Abel Demelash - አቤል ደመላሽ
Статистика- Последний пост
- 9 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 202
- 1/48двое суток
- 231
- 1/72трое суток
- 249
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/S_mKP0tw0ME
#ሰርጀሪው_በድል_ተጠናቆ_ወደ_ቤቱ_ገብቷል 🙏🥰 ዮኒ ላከኝ በብርቱ ታሞ እንደነበር የሚታወቅ ነው እነሆ ያንን ፈታኝ የሕመም ጊዜውን ካለፈ በኃላ በLancet Hospital የመጀመሪያው ሰርጀሪ ተደርጎለትና በድል አጠናቆ ዛሬ ወደ ቤቱ በመግባቱ ለተጨነቃችሁለት ለፀለያችሁለት እና ላገዛችሁት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ከልብ እናመሰግናለን ለማለት እወዳለሁ ። #ለእግዚአብሔር_ሁሉ_ይቻላል 🙏
#ታላቅ_የምስራች_ዜና_ከሆስፒታል 🥰 የመትረፍ ዕድሏ 20 ፐርሰንት ነው መናገርና መንቀሳቀስ ላትችል ትችላለች የተባለችው እህታችን ዘማሪት ብሩክታዊት ብዙ ሰአት ከፈጀው ሰርጄሪ በሁዋላ ከቀን ቀን ጤንነቷ አስደናቂ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተሰምቷል ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#አሳዛኝ_ዜና_ደርሶኛል 🥺💔#ዘማሪዋ_ከወለደች_በኃላ_አርፋለች በሀዋሳ የአለም ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ሕብረት አባል እንዲሁም በድል ብስራት ቸርች ያለገለገለች ቀጥሎም በነዋት የወንጌል አገልግሎት ሕብረት መስራች ከሆኑት መካከል አንዷ የሆነችው ለህብረቱም መዝሙሮችን በመስጠት ስታገለግል የነበረችው እህት ዘማሪት ድንቅነሽ / ሚጦ ልጇን እንደተገላገለች ከሰዓታት በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ወዳገለገለችዉ ጌታ ሄዳለች ። #ለቤተሰብዋ_እና_ወዳጆቿ_ሁሉ_መፅናናትን_እመኛለሁ ©️ Abel Demelash - አቤል ደመላሽ ቴሌግራም 👉 https://t.me/AbelDemelash1
видео или голосовое, без подписи
#ዘፈን_በቃኝ_እዘምራለሁ - #ድምፃዊ_አቤል_ሙሉጌታ 🙏🥰 በመዝሙርም ሆነ በዘፈን ዓለም ስሙ በጉልሕ የሚታወቀው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ፣ ለዓመታት ሲታገለው ከነበረውና "ውስብስብና አጋንንታዊ" ካለው የዘፈን ዓለም ተለይቶ ሙሉ በሙሉ ወደ ጌታ መመለሱን በታላቅ ደስታ አበሰረ። አቤል ወደ ኋላው መለስ ብሎ ሲመለከት፣ የዘፈኑ ዓለም ከስካርና ከመንፈሳዊ ዕረፍት ማጣት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ይገልጻል። "በሃጢአት ስረክስ፣ ደግሞ ፊቱን ስፈልግ፣ ሳመነታ ሰይጣን ዘመኔን ሊበላው ሲያባብለኝ የልጅነቴ አምላክ ደረሰልኝ" በማለት የእግዚአብሔርን ታዳጊነት መስክሯል። አቤል ለዓመታት ሲመላለስበት የነበረውን ሕይወት በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይገልጸዋል፣ “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፦ የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል ዕውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል” (2ኛ ጴጥሮስ 2፥22) ይህ ቃል በእርሱ ሕይወት ደጋግሞ ቢፈጸምም፣ ዛሬ ግን ያ ቀን ማክተሙንና ሸክሙ መውደቁን በደስታ ተናግሯል። አቤል አሁን ለሕዝብ ያቀረበው "እሰይ" የተሰኘው ዝማሬ የተጻፈው በ2003 ዓ.ም. እንደነበር ገልጿል። በዚያን ወቅት በከፍተኛ ናፍቆት "ከእርያ ጋር ሆኜ አባቴ ቤት ሄጄ ባሪያ በሆንኩ" እያለ በናፈቀበት ወቅት የጻፈው መሆኑ፣ ዛሬ ለደረሰበት የዕውነተኛ ነጻነት መሰረት ሆኖታል። አሁንም በዘፈኑ ዓለም ውስጥ ላሉ ጓደኞቹ "ሽንገላ የለኝም" በማለት፣ ዘፋኝነትና ስካር የማይነጣጠሉ መሆናቸውንና እርሱን የታደገው አምላክ እነሱንም እንዲታደጋቸው ያለውን መልካም ምኞት ገልጿል። "ከዚህ በኋላ በዘፈኑ ዓለም የለሁም! ዳግም ዞር ብዬ አላየውም! ስሙ ይባረክ፤ ኢየሱሴ ጌታ ነው!" ብሏል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#ከእስልምና_ወደ_ኢየሱስ_ሙሉ_ቤተሰቦች_መጡ 🙏🥰 በኦሮሚያ ክልል ጉጁ ዞን በቦሬ ከተማ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በተዘጋጀው ኮንፍራንስ አንድ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ የነበረ ወንድም ወደጌታ መጥቷል። በሲዳማ ክልል መካከለኛ ሲዳማ ዞን አርቤጎና አከባቢ አንድ ወንድም ከነ-ቤተሰቦቻቸው ከቤተክርስቲያን ወደ እስልምና ኮብልለው የነበረ ሲሆን በዚህም ምዕመኑ በጌታ ፊት ስለርሱና ስለ ቤተሰቡ በጸሎት ተንበርክኮ ለብዙ ጊዜ የቆየ ሲሆን በትናንትናው እለት ከነ ቤተሰቡ በንስሃ ወደ ጌታ ተመልሷል። ክብር ለጌታ ይሁን!! መጽሐፉ እንደሚናገረዉ "እርሱ ያለዉ ሕይወት አለዉ፤ ኢየሱስ የሌለው ሙት ነው! በሕይወት የለም! ሕይወት ኢየሱስ ነው!! ሰው ሕይወት አለው የሚባለው ኢየሱስ ሲኖረው ነው!! "ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።" 1ኛ ዮሐ - 5፥12 እኚህ አገልጋይ ያዕቆብ ዮዶሩ የተባሉት በሲዳማና በአጎራባች ኦሮሚያ አካባቢዎች እያገለገሉ የሚገኙ ጌታ የሚጠቀምባቸዉ ድንቅ አገልጋይ ናቸዉ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи