Ye Fikr gitm 😍😘❤
Статистика✍የስነፅሁፍ ተሰጥኦዎች 📜ግጥም❤ 💆የጭንቅላት ጨዋታዎች 💭አባባሎዎች፣ 👽Psychology Facts 😭old music😘🍫🍫 ❤️ልብ_ወለድ እና ጠቃሚ ምክሮች ያለገደብ #ከልብ_ዲያሪ ወደናንተ ይደርሳሉ በተጨማሪም💎 ✍ግጥም 💖የፍቅር❤️ የይቅርታ🙏 የመልካም ምኞት መግለጫ እና የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች ያገኙበታል ተቀላቀሉት ትወዱታላችሁ ችግር ካለ @Oneday678 በዚህ አናግሩን
- Последний пост
- 29 дек.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Музыка
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እንደዚ ቀለል ያሉ መንፈስን የሚማርኩ ሥዕሎችን በትህዛዝ ማሳል የሚፈልግ ሰው ካለ ያናግረኝ በማታመን ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ 0983777730 በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ ጥራታችን መለያችን ነው !! @yefikrgitm8
አንድ ሽማግሌ ወደ አንድ የሞባይል ጥገና ሱቅ ሔዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ" ብለው ሰጡት። የሞባይል ጠጋኙ ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በኋላ "አባባ ስልክዎ ምንም አልሆነም ይሠራል" አላቸው። ሽማግሌው ዓይናቸው ዕንባ አቀረረና "ስልኩ ካልተበላሸ ... ልጆቼ የማይደውሉልኝ ለምንድን ነው?" አሉ በደከመ ድምፅ። ለወላጆቻችን የምናደርገው ትልቁ ሥጦታ ቢኖር ጊዜ መሥጠት ነው። የመኖራቸው ትርጉም የሚገባን ሲለዩን ነው። ዕድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በሕይወት ካሉ አሁኑኑ እንደውል። ይህንን ለማንበብ ጊዜ ካገኘን መቼም ለነሱ ለመደወል ጊዜ አናጣም። "በምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር" ዘዳ 5:16 ©®™ One Heart ━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን ❤️
አወቅሽኝ አወኩሽ . . . ተዋወቅን በፍቅር ነጠቅን ጨረቃን ዳሰስናት ኮኮቦችን ቆጠርን ቅዳሴ እና አዛንን አስቀደስን አፈጠርን አወኩሽ ወደድኩሽ ከልብ ተመኘሁሽ ለነብሴ ፈለኩሽ አጌጥን በፍቅራችን አስቀናን ላገሩ ኮራን በመንደሩ ወጣቶች ተያይተው "ሲያምሩ...ሲያምሩ" እየተባባሉ ወደድሽኝ ወደድኩሽ . . . ተዋደድን በፍቅር አበድን ነጎድን...ነጎድን...ነጎድን ከአፍ ባልወጣ ቃል መፋቀራችንን ሀገር ምድሩ ያውቃል መገረም መደነቅ ለኛ ምንም ነው ተፋቅረን አየነው ደላኝ ባንቺ ፍቅር ደላሽ በኔ ፍቅር እኔ ለንቺ አንቺ ለኔ ካለን ሁሉም ነገር ይቅር አፈቀርሽኝ አፈቀርኩሽ . . . ተፋቀርን የዛሬን ትዝታ ለነገ ወቀርን። ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @yetsberaleb @yetsberaleb
ማለዳ ነበርን🌅🌄 ለወግ ማዕረግ ባይደርስም ዳር ማፍቀር ኪሳራ የለውም.... ትዝታም ቢሆን የውብዳር ባይደርስም እስከ ፍፃሜ... ባይቆይም እስከዘላለም የእውነት ፍቅር አለው ቀለም🥰 ተሳክቶልን ባንዘልቅም ባሳለፍነው አትርፈናል... ለልብ ሰማይ ቀን አይጠልቅም በተሳሳምንበት በተቃቀፍንበት😌 በዚያ ጎዳና ላይ... ምን ዛሬም ባናልፍም መሽቶብናል ብለን... ማለዳ እንደነበርን አንዋሽም አንድ ቀን አዎ.... ፍቅርማ ነበረን.... በአፍላነት የተቋጨ🥺 በለጋነት የተቀጨ እስከሞትም ባያኖረን... ድልድይ ሆኖ ያሻገረን ባሳልፍነው ያለፍንበት ፈፅሞ የማንከስርበት☺️ አዎ.... ፍቅርማ ነበረን ለወግ ማዕረግ ባይደርስም ዳር ማፍቀር ኪሳራ የለውም.. ትዝታም ቢሆን የውብዳር🤗 ዘውድአክሊል✍✍
አንድ ሰው አለ...! እኖራለሁ ብሎ፥ ራሱን ለማየት፥ ልጁን ያባበለ፤ እግሩን በእሾህ አጥሮ፥ አፈር እየጋጠ፥ ፍቅርን የተከለ፤ . ዘሩን ለማሳደግ፥ ራሱን የገታ፥ ርኀቡን አምቆ፤ ነጌውን ለማንገሥ፥ አቀርቅሮ ታይቷል በእንባ ጎርፍ ደምቆ፤ . ₁አለ፥ በውሳጣዊ ዓይን 'ሚ^ታይ ነው ዘልቆ! . . እኔን የሚል አጥቶ፥ ሳይደላደለው በመቃተት ቆሞ፤ ሰው ሰው ሳይሸትት፥ በሲቃ እየኖረም፥ በዝቶበት ተቃውሞ፤ ክብር ሳይከጅለው፥ ለማክበር ሲታገል፥ እሱነቱን ጥሎ፤ እሱ ተጎንጕኖ፥ ደስታን የሚያሳይ፥ ከድኅነት ታግሎ፤ . ፩ሰው አለ ያይደለ ጎዶሎ...! . . ማሳደግ፥ ትልቅ ድል፥ በሚል ብሂል ታጥሮ፤ በልብ ሞገሥነት፥ ኃይል ለራሱ ሰጥቶ፥ ሳያሳይ ሮሮ መኖርን ያኖረ፥ ዝቅ በማለት ቤት፥ ከፍታን ያሳየ፤ ከምንሰማው ውጪ፥ ፍቅርን የሚሠራ፥ ለልጁ የተለየ፤ . 1ሰው አለ ለዝና የዘገየ...! . . ሲሰቃይ፦ ልጅ በጀርባ አዝሎ፥ ምግብ እስከ ማብሰል፤ የምሬቱ ውጤት፥ ፊቱ ያጠቆረው፥ ከሰል እስከ መምሰል፤ ውርጭ ሳይበግረው፥ ማልዶ እየተነሣ፥ ከሥራ እየዋለ፣ ቀና፥ አንድም ብርቱ፥ ልጁን ጀግና ያስባለ፤ . 1ሰው አለ...! . ማቀርቀሩን ለክብር፥ ማልቀሱን ለፍቅር፥ ብለን ብንሰይመው፤ አባትም'ኮ አለ፥ የሰው ክፉ ሲያይ፥ እምባ የሚቀድመው! አባት...! ... አባት...! ... ━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን ❤️ Join us 👇👇👇 @yetsberaleb
❤️🔥👑#እማ👑❤️🔥 🪔የማላድገው ልጅሽ🪔🤱 ሁሌ ምትናፍቂኝ ፣ከጉያሽ ሳልጠፋ፣ ማትሆኚው የለም ፣እኔ እንዳልከፋ፣ እንደ ቅጠል ረገፍሽ ፣ቀስ በቀስ እናቴ፣ አንቺ ባትኖሪማ ፣ እቺ እለም ምንድናት ባዶ ናት ሕይውቴ፣ ስስት የለብሽም ፍቅርሽን፣ ስሰጭን፣ እኩል ነው ምታይን ፣ሳታበላልጭን፣🙎♀🙎 ምን ብዬ ልግለፅሽ፣ እኔ የሉኝ ቃላት፣ ክንቱ ነው ቃላቴ ፣ ቢናርም አይገልፀው ያንቺን እናትነት፣ እንችን ክፋ አይንካሽ ፣ምንም አትሁኚ፣ ካንቺ ያስቀድመኝ ፣የማላድገው ልጅሽ ሁሌ ያንቺ ሞኚ፣ ለፍተሽ አሳደግሺኝ ፣የሰው ፊት እንዳላይ ፣ እናት ብቻ አይደለሽ ፣ ከእናትም በላይ፣ ብቻ ምን ልንገርሽ ፣ሕይወቴ ነሽ አንቺ፣ የፍቅር ቅኔ ነሽ ፣ መቼም ማትፈቻ፣ እማ እውድሻለው ፣ነፍሴ እክትወጣ፣ ሕልምም አያሳየኝ ፣ብሞት ይሻለኛል፣እኔ አንችን ከማጣ፣ እማ አምላክ ቢጥርው፣ ወትሮም ከእድሜሽ፣ላይ፣ ምንም አትሁኚብኝ፣nefffffffአመት ኑሪልኝ ፣ውስደሽ ከኔ ላይ❤️ 🤱 🤱 🤱🤱 🤱. 🤱🤱🤱. 🤱🤱🤱🤱🤱 🤱 🤱. 🤱 🤱. 🤱.🤱 🤱 🤱. 🤱. 🤱. 🤱👩🍼 🤍 🦋 🦋. 🤱 🤱 🤱 ለእናታችሁ እንብቡላት ደስታዋንም አጋሩን በComment 🥰🥰 𝙷𝚊𝚙𝚙𝚢 𝚖𝚘𝚝𝚑𝚎𝚛'𝚜 𝚍𝚊𝚢❤️🔥 🌼👑👑🌼 @yetsberaleb 😢😢
የኔና ያንቺ ህይወት ━━━━━━━✦✦━━━━━━━ ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ የኔ ሠላማዊ የኔ ሁለንተና የኔ ልዪ'ኮ ነሽ የኔ......የኔ የኔ......የኔ በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው የኔና ያንቺ ህይወት... ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ መጣላት መታረቅ መታረቅ መጣላት ደሞ ትንሽ ኩርፍ ደሞ መዘጋጋት... አሁንም መታረቅ አሁንም መጣላት ደሞ ሌላ ማኩረፍ ሌላ መዘጋጋት.... እውነት እውነት ስልሽ... የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር። 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @yetsberaleb
* በዝምታዬ * ፡ በዝምታዬ ነው ያፈንኩት ስቃዬን፣ ለሰው ሳላወጋ ደብቄ ህመሜን፣ ደብኜ የቻልኩት ካንች መለየቴን፣ ፡ በዝምታዬ ነው ሳጣሽ የሸኘሁሸ፣ በልቤ አንብቼ የተሰናበትኩሽ፣ ምልጃም አላሰማው እያልኩኝ ተመለሽ፣ ፡ ብቻ እያየሁት የእግርሽን ዳና፣ ተመኘው ምቾትን በመራሽ ጎዳና፣ ስትሄጂ ሸኘሁሽ እኔም ዝም አልኩና፣ ፡ አቅሜ እሱ ነበር ያለው በመዳፌ፣ ክደት ከርችሞታል አይናገር አፌ፣ ዝም አልኩኝ ሲዘረፍ ሲከፈት ደጃፌ፣ የኔ ያልኳት ርቃኝ ሀዘኔን ሸክፌ፣ ልቤ ተቀዳዶ ላይጠግነው መርፌ፣ አልከስሽ ለዳኛ የውስጤን ጡር ፅፌ፣ ለፍቅር ተማርኬ ላንቺ ተሸንፌ፣ ዝም አልኩ ስትሄጂ ሲደፈር ደጃፌ፣ ፡ ዝም ስል ዝም አላልኩ፣ እንደው ተብከነከንኩ፣ ትፋሼን አርዝሜ ቁናውን ተነፈስኩ፣ ዕንባዬን ሳላፈስ አምርሬ አለቀስኩ፣ በፍቅር እየኖርኩ ፍቅርን ረገምኩ፣ መሞሸሬ ቀርቶ ይባስ ብቸኛ ሆንኩ፣ ውስጤ እሬታ በዛ ዝም ስል ዝም አላልኩ፣ ከራሴ ተላተምኩ፣ ለሽንፈት ተሸነፍኩ፣ ፡ ዝም ብዬ ልሸኝሽ፣ ቸው እንኳን ሳልልሽ፣ መልካሙን ምኞቴን 'ባፌ ሳልገልፅልሽ፣ ይሄን የማረግው ስለምን መሰለሽ፣ ደጅ ደጁን እንዳይ ነው ብዬ ትመጫለሽ፣ ✍@yetsberaleb 😢😥
ዛሬ ላይ ስመጥር ከሆኑ ባለሀብቶች💰 መሀከል አንዱ #እንሆን_ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ በዓለም ካሉ አዋቂዎች እና ምሁሮች አንዱ እንሆን ይሆናል፡፡ ነገር ግን የትኛውም ሀብታችን🚘 ፣ የትኛውም ዕውቀታችን አይደለም ሞትን እንድናመልጥ በህይወታችን ላይ የአንድ ሰከንድ ዕድሜን አይገዛልንም፡፡ ታዲያ ያለን ሀብት ፣ ዕውቀት ፣ ዝና ይሄን ማድረግ ካልቻለ ለምን ለሰዎች ክፉ እንሆናለን? ለምን እራስ ወዳድ እንሆናለን? ዛሬም ፣ ነገም ፣ ከነገ ወዲያም ሁሌም ለሰዎች መልካም እናስብ፤ መልካም እናድርግ🙏 መልካም ቀን 🥰 @yetsberaleb
ችርስ ለማይሆን ፍቅር ብለን ብዙ ዋጋ ከፍለን ክህደት ለተከናነብነውና ሠው ማመን ላቃተን🥂🍻🥂🥂
"መስሏት ነበር እሷ" ያኔ ጥላኝ ስትሄድ _ ከጎኔ ስትርቅ ሁሌም የማለቅስ _ደግሜ የማልስቅ መስሏት ነበር እሷ 😏 ያኔ ስትገፋኝ _ ቀልዳ በፍቅሬ ወድቄ የምቀር _ እዛው አቀርቅሬ ቆይ ምኔ ሞኝ ነው 🤔 አንድ ሴት ብትሄድ _ ሊያውም የማትወደኝ አንገቴን ደፍቼ _ ሁሌ እንባ ሚወርደኝ ንገሯት ለዛች ሴት _ ለዛች ለማታውቀኝ አንድ ተራ እንቅፋት ከሂወት መንገዴ _ አይችልም ሊያግደኝ #ሼን ✍ ━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን ❤️
➖➖➖➖➖🙏➖➖➖➖➖ በእርሱ ቁሰል 😢 ተገረፈ ተወነጀለ ተተፋበት ተሰቀለ እሱ ስለ እኛ ሞትን ተቀበለ አቤት ትህትና አቤት አቤት ፍቅር❤ ኢየሱስ መጣ እኛን ሊያድን ወደምድር በእለተ አርብ መስቀል አሸከሙት ይህም አልበቃቸው በጅራፍ ገረፉት ህዝቡም በጥላቻ ምራቅ ተፉበት ያኔ ያመሰገኑት አሁን ሰደቡት ይሰቀል ይሰቀል እያሉ ሲጮሁ አላወቁም ነበር ለእኛ መሆኑን? እሱ እኮ ንጉስ ነው የሰማይ የምድር ዝቅ ያለው ፍቅርን ሊያስተምር እግር ያጠበው ትህትናን ሊያሳይ በሰው እጅ ተሰቅሎ ሆነ ለሰው ሲሳይ ከ99 በጎቹ አንዱ ቢጠፋበት ለፈጠረው ፍጡር በጣም ሳስቶለት ወረደ ወደምድር ሊሆን መስዕዋት እናቱስ ግን እንዴት ቻለች እንባዋን ወደምድር ረጨች ፀሀይም አኩርፋ ብርሀኗን አጠፋች የአምላኳን ገላ አላሳይም አለች ጨረቃም ከእሷ አቅም ደም ለበሰች ጴጥሮስም አላውቀውም ብሎ ካደው ዶሮ ሲጮህ ትዝ አለው አምላኩ ያለው አዎ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን በእኛ ሀጥያት እሱ ተሰዋልን በሱ ፍቅር ከሀጥያት ነፃን መገረፍ ያለብን እኛ የተገረፈው እሱ መሰቀል ያለብን እኛ የተሰቀለው እሱ መከራን ተቀበለ አስጠጋን ወደራሱ ይህ ነው እግዜአብሄር ለሰው ልጆች ብሎ እራሱን ሚያዋርድ ፍቅርን ለማስተማር ፍቅር ሆኖ የሚወርድ ይህ ነው እግዘብሔር ፍጥረቱን ሚወድ ተፃፈ በሽልማት Join us 👇👇👇 @yefikrgitm8
┉✽»🌺ማን ይሆን🌺✽┉ ❣:¨·.·¨: ❣ ══════❁✿❁ ══════ : ማን ይሆን 🌹 አይኑ ተመልክቶ ልቦናው ያልቃኘ ……… የያዘውን ትቶ ሌላ ያልተመኘ ……… አካዊ ወረት ያረገጠ ወዳጁን አለ ወይ ከሰዎች ያልጎዳ ወዳጁን ውድ ፍቅረኛውን ልቡን እንዳፈቀረ። 🌹 ……በሷ ተወስኖ ዘላለም የኖረ እስከመጨረሻው መንፈሱ ሳይላላ ከሚወዳው በቀር ያልተመኘ ሌላ ማናው ይህንን የሰራ በቃሉ የሚገኝ ባስቀመጡት ስፍራ ያልተለዋወጠ ማን ይሆን ወዳጁን በሌላ ያልሸጠ። ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🌹🌹በእሾህ ተከበሽ🌹🌹 ፅገሬዳ አበቦች በድንገት ሳያቸው ትዝ ትዪኛለሽ እሾህሽ ብዙ ነው የግሉ ሊያረግሽ ከልብ ለተመኘሽ እኔ ግን ከርታታው ጉልበተኛ ባልሆን ገንዘብ ባይኖር ኪሴ እውነተኛ ፍቅሬን ተጠቀምኩኝና አረኩሽ የራሴ። 📝📝📝📝📝📝📝📝 ✍️ one day
አንተ መሄድ ስትወድ ከኔ የበለጠ የሚያደርስ መች አጣህ እንደት አክብረኧኝ ከጀርባዬ ወጣህ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋን የሚሸከም መላይክት እያለህ ከኔ ከተናኩት ጀርባ ላይ ለመውጣት እንደምን አስቻለህ ምን አገኘህብኝ ሳለሁ የተጠላሁ እንዴት ተሸክሜህ ቤተልዬም ገባሁ
🥲ትናንት እና ዛሬ🥲 አላወቅሺም እንጂ አፍቅሬሽ ነበረ ዳሩ ምን ያረጋል ሌላው ይዞሽ ሲሄድ ልቤ ተሰበረ። የሆነው ሆነና እንዳሰብኩት ሳይሆን ከጎኔ ባጣሽም በትናንት ሀዘኔ የዛሬው ህይወቴን ከቶ አላበላሽም። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝 @Remu890 @onelove58