር እያመለክሽው አልመሰለሽም?" "ገንዘብ አልወድም እያልከኝ ባልሆነ" "አልጠላም፤ ነገርግን አገልጋዬ ላይ ጥገኛ መሆን አልፈልግም" "ተገልጋይ በአገልጋዩ ፍቅር አይወድቅም ያለህ ማነው?" "እኔ ጌታ ነኝ፣ ከአገልጋዬ ጋር በፍቅር ወድቄ ክብሬን ማጣት አልፈልግም" "ያለ ሃብት ክብር የለም ባክህ" "ከማንነትሽ የማይመነጭ ክብር - ክብር አይደለም" "ስለየትኛው ክብር ነው የምታወራው?" "ስለ ሁሌያዊው ክብር፤ በስብዕናሽ ጥራት ብቻ ስለሚገነባው ክብር፤ ሰዎች ሊሰጡሽ ወይም ሊከለክሉሽ ስለማይችሉት ክብር፤ በሁኔታዎች ላይ ስለማይንጠለጠለው ክብር፤ አንቺ ስለራስሽ ባለሽ ግንዛቤ እንጂ ሌሎች ስላንቺ ባላቸው ግምት የማይቆመው ክብር..." "ሌሎች ካላከበሩኝ እኔ ዋጋዬን ብቆልል ምን ያደርጋል?" "ለራሱ ክብር የሌለውን ሰው ሌሎች አያከብሩትም፤ ክብር ውስጣዊ ነው" "እርሱ ቅዠት ነው፣ ክብር አይደለም" "ያልተረዱትን ማኮሰስ የተለመደ ስንፍና ነው" "ኖረው ያላዩትን ድሎት ማጥላላትም ያው ነው" "ያለኝ ይበቃኛል ማለትን ማወቅ ግን የስብዕና ከፍታ ነው" "ለብቻህ ፃድቅ መሆን አትችልም ባክህ" "ለብቻ መቆም ነው ጽድቄ" "ግትር ተብሎ መገለል አያስፈራህም?..." "በራስ ፊት ማፈር ብቻ ነው የሚያስፈራኝ" "ለምን ባሕታዊ አትሆንም ታዲያ?" "እዚህ ያለሁት ራሴን ብቻ ለመሆን ነው" "በዚህ አቋምህ እኮ ነው ሰው ሁሉ የሚሸሽህ" "ከእኔ አይደለም የሸሸው ከህሊናው ሙግት ነው" "ህሊና ህሊና አትበለኝ ባክህ... ድሃ ሆኜ ህሊናዬ ባይወቅሰኝ ሆዴ ዝም ይለኛል?" "አፍሽ የሚጎርሰውን እጅሽ መመጠን እስካልቻለ ድረስ ሆድ መቼም በቃኝ አያውቅም" "ሃብት እኮ አይጠገብም" "በቃኝ ማለት ግን ይቻላል" "ትንሽ ነገር አያረካማ..." "ከእጅሽ ያለው ትንሽ እንደሆነ ማሰብ ካላቆምሽ ምድር ሙሉዋን ሃብትሽ ብትሆንም አትረኪም" "ከጓደኞቼ አንሼ መታየት አልፈልግም" "ፉክክር እስካለ ድረስ ለራስ መኖር አይቻልም" "ካልተፎካከርክማ መጨመር አትችልም" "መኖር የሚመዘነው ባገኘነው ሃብት መጠን ሳይሆን ለራሳችን በፈጠርነው አፍታ ልክ ነው፤ በማግኘት ላይ ብቻ ከተመሰጥሽ ለመኖር ጊዜ ስለማትሰጭ ምንም ማድረግ የማትችይባቸው ቀናት ሲመጡ ጸጸት ይቆጣጠርሻል፤ ፉክክር ጉድለትሽን ብቻ እንጂ ሙላትሽን እንድታይ ዕድል አይሰጥም... ሃብት ይኑርሽ፣ ግን ደግሞ ኑሪበት" "ኑሪበት ስትል..." "አፍታ ፍጠሪበት፣ ቆም ብለሽ ስክነት ግዢበት፣ ወደፊት አገኘዋለሁ ከምትይው ላይ ዓይንሽን ንቀይና ባገኘሽው ላይ ትንሽ አተኩሪ፣ አጣጥሚው... ወደድሽም ጠላሽ ከዚህች ቅጽበት ውጪ እርግጠኛ ጊዜ የለንም... አንዳንዴ ከእጅሽ ያለው ሁሉ ያንቺ እንዳልሆነም አስቢ - ለሌሎች በኛ በኩል እንዲደርስ እጃችን የሚገባ አደራም ይኖራል - እርሱን ለሚገባው ማድረስንም ልመጅ" "አደራ" "አዎን አደራ... አስር ቤቶች ቢኖሩሽ የምትኖሪው በአንዱ ብቻ ነው፣ መቶ መጫሚያ ቢኖርሽ በአንድ ጊዜ የምታደርጊው አንዱን ነው፣ አስር መኪና ቢኖርሽ በአንድ ጊዜ የምታሽከረክሪው አንዱን ብቻ ነው... አንዳንድ ነገሮች እጃችን ላይ ሲበዙ ሁለት ነገር ማሰብ ይቻላል፤ የመጀመሪያው የእርካታ እጦታችን ነው፣ የነበረን ሲያንስብን ለመጨመር እንሮጣለን፣ መጨመሪያውን ለማግኘት መኖርን እንገብራለን... ሁለተኛው መጋራት አለማወቅ ነው፣ አንቺ አንዱን በሌላው ላይ ለመደረብ ስትከንፊ የነገዋን ጸሐይ ማየት ብርቅ የሆነበት ደግሞ በየዕለቱ ይረግፋል..." "ሰርቶ አይበላም ታዲያ?" "ሳይሞክር ቀርቶ አይደለም - የላቡን ያህል ማግኘት ምጥ ሆኖበት እንጂ... የማይገባቸውን በሚሰበስቡ ጥቂቶች ምክንያት የሚገባቸውን የማያገኙ እልፎች መብዛት፣ ዓለማችን ያነበረችው ዕብድ የገበያ ስርዓት ውጤት ነው" "ገበያው ምን አደረገ?..." "አግበስባሽነትን አበረታ፣ ከሰው ሁሉ እጅ ላይ ያለውን እያንኳሰሰ የሌለን በመጨመር ውጥረት ውስጥ ከተተ፣ ትናንት በብዙ ውዳሴ አማልሎ ከእጅሽ ያስገባውን ቁስ ዛሬ ከፈጠረው ሌላ ቁስ ጋር እያነፃፀረ ያሳንስብሻል፤ እርሱን ለመቀየር ስትሮጪ ደግሞ ሌላ አዲስ መጥቷል... የዘመኑን ሩጫ በነባር ፍጥነት መስተካከል አልሆንላቸው ያለ በማግኘት ላይ ብቻ ተመስጠው የማይገባቸውን ይመኛሉ፤ ይሄኔ ገበያው ማጭበርበርና የራስ ያልሆነን መሰብሰብ በሚፈቅዱ ሰዎች ይሞላል... ይህ በሌላ ጎኑ ጥሪት አልባውን ይገፋል..." "ሃብትን ታወግዛለህ ልበል?" "ሃብትን አናወግዝም፣ ከሃብት ብዛት የሚመጣውን ትዕቢት እንጂ - ይላል ዮሃንስ አፈወርቅ" "ትዕቢተኛ ነሽ እያልከኝ ነው?" "አንቺ አልሽ!" "በኑሮህ ግን ደስተኛ ነህ?" "ከባድ ጥያቄ ነው፤ ግን ደግሞ ያለኝ ስለሚበቃኝ በጎደለኝ ላይ ለማተኮር ብዙ ዕድል አልሰጥም" "እኔ ግን ደስተኛ አትመስለኝም" "ደስተኝነት ለራስ እንደሚሰማው ነው፣ ለሌሎች እንደሚታየው አይደለም" "እኔ ግን ከስንት አንዴ ነው ደስታ የሚሰማኝ" "ይህንን ነው ያልኩሽ፣ ደስታ የሃብት ውጤት አይደለም፤ አዕምሮአዊ ቅኝት ነው" "እና ምን ላድርግ?" "ዓይኖችሽን ከጉድለት ገጾችሽ ላይ ንቀይ... በረከቶችሽን ቁጠሪ፣ እዚህና አሁን ኑሪ" "እርሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?" "ደስታ የምናጣው በእልፊት ጸጸትና በመፃኢ ፍርሃት ውስጥ ስለምንቦራጨቅ ነው፤ ሁለቱም ከአንቺ ቁጥጥር ውጪ ናቸው... አሁንና እዚህ ግን ምርጫዎችሽን እንጂ ስህተትና ስጋትሽን አትኖሪም..." "ስለ ነገ ካላሰብኩ ምኑን ኖርኩት?" "የተሰጠሽ ዛሬ ላይ ሳትኖሪ በሌለ ነገ ውስጥ መኖር አትችይም፤ ነገም ሲደርስ ያው ዛሬ ነው፣ ካልኖርሽበት ሌላ ነገ ያስጠብቅሻል፣ ከተገለገልሽው ግን የአፍታ ዘላለማዊነትን ሃቂቃ ይገልጥልሻል" "ሃብታሞች ሁሉ እየኖሩ አይደለም ብለህ ነው የምታስበው?" "የፍርድ ወንበር ላይ አልተቀመጥኩም፤ ግን አስታውሽ፣ የሁላችንም የመኖር ትርጉም አንድና ያው አይደለም" "ስለነገ የሚያስቡ እየኖሩ አይደለም እያልከኝ..." "ለመኖር ጊዜ ካልሰጡ አዎን፣ እየኖሩ አይደለም" "ጊዜ መስጠት ስትል..." "ወደ ተራራው ጫፍ ለመውጣት የሚያስቡ መንገዳቸው ላይ በየመሐሉ አረፍ ማለትን ይማሩ ማለቴ ነው... የሰበሰብሽውን ለመብላትም ጊዜ ያስፈልግሻል" "ተራራው ግን ጫፍ የለውም" "ልክ ነሽ፣ በሄድሽ ቁጥር የአንዱ ተራራ ጫፍ የሌላኛው ተራራ መነሻ መሆኑ ይገለጥልሻል" "ፍለጋው አያልቅማ" "አዎን - ትርፉ መባከን ነው፤ ባገኙት መብቃቃት ግን ነፃ ያወጣል" "መጨመር ሲያስፈልግስ?..." "ላለው የሚያስፈልገው ሁሉ ይጨመርለታል" "ምን ላለው?" "ምስጋና!!" _ @bridgethoughts
❗️ . . . 🔔 ባለፈው እንዳልኩህ ነው... 🔔 . . . 🔘 ቅድሚያ የሰጠኸው ሰው - ከፊትህ አክብሮትን ሳይሆን ፍርሃትን ካነበበ፣ 🔘 አደራ የሰጠኸው ሰው - የልብህን ማመን ሳይሆን የድርጊትህን ሞኝነት ካሰበ፣ 🔘 ሙሉ ጊዜህን የሰጠኸው ሰው - ፍቅርህ ሳይሆን ስራፈትነትህ ከተሰማው፣ 🔘 ያለህን ያካፈልከው - ችሮታህን ረስቶ መጠኑ አንሶ ከታየው፣ 🔘 የረሳህለት ሰው - ይቅር እንዳልከው ሳይሆን እንዳልተሰማህ ሆኖ ከገባው፣ 🔘 ያገለገልከው ሰው - እርዳታህን ትቶ ግዴታህን ብቻ ካሰበው፣ 🔘 የበላይ ነኝ የሚል - የሃሳብህን ፋይዳ ከቆምክበት መደብ ካለካካው፣ 🔘 የእጅህን ንጽህና የሚያውቅ - 'ዕድል ስላላገኘህ እንጂ መስረቅ ስላልፈለክ አይደለም' ማለት ከዳዳው፣ 🔘 ቆርሰህ ያካፈልከው - የሰጠኸውን ሳይሆን ከእጅህ የቀረውን ከተመኘው፣ ➡️ ደግሞ ወዲህ... 🔹 ግማሽ መንገድ የሄድክለት - ከጠበቀህ በቆመበት፣ 🔹 ስለሚያውቅህ ጡብህን ንቆ - የሩቅ መናኛ ካየህ አድንቆ፣ 🔹 ለወፌ ቆመች ተለጉሞ - ይድፋህ ለማለት ካደረ ቆሞ፣ 🔹 እንዲለወጥ እጅ ያላቀበለ - ለትችት ከተቀባበለ፣ . . . ⚠️ ወዳጄ - ያንጊዜ መንቃት ጥሩ ነው... ___ @bridgethoughts
. . . 👍 ታዘባርቀኛለች.... አልደርስባትም... በየቀኑ ቅኔ ትሆናለች... “እንደዚህም መኖር ይቻላል እንዴ?” የምታስብለኝ ብዙ ነው... ለማኅበረሰብ ወግና ሥርዓት ስትገዛ አላውቃትም... ➡️ ‘ሰው ግን እንዴት እንዲህ በሚያምር መንገድ ያምፃል?’ ታስብላለች... ያውም ‘እንዲህ የማደርገው ለዚህ ነው’ በሚል ማብራሪያ ሳታጅበው... ያውም ክብሯን እንደ በትረ መንግሥት ይዛ... በዙሪያዋ ያሉ ሁሉ እንዲህ መኖር አለባት የተባለውን ሳይሆን የምትኖረውን ልክነት እየተነተኑላት… ድርጊት የተሻለ ያሳምናልና - ፍሬዎቿ ውስጥ የቀሰሙት እውነት ልዕለ ስብዕናዋ ሆኖላት... ➡️ እጇ ከመስጠት አይሰንፍም... ለመቀበል ግን ሩቅ ናት... ስታማርር አልሰማሁም... የተሸከመችው ጓዝ እኔን እያንሻፈፈኝ እርሷ ፈገግታዋ ሳይነጥፍ በሚዳሰስ ኃይል መንገዷን ትቀጥላለች... ለራሷ ያላት ቦታ በየትኛውም ውጪያዊ ክስተት የማይነካካባት እርሷ!... ➡️ ደግሞ ለስላሳ ትሆናለች... ጥል ቀርቶ በጎኗ ያለፈ ሁሉ ከፍቶት እንዲያልፍ የማትሻ፣ ሁለት ፀጉር ያላቸው የዘመን ባለፀጎችን ሳይቀር እንደ ህፃን አባብላ መሸኘት የምትችል.... ደግሞም ተዋጊ… ድንበሯን ያለፈ ሁሉ ያቺን ቀን እስኪረግም፣ "የሞተ ገድሎ አይፎከርም" እንዲሉ አሸንፋ ይቅር ብላ እስክትመለስ የማታቆም.... ➡️ ታስገርመኛለች… እንደ እርሷ መሆን ያማልለኛል… ታዘባርቀኛለች… ➡️ እንደዋዛ የምትኖረውን የህይወት ፍልስፍና ሞክሬ በእርሷና በራሴ መሃል የጠፋሁት ጥቂት አይደለም... ታስፈራኛለች… ተነጥዬ ልተነትናት ላያት አልችልም፣ ትፈትነኛለች… ‘እንዴት ቻልሽበት?’ ጥያቄዎቼን ብዙ ሳታብራራ ታተናቸዋለች... ➡️ ‘የምር የሚኖረው እንዲህ ይሆን እንዴ?’.... እንጃ!?!? ➡️ የሆነው ሆኖ በዘመኔ ሁሉ ዓይኖቼ እርሷ ላይ ነበሩና በደመነፍሴ ነው የማውቃት... እርሷን!! ➡️👈 ተፃፈ - በእሙዬ ➡️👈 ✈️ @yeesua_queen
⚠️ . . . In a world still divided by lines we invented, the voice of echoes louder than ever through. “Until the philosophy which holds one race superior and another inferior is finally and permanently discredited and abandoned… everywhere is war.” Look around. Different flags, same pain. Different languages, same tears. This is not just a song. It is a mirror. A reminder that true peace is not signed on paper, but realized in consciousness. The war is not only out there. It is within us. And so is the peace. 🦢🦢 ____ @bridgethoughts
❗️ . . . "ጥቃትን እየለመድንና ለሺዎች ሞት ግድ የለሾች እየሆንን መጥተናል" ~ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ __ መጋቢት 27/2018 ___ @bridgethoughts
📩 . . . 🔻ግለሰብ ሆነህ አንድ ሰው ብትፈነክት፣ ወይ እስር ወይ ብድር ይቆይሃል... 🔺ግለሰብ ሆነህ አንድ ሰው ብታስፈራራ፣ ወይ ፖሊስ ወይም ቦክስ ይጠብቅሃል... 🔹ግለሰብ ሆነህ የአንድ ሰው ንብረት ብታወድም፣ እማኑኤል አልያም ጸበል ይሰዱሃል... 🔵ፖለቲከኛ ስትሆንስ?... 🟠መሪ ስትሆንስ?... 🟢የሃብታም ሃገር ቁንጮ ስትሆንስ?... ❕ በአንተ ዕብደትና ዕብሪት ምክንያት: አንድ ግለሰብ፣ አንድ ማሕበረሰብ፣ አንድ ሃገር አይደለም ሙሉዋ ዓለም በፊትህ እንደ ዶሮ ብትፈነገል እንኳ አንዳች የሚናገርህ የለም... ምናልባትም 'ግፋበት' የሚልህ ይበዛ ይሆናል... ____ ❕ ወደድንም ጠላን የዓለም ስርዓት በጉልበተኞች የተፈጠረ ነው... ምድሪቱ የእኔና አንተን መስተጋብር የሚያስተናግድ ስሪቷን - 👉 ጦርነት መስራት ሃብት በሆነላቸው፣ 👉 ገንዘብ ማግበስበስ በማይሰለቻቸው፣ 👉 ቢያብዱም 'ታከሙ' በማይሏቸው [አንድ እጅ በማይሆኑ ሰዎች] ምክንያት ያኔ - ጥንት - ድሮ አጥታዋለች... ____ "አንድ እግር በርበሬ፣ መንቀል አቅቷችሁ፣ አቃጥሎ ለብልቦ፣ አንድዶ ፈጃችሁ" ያለችው ማን ነበረች?... ____ ምዕራባውያን ግን፣ ዛሬም የአፍሪካ መሪዎችን "አምባገነን" ብለው ይጠራሉ ኣ?... አፍሪካውያን ይህን ሲሰሙ "በሕዝባችን ምን አገባችሁ?" የሚሏቸው ይመስለኛል... [የድችሪና የጉልጉሊ] ትንግርት ዓለም... ____ @bridgethoughts
📣 Today's Reminder ➡️ Don't Escape Life - Experience it. 🟢🟢🔴 @bridgethoughts
🔺 የዚህ ዘመን 'ውበት' ምንድነው?... [መጠየቅ እንጂ መመለስ ግቡ ያልሆነ የዕረፍት ቀን ሃሳብ...] 💠💠💠 አንድን ሰው (ተባዕት ወይም እንስት) በቆንጆ ወይም ፉንጋነት ቅርጫት ውስጥ የምንዶልበት መሳሪያ ምንድነው?... ማለቴ፤ 'እከሊት ቆንጆ ናት'፣ አልያም 'እከሌ ማራኪ ነው' የምንለው በምን መለኪያ ነው?... ጥያቄውን - ብትፈልግ በባዮሎጂካዊ፣ ሲያሻህ በባሕላዊ፣ አልያም በስነልቡናዊ መንገድ እየመዘንክ አብሰልስለው... እኔ ግን ለሁለታችንም እንዲቀርብ ሃሳቤን በባዮሎጂካል [በገላ፣ በአካል ቅርጽ፣ ወይም በላዕላይ ገጽታ] ውበት በኩል አስታክኬ ልጋራህ... ይህን ስልህ ታዲያ 'መስፈርታችን ዓለም አቀፍ መለኪያዎች ናቸዋ' እንዳትለኝ... እንኳን በዓለም አቀፍ በሃገር አቀፍ ድንበር ውስጥም ለውበት የሚሆን ወጥ መለኪያ የለንም... ለምሳሌ 🔤 ⬜️ አንድን የሱርማ ወንድ፣ 'ቆንጆ ሴት ምን ዓይነት ናት?' ብትለው የሚሰጥህ መልስ ከአንድ አዲስአበቤ ወንድ የሴት ውበት ትንተና ጋር በጭራሽ ላይገጥም ይችላል... 🟢 የአንዲት ከተሜ ወጣት የውበት መስፈሪያና የቁንጅና ትንተናም ለአንዲት የሐመር ልጃገረድ የማይዋጥ ሊሆን ይችላል... 🟠 እንዲያውም የውበት ብያኔ ከሁሉአቀፍአዊነት ይልቅ ሰፈርተኝነት ይጫነዋል... ሰሜኑም ሆነ ደቡቡ፣ ምስራቁም ይሁን ምዕራቡ ያላቸው የውበት ቀኖናና የቁንጅና ዶግማ አንድና ያው አይደለም... “Taste classifies, and it classifies the classifier.” ~ Pierre Bourdieu 🔹🔹🔹 ተረቶቻችንና የሰርግ ቤት ዘፈኖቻችን የውበት መስፈርት ለክተው የሚነግሩ - የፉንጋነትንም ጥግ የሚዘክሩ በነበረበት ዘመን የተወለዱ የዚህ ዘመን ጎልማሶች ውበትን የሚረዱበት መነጽር በወላጆቻቸው ምናብ ልክ ተሰርቶላቸዋል... ዛሬ ደግሞ መደበኛውና ማሕበራዊው ሚዲያ የሚያጸድቀው ሆኖም ከጀርባ የፋሽን ኢንደስትሪው የሚመራው የውበት ልኬት በዙሪያችን አለ... በዚህ ምክንያት፣ ውበት ከተፈጥሮአዊ ምልክትነቱ ይልቅ የገበያ ቀለምነቱ ጎልቶ ይታያል... ይህ ዘመን በዚህ ረገድ ዝቅተኝነት፣ መስሎ አዳሪነት፣ ያለ አቅም ኗሪነት፣ እንዲሁም የሰው ሰራሽ መጊያጊያጫ ሰብሳቢነት የሚስተዋልበት የ Consumerist ማሕበረሰብ ምንጭ ነው ማለት ይቻላል... ከአንዳንድ የሶሻል ሚዲያ፣ [በተለይም ቲክቶክ] የፎቶና ቪዲዮ ፖስቶች ስር የምታዩአቸው የሙገሳና የነቀፋ ቃላት ዘመኑ ውበትን የበየነበትን መንገድ ለመረዳት ቀላል አማራጭ ከመሆን ባሻገር ሰዎች በላዕላይ ጌጥ እንጂ በልቡና ፈርጥ በኩል በጭራሽ እንደማይስተዋሉ ትልቅ ማሳያ ሆነው ያገለግላሉ... አዎን - ብዙ እንስቶችን በመልካቸው እንዲሸማቀቁ የሚያደርጉ ዕልፍ ስድቦች አሉን... ለወንዶች ሲሆን ደግሞ [ገንዘብ ይኑራቸው እንጂ] ሁሉንም ነውራቸውን የሚሸፍን ስምምነት አጽድቀናል... 'ከጉማሬ መለስ ካለ በቂ ነው'... በዚሁ ግርምቢጥ ዘመን፣ ብዙ ሴቶች [አንዳች ቁምነገር ሳይኖራቸው] መስታወት ፊት ቀርበው ስለተወናወኑ ብቻ ዕልፍ Like፣ ውዳሴና ጭብጨባ የሚያዘንብ መንጋ ከስራቸው ይኮለኮልላቸዋል... [ጥበብ፣ ዕውቀት፣ ፈጠራና ብስለት በፊት ገጽታና በአካል ቅርጽ ፊት አፈርድሜ ይበላሉ ማለት ነው...] 💠 ይህ ጉዳይ በደንብ የሚገባህ፣ Plane ለመስራት የሚታትር ወጣት Post ስር የምታያቸውን ስድቦች ምሬት እና 'ከመልክ' እና ጌጣጌጥ ውጪ ምኗንም ባላሳየችን አንዲት ሴት ልጥፍ ስር የምታያቸውን ሙገሳዎች ስታነፃጽር ነው... ዳዴ በሚል ሞካሪ ፊት 'ወፌ ቆመች' የሚሉ አንደበቶች ተዘግተው፣ 'ይድፋህ' የሚሉ ስራፈቶች መብዛታቸው የውበት ሚዛን ለመዛነፉ ዓብይ ማሳያ ነው... 💠💠💠 እኔና አንተ "ውበት እንደ ተመልካቹ ነው" ለሚለው ብሉይ ጥቅስ እንግዶች አይደለንም... ሆኖም ጥቅሱ የውበት ብያኔያችንን ምንጭ አይጠቅስም... የዓይናችን ሚዛን የተሰራበትን ማሕበረሰባዊ ልቃቂትም አያፍታታም... የውበት መለኪያችን የተሰራው በስምምነት ነው... የእኔና አንተ የውበት ደርዝ በሚዲያው፣ በመንደርተኛው፣ በኢኮኖሚ ስርዓቱ፣ በባልንጀሮቻችን እና አነዋወራችን ተጽዕኖ የተቀነበበ ነው... People don’t choose what is beautiful. They are trained to see it that way. እውነት ለመናገር ውበት እንደ ተመልካቹ ብቻ አይደለም - የተመልካቹን ሚዛን እንደሰራው መረዳትም ጭምር እንጂ... Beauty is experienced subjectively, but that subjectivity is socially conditioned. 🔸🔸🔸 የጠቢቡን ቃል ተውሰን የተበተነውን ስንሰበስብ፣ እንዲህ እንላለን... “Beauty is not in the face; beauty is a light in the heart.” ~ Khalil Gibran ___ @bridgethoughts