tgindex
Alif Geopolitics

Alif Geopolitics

Статистика

🇪🇹 🌍 በሀገራችን ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ እና በሙስሊሙ ዓለም የሚኖሩ አዳዲስ ክስተቶች ከታማኝ ምንጮች የሚቀርቡበት ገፅ ነው ✍️

Последний пост
9 апр.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 920
−12 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
495
20 постов
Вовлечённость
10,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 9 апр.25013из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 የኢራን ጦርነት ውጤትና ቀጣይ ተፅዕኖው… የጦርነት አሸናፊ የሚለካው ተዋጊ ኃይሎቹ ወደ ጦርነቱ ሲገቡ ባስቀመጡት ግባቸው ልክ ነው፡፡ አሜሪካ እና እስራኤል ወደ ጦርነቱ ሲገቡ ያስቀመጡ ግብ በኢራን የመንግስት ለውጥ ማድረግ፣ የኒውክሌር መሰረተ ልማቷን ማውደም እና የሚሳኤል አቅሟን ማዳከም እንዲሁም ከተቻለ የበለጸገ ዩራኒየም ክምችቷን ከዚያች ሀገር ማውጣት እና ሀገሪቱን በጎሳ በመከፋፈል ትንንሽ ሀገራትን መፍጠር ነበር፡፡ ኢራን በበኩሏ እነዚህ ከላይ የተገለጹት የጠላት ግቦች እንዳይሳኩ ማድረግ ብቻውን ግቧ ነበር፡፡ በጦርነቱ ሁሉም እንደሚረዳው ኢራን ከፍተኛ የአየር የበላይነት የተወሰደባትና ይህን ከተከትሎ ብዙ ቁልፍ መሪዎቿን፣ ብዙ የሚሳኤል ክምችቷን እንዲሁም የኃይል መሰረተ ልማቷን ያጣች ቢሆንም እስከመጨረሻው ቀን ድረስ ባለስቲክ ሚሳኤል ስታስወነጭፍ የጠላት አውሮፕላን እና ድሮኖችን እየመታች ስትጥል እንዲሁም ሆርሙዝ ላይ ሙሉ ቁጥጥሯን በማረጋገጥ በራሷ ያስቀመጠችውን ግብ አሳክታ መዝለቅ ችላለች፡፡ በተቃራኒው እስራኤል እና አሜሪካ ኢራንን ማዳከም የቻሉ ቢሆንም ያስቀመጡትን ግብ አንዱንም ሙሉ በሙሉ ማሳካት አለመቻላቸው እንዲሁም በእስራኤልም ሆነ በባህረ ሰላጤው አገራት ያሉ የፀረ ሚሳኤል ክምችቶች ከዕለት ወደ ዐለት እያነሱ መምጣታቸው ለድርድር እንዲዘጋጁ ግድ ብሏቸዋል፡፡ አሜሪካ እነዚህን ፀረ ሚሳኤሎች ለመተካት ብትፈልግ እንኳ ያላት ክምችት ውስን በመሆኑ በእስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን ማንቀሳቀስ ይኖርባታል። ይህ ቢደረግ እንኳ አሜሪካ ያላት በተለይም የታድ ፀረ ሚሳኤል ክምችት በጣም ውስን በመሆኑ ምርቱን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ያስፈልጋል፤ ይህም በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ በተግባር የማይቻልና እጅግ ውድ ነው። አሜሪካ የሎጂስቲክ ወይም የአስቻይ ሁኔታ ጉዳይ ሳይሆን ፀረ ሚሳኤል ምርት እጥረት ገጥሟታል፡፡ በተቃራኒው ኢራን በጦርነቱ ጅማሬ ሚሳኤሎቿ ከነበራቸው 5% ኢላማ የመምታት ንጻሬ በቅርብ ቀናት 25% ደርሷል፡፡ ኢራን የአሁኑ ሰዓት ኃይሏን መልሳ ለመገንባት ወታደራዊ አድቫንቴጅ ይኖራታል። የሁለት ሳምንት የእረፍት ጊዜ ኢራን የባሊስቲክ ሚሳኤል ቤዝ መግቢያዎቿን እንድታጸዳና በምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙትን ጨምሮ በርካታ ቤዞቿን ወደ ሥራ እንድታስገባ ይረዳታል። በተመሳሳይ ጊዜ ድሮኖችና ሚሳኤሎች ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ወደሆኑ ራቅ ያሉ ቦታዎች በምስጢር እንዲዛወሩና እንዲሰራጩ ማድረግ ያስችላል። ድሮኖች ከመጋዘን ወጥተው በተራራዎችና በሸለቆዎች መካከል ወደሚገኙና ለመለየት ወደማይቻሉ ‘የመተኮሻ መንገዶች’ ሊሰራጩ ይችላሉ። ባጭሩ ይህ ማለት ኢራን ከሁለት ሳምንታት በኋላ ጦርነቱን ለመቀጠል ወስና እጅግ ግዙፍና የተቀናጀ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶችን በጠላት ላይ ልትሰነዝር ትችላለች ማለት ነው። በተኩስ አቁሙ እና በድርድሩ ጊዜ፣ የኢራን አቋም ካለፉት ጊዜያት በበለጠ ይጠነክራል። ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የመደረጉ ዛቻ ቀደም ብሎ የተሞከረ ካርድ ነው፤ አሜሪካም ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ዓላማውን ማሳካት ባለመቻሉ አሁን ላይ ያላት ተሰሚነት ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ያነሰ ነው። በሌላ በኩል ኢራን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥን በመዝጋት የዓለምን የነዳጅ አቅርቦት ማሽመድመድ እንደምትችል አሳይታለች፤ ይህም በጣም ጠንካራ ካርድ ነው። የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም የኢራን ኮማንደሮችና ውሳኔ ሰጪዎች እቅዶቻቸውን እንደገና እንዲያደራጁና እንዲያስተካክሉ ይረዳቸዋል። እንዲሁም የደህንነት ሁኔታዎች ከፈቀዱና ከፍተኛ ጥንቃቄ ከተደረገ፣ አዲሱ መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን እንዲታይ ዕድል ይሰጣል፤ ይህም በአገር ውስጥ በራስ መተማመንን የሚፈጥርና የኢስላማዊ ሪፐብሊኩን አመራር ቀጣይነትን የሚያረጋግጥ ይሆናል። በዚህም የተኩስ አቁሙ ለኢራን ጠቃሚ ሊሆን የሚችለው አመራሩ ስለ አሜሪካ እና እስራኤል ማንነት ሙሉ ግንዛቤ ኖሮት ወደ ድርድሩ ሲገባ ብቻ ነው። ባለፉት ሁለት ጊዜያት ኢራን ስትደራደር ጥቃት ስለደረሰባት በአሜሪካው ላይ ሙሉ ጥርጣሬ ሊኖራቸው ይገባል። በጦርነቱ ወቅት ኢራን አሜሪካ ለይ ጫና ማድረጊያ አማራጭ አድርጋ በማሰብ በአረብ ሀገራት ላየ የፈጸመችው ጥቃት የእሷን እቅድ ያሳካ ቢሆንም በዘላቂነት በሀገራቱ ዘንድ እንዳትታመን ከእራኤልም በላይ ስጋት ሆና እንድትታይ ያደረጋት ሲሆን ውጤቱ ጥሩ ነው ወይስ መጥፎ የሚለውን አሁን ማወቅ አይቻልም፡፡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዘላቂ ባይመስልም አሁን ባለው ሁኔታ ኢራን ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ አራሷ ባስቀመጠችው የድርድር መርህ መሰረት ከበፊቱ ይልቅ በተሻለ ጥንካሬ የምትደራደር ይሆናል፡፡ በዚሁ ወቅት የእስራኤል ተጋላጨነት እና የችግሮች ሁሉ መነሻነት ይበልጥ የታየበት፣ ቻይና የበለጠ ወደሚዛናዊ የዓለም ኃሓልነት የመጣችበት፣ ሳዑዲ አረቢያ የተሻለ የመከላከያ አቅም እንዳላት የታየበት ሆኖ አልፏል፡፡ @Alif_Online_Official

  • 18 мар.288из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇸🇦🌙 #ሰበር የሸዋል ጨረቃ ዛሬ አለመታየቷን ተከትሎ ነገ የረመዳን 30ኛው ቀን ሆኖ ከነገ ወዲያ ጁሙዓ 1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል ፊጥር መሆኑ ተረጋግጧል። @Alif_Online_Official

  • 27 нояб.5324из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇸🇦🇵🇸🇺🇲🇮🇱⚡ መሐመድ ቢን ሳልማን ከእስራኤል ጋር ይጀምረዋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ካዘገየ በኋላ ትራምፕ እንደተበሳጨ ተዘግቧል! ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከመሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በዋይት ሀውስ በነበረው ውዝግብ ምክንያት “ተስፋ ቆርጦና ተቆጥቶ” እንደነበር የእስራኤሉ ቻናል 12 ዘግቧል። ትራምፕ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በፍጥነት እንዲጀምር ልዑሉ ላይ ግፊት እንዳደረገበት ውይይቱን የሚያውቁ ምንጮች ገልጸዋል። ቢን ሳልማን በመርህ ደረጃ እስራኤል ጋር እርቅ መፍጠርን ባይቃወምም፣ ከጋዛው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በኋላ በሳዕዲ አረቢያ ህዝብ ውስጥ የሚታየው ጠንካራ ፀረ-እስራኤል ስሜት በዚህ ጊዜ እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ የማይቻል ያደርገዋል ሲል ለትራምፕ ምላሽ ሰጥቷል። አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ውይይቱ ጨዋነት የተሞላበት መሆኑን እና ልዑሉ ሙሉ በሙሉ እርቁን እንደማይቃወም አፅንዖት ሰጥተዋል። ቢን ሳልማን ወደፊት በሩ ክፍት እንደሆነ ቢገልጽም፣ የሁለት ሀገራት መፍትሄ ጉዳይ ተግባራዊ መደረጉ ዋና ቅድመ ሁኔታ መሆኑን በዲጋሚ አረጋግጧል። @Alif_Online_Official

  • 25 авг. 2025 г.6404из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇵🇸🇸🇦🕋  #ሻም ካዕባ በኢብራሂም (ዐ.ሰ) ዳግም ሲገነባ በኑህ (ዐለይሂ-ሰላም) ዘመን ታላቅ ጎርፍ ተከስቶ መስጂድ አል-ሀረምን ከካዕባ ዋና መሠረተ ልማቶች በስተቀር ሙሉ በሙሉ ስላጠፋው ነበር። ይሁን እንጂ ካዕባ ምድር ላይ የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት የነበረ መስጂድ ነው! ኢማም አል-በገዊ እንዳሉት ካዕባ በመጀመሪያ የተገነባው አደም (ዐ.ሰ) ወደ ምድር ከመላኩ 2000 ዓመታት በፊት በመላኢካዎች ነው። በኋላ፣ አደም (አለይሂሰላም) የካዕባን መሰረት አንድ ጊዜ እንዲጥል ታዘዘ። መስጂድ አል-አቅሳ የተገነባው ከካዕባ በኋላ 40 አመት ብቻ በመሆኑ፣ ከመጀመሪያዎቹ የሰው ልጅ የምድር ላይ ህይወት ጀምሮ ምናልባትም ከዚያ በፊትም እንደነበረ መረዳት ይቻላል። መስጂድ አል-አቅሳ አጠገብ ስለሚኖሩት ሰዎች ብዙ ሀዲሶች አሉ። ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ሲናይ ድረስ ያለውን የዛሬዋን ሶርያን፣ ፍልስጤምን፣ ሊባኖስን እና ዮርዳኖስን የሚያጠቃልለው የሻም ሕዝብ ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‘የአላህ የተመረጠች ምድር ሻም ናት በውስጧም የሱ የተመረጡ ህዝቦችና ባሮቹ አሉ። ከኔ ህዝቦች ቡድን ያለ ምንም ሒሳብና ቅጣት በእርግጥ ጀነት ይገባሉ። [ጦበራኒ] ዐውፍ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “አል-ሻም ከመውደሟ አርባ አመት በፊት አለም ትወድማለች። (ኢብኑ አሳኪር) ሙጃሚ ኢብኑ ጃሪያህ ከአላህ መልእክተኛ እንዳስተላለፉት፡- “ኢብኑ መርየም (ኢሳ) ደጃልን በ-ሉድ በር ላይ ይገድለዋል (ሉድ ኢየሩሳሌም አከባቢ የምትገኝ መንደር ነች)። (ቲርሚዚ እና አህመድ) ናሂክ ኢብኑ ሱረይም አል-ሳኩኒ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል:- "ከእናንተ ከፊሉ አሕዛብን በእርግጥ ትዋጋላችሁ በዮርዳኖስ ወንዝ በኩል ዳጃልን እስክትዋጉ ድረስ። እናንተ ከእርሱ በስተምስራቅ ትሆናላችሁ እነርሱም ከሱ በስተ ምዕራብ ይሆናሉ። (መጅመእ አል-ዘዋኢድ) አቡ ደርዳእ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- “ከአል-ሻም በላይኛው ሜሶፖታሚያ እስከ ሩቅ ጫፍ ድረስ፣ በውስጧ ያሉት ነዋሪዎች፣ አብረው ከሚስቶቻቸው፣ ከልጆቻቸው እና ከአገልጋዮቻቸው (ወንዶች እና ሴቶች) ጋር፣ ሪባጥ (የሙስሊሞችን ድንበር በአላህ መንገድ በመጠበቅ) ላይ ናቸው። ማንም ቢሆን በነዚህ ቦታዎች ቦታን የያዘ ሪባጥ ላይ ነው። ከነዚህ ግንባሮች የትኛውንም ግንባር የሚይዝ ጂሃድ ውስጥ ነው። (ኢብኑ አሳኪር) አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- “የእኔ ኡማ በደማስቆ ደጃፍ እና በይት አል-መቅዲስ (ኢየሩሳሌም) በሮች እና አከባቢያቸው ላይ ትግሉን አያቆምም። የሚክዷቸው ሰዎች ክህደት ወይም የሚተዋቸው ሰዎችም ምንም አይጎዷቸውም። እነሱ የመጨረሻዋ ሰዓት እስክትመጣ ድረስ አሸናፊዎች ሆነው ይቀጥሉ። (ጦባራኒ) አቅሳ ለሻም ሻምም ለኢስላም ዳግም ማንሰራራት መሰረት ናቸው, የመጨረሻው ዘመን ዋና ዋና ክዋኔዎች የሚስተናገዱትም በዚህችው ምድር ነው። ፍልስጤማውያንም ለሙስሊሙ አለም የመጀመሪያውውን የጂሃድ ግንባር ይዘው በፅናት ቆመዋል። @Alif_Online_Official

  • 15 авг. 2025 г.4255из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇬🇧🕌 በአሁኑ ጊዜ እስልምና በእንግሊዝ ግዙፉ ከተማ በርሚንግሃም ውስጥ ትልቁ ሀይማኖት ሆኗል፡ 34.2% ነዋሪዎች ሙስሊም መሆናቸው ሲገለጽ  32% ነዋሪዎች ክርስቲያን መሆናቸው ሪፖርት ተደርጓል። @Alif_Online_Official

  • 8 июл. 2025 г.53061из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇮🇶🇸🇦 ከርብ "كَرْب"ብዙ ሥቃይን የምታመጣ ምድር" በላዕ "بَلاء" ማለት ደግሞ መከራ ማለት ነው። ከርበላዕ ላይ የተከሰተው ክስተት በታሪክ አጋጣሚ እንዲህ ሆኖ ነበር ብለን የምናልፈው ሳይሆን ሀቅን ይዞ የመፅናትን ሞት ፊታችን ተደቅኖም በእውነት መስመር ለዓላማ መቆምን የምናይበት ዘላለማዊ ህያው ክስተት ነው። ሁሰይን ከውዱ ሰው ረሱል ልጅ የሴቶች ሁሉ ቁንጮ ፋጢማ ቢንት ሙሀመድ እንዲሁም ለዓለማቱ እዝነት ለተላኩት ነቢይ ቅርብ ያውም የአጎት ልጅ ከሆነው አራተኛው ኸሊፋ ዐሊ የተወለዱ መሠረታቸው ሁሉ ያማረ ሰሃባ ናቸው። ለእኚህ ድንቅ ሰው በልጅነታቸው ረሱል የነበራቸውም ውዴታ ቃላት የማይገልጹት የአባት እና የልጅ ሲሆን ልጄ ብለው ጠርተዋቸውም ያውቃሉ ዱኒያ ላይ ለኖረ የአደም ዘር በዚህ ሁሉ እድለኝነት በረሱል እቅፍ ስር ከማደግ ከዚያም ሙስሊም ሆኖ ለሀቅ ቆሞ ሞትን ከመጋፈጥ የበለጠ ሸረፈ የለም። የዚድ የአቡ ሱፍያን የልጅ ልጅ እና የሙዓውያ ልጅ ነበር። የተወለደው በ26ኛው ዓመተ ሂጅራ ሲሆን ገና በለጋ እድሜው አባቱ ቁስጥንጥንያ ላይ የዘመተውን ጦር አዛዥ አድርገው ሾሙት። ሁሰይን በዚህ ጦርነት ከየዚድ ጋር ተሰልፈው ተዋግተዋል። ቡኻሪ በዘገቡት ሀዲስ ረሱል እንዲህ ብለዋል:- “ከዑመቴ (ከህዝቤ) የቄሳርን ከተማ የሚያጠቃው የመጀመሪያው ጦር ይቅርታ ይደረግለታል/አላህ ምህረት ያደርግለታል። ስለዚህም ይህን እድል ያገኘው በየዚድ ይመራ የነበረው ሰራዊት መሆኑን እንገነዘባለን። 💠 ለሁሰይን እና የውዱ ሰው የረሱል ቤተሰቦች መገደል ተጠያቂው ማነው? 1, የኩፋ ሰዎች, ሑሰይንን ምንም ቢሆን እንደግፍሃለን ብለዋቸው ነበር። በመጨረሻ ግን ሁሰይን በከርበላዕ ውስጥ ለአምስት ቀናት ያህል ከበባ ውስጥ ሲቆዩ፣ በተግባር ከጎናቸው ሊቆሙ የተነሱ ሰዎች አልነበሩም። ሁሰይንን ለመርዳት ማንም አልወጣም። 2, ኢብኑ ዚያድ, ከሁሰይን ጋር በነበረው ግንኙነት እብሪተኝነት እና ጭካኔ አሳይቷል። አላህም በዱኒያ ጭምር ቀጥቶታል። ህይወቱ በጦርነቶች የተሞላ ነበር፣ ሞቱም አካለ ጎደሎ ሆኖ ጭንቅላቱ ተቆርጦ መፈፀሙ እና ጭንቅላቱ ለፍርድ ቀርቦ በዱኒያ ተዋርዷል። ይህ ብቻ ሳይሆን በሕዝብ ፊት እባብ ራሱ ላይ ወጥቶ በአፍንጫው ጭምር ገብቶ ጠፍቷል። 3. ዑመር ኢብኑ ሰዕድ, አንዳንድ ዑለማዎችም ኢብኑ ዚያድን ባለመቃወሙ እና ሁሰይን ጋር አልዋጋም ባለማለቱ እሱም ጥፋተኛ መሆኑን ይመሰክራሉ። 4, ሽምር እና ቡድኑ, በሁሰይን ላይ የመጨረሻውን ድብደባ የፈፀመው እና በመጨረሻም የገደለው ይህ ሰው ነበር። 5, የዚድ ኢብኑ ሙዓውያህ ብን አቡ ሱፍያን ከዚህ ታሪካዊ ወንጀል እና ኢስላም እና የመልእክተኛው ቤተሰቦች ክብር ላይ ለማሰብ የሚገብድ ግፍን ፈፅሟል። ኢብኑ ዚያድን ወደ ኩፋ የላከው የዚድ ነበር። በከርባዕ ላይ ለተፈጠረው እልቂት ጥፋተኛነቱን በሚገባ ይካፈላል። ሁሰይንን ለመግደል አስቦ ላይሆን ይችላል። የሁሰይን ጭንቅላትን ባመጡለት ጊዜም "እንዲገደል አልጠየቅኩም" ብሎ ነበር። እንዲሁም በጨርቅ ጠቅልሎ ለሁሰይን ቤተሰብ አስረክቧል። ነገር ግን ሁሰይን ግድያ ላይ በቀጥታ ከተሳተፉት ወንጀለኞች ማንንም አልቀጣም ስለዚህ ከጥፋቱ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ምንም ጥርጥር የለውም። የኢማም አህመድ ቢን ሀንበል ልጅ "የዚድን መውደድ አለብኝ ወይ? " ብሎ አባቱን ጠየቃቸው። ኢማሙ አህመድም “አማኝ ሆኖ/ኢማን ኖሮት የየዚድን መውደድ የሚችል አለን?” ሲሉ ለልጃቸው መለሱ። ልጁም “እርግማን እንርግመው ዉይ?” ሲል ጠየቀ። ኢማሙ አህመድም “ማንንም ሰው በስም ስረግም አይተሃልን?” ሲሉ መለሱለት። ሁሰይንን እና ሀሰንን ረሱል እጅግ ይሳሱላቸው ነበር ለቅሷቸውን ከሰሙ የያዙትን ትተው ያባብሏሰ ነበር  ደግሞ የፋጢማ እና የዐሊ ልጅ ናቸው። አላህ በሁሉም ነገር ላይ ውስጥ አዋቂ ነው። ሁሰይን የከሃዲ መብዛት ያላስፈራቸው ደግሞ ግልፍተኛ ሳይሆኑ ነገሮችን ላለማባባስ የሞከሩ አስተዋይ ነበሩ ሁሰይን አለንልህ ያሏቸውን ወንድሞቻቸውን ያመኑ እነሱ ዘንድም የሄዱ ታማኝ ነበሩ ሁሰይን ከበባ ውስጥ ገብተውም የረሱልን ቤተሰብ ከማያከብር አገዛዝ ጋር ቃል አልጋባም ያሉ ፅኑ ነበሩ ሁሰይን የሚጠጣ ውሃ ተነፍገው ለከሃዲ እጅ ያልሰጡ በሃቅ በመሞት ድል ማድረግን የመረጡ ነበሩ ዛሬ ጋዛ ዙሪዋን ሙስሊሞች ከበዋታል ግን የሚጠጣ ውሃ የሚበላ ምግብ የላትም ዛሬ ጋዛ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ ብዙ መቶ ሺህ ጦር ብዙ ትሪሊዮን ሀብት ያላቸው ሙስሊም ጎረቤቶች አሏት ግን ከአይሁዶች ጥቃት የሚከላከል ከረሃብም የሚታደጋት የለም ዛሬ ጋዛ ከበባ ውስጥ ነች ህይወትን ለማዳን ምግብ እና ውሃ ደግሞ ከቦምቡ ውርጅብኝ ፋታ ትፈልጋለች ግን ለዱኒያ ተብሎ አላህን ከማያውቁ ጋር መወዳጀትን እንቢ ብላ ፀንታለች እውነተኛ ድል ጦርነትን በማሸነፍ ጠላትን በመግደል ውስጥ ብቻ አይመጣም አንዳንዴ እንደ ሁሰይን በከሃዲ በመገደል ውስጥ ጀነትን የሚያወርስ ድል አለ, እንደ ጋዛም ሁሉም ሲብረከረክ ፈሳድ የተሸከመ ጠላትን ተጋፍጦ ክህደትን አዋርዶ በመገደል ድል ማድረግም አለ። @Alif_Online_Official

  • 24 июн. 2025 г.4322из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇮🇷⚡🇮🇱 ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የተስማማችበት ምክንያት ምንድነው እስራኤልስ አሸናፊ ነች? በጦርነቱ ጅማሮ ጥቃት ከውስጥ በተዘጋጀ የጥቃት እቅድ እና በእስራኤል ሰፊ የአየር ድብደባ ምክንያት አብዛኛው የኢራን ረጅም እና መካከለኛ ርቀት የአየር መከላከያ ተጠራርጎ ወደመ። ከጦርነቱ 2 እና 3 ቀን በኋላ እስራኤላውያን ከሞላ ጎደል በሙሉ ነፃነት በኢራን ሰማይ ላይ ይንቀሳቀሳ ነበር። ይህ የኢራንን አየር ክልል ነጻ የማድረግ ስራ በመጀመሪያ በምዕራቡ አቅጣጫ, ከዚያም ቀስ በቀስ ወደ መሃል እየሰፋ ሄደ፡፡ ሰው አል ድሮኖችም ጭምር በነፃነት በኢራን ሰማይ ሲሰሩ አይተናል፡፡ ይህም የሆነ ነገር ልክ እንዳልሆነ ትልቅ ምልክት ነው። ይህ የአየር የበላይነት ጉዳይ የኢራንን የሚሳኤል ሁኔታን መረዳት ያስችላል። ኢራን አሁንም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳኤሎች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ላውንቼር ያላት ሲሆን ጥያቄውም ይህ አይደለም ። ጉዳዩ በጠቅላላ የእስራኤል አየር የበላይነት ባለበት ሁኔታት ከጠላት አፋጣኝ የቅድመ መከላከል ጥቃት ሳይደርስ መጠነ ሰፊ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸም አይችልም። ኢራን ላውንቼሮችን ከምድር ስር ባወጣች ጊዜ እስራኤል በሰማይ በለቀቀቻቸው ድሮኖች ታየና አስቀድማ ታወድማለች። ይህም ኢራን በትንንሽ የመምታት እና ወዲያው መሳሪያ የመደበቅ ስልቶች የሚሳኤል ጥቃቶችን እንድትፈጽም ያስገደዳት ሲሆን ከማዕከላዊ እና ምስራቃዊ የጦር ሰፈሮች የቆዩ የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን በመጠቀም ብቻ ተወስና በከፍተኛ መጠን ምላሽ የመስጠት አቅሟ ቀስ በቀስ ቀንሷል። በነዚህ ሁኔታዎች ጦርነቱን ማስቀጠል አይቻልም, ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ጀምሮ፣ 'አስፈላጊነታቸው አነስተኛ በሆኑ' ኢላማዎች ላይ በየጊዜው አንዳንድ ጥቃቶች ቢደረጉም እውነተኛ የኢራን ራስን የመከላከል አቅም አስቀድሞ ጠፍቷል። በየእለቱ ከ10-20 ሚሳኤሎችን ማስወንጨፍ ለሰፊ ወታደራዊ አላማ መሳሪያ ካልሆነ በስተቀር ከእስራኤል ጥቃት መጠነ ሰፊነት አንጻር ኪሳራ ነው። በወታደራዊ አነጋገር፣ እስራኤል ግልፅ አሸናፊ ነች፣ ይህ ምንም አይነት የሚደበቅ ነገር የለውም። ይሁን እንጂ በፖለቲካው እስራኤል ተሸንፋለች። እስራኤላውያኑ አብዛኛውን ዋና አላማቸውን አላሳኩም። ኢስላማዊው ሪፐብሊክ አሁንም አለ፣ የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር አሁንም አይቆምም የተገደሉ የጦር መሮዎችም ተተክተዋል። በዚህ ጦርነት የእስራኤል ዋና ስኬት የኢራን አየር መከላከያ ጣቢያዎችን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እና በዚህም ምክንያት ከኢራን መጠነ ሰፊ የሚሳኤል ተኩስ እንዳይደስባት ማድረጓ ነው። ይህም ኢራንን አጣብቂኝ ውሠጥ አስገብቷታል ምክንያቱም ከአሁን በኋላ ጦርነቱ እየተባባሰ በሚሄደው ልክ መቋቋም አትችልም፡፡ በቀጣይ ችግሩ እስራኤል ይህንን የተኩስ አቁም እራሷን እንደገና ለማስታጠቅ ትጠቀመዋለች። ለሌላ ጦርነት፣ ለበለጠ ጥቃት ትዘጋጃለች፣ ቀስ በቀስ በመጀመሪያ ሞክራው ዯልተሳካላትን ለማሳካት በኢራን ውስጥ የስርዓት ለውጥ ለማምጣት ትመለሳለች። በተጨማሪም 'የሊባኖስን ሞዴል' በኢራን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ትሞክራለች በተኩስ አቁም ወቅት ኢራን ውስጥ ኢላማዎችን በትንሽ ምላሽ ወይም ያለምንም ምላሽ እንደፈለገች ለመምታት መመለሷ አይቀርም። ኢራን ይህን ጉዳይ እንዴት ትቆጣጠረዋለች? ኢራንም አቅሟን እንደገና መገንባት አለባት። አሁንም፣ ሚሳኤሎች እና ላውንቼሮች ጉዳይ አይደሉም። ኢራን በምዕራቡ የሚገኙትን የሚሳኤል ማዕከላት የፈራረሱትን የዋሻ መግቢያዎችን ትጠግናለች፣ ከተብሪዝ በስተቀር ሁሉም የሚሳኤል ቤዞች እንደገና ስራ ይጀምራሉ። ከዚያስ ምን? የአየር መከላከያ ስርኣቱ ወድሟል፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታ ወዲያውኑ እራሱን ይደግማል፡፡ ኢራን ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት የአንድ ወገን እንዳይሆን፣ አቅሟን መልሳ ለመገንባት እና የራሷን ህልውና የሚያረጋግጥ እንዲሁም ማንኛውንም አዲስ የእስራኤል ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል መፍትሄ ለማግኘት የሚያስችል መንገድ መፈለግ አለባት። ይህን ማድረግ የሚቻልበት ብቸኛው መንገድ ኑክሌር ቦምብ ለመታጠቅ መጣደፍ ነው, ምንም የሚጨመር ምንም የሚቀነስ ነገር የለውም፡፡ @Alif_Online_Official

  • ✍️ Daily Updates, detailed analysis and informed openions focusing on Ethiopia, Middle East and beyond✈️🌍 Telegram @Alif_Online_Official

  • 25 мая 2025 г.5173из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇪🇹⚡ ኢትዮጵያ ውስጥ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር እና ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ አስታውቀዋል። @Alif_Online_Official

  • 13 апр. 2025 г.707из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇪🇹⚡ ከሳምንታት በፊት አንድ ቆሻሻ ግለሰብ እጅግ የከበረ ውድ ሰብዕናን ከዚያም በዓለማቱ ጌታ ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት ያለውን ብቸኛ ኃይማኖት ሰደበ በመንግሥት እዝነት ተጠያቂ ሳይሆን ቀረ። ለዓመታት በሺዎች የሚቆጠር ሄክታር የያዙ አብያተ ክርስቲያናት እና በየመቶ ሜትሩ አግልግሎት የሚሰጡ ቸርቾች ባሉበት ወረዳ አንድ መስጂድ ሲገኝ ህገወጥ ተብሎ ሲፈርስ መንግስትም ሙስሊሙን ሳይፈራ ሙስሊሙም በዕለቱ እንኳን ሳይቆጨው ቀረ። የሙስሊሙ መብት መከበር አለበት የሚለው ትግል ልክ ኢህአዴግን ለመጣል ሲደረግ ከነበረው ትግል ጋር እኩል የመጨረሻ ዓላማው የመንግሥት ለውጥ ማምጣት በሚመስል መልኩ በመንግሥት ለውጥ ተቋጨ። ህልውናህ እውቅና እንዲያገኝ ከምታደርገው ትግል በላይ ህልውናህ ከተከበረልህ በኋላ መሰረታዊ ጥያቄዎችህ መልስ እንዲያገኙ የመጠየቅ ጊዜህ ረዥም እና የማያልቅ መሆን አለበት ምክንያቱም የኢትዮጵያ ትልቁ አካል ሙስሊም መሆኑ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ያንን ክብርህን ተጠቅመህ በዘመናት ያጣሃውን ለማግኘት ተቋማቶችህን መሬት እንዲረግጡ ለማድረግ የበለጠ መታገል እንጂ የመንግስትን ችሮታ ጠባቂ መሆን አያዋጣም። ህዝበ ሙስሊሙን የሚመራው አካል በሚመራው ህዝብ ላይ የደረሰውን በደል በደንብ አጉልቶ አሳይቶ መልስ ከመሻት ይልቅ በዳዩንም ተበዳዩንም ተው ብሎ ወደቤት ከገባ ለሚመራው ህዝብ ሳይሆን ውግንናው ፖለቲካዊ ሆኗል ማለት ነው። አሁንም ቢሆን የገንዘብ እጥረት ሲገጥም ለህዝቡ በግልጽ በማሳወቅ የፋይናንስ አቅሙን ማሳደግ, በደሎች ሲኖሩ በመንግሥት እና ህዝብ መካከል አስታራቂ ለመሆን ከመጋጋጥ ይልቅ ከወከለው ህዝብ ጎን ሆኖ መንግሥትን መጠየቅ ከዚያም የህዝብ ድጋፍ እንዳለው ለመንግሥት ግልፅ በማድረግ መንግሥትን ቻሌንጅ ማድረግ የመጅሊስ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል። ይሄንን እያደረግን ነውኮ የሚሉ ከሆነ ሁለት ነገር መረዳት እንችላለን አንድም የሚያደርጉት ጥረት በቂ አይደለም ኃላፊነታቸውን መልቀቅ አለባቸው ወይም ደግሞ ጥረታቸው ያልተሳካበትን ምክንያት ለህዝብ አሳውቀው የሚፈልጉትን ድጋፍ መጠየቅ አለባቸው። @Alif_Online_Official

  • የሰው ልጅ ረሺ ነውና እኛም ሙሀመድ ሰኢድን ነበር ብለን መርሳታችን አይቀርም :: አራት ልጆቹ ግን የማይረሱት ሁኖ ያጎድላቸዋል:: አሁን ያለንበት ሀዘን ስሜት ሳይተንፍስ ማንንም ሳንጠብቅ አሻራችንን አሁን እናሳርፍ የአካውንት ስም:- ነጃት አብዱልመናም ጡሃ (ሚስቱ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000458278297 ሼር ፖስት በማድረግ በዋትስአፕም በቴሌግራም ግሩፕም ለሰዎች በመላክም በዚህ ኸይራ ስራ አሻራችንን እናሳርፍ

  • видео или голосовое, без подписи

  • ይህን ህፃን ያያችሁ ወይም ስለሱ የሰማችሁ ካላችሁ ተባበሩን ያጀመአ ከመግሪብ ሰላት በፊት በፊት ከ ከታ አካባቢ ጠፍቶብናል ወላጆች ተጨንቀዋል የበኩላችሁን ሼር በማድረግና በመፈለግ ተባበሩን ስሙ ማሂር ይባላል 0920208015 የአባቱ ሰልክ ነው በዚህ አሳውቁን 🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽

  • видео или голосовое, без подписи

  • 28 февр. 2025 г.458из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇸🇦🌙 የረመዳን ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ 1446-ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል። @Alif_Online_Official

  • አልሐምዱ ሊላህ! ሸዕባን አጠናቀናል። ቅዳሜ ረመዷን 1 ነው። ምሽቱን ተራዊሕ እንጀምራለን።

  • 6 февр. 2025 г.67721из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇵🇸⚡🇮🇱 እስራኤል በጋዛው ጦርነት 20 ሺህ በላይ ወታደሮቿን አጥታለች! ባሳለፍነው እሁድ በመከላከያ ሚኒስቴር የሥራ ፕሮግራሞች ኮንፈረንስ ላይ በእስራኤል አዲስ የተሾመው የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር ንግግር ሲያደርግ በጋዛ የተገደሉት እና የቆሰሉት የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር ሰራዊቱ በይፋ ከዘገበው እጅግ የላቀ መሆኑን አምኗል። ኦክቶበር 7 ቀን 2023 ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የእስራኤል ጦር 844 ወታደሮች እንደተገደሉ እና 5,696 አካል ጉዳተኞች ሆነዋል ሲል ጦሩ ይፋ ያደረገ ቢሆንም አዲሱ ተሿሚ ግን ቢያንስ 5,942 የተመዘገቡ "በጦርነቱ ልጃቸው የሞተባቸው ቤተሰቦች" እንዳሉ ተናግሯል—የጦሩ አዛዥ "bereaved families" የሚለውን ቃል የተጠቀመ ሲሆን ይህ ቃል የሞቱ ወታደሮች ቤተሰቦችን ለመግለጽ ብቻ የሚያገለግል ነው። በተጨማሪም ከ15,000 በላይ ወታደሮች የአካልና ስነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ማገገሚያ ሥርዓቱ ውስጥ መግባታቸውን መግለፁን ተከትሎ እስራኤል በወታደራዊ ጉዳቷ ላይ ሆን ብላ ከእውነታው ሪፖርት እያደረገች ነው የሚለውን ጥርጣሬ አጠናክሮታል። እንዲህ ያሉ አለመግባባቶች ሲጋለጡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ሃሬትዝ በታህሳስ 2023 እንደዘገበው የእስራኤል ጦር በጥቅምት እና ታህሣሥ መካከል 1,593 ወታደሮች ተጎድተዋል ሲል፣ የሆስፒታል መረጃዎች እንደሚያሳዩት ትክክለኛው ቁጥሩ 10,548 ወታደሮች እንደተጎዱ ነበር። ጋዜጣው በ 2024 በየወሩ ወደ 1,000 የሚጠጉ ወታደሮች እየተጎዱ ወደ ማገገሚያ ማዕከላት እየገቡ መሆናቸውን ገልጿል። እነዚህ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ እስራኤል በጦርነቱ ቢያንስ 5,942 ወታደሮቿን ማጣቷ እና 15,000 ወታደሮቿ አካል ጉዳተኛ መሆናቸው እውነት መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። @Alif_Online_Official

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 5 февр. 2025 г.3982из Alif_Online_Official

    ♻️🔻🇸🇦🇵🇸🇺🇲🇮🇱⚡ አሜሪካ እና እስራኤል ለፍልጤማዊያኑ ሉዓላዊት ሀገር እውቅና ሳይሰጡ ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አትጀምርም፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ሳዑዲ አረቢያ የሉዓላዊ ሀገረ ፍልስጤም ምስረታ ላይ ያላትን የማይናወጥ እና ለድርድር የማይቅርብ አቋሟን ዳግም ታረጋግጣለች፣ ይህ አቋም በፅናት የሚቀጥል እና ለፖለቲካዊ ድርድር የማይቀርብ መሆኑን አጽንኦት እንሰጣለን" ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዳሩን ባወጣው መግለጫ ሳዑዲ ለፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገርነት መከበር የገባችው ቁርጠኝነት ስር የሰደደ እና የማይናወጥ ነው ሲል በድጋሚ አሳስቧል። "ይህ ጽኑ አቋም በሀገሪቱ የሹራ ካውንስል መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በልዑል አልጋ ወራሽ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሀመድ ቢን ሰልማን በግልፅ የተረጋገጠ የሳዑዲ አቋም ነው" ልዑሉ በንግግራቸው ሳዑዲ አረቢያ ምስራቅ እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ ያደረገች ነጻ ሀገረ ፍልስጤም እስካልተመሰረተች ድረስ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደማይኖር በግልፅ ተናግረዋል" ይላል መግለጫው፡፡ በተጨማሪም ሳዑዲ አረቢያ የእስራኤልን የሰፈራ ማስፋፋት፣ የመሬት ወረራ እና ፍልስጤማውያንን ከትውልድ አገራቸው በግዳጅ ለማፈናቀል የሚደረጉ ሙከራዎችን ጨምሮ የፍልስጤማዊያንን መብቶች የሚጎዳ ማንኛውንም ድርጊት በጽኑ አትቀበልም ያለው መስሪያ ቤቱ ሳዑዲ አቋሟ ለድርድርም ሆነ ለፖለቲካዊ አጀንዳ የሚቀርብ እንዳልሆነ በድጋሚ አረጋግጧል። የፍልስጤም ህዝብ በፍትሃዊ መንገድ ምላሽ ሳያገኝ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም በቀጠናው ሊመጣ እንደማይችል ሳውዲ አረቢያ ለቀደሙትም ሆነ አሁን ላለው የአሜሪካ አስተዳደር ግልፅ አድርጋለች ሲል መግለጫው ተጠናቋል። @Alif_Online_Official

Alif Geopolitics — tgindex