ዚክራ የጥያቄና መልስ መወዳደሪያ📚📚📚📚📚📚
Статистикаየግሩፑ አላማ ስለ እስልምናችን ጥያቄና መልስ በመወዳደር መተዋወስ ነው አድድድድድድድ ያድርጉ ግሩፑን ሼር በማድረግ ለሌሎች እህት ወንድሞች እናድርስ በኛ ምክኒያት ሌሎች ይጠቀማሉ
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 83
- 1/48двое суток
- 95
- 1/72трое суток
- 102
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
- {الر كِتَابٌ أَنْزَلْنَاهُ إِلَيْكَ لِتُخْرِجَ النَّاسَ}. - باسل -رحِمهُ الله-.
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
- ﴿إِنَّ الَّذينَ سَبَقَت لَهُم مِنَّا الحُسنى﴾. - خالد الغامدي.
على هامان يا فرعون؟؟ ፈገግታ ከፊርዓውን ጅልነት ጋ… ♾️♾️♾️♾️♾️♾️♾️♾️ ፊርዓውን ከነበረበት ድንበር ያለፈ ጥመት ጋ ጅል (ፋራ) ነገር ነበር አሉ። አማካሪው ሃማን ደግሞ እንደ የትኛውም የንጉሶች አማካሪ ብልጣብልጥ ነበር አሉ። እናም ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት በፊርዓው “የጌትነት ሙገታ” ያመነች አሮጊት ፍየልዋ ይሞትባትና ወደ ፊርዓውን ቤት ትመጣለች። ስትመጣ ፊርዓውን አልነበረም ሃማንን አገኘችው። "ጉዳይሽ ምን ነበር?" ሲላት "ፍየሌ ሞታብኝ ፊርዓውን ሕያው እንዲያደርጋት ነበር የመጣሁት።" ትለዋለች ሃማን ብልጥ ነበር; ብለን የለ? "ነይ በቃ ፊርዓውን አሁን ግመል እየፈጠረ ስለ ሆነ ይቆይብሻል። ስለዚህ ሌላ ፍየል ልስጥሽ።" ይላትና ሌላ ፍየል ሰጥቷት ትሄዳለች። ፊርዓውን ወደ ቤቱ ሲመለስ ሃማን "አንዷ አሮጊት ፍየሏ ሙቶባት ሕያው እንድታደርግላት መጥታ ነበር።" ሲለው ፊርዓውን ደነገጠ። ሃማን "አይዞህ! ፊርዓውን ግመል እየፈጠረ ነው። ብያት ሌላ ፍየል ሰጥቻት ሄዳለች። አትመጣም።" አለው። በዚህ ጊዜ ፊርዓውን እንደ መረጋጋት አለና በረጅሙ ተንፍሶ………… «ግመል መፍጠር እኮ እንዴት እንደ ሚያደክም ብታይ» አለው። ሃማን ፈገግ አለና… … على هامان يا فرعون ኧረ ፍርዓውን! በሃማን ላይ❓አለው በሃማን ላይ ሙድ ትይዛለህ ወይ እንዴ ጭራሽ ልትሸውደኝ ያምርሃል ማለቱ ነው። ከዛኔ ጀምሮ ሰዎች በሚያውቁት ነገር ላይ ሊሸውዳቸው ለሞከረ ሰው على هامان يا فرعون ኧረ ፍርዓውን! በሃማን ላይ❓አለው እያሉ አባባል አድርገው ይዘውታል። ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓ @tolehaahmed1 ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
- {فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَنْ يَخَافُ وَعِيدِ}. - أحمد بن طالب. • رواية حفص عن عاصم.
የቀልብ ፈውስ ፈላጊ ጩኸት! ○●○●○ "ما تقول السادة العلماء في رجل ابتلي ببلية، وعلم أنها إن استمرت به أفسدت عليه دنياه وآخِرته، وقد اجتهد في دفعها عن نفسه بكل طريق فما يزداد إلا توقداً وشدة، فما الحيلة في دفعها وما الطريق إلى كشفها؟" "የተከበራችሁ ዑለሞች ሆይ! በከባድ ፈተናና መከራ በተፈተነ ሰው ጉዳይ ዙርያ ምን ትላላችሁ? ይኸውም ፈተናው ከቀጠለበት የዱንያ ሕይወቱንና የነገዋን አኼራውን እንደሚያበላሽበት ያወቀ፣ ከራሱም ላይ ለማስወገድ በቻለው መንገድ ሁሉ የታገለ፤ ነገር ግን ጥረቱ የሸህዋውን እሳት ከመጫር ውጭ ምንም ያልጨመረለት ሰው ነው! ታዲያ ይህ መከራ የሚወገድበት ብልሃት ምንድን ነው? ከዚህስ ገፍላና ጨለማ መውጫው መንገድስ ወዴት ነው?" ይህች ከአንድ የቀልብ ፈውስ ፈላጊ አንደበት የወጣችው የነፍስ ጩኸት፣ ዛሬ በዘመናችን የብዙዎችን ስውር ቁስል የምታስተጋባ ድምፅ ናት። በሸህዋና በወንጀል የታነቀ፣ ከውድቀት ለማምለጥ የሚያደርገው የውስጥ ትግል ሁሉ ከሽፎ ወደ መክሰር አፋፍ የተጠጋ በወንጀል የቆሰለች ነፍስ የምታወጣው የህመም ድምፅ! ይህችው ጩኸት ዛሬም በተዘጋጁ ስክሪኖች ጀርባ፣ በአዲሱ የዲጂታል ብቸኝነት ማዕዘናት ውስጥ ትደገማለች፤ በጣት ጠቅታ በተመቻቹ የፈተና ወጥመዶች ተሸንፈው፣ በስውር ሱሶችና በከበዱ ወንጀሎች ተጠፍረው የሚማቅቁ ነፍሳት ጥሪ ነች። በዚያ የገፍላ ድቅድቅና የውስጥ ቀውስ ውስጥ ሆነው፦ "ከዚህ ድቅድቅ ጨለማ መውጫው ወዴት ነው? ነፍስስ የራሷን ቁስል ማከም ሲሳናት ብልሃቱ ምንድን ነው?" እያሉ ይጮሃሉ። ይህ ጥያቄ ተራ የፈትዋ ምላሽ አልነበረም የተሰጠው፤ የቀልብ ሐኪም የሆኑት ኢማም ኢብኑ አል-ቀይም አል-ጀውዝያ (ረሒመሁላህ) "አልዳእ ወል-ደዋእ" (ሕመሙና መድኃኒቱ - ወይም አል-ጃዋብ አል-ካፊ) በተሰኘው ድንቅ መጽሐፋቸው የለገሱት፣ የነፍስን ቁስል የሚያሽር መንፈሳዊ መድኃኒት ነው። ኢብኑ አል-ቀይም (ረሒመሁላህ) የፊቅህና የሐዲስ ሊቅ ብቻ አልነበሩም፤ ወደ አላህ የሚጓዙ ነፍሳትን ሕመም የሚረዱና ከወሕይ ኑር መድኃኒት የሚቀምሙ መንፈሳዊ ሐኪምም ነበሩ። ይህ ድንቅ ጥበባቸው በኢስላማዊው የመንፈስ ማጽዳት (ተዝኪየቱ አን-ነፍስ) ታሪክ ውስጥ ባበረከቱት ታላቅ አሻራ ይገለጣል፦ በ"መዳሪጁ አስ-ሳሊኪን" መጽሐፋቸው፦ ﴿إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ﴾ (አንተን ብቻ እንገዛለን፤ በአንተም ብቻ እንታገዛለን) መሠረት አድርገው፣ ተጓዡን ነፍስ ከተውበትና ከንቃት ማዕረግ ጀምረው እስከ መሓባህ (ፍቅር) እና ሪዳ (ውዴታ) ማዕረጎች ድረስ ደረጃ በደረጃ ይመሩታል፤ በዓቅልና በቀልብ ማስተዋል መካከል ያለውን ጥበብ እያዋሃዱ ወደ አላህ የሚወስደውን የመንገድ ካርታ ይስላሉ። በ"ሚፍታሁ ዳሪ አስ-ሰዓዳህ" መጽሐፋቸው፦ በፍጥረትና በሸሪዓ ምስጢራት ውስጥ በመጥለቅ፣ እውነተኛ ሳዓዳህ (ደስታ) በዒልምና በማስተንተን (ተፈኩር) እንዴት እንደሚገኝ ያሳያሉ። በ"አል-ዳእ ወል-ደዋእ" መጽሐፋቸው፦ በሥነ-ልቦናዊና መንፈሳዊ ሕክምና ጥበባቸውን ያሳያሉ። የወንጀል ሱሶችን ስር ነቅሎ የሚያወጣ ተግባራዊ መመሪያ ያቀርባሉ፤ የመዓሲን ጉዳት በግለሰብና በኡማው ላይ በጥልቀት በመተንተን፣ እውነተኛውን መድኃኒት ያመላክታሉ። በዚህ ዘመን ያሉ የመንፈስ ሕመሞችን ለማከም ከዚህ ታላቅ መጽሐፍ የተወሰዱ ወርቃማ መመሪያዎችን ለናሙና ያህል እንመልከት፦ 1. መድኃኒት የሌለው መዓሲም ሆነ ሕመም የለም የመጀመሪያው የፈውስ እርምጃ የሱኡ ዘን (የተስፋ መቁረጥን) ጭጋግ መግፈፍ ነው፤ ወንጀልህ ምንም ያህል ቢከብድ ወይም ሱስህ ቢጠነክር፣ ኢብኑ አል-ቀይም ነቢያዊውን ታላቅ መመሪያ ያቀርቡልናል፦ "لكل داء دواء" "ለእያንዳንዱ ሕመም መድኃኒት አለው" ምንም እንኳን በዘመናዊው የዲጂታል ወንጀልና ሱሶች ብትከበብም፣ አላህ በነፍስህ ላይ የሸህዋን ሕመም አላመጣብህም የሚፈውሰውን መድኃኒት ያዘጋጀልህ ቢሆን እንጂ፤ በቂው ነገር እውነተኛ የመፈወስ ፍላጎት መኖሩ ነው። 2. ዱዓ (የጦር መሣሪያና የእጅ ጥንካሬ ምሳሌ) ብዙዎች፦ "ብዙ ዱዓ እናደርጋለን፤ አዝካሮችንም እንላለን፤ ታዲያ ለምን አንፈወስም?" ብለው ይጠይቃሉ። ኢብኑ አል-ቀይም ረቂቅ በሆነ መንፈሳዊ ምሳሌ የሕመሙን ምንጭ እንዲህ ያመላክታሉ፦ "والأدعية والتعوذات بمنزلة السلاح، والسلاح بضاربه لا بحده فقط. فمتى كان السلاح سلاحاً تاماً لا آفة به، والساعد ساعد قوي، والمانع مفقود؛ حصلت النكاية في العدو. ومتى تخلف واحد من هذه الثلاثة تخلف التأثير." "ዱዓዎች እና አዝካሮች እንደ ጦር መሣሪያ ናቸው፤ መሣሪያ ደግሞ በስለቱ ብቻ ሳይሆን በጨባጩ ጥንካሬም ጭምር ይሠራል! መሣሪያው ሙሉና ጉድለት የሌለበት ሲሆን፣ ጨባጩ እጅ ጠንካራ ሲሆን፣ እንዲሁም ከልካይ ነገር (ማኒዕ) ሲወገድ በጠላት (በሸይጧንና በነፍስ) ላይ ድል ይገኛል። ከነዚህ ከሦስቱ አንዱ ከተጓደለ ግን ውጤቱ ይቀንሳል!" ዱዓና አዝካር ወሳኝ መሣሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን ወንጀልን ለማሸነፍ በኢኽላስና በቁርጠኝነት ከተሞላ ቀልብ (ጠንካራ እጅ)፣ እንዲሁም እንደ ወንጀልን ማቃለል ካሉ የዱዓን ተቀባይነት ከልካዮች የጠራ መሆን አለበት። 3. በቁርኣን የመፈወስ ልምድ፦ ኢብኑ አል-ቀይም በመካ እያሉ ታመው በነበረበት ወቅት፣ እንዴት በፋቲሃ ፈውስ እንዳገኙ ልምዳቸውን ያካፍሉናል፦ "ومكثتُ بمكة مدة يعتريني أدواء ولا أجد طبيباً ولا دواء، فكنت أعالج نفسي بالفاتحة، فأرى لها تأثيراً عجيباً.. فكنت أصف ذلك لمن يشتكي ألم، وكان كثير منهم يبرأ سريعاً." "በመካ ሳለሁ ሕመም ያጋጥመኝ ነበር፤ ሐኪምም ሆነ መድኃኒት አላገኝም ነበር፤ እናም ነፍሴን በሱረቱል ፋቲሃ እከታተላት ነበር፣ ድንቅ የሆነ ተፅዕኖንም አይበታለሁ... ሕመም ለሚያስቸግረው ሰው ሁሉ እጠቁመው ነበር፤ ብዙዎቹም በፍጥነት ይድኑ ነበር!" ቁርኣን ተራ የቲላዋህ ዒባዳ ብቻ አይደለም፤ በቅንነትና በፈውስ እምነት ካነበብከው፣ የሸህዋን ስር ከቀልብህ ውስጥ ነቅሎ የማውጣት መንፈሳዊና ሥነ-ልቦናዊ ኃይል ያለው ኑር ነው...እያሉ ይቀጥላሉ ኢብኑ አል-ቀይም:: ለቀልባችን የፈውስ መድኃኒት የቀመሙልን እኚህን ታላቅ ኢማም አላህ መልካም ምንዳቸውን ይክፈላቸው! የእኛንም የነፍሶቻችን ስብራት በተውበት ይጠግንልን!
видео или голосовое, без подписи
-﴿ وَتَنْزِعُ الْمُلْكَ مِمَّنْ تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَنْ تَشَاءُ﴾ -القارئ: ياسر محمد .
የማለዳ መልእክት (41) ~ የብዙ ፈተናዎችና ብጥብጦች ሰበብ ሶብር ማጣት ነው። በሚገጥሟቸው ፈተናዎች ተበሳጭተው ወደ ሃይልና ብጥብጥ በመግባታቸው የተነሳ ስንቶች ህይወታቸውን አጥተዋል?! ስንቶች አካላቸው ጎድሏል?! ስንቶች ንብረታቸው ወድሟል?! ስንቶች ለረጅም የወህኒ ቆይታ ተዳርገዋል?! ስንቶች ቤተሰቦቻቸውን አጥተው የቁጭት እሳት እየለበለባቸው ነው?! ስንቶች አገራቸውን ጭምር አጥተዋል?! ስንቶች መስጂዳቸውን፣ ደዕዋቸውን፣ ዲናቸውን አጥተዋል?! በሶብር ማጣት ስንቶች ትዳራቸውን አጥተዋል?! ስንቶች የተሻለ ስራቸውን አጥተዋል?! ሶብር ማጣት ብዙ ነገር ነው የሚያሳጣው። ብዙዎች ከሶብር የሚርቁት ወደ ዓላማቸው ለመድረስ ካላቸው ጉጉትና ችኮላ የተነሳ ነው። ነገር ግን የሚዘነጉት ነገር ሶብር በራሱ ወደ ዓላማ መቃረቢያ ሁነኛ መንገድ መሆኑን ነው። በሶብራቸው ደካሞች ካለሙበትት ደርሰዋል። አላህ እንዲህ ይላል፦ { وَأَوۡرَثۡنَا ٱلۡقَوۡمَ ٱلَّذِینَ كَانُوا۟ یُسۡتَضۡعَفُونَ مَشَـٰرِقَ ٱلۡأَرۡضِ وَمَغَـٰرِبَهَا ٱلَّتِی بَـٰرَكۡنَا فِیهَاۖ وَتَمَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ ٱلۡحُسۡنَىٰ عَلَىٰ بَنِیۤ إِسۡرَ ٰۤءِیلَ بِمَا صَبَرُوا۟ۖ وَدَمَّرۡنَا مَا كَانَ یَصۡنَعُ فِرۡعَوۡنُ وَقَوۡمُهُۥ وَمَا كَانُوا۟ یَعۡرِشُونَ } "እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆቿንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው። የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስ ^ራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች። ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን።" [አልአዕራፍ፡ 137] ፈተና ሲገጥመን ሶብር፣ ዱዓእ፣ ጥረት ላይ መበርታት ይገባል። ያኔ ፈተናው በአላህ ፈቃድ ይገፈፋል። ኸባብ ብኑል አረት ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦ شَكَونا إلى رَسولِ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم وهو مُتَوسِّدٌ بُردةً له في ظِلِّ الكَعبةِ، فقُلنا: ألا تَستَنصِرُ لنا، ألا تَدعو لَنا؟ فقال: قد كان مَن قَبلَكُم يُؤخَذُ الرَّجُلُ فيُحفَرُ له في الأرضِ، فيُجعَلُ فيها، فيُجاءُ بالمِنشارِ فيوضَعُ على رَأسِه فيُجعَلُ نِصفَينِ، ويُمشَطُ بأمشاطِ الحَديدِ ما دونَ لَحمِه وعَظمِه، فما يَصُدُّه ذلك عن دينِه، واللهِ لَيَتِمَّنَّ هذا الأمرُ، حتَّى يَسيرَ الرَّاكِبُ مِن صَنعاءَ إلى حَضرَمَوتَ، لا يَخافُ إلَّا اللهَ، والذِّئبَ على غَنَمِه، ولَكِنَّكُم تَستَعجِلونَ. "የአላህ መልእክተኛ ﷺ በከዕባ ጥላ ስር ኩታቸውን ተንተርሰው ሳሉ ስለሚደረስብን መከራ አቤቱታ አቀረብንላቸው፤ ‘እርዳታን አትለምንልንምን? ዱዓእ አታደርግልንምን?’ አልናቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ። ‘ከእናንተ በፊት በነበሩት ህዝቦች ዘንድ አንድ ሰው ተይዞ መሬት ይቆፈርለትና በውስጧ ይገባ ነበር፤ ከዚያም መጋዝ መጥቶ በራሱ ላይ ይደረግና ለሁለት ይከፈል ነበር። በብረት ማበጠሪያዎችም ሥጋው ከአጥንቱ ይበጠር ነበር። ይህ ሁሉ ግን ከሃይማኖቱ አይመልሰውም ነበር። በአላህ እምላለሁ! ይህ ጉዳይ (እስልምና) ሙሉ ይሆናል! ተጓዥ ከሰንዓ ተነስቶ እስከ ሐድረመውት ድረስ፣ ከአላህና በበጎቹ ላይ ከሚመጣ ተኩላ በስተቀር ምንም የሚያፈራው ነገር ሳይኖር የሚጓዝበት ጊዜ ይመጣል። ነገር ግን እናንተ #ትቸኩላላችሁ።’ " [አልቡኻሪይ፡ 6943] አስተውሉ! ያ ሁሉ የመከራ ዶፍ እየወረደባቸው ስሞታ ቢያሰሙ ነው "ትቸኩላላችሁ" ብለው የገሰጿቸው። ከዚህ የማይቀርቡ ፈተናዎችን መታገስ አቅቶን ለስንት የባሰ መከራ ተደርገናል?! ይልቁንም አስፈላጊ ሰበቦችን በማድረስ እንደታዘዝነው በመታገስ ፈረጃን ከአላህ እንጠብቅ። ካልሆነ ግን የሚቀረው ምርጫ የከፋና የመረረ ይሆናል። አዎ! ሶብርን መልቀቅ ለከፋ ፈተና መጋለጥ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ عامة الفتن التي وقعت من أعظم أسبابها: قلة الصبر؛ إذ الفتنة لها سببان: إما ضعف العلم، وإما ضعف الصبر "የደረሱ ፈተናዎች (ሁከቶች) እንዳለ ከዋና መንስኤዎቻቸው ውስጥ አንዱ የትዕግሥት ማነስ ነው። ምክንያቱም ለፈተና ሁለት መንስኤዎች አሉት፡ ወይ የእውቀት ማነስ ወይም ደግሞ የትዕግሥት ማነስ ናቸው።" [አልፉሩዕ፡ 10/181] || (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 16 /1448) =
ከ ቁርአን ማዕድ مَا وَدَّعَكَ رَبُّكَ وَمَا قَلَى ተፈኩር፦ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆነሽ ብቸኝነት ሲሰማሽ፣ ያቀድሽው ሁሉ እንዳልነበረ ሆኖ ሲፈርስ፣ እና ትናንት አብረውሽ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ድምፃቸውን አጥፍተው ጥለውሽ ሲሄዱ... ልብሽ 💔 "ብቻዬን ነኝ" ይላል። ይባስ ብሎ ደግሞ የሰራሽው ወንጀልና ስህተትህ እየታወሰሽ "አላህ እኔን አይፈልገኝም" ብለሽ በሀሳብ ትጨነቂያለሽ። ግን ቆም ብለሽ አስቢ! የሰዎች መራቅና መጥላት እንዲህ ልብሽን የሚያደማው ከሆነ፣ የአጽናፈ ዓለሙ ጌታ "አልተውኩሽም፣ አልጠላሁሽም" የሚልሽ ጣፋጭ ድምፅ እንዴት ዘነጋሽው? ከአንገት ስርሽ በላይ የሚቀርብሽ ጌታ እያለሽ እንዴት ብቸኝነት ይሰማሻል? እሱ እዝነቱ ከቁጣው የቀደመ ሩህሩህ ነው። ሰዎች ቢያገሉሽም እሱ ግን አልተወሽም። ተስፋ መቁረጥን ከልብሽ አውጥተሽ ጣይውና ዛሬውኑ ወደ እሱ ተመለሺ። በሩ ሁሌም ክፍት ነው፤ አንኳኪው! ❤️🩹 ያረብ! ከእዝነትህ ተስፋ ከሚቆርጡት አታድርገን... 🤲🏽 🍂 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah
የአላህ እዝነት እኮ የሚገርም ነው፤ የሰራነውን መጥፎ ነገር ለማበስ የሚጠይቅን ዋጋ ከባድ ቅጣትን ሳይሆን፣ ሌላ ሰውን መጥቀም ወይም ለአላህ መስገድን የመሰለ ውብ ተግባርን ነው! إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ 🍂 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи