tgindex
Abdu Book Center

Abdu Book Center

Статистика

በመጻሕፍት መደብራችን ፡ የታሪክ መጻሕፍት የትምህርት አጋዥ እና መማሪያ መጻሕፍት የተለያዩ ልበ-ወለድ እና መንፈሳዊ መጻሕፍት ቆየት ያሉና አዳዲስ መጻሕፍት ሌሎችም.. አድራሻችን=አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ አባቢያ ራሕመት ታቦር ሕንፃ ፊትለፊት ለበለጠ መረጃ በ0929574133 ደዉልሉን @Abduseller

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 990
+9 за 2 дн.
Сутки
+5
+0,25%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
364
22 постов
Вовлечённость
18,3%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
213
1/48двое суток
244
1/72трое суток
263

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • «ገንዘብ የሚባለዉ የተወሰነና የተረጋገጠ ዋጋ ያለዉ ሲሆን ዋጋዉም የማይጨምርም የማይቀንስም መሆን አለበት።ያ ገንዘብ የተሰኘዉ ነገር የሚዋዥቅ ከሆነ ሌሎች የሚቀንሱና የሚጨምሩ ንግድና ዕቃዎችን ልንለካበት አንችል።»   (ኢብኑል ቀይም፣ዒላሙል ሙወቂዒን፣2/137-138) ፀሀፊ አብዱልቃድር ሐጅ ኑረዲን(ሀሰን ኢንጃሞ) መጽሐፉን የምትፈልጉ፦  በዚህ አነጋግሩኝ 👉👉👉👉 @Abduseller

  • “የብሔር” ማንነት እዉነት ሳይሆን ቅዠት (Delusion) ስለመሆኑ ለማስገንዘብ የታለመ ይህ ለእኔ የመጀመሪያ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ በዓለማችንና በዋናነትም በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠረ ላለው “የብሔር” ማንነት ግጭትና አለመረጋጋት መሠረታዊ መፍትሔ ሊሆን የሚችል ጥልቀት ያለውና አስገራሚ መጽሐፍ እንደሆነ አምናለሁ። አቀራረቡ ከፖለቲካ አመለካከት የጸዳ፣ አድሏዊነት የሌለው በመሆኑ ማንንም ለመጉዳትም ሆነ ለመጥቀም የታለመ መጽሐፍ አይደለም። በመሆኑም መጽሐፉን በአዎንታዊነት፣ በትዕግሥት በማንበብ እያንዳንዱ አንባቢ አመላካከቱን እንዲያሰፋ አሳስባለሁ። ​ተስፋ በዳሳ ደበሳ (ዶ/ር)

  • #ከመፅሃፉ_ውስጥ_የተቀነጨቡ --​ይህ ዘግይቷል ብለህ ከማድረግ አትቆጠብ ፤ ወደ ኋላም አታፈግፍግ :: -----​“ባህላችን ሰዎች ስለ ራሳቸው ጥሩ እንዲሰማቸው እያደረገም :: ” ​“ብዙ ሰዎች ትርጉም የሌለው ህይወት አዝለው ይዞራሉ፤ ጠቃሚ ነው ብለው ያመኑበትን ስራ በሚሰሩበት ጊዜ እንኳ ሳይቀር የሚያንቀላፉ ይመስላሉ :: -​ያለ ፍቅር ክንፎቻቸው እንደተሰበሩባቸው ወፎች ነን :: -​ለሌላ ሰው ሙሉ በሙሉ ሀላፊነት ለመውሰድ ከፈለግህና ከውስጥህ የመነጨ ፍቅር እንዲኖርህ ለመማር የምትችል ከሆነ ልጆች ሊኖሩህ ይገባል ::” -​እርጅና እድገት ነው :: -​“በጋብቻችሁ አስፈላጊነት ላይ ያላችሁ እምነት ነው ::” “ሰዎች መጥፎ የሚሆኑት ስጋት ወይም ፍርሃት ሲኖራቸው ነው” -​ሁላችንም አንድ አይነት ጅማሮ አለን - መወለድ - ሁላችንም አንድ አይነት መጨረሻ አለን - መሞት :: -​“ቂም በቀል ወይም እልከኝነት ይዞ መቀመጥ ምንም ጥቅም የለውም :: ፍቅር ማለት የአንድ ሰውን ሁኔታ (ችግር) እንደ ራስህ አድርገህ ማሰብ ከተቻልከ ነው ::

  • 📚እስላማዊ ቅርሶች ዓይነትና ስርጭት ከሰሜን ሸዋ እስከ ደቡብ ወሎ 📚 1. ጀዉሐር ብን አል-ሐይደር ቢን አልይ (1853-1936 እ.ኤ.አ) ​እኒህ ምሁር፤ በአክብሮት አጠራር ሸህ ሾንኬ፤ አባዬ ሾንኬ በመባል ይታወቃሉ። ቀኑን ሙሉ በማስተማር ሲያሳልፉ፤ ማታውን ክፍል ጊዜ ደግሞ፤ በጽሑፍ ዝግጅት ላይ ይጠመዱ ነበር። የምክርና የተውሒድ ሥራቸውም በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ተሰራጭቶ እስከ አሁን ድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። በእስልምና ሥነ-ፅሑፍ በርካታ ሥራዎችን አበርክተዋል። ከሥራዎቻቸው ውስጥ፤ ጥቂቱ የታተሙ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ ለህትመት ሳይበቁ ቀርተዋል። በሾንኬ መስጊድ (የቀድሞ ስሙ ያልተገለጠ ኋላ በሳቸው ስም የተጠራ መስጊድ) በሚያስተምሩበት ወቅት፤ ከአገር ውስጥ ከደቡብ፤ ከጉራጌ፤ ከጅማ ከአርሲና ባሌ ሰዎች መጥተው በሳቸው ስር ይማሩ ነበር። ከኢትዮጵያ ውጭ ደግሞ ከየመንና ከሌሎችም አገራት እየመጡ ትምህርታቸውን ይከታተሉ እንደነበር መረጃዎች ተገኝተዋል።.......

  • 📚ፍልስምና(ስነልቦና፣ጋብቻ፣የአዕምሮ ህክምና ✍️ Tewodros Teklearegay ​"አንዳንዴ ጊዜ ወላጆቻችን ት/ቤት ገብተው አለመማራቸውን እናይና ትዳር ያልተማረ ሰው ሁሉ የሚያደርገውን አድርገን እናስባለን። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ወላጆቻችን ተምረዋል። ከሕይወት ተምረዋል። እንደውም ሰው ኖሮ ይማራል ፤ ተምሮ አይኖርም።" ✍️​አቶ እድሜዓለም ግዛ ( ስለ ሕፃናት የባህሪ ጥናት / Child psychology ) ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ​" የአእምሮ ቁስለት ማለት ችግሩ ይሄ ነው። ይህች ልጅ ለምን ሮጣ ወንድ ጋ እንደምትሄድ አታውቅም። ራሷን ከወንድ ጋር ተኝታ ነው የምታገኘው፤ ለምን እንደምትሄድ አታውቀውም። ግን ትሄዳለች።" ✍️​ወ/ሮ ትዕግሥት ዋልተንጉሥ ( ስለ አእምሮ ቁስለት / Trauma ) ፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ​" ወደ 360 የአእምሮ ሕመም ዓይነቶች አሉ ተብሎ ነው የሚታሰበው። "አፍንጫዬ ተጣሟል" ፤ "አፌ ይሸታል" ፤ "መንግሥት ይከታተለኛል" የሚሉትን የመሰሉትና እኛ የአእምሮ ሕመም ናቸው ብለን የማናስባቸው ዓይነቶቹ የአእምሮ ሕመም ዓይነቶች ማለት ነው ፤ ከባዶቹ 2% ቢሆኑ ነው።" ✍️​ዶ/ር ዮናስ ባሕረ ጥበብ ( ስለ አእምሮ ጤና ፤ ሕመም እና ሕክምናው )

  • #አዉቴዝራማ "የዓለም ሥርዓት ነዉረኛ ሆኗል። ሥርዓት ተጥሷል ሰዉነት ረክሷል፡ ትርምስ ቦታውን ይዟል። ምድር በነፍስ በላዎች እጅ ወድቃለች። ይህ ግን አይቀጥልም። ለውጥ አለ ትርምስን የሚረታ ሥርዓት ከፊት እየጋለበ ነው።" አባ ኪሩብ በዝምታ ይጠብቃሉ። አጠገባቸው ቁጢጥ ብለው ዐይን ዐይናቸውን የሚያዩትን አባ መዓዛን ተመለከቷቸው። አባ መዓዛ ንግግር የሚጀምሩበት መግቢያው እንደቸገራቸው ሁሉ ወደርሳቸው ሲዞሩ ፈጥነው "ምን ምን እያስጨነቀዎ ነዉ አባቴ" ብለው ጠየቋቸው። ​ከገጽ 32 የተወሰደ አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ ራሕመት ታቦር ሕንፃ ፊትለፊት ምድር ባቡር የገበያ ማዕከል ዉስጥ። በሁሉም የአዲስ አበባ ከተሞችና የክ/ሃገር ከተሞች የdelivery(የማድረስ አገልግሎት) እንሰጣለን። ያሻዎ መጽሐፍት ወደዉጭ ሃገራትም በመረጡት የትራንስፖርት አማራጭ Deliver እናደርጋለን፥እንልካለን። ለበለጠ መረጃ፦በ0929574133 ይደዉሉልን መጽሐፍት ለማዘዝ፦ @Abduseller    በቴሌግራም👇👇👇 https://t.me/Abdubook በtiktok፦👇??👇👇👇 https://www.tiktok.com/@abdubookdelivery?_r=1&_t=ZM-91WLxJQpsol

  • без подписи

  • #ፌሚኒዝም_አንደኛዉ_የዓለም_ጦርነት_ሚሊዮን_ወጣት_ወንዶችን_ስላሳጣ_ፋብሪካዎች_በሴቶች_እንዲንቀሳቀሱ_ተፈለገ Burhan Addis 2010 ዓመተ ኢትዮጵያ ላይ ያሳተመዉ «እስልምና በ20ኛዉ ክ/ዘመን »መጽሐፉን ለ10ኛ ጊዜ እያነበብኩ ምዕራፍ አንድ የዘመናዊነት አጀማመርና የተፅዕኖዉ መልኮች በተሰኘዉ ርዕስ ንዑስ አርእስት ስር ስለ ፌሚኒዝም እንዲህች የምትል ፅሁፍ ከትቦ እናገኘዋለን። #ፌሚኒዝም_አንደኛዉ_የዓለም_ጦርነት_ሚሊዮን_ወጣት_ወንዶችን_ስላሳጣ_ፋብሪካዎች_በሴቶች_እንዲንቀሳቀሱ_ተፈለገ ዘመናዊነት የምትፈልጉትን ዓላማ በምትፈልጉት መልኩ አሳምኖ መፈጸም ያስችላል።ዉሸት የሚሆነዉ ጥቅም ሳይሰጣችሁ ከቀረ ብቻ ነዉ በዘመናዊነት ፍልስፍና።በዚህ መፅሐፍ በሰፊዉ እንደምናየዉ እንግሊዝ ብዙ ዉሸቶችን ፈጽማለች።የአፍሪካና የዓረቦችን ህልውና የሚፈትኑ እና እዚህ ድረስ ለዘለቀው የአንድ መቶ ዓመታት የመከራ ታሪክ እንዲዳረጉ ያደረጋቸው በሦስት ውሎች ነው። የሳይክስ-ፒኮት ስምምነት፣ የባልፎር ስምምነትና የቨርሳይ ስምምነቶችን ልብ ካልን የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይ፣ የአውሮፓውያን ደባና ዉሸት በግልጽ እንደርስበታለን። ​ሴቶች ከዘመናዊነት ዉልደት በፊት የቤተሰብን ሞራል ጠብቀዉ ይኖሩ ነበር። የአዲስ ትውልድ ግንባታ ላይ የሴቶች ሚና የላቀ ነው። ጠንካራ ቤተሰብ ባልዳበረበት ማህበረሰብ ዉስጥ ስለሰፊ ህዝብ ምግባር ማሰብ ከንቱ ነው። በጦርነቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወታደሮች ሞቱ። አብዛኞቹ ወታደሮች ወንዶች ስለነበሩ በአውሮፓ በብዛት የቀሩት ሴቶች ነበሩ። ባለሀብቶች በገንዘብ የሚቃኙዋቸውን ምሁራን ተጠቅመው አዲስ የሴቶች መብት አስተሳሰብ እንዲፈጠር አደረጉ። መንግስታቱም በቱጃሮቹ ሎቢ ተፅዕኖ ይሸፈኑ ስለነበር ንቅናቄዉን ደገፉ። ​ፌሚኒዝም የተሰኘ አስተሳሰብም ተወለደ። በዚህም ሴቶች ከወንዶች እኩል ናቸው በሚል ሽፋን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች የጉልበት ሠራተኞች ሆኑ። በተለያዩ ተቋማትም አገልጋይ ተደረጉ።.....

  • አባቶቻችን በመሰላቸው ኖሩ፤ ሀገር ገነቡ፤ አፈረሱ። ሶሻሊዝምን አመጡ፤ ዲሞክራሲን ሞከሩ፤ ኮንፌዴሬሽንን አዋቀሩ፤ ፌደራሊዝምን አቆሙ። ደርቡሽን አሳደዱ፤ እርስ በእርስ ተጨጫረሱ። አሁን የእኛ ተራ ነው። አባቶቻችን አርጅተዋል። ደክመዋል። ቀጣዩ ትውልድ ታሪክ ሲጽፍልን ያለፈውን ትውልድ ታሪክ ሲያጠፋ ነበር ብሎ ምህረት አያደርግልንም። በታሪክ ላይ የሚተው ክፍት ቦታ ሁሉ አጸያፊ ወንጀል ነው። «ምናልባት አንድ ቀን.....» ሄኖክ በቀለ ለማ አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ ራሕመት ታቦር ሕንፃ ፊትለፊት ምድር ባቡር የገበያ ማዕከል ዉስጥ። በሁሉም የአዲስ አበባ ከተሞችና የክ/ሃገር ከተሞች የdelivery(የማድረስ አገልግሎት) እንሰጣለን። ያሻዎ መጽሐፍት ወደዉጭ ሃገራትም በመረጡት የትራንስፖርት አማራጭ Deliver እናደርጋለን፥እንልካለን። ለበለጠ መረጃ፦በ0929574133 ይደዉሉልን መጽሐፍት ለማዘዝ፦ @Abduseller በቴሌግራም👇👇👇 https://t.me/Abdubook በtiktok፦👇??👇👇👇 https://www.tiktok.com/@abdubookdelivery?_r=1&_t=ZM-91WLxJQpsol

  • “…ኢትዮጵያ በታሪኳ ያሳለፈቻቸው መሪዎች (ከዓፄ ኃይለ ሥላሴ እስከ ደርግ፤ ከኢህአዴግ እስከ ብልፅግና ሥርዓት) ሥልጣናቸውን ያቆሙት በተቋማት ጥንካሬ ላይ ሳይሆን በራሳቸው ግላዊ አውሬነትና አንበሳነት ላይ ነው። ሕዝቡም ሆነ የፖለቲካ ሊቃውንቱ ‘መንገዱን’ (ሕገ-መንግሥታዊና ተቋማዊ ፍኖትን) ከመሪው ማንነት መለየት ተስኗቸዋል ወይም አልፈለጉም ወይም ባላይ ማለፍን መርጠዋል። መሪው ሲወገድ ተቋሙን አስቀጥሎ መሪን በሕግና በሥርዓት ከመሾም ይልቅ አሮጌውን መዋቅር አፍርሶ ሌላ አዲስ ምሳሌም አውሬ የመፈለግ አባዜ ውስጥ መግባቱ፤ ሀገሪቱን ሁልጊዜ ከዜሮ እንድትጀምር አድርጓታል።” «የቃል ፌርማታ » ቃልኪዳን ኃይሉ ገብሬ አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ ራሕመት ታቦር ሕንፃ ፊትለፊት ምድር ባቡር የገበያ ማዕከል ዉስጥ። በሁሉም የአዲስ አበባ ከተሞችና የክ/ሃገር ከተሞች የdelivery(የማድረስ አገልግሎት) እንሰጣለን። ያሻዎ መጽሐፍት ወደዉጭ ሃገራትም በመረጡት የትራንስፖርት አማራጭ Deliver እናደርጋለን፥እንልካለን። ለበለጠ መረጃ፦በ0929574133 ይደዉሉልን መጽሐፍት ለማዘዝ፦ @Abduseller በቴሌግራም👇👇👇 https://t.me/Abdubook በtiktok፦👇??👇👇👇 https://www.tiktok.com/@abdubookdelivery?_r=1&_t=ZM-91WLxJQpsol

  • ከ 5 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች የተሸጡለት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ይህ መጽሐፍ በሥራ ቦታ፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ ወይም በቤት ውስጥ ለሚያጋጥሙህ ወሳኝ ድርድሮች በተግባር የተፈተኑ ስልቶችን ይዞ ቀርቧል። ​ሕይወት የድርድር ውጤት ናት። አንተ የንግድ ሥራ መሪ፤ ሻጭ፤ ወላጅ፤ የማኅበረሰብ መሪ ወይም የትዳር አጋር ብትሆን... የላቀ የድርድር ክህሎት ለውጤታማ ግንኙነትና ትብብር መሠረትህ ነው። የቀድሞው የ FBI ታጋቾችን አስለቃቂ በሆነው የድርድር መሪ ክሪስ ቮስ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የሚሠሩ የማሳመኛ መሣሪያዎችን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ገልጧቸዋል። ​ ​ኒው ዮርክ ታይምስ (የከፍተኛ ሽያጭ ባለቤቶች) ​ዋል ስትሬት ጆርናል (የከፍተኛ ሽያጭ ባለቤቶች) ​በንግድ ስምምነት ዙሪያ መደራደር፤ ​መኪና መግዛት (ወይም መሸጥ)፤ ​የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ፤ ​ቤት መግዛት፤ ​የቤት ኪራይን በደጋፊ መደራደር፤ ​ከትዳር አጋርህ ጋር መመካከር ወይም ከልጆችህ ጋር መግባት የሚያስችሉህ ጥበቦች ሁሉ ተካተዋል። ​ታክቲካዊ ስሜት መጋራት፤ በንቃት ማዳመጥ እና የውስጥ ስሜትን የመረዳት ክህሎቶችን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋገረው “Never Split the Difference” በማንኛውም አcondition/አስቸጋሪ ውይይት ወይም ግጭት ውስጥ የውድድር ብልጫ ይሰጥሃል። መጽሐፉ ሁኔታዎች ምንም ዓይነት ቢሆኑ፤ በሌሎች ላይ ተፅዕኖ የማሳደር ጥበብን የምትማርበት ልዩ መድረክ ነው። አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ ራሕመት ታቦር ሕንፃ ፊትለፊት ምድር ባቡር የገበያ ማዕከል ዉስጥ። በሁሉም የአዲስ አበባ ከተሞችና የክ/ሃገር ከተሞች የdelivery(የማድረስ አገልግሎት) እንሰጣለን። ያሻዎ መጽሐፍት ወደዉጭ ሃገራትም በመረጡት የትራንስፖርት አማራጭ Deliver እናደርጋለን፥እንልካለን።

  • #ድንቅ_መጽሐፍ ከተወዳጁ ደራሲ #ሮበርት_ግሪን ​በእያንዳንዱ ቀን በሕይወት የምንገጥመው ጦርነት ብዙ ነው፤ ቀናችንን ብሎም ዘመናችንን ድል አድርገን ለመኖር ጦርነቶቻችንን የምናሸንፍባቸው የተረጋገጡ ስትራቴጂዎች ያስፈልጉናል። ​ይህ የተለያዩ ዘመናትንና ሥልጣኔዎችን በመቃኘት ፖለቲካዊ፣ ፍልስፍናዊ እና ሃይማኖታዊ ጥበቦችን በማካተት የተዘጋጀው ​“የጦርነት ስትራቴጂ” ​መጽሐፍ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ዉስብስብ ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችሉንን 33 ስትራቴጂዎች ይዟል። መጽሐፉ ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ጥልቅ ትምህርቶች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፤ ከናፖሊዮን እስከ ማርጋሬት ታቸር እንዲሁም ከካርል ቮን ክላውዘቪትስ እስከ ሱ ን ዙ ያሉ ታዋቂ መሪዎችንና ዲፕሎማቶችን እንዲሁም የቢዝነስ መሪዎችንና የደፋር ተዋጊዎችን ተሞክሮ በማካተት በሕይወት የሚያጋጥሙንን ጦርነቶች የማሸነፊያ ስልቶችን ያስታጥቀናል።

  • ይህ መጽሐፍ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል እና ፋይናንሺያል ታይምስን ጨምሮ በበርካታ መጽሐፎችና የንባብ ማዕከላት ዓመቱ ምርጥ መጽሐፍ ተብሎ ለመሰየም የበቃ ነው!!! ​ምልክት፡ አፋንን ተመልከት። ​ልማድ፡ መጽሐፍን አንብብ። ​ሽልማት፡ ልማድን የመቀየር ጥበብን ሙሉ በሙሉ ተረዳ። #​ብሉምበርግ_ቢዝነስ_ዊክ “አዝናኝ፤ አስደናቂ፤ ማራኪ፤ ስለ ልማድ ምስረታ እና የለውጥ ሳይንስ ጥልቅ እይታ የያዘ መጽሐፍ።” #ዘ_ኒው_ዮርክ_ታይምስ ቡክ ሪቪው ​“ጥቂት መጽሐፍት ለንግድ እና ለኑሮ እንደ አስፈላጊ መመሪያ ይቆጠራሉ፤ The Power of Habit ግን ከዚህ የተለየ ነው። ቻርልስ ዳሂግ ልማዶች እንዴት እንደሚፈጠሩ ብቻ ሳይሆን፤ መጥፎ ልማዶችን እንዴት ማስወገድ እና በምትካቸው እንዴት ጥሩዎቹን ልማዶች ማዳበር እንደሚቻል ያብራራል።” #ፋይናንሺያል ታይምስ ​“በጣም ምርጥ መጽሐፍ ነው።” ዴቪድ አለን፤ የGetting Things Done: The Art of Stress-Free Productivity ባለ ምርጥ ሽያጭ ደራሲ ​“ይህንን መጽሐፍ ካነበብክ በኋላ ራስህን፣ ድርጅትህንም ሆነ አጠቃላይ ዓለምህን በጭራሽ በቀደመው መንገድ አትመለከታቸውም።” #ዳንኤል ኤች ፒንክ፤ የDrive እና A Whole New Mind መጽሐፎች ባለ ምርጥ ሽያጭ ደራሲ ​“ፍጹም አስደናቂ መጽሐፍ ነው።” #ዋየርድ

  • ምን ሆኛለሁ? ልጅነትዎ አሁን ድረስ እርስዎ ላይ ጠባሳ አስቀምጦ እንዳለፈ ይሰማዎታል? "ምን ሆኛለሁ?" ከልጅነታችን ጀምሮ ያሳለፍናቸዉ ትናንሽ ነገሮች ትልቅ ከሆንን በኀ‍ላ ሊከተሉን እንደሚችሉ ያሳያል። ያኔ ያላስተካከልናቸው ችግሮች በግንኙነታችን ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ፣ ለራሳችን ያለንን ስሜት እና የሚሰሙንን ስሜቶች እንዴት እንደምንጠብቅ ያብራራል። እራሳችሁን ምን ሆኛለሁ? ብላችሁ ጠይቃችሁ የምታውቁ ከሆነ፣ ይህን መፅሀፍ አንብቡት። ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ታገኙበታላችሁ። በ ምን ሆኛለሁ❔ እንታረቅ❕ በትንሽ በትልቁ የሚከፋችሁ፤ በጀሯችሁ የገባውም ያያችሁትም ሁሉ እውነት የሚመስላችሁ፤ ልክ የሌለው ፍቅርና ጥላቻ የሚያናውዛችሁ፤ ከራሳችሁም፣ ከፈጣሪም፣ ከሰውም፣ ከተፈጥሮም የሚያጋጫችሁ፤ ምን ሆኛለሁ❔መጻሕፍን አንብቡና እንነጋገር ❕ እንታረቅ❕ ምን ኾነን ነው❔

  • ከመጽሐፉ የተወሰደ 📚 ​«እኔ ማን ነኝ?» የብርሃን ጉዞ ነው። ለመፈለግ ሳይኾሆን፤ ለማግኘት ሲኾን ግን፤ የጨለማ ጉዞ ይኾናል። «ማን ነኝ?» ብለህ ስትጠይቅ እንጂ፤ «እንዲህ ነኝ» ብለህ መልስ ስትሰጥ ተስፋ ትቆርጣለህ። ማንነት ጥያቄ ውስጥ እንጂ መልስ ውስጥ የለምና። ​ዳዊት፤ ከላይ የጻፈውን በሙሉ ሲያነበው፤ እንዳልጻፈው ገባው። አጣጥፎ ጣለው፤ እናም ቀድዶ ጣለው። ​«እንኳንም ሌላ ሰው አላነበበው፤ እንኳንም አልታተመ» አለና ከተቀመጠበት ተነሥቶ ወጣ። 📚 ምላስ ዐጫጭር ታሪኮች ✍️ከዳዊት ጸጋዬ

  • በአእምሮ ጓዳ ታፍነው ገና ያልተተነፈሱ እና ገሃድ ያልወጡ ሐሳቦች እና ምስሎች ነፃ የሚወጡበትን የትረካ ቴክኒክ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ሲጠቀም ለመገንዘብ ችዬአለሁ። አንዳንዶች ይህን የትረካ ቴክኒክ የንቃት ኅሊና ጅረት (Stream of Consciousness) በማለት ይጠሩታል። ​በእኔ ዕይታ ደራሲው በትረካ ጉዞው ስለ "Stream of Consciousness" ስያሜውን ከመስጠት ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከተውን የአሜሪካዊውን ሳይኮሎጂስት ዊሊያም ጄምስን ጽንሰ ሐሳቦችን እና በኃላም የ "Stream of Consciousness" ጅረት ምንጩን በተመለከተ ጠቃሚ ንድፈ ሐሳብን የቀመረውን የሩሲያዊውን ቪጎትስኪን መርሆች በተሳካ ሁኔታ ጥቅም ላይ አውሏቸዋል። አእምሯችን የሐሳቦቻችን መንሸራሸሪያ ሜዳ ቢሆንም፤ ጅረት ላይ እንደ ድልድይ ሆነው ለሚያገለግሉን የስሜት ሕዋሳቶቻችን ዕገዛ ፈስሰው የመጡት ከገሃዱ ዓለም ነው። ስለዚህም ገጸ ባህርዩ ቤቱ አንዳንድ ጊዜም ከራሱ የሐሳብ ምህዋር ወጣ ብሎ ስለ ወቅታዊ ፖለቲካ ትኩሳት፣ ስለ ኮሪደር ልማት፣ ስለ ኢኮኖሚው ውድቀት፣ ስለ ኤርትራውያን ስደተኞች ወዘተ ማንሣቱ በቀጣይነት በአእምሮው ጓዳ ለሚያሰላስላቸው ሐሳቦች ጥራፊ ፍለጋ እየባተለ እንደሆነ መረዳት ግድ ይላል። በዚህም ሂደት በልብ ወለድ እና በቤ-ልብ ወለድ መካከል ያለው ድንበር በእጅጉ ሳስቶ አንባቢው ግራ ሊጋባ ይችላል። ከዚህም የተነሣ "ቡናዬ እስኪበስል" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ የትርክት ስልቱ በዋናነት "Stream of Consciousness" ሆኖ፤ የዘውግ ምደባው ግን ለ"Creative Non-fiction" ወይም ለ"Fiction-Non-Fiction" የቀረበ ነው። ​ኢንጂነር ጌታሁን ሔረሞ

  • «ሙት ምን አቅም አለዉ?»ለምትሉ.... ከእያንዳንዱ ነዋሪ ሙት አቅም አለዉ! በሞተ ሰዉ ቃል ህያዉ ይኖራልና። የሞተ ቅጠል ለአዲሱ ቅንጥብ ግብአት አይደል...?? እነሆ ጀርባዬ ባዶ ነዉ ምክንያቱም የማንንም ሃሳብ በጀርባዬ ላለማዘል ስል....!!! 📚📚 «ክብካቦት» ✍️ሳይላለም ተሰማ

  • «ትልቅ የመሆን ተስፋ የመከነብሽ፣ወደፊት የሚገፋ፣ፅናትን የሚሰጥ መንፈሳዊ ጥንካሬ የሌለሽ....ሬል ሆይ! ምንኛ የተረገምሽ ነሽ! እንደ ባህር ወለል ቢጨምሩበት፣ቢያክሉበት ለማይሞላ ሆድ መሽቶ እስኪነጋ የምቶኳትኝ አጋሰሷ ሬል ሆይ! ምንኛ አሳዘንሽኝ፣ምንኛ አሳቀቅሽኝ!» 📚 የአምባዉ ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ ✍️ፍቅረማርቆስ ደስታ

  • እንቁላል ለመጣል ምድምድ ስፍራ እንደምትፈልግ ዶሮ፤ ዝርዝር ራሴን የምመለከትበት ስፍራ በመፈለግ ደከምኹ። የዝርዝር ራስ ሆጭሆጭታን መስማት ደግሞ ናላን ያዞራል። ተከብቤም በሰው መኻል፤ ተነጥዬም ብቻዬን፤ ዐውቀው ይሆን ራሴን ብዬ መረመርኹ። ግን ራስ ሁልጊዜ እንግዳ ነው። እንግዳ ደግሞ ያው እንግዳ ነውና በል እስኪ አንተ ስታወራ እኔ ልስማ ብዬ፤ አንዲትም ቃል ሳላወጣ ራሴን አደመጥኹት። ​መዳፍ ላይ አንሰራፈን የምናነበውን መጽሐፍ “እኔ” ብለን እንደማንጠራው፤ እንደዚኹም እኮ የሚነበብ ራስንን እኔ ብሎ መጥራት ያስገምታል ብዬ በጽሞናዬ ቆየሁ። ​ደግሞ “መገኘት ማየት ከሆነ፤” ለመመልከቻ ምቹ ስፍራ ለማግኘት እስኪደክሙ መንከራተት. . .... 📚"ገበታ" ዳረጎት ዐሳቦች ✍️ፍቃዱ አየልኝ

  • #ሀብታም_የመሆን_ጥበብ ​"ሀብታም የመሆን ጥበብ የወደፊት የሀብት እድል ፈንታቸውን በራሳቸው መወሰን ለሚፈልጉ ትክክለኛው መነሻ ነው። ሮበርት ኪዮሳኪ ሰዎችን እንዴት ሚሊየነር እንደሚሆኑ ያስተምራል፤ በዚህ የተነሳ ሚሊየነሩ መምህር የሚል ቅጽል ስም አትርፏል።" — ዩ.ኤስ ቱደይ ጋዜጣ ​"ሀብታም መሆን የሚያስችለንን ጥበብ የምንሻ ከሆነ ይህን መጽሐፍ እናንብብ። በተለይ ልጆቻችን በገንዘብም ቢሆን ደልለን ይህንን መጽሐፍ እንዲያነቡት ብናደርግ መልካም ነው።" — ማርክ ቪክተር ሀንሰን ቺክን ሶፕ ፎር ዘ ሶል' ተባባሪ ደራሲ ​"የጂ. ፒ. ሞርጋን ኩባንያ ይህንን መጽሐፍ ሀብታም የመሆን ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በጠቅላላ ሊያነቡት የሚገባ መጽሐፍ እንደሆነ ገልጿል።" — ዎል ስትሪት ጋዜጣ ​"ሰዎች ትምህርት ቤት ውስጥ በሚያሳልፏቸው በርካታ ዓመታት ስለ ገንዘብ ምንም ነገር ባለመማራቸው በቀሪው የሕይወት ዘመናቸው ከፍተኛ ትግል ይጠብቃቸዋል። የትምህርት ሥርዓቱ ደግሞ ገንዘብን እንዲሠራላቸው ከማድረግ ይልቅ ለገንዘብ እንዲሠሩ አድርጓቸዋል።" — ሮበርት ቲ. ኪዮሳኪ