Bisratfm101.1
СтатистикаBisrat FM 101.1 is a radio station established by Oyaya Multimedia. Journalist Messele Mengistu, is the owner of Oyaya Multimedia and who remained in the hearts of the Ethiopian radio listeners for the past 10 years, has just realized his long time dream
- Последний пост
- 13:18
- Последнее чтение
- 13:53
- Постов за неделю
- 139
- Всего постов
- 3 937
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 406
- 1/48двое суток
- 465
- 1/72трое суток
- 501
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ነሐሴ 11፤2018 - በጋምቤላ ክልል የተሰበሰበው የደም መጠን 22 በመቶ ብቻ ነው፡፡ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በጋምቤላ ክልል የተሰበሰበው የደም መጠን 22 በመቶ ብቻ መሆኑን ይህም ዝቅተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ገልጿል። የህክምና ተቋማት ቁጥር በመበራከቱና የጤና አገልግሎት ተደራሽነትም በመስፋፋቱ የደም ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ባንኩ አስታውቋል። የኢትዮጵያ የደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ገብረአብ ፍስሃ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በበጀት አመቱ እንደሀገር የተለያየ መጠን ያለው ደም ተሰብስቧል።በዚህም መሰረት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 57 በመቶ፣ በትግራይ ክልል 61 በመቶ እንዲሁም በደቡብ ክልል 63 በመቶ የሚሆን ደም መሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት። አቶ ገብረአብ አያይዘውም በጋምቤላ ክልል 22 በመቶ የሚሆን ደም ብቻ መሰብሰቡን ገልጸዋል። ይህም በክልሉ ያለው የደም ልገሳ አፈፃፀም ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል። በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 550 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር። ከዚህም ውስጥ 476 ሺህ 367 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል።በዚህም የእቅዱን 87.5 በመቶ አፈፃፀምን ማሳካት የተቻለ ሲሆን 12.5 በመቶ የሚሆነው ቀሪው ዕቅድ ሳይሳካ ቀርቷል።ይህ አፈፃፀም አንዳንድ መሻሻሎች መኖራቸውን የሚያሳይ ቢሆንም ከሕክምና ተቋማት የደም ፍላጎት አንፃር በታቀደው ልክ ውጤት ማስመዝገብ እንዳልተቻለ ባንኩ ጨምሮ ገልጿል። በመሆኑም የደም አቅርቦትን ለማሳደግ ተጨማሪ የልገሳ ሥራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። በሳምራዊት ስዩም #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - ሰርጂዮ ቡስኬት ወደ ባርሴሎና መመለሱ ተሰማ! የቀድሞ የባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተጨዋች የነበረው ሰርጂዮ ቡስኬት ወደ ቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና በአዲስ ሃላፊነት ተመልሷል። ተጨዋቹ የመጨረሻ የእግርኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ክለብ ኢንተርሚያሚ ማጠናቀቁ ይታወሳል። አሁን ላይ ሰርጂዮ ቡስኬት የባርሴሎና ቢ ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ በሃላፊነት መሾሙ ተነገሯል። በቀጣይ ሰርጂዮ ቡስኬት ዋና ቡድን ማሰልጠን የሚያስቸለውን ላይሰንስ(ፍቃድ) እንደሚያገኝ ይጠበቃል። ✍️በአህመዲን ከማል #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - ጁቬንቱስ ቪካሪዮን ለማስፈረም ተስማማ! የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ የቶተንሀሙን ግብ ጠባቂ ቪካሪዮ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል።ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂውን የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል እንደሚያስፈርሙት ተገልጿል። የጣሊያኑ ክለብ የአስቶን ቪላውን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን ለማስፈረም ተቃርበው የነበረ ቢሆንም ዝውውሩ ተቋርጧል። አስቶን ቪላ የማርቲኔዝ ዝውውር ቢቋረጥም ጃፓናዊውን ግብ ጠባቂ ዚዮን ሱዙኪ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሱ ተሰምቷል። አስቶን ቪላ ለግብ ጠባቂው 35 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሂሳብ ለማስፈረም ከፓርማ ጋር ተስማምቷል። ቪጋሪዮ በቀጣይ ቀናት ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ✍️በአህመዲን ከማል #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - ብራይተን ለካርሎስ ባሌባ ዝውውር ሒሳብ ይፋ አደረገ! የብራይተን እግርኳስ ክለብ ለካርሎስ ባሌባ ዝውውር በሩን ክፍት እንዳደረገ ተገልጿል። ካሜሮናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ላለፉት ዓመታት በማንችስተር ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለግ እንደነበር ይታወሳል። ብራይተንም ለካርሎስ ባሌባ ዝውውር 100 ሚሊዮን ፓውንድ መጠየቁ አይዘነጋም። አሁን ላይ በወጣው መረጃ ብራይተን በተጨዋቹ ዝውውር ጉዳይ በሩን ክፍት ያደረገ ሲሆን ከ60እስከ 65 ሚሊዮን ፓውንድ የሚቀርብለት ከሆነ ተጨዋቹን የመሸጥ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል። ኒውካስትል ዩናይትድ ሌላኛው የተጨዋቹ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ማለቱ ሲነገር ምን ያህል ገንዘብ እንዳቀረበ በይፋ የተገለፀ ነገር የለም። ✍️በአህመዲን ከማል #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - የምትፈልገውን ወንድ ተዋናይ ለመሳም ስትል ፊልም ፕርዲዩስ ያደረገችው ቻይናዊት መነጋገሪያ ሆናለች፡፡ ስሟ ያልተጠቀሰው ቻይናዊት የድራማውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን ተስማምታ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጧ ተሰምቷል፡ አንደኛው የዋናዋን የሴት ተዋናይ ሚና እሷ ራሷ እንድትጫወት ነበር፤ ሁለተኛው ደግሞ በስክሪፕቱ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የእሷ እንዲሆን ነበር። በዚህ የተነሳ የ23 ዓመቱ ቻይናዊ ተዋናይ ዞንግ ዩፌይ የድራማውን ዋና የወንድ ሚና እንዲጫወት ተመረጠ። ወጣቱ ተዋናይ ከዚህ በፊት በአጭር ድራማዎች ላይ ጥቂት የድጋፍ ሚናዎችን ብቻ በመጫወቱ ይህንን ፕሮጀክት እንደ ትልቅ የስራ እድል ተመልክቶት ነበር። ይሁን እንጂ ቀረጻው ከጀመረ በኋላ ያላሰበው ነገር ገጥሞታል፡፡ ዞንግ እንደተናገረው፣ በመጀመሪያው የፍቅር ትዕይንት ላይ ሴቷ ተዋናይ ከእሱ ፈቃድ ውጭ በጣም ቅርብ በሆነ መልኩ ትስመዋለች። እሱ ለመራቅ ሲሞክርም ጭንቅላቱን በእጇ ይዛ እንዳይርቅ በማድረግ እንደሳመችው ነው የ23 አመቱ ወጣት ተዋናይ የተናገረው ፡፡ ፅሁፋ ከ60 በላይ የመሳም ትዕይንቶችን እንደያዘ ተገልጿል። የቀረጻ ቡድኑ ይህ ቁጥር ከመጠን በላይ መሆኑን፣ የታሪኩን ፍሰት ሊያበላሽ እና ተመልካቾችም ከታሪኩ እንዲርቁ ሊያደርግ እንደሚችል ለሴትየዋ ቢያስረዱም ምክራቸው አልተሰማም። እሷም ከቡድኑ የቀረበላትን ምክር በመቃወም ብዙ አጭር ድራማዎችን እንዳየች እና የምታውቀውን እንደምታውቅ መናገሯ ተዘግቧል። እዚህ ላይ የታሪኩ አስቂኝ ክፍል ቢኖርም፣ የተዋናዩ ቅሬታ ግን ከቀልድ በላይ የሆነ ጉዳይን አንስቷል። ወጣቱ ተዋናይ ይህ ድራማ የስራ እድሉን እንዳያሳጣው በመፍራት በወቅቱ ተቃውሞ ለማሰማት እንደተቸገረ ተናግሯል። በቀረጻ ስብስቡ ላይ ያሉ ሰዎችም እየተመለከቱ ዝም ማለታቸው ሁኔታውን ይበልጥ እንዳከበደው ገልጿል። ችግሩ ግን በቀረጻ ስብስቡ ላይ ብቻ አልቆመም። ፊልሙ ተጠናቆ ወደ ኤዲቲንግ ከገባ በኋላ፣ ሊሰራጭበት የነበረው የድራማ መድረክ ጥቂት ክፍሎችን ከመረመረ በኋላ ስራውን አልቀበልም ማለቱ ተገልጿል። ምክንያቱም የፍቅርና የመሳም ትዕይንቶቹ ከመጠን በላይ ግልጽ እና ብዙ በመሆናቸው የስርጭት ደንቦችን ሊጥሱ ይችላሉ ተብሎ ነው። ታሪኩ በቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ ብዙዎች ትዕይንቶቹን ተመልክተው ሲቀልዱ ሌሎች ግን ከዚህ የበለጠ ከባድ ጉዳይ እንዳለ ተናግረዋል። በተለይም በፊልምና በቴሌቪዥን ስራ ውስጥ ዝና ወይም ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የሌሎችን የስራ መብትና የግል ድንበር እንዳይጥሱ ስለሚያስፈልገው ጥንቃቄ ክርክር ተነሳ። በመጨረሻ ይህ የ50 ክፍል ድራማ የተፈለገውን የፍቅር ታሪክ ለተመልካች ማድረስ ባይችልም፣ ከ60 በላይ የመሳም ትዕይንቶች፣ የባለሀብቷ የበላይነት እና የወጣቱ ተዋናይ ቅሬታ ግን ለድራማው ከተጠበቀው በላይ ትልቅ ዝና ሰጥተውታል። በቤዛዊት አራጌ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ነሐሴ 11፤2018 - አገልግሎቱ በ769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው ለሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዌ ጉዲና ወረዳ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን አስመርቋል። ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት በቶርበን፣ ባቴ፣ ሐሎ ጎባ እና ሐሮ ኦባ ቀበሌዎች ሲሆን፣ በአጠቃላይ 769 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ናቸው፡፡ አራቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በድምሩ 900 ኪሎ ዋት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላቸው፡፡ በፕሮጀክቱ 7.74 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 30.29 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 10 የዲስትሪቡዩሽን ትራንስፎርመሮች ተተክለው ሥራ ጀምረዋል። ማህበራዊ ተቋማትን ጨምሮ ከ5 ሺህ 276 በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶቹ፤ በአሁኑ ወቅት በአራቱም ቀበሌዎች ከ844 በላይ አባወራዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን እየተገነቡ ከሚገኙ 8 የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ውስጥ 6ቱ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ ከዋናው የኃይል ቋት ርቀው ለሚገኙ የገጠር ማህበረሰቦች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ከማስፋፋት ባለፈ፣ በገጠር አካባቢዎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማጠናከር የሚያግዙ ናቸው። የፕሮጀክቶቹ ግንባታ የተከናወነውም ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክና ብርሃን ተደራሽነት (ADELE) ፕሮግራም አካል ነው። #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - በደቡብ ክልል የረጅም ጊዜ የወሊድ መከላከያን መጠቀም የቻሉት 36 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ብቻ ናቸው በክልሉ በተጠናቀቀዉ የ2018 በጀት ዓመት የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚነትን 50 በመቶ ለማድረስ ሲሰራ እንደነበር ተገልጿል ። በበጀት ዓመቱ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ማግኘት ከሚገባቸው ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ሴቶች መካከል የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የቻሉት 36 በመቶ የሚሆኑት ብቻ መሆናቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የቤተሰብ ዕቅድ ፣የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የጤና ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብረሀም ወንድሙ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል ። ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4 በመቶ መሻሻል የታየበት ቢሆንም በበጀት ዓመቱ ለማድረስ ከታቀደዉ 50 በመቶ አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ አፈፃፀም መሆኑ ተጠቁሟል ። የ አሌ ፣የኮሬ ፣የኮንሶ ፣የጋርዱላ ፣የአሪ እና የቡርጂ ዞኖች ዝቅተኛ አፈጻጻም ካስመዘገቡት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።ቢሮዉ ጥራት ያለው የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የምክክር አገልግሎትን ማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎችን ከመስራት ባሻገር ፕሮግራም ተኮር ድጋፋዊ ክትትልን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል። በተጨማሪም የግብአት ስርጭትና ሪፖርት ክትትልን ጨምሮ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል ። በመባ ወርቅነህ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - ✍የአርሰናሉ አምበል ኦዴጋርድ ያለንበትን ደረጃ አሳይተናል ሲል ከጨዋታዉ በኋላ ተናገረ። በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ አርሰናል 3ለ0 ካሸነፈ በኋላ የጨዋታዉ ኮከብ ሆኖ የተመረጠዉ ኦዴጋርድ ዓመቱን በድል መጀመር ፈልገን ነበር የቡድናችን አዳዲስ ፈራሚዎች ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገዋል ጉማሬሽ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ልዩ ነው ዞሊስም ምርጥ ነበር ያለ ሲሆን “ከድሉም በተጨማሪ ምርጥ ጨዋታ አድርገናል በዚሁ አቋም መቀጠል አለብን “ ፕሪሚየር ሊጉን በድጋሜ ማሸነፍ እንፈልጋለን በማለት " ኦዴጋርድ ሀሳቡን ሰቷል። ✍በተፈራ ታመነ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
без подписи
ነሐሴ 11፤2018 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን! በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ጀምሮ በ1960ዎቹ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ ሆኖም ብዙ ርቀት ሳይጓዞ በወሊድ ጊዜ ሴቶች ላይ ችግር ያመጣል በሚል ምክንያት እንደተቋረጠ ይነገራል። ከሦስት አስርት ዓመታት በሗላ በ1990ዎቹ የሴቶች እግር ኳስ እንቅስቃሴ ዳግም የተጀመረ ሲሆን በ1992 ዓ/ም የውድድር ቅርፅ ይዞ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጨዋታዎች መጀመራቸውን መረጃዎች ያሣያሉ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የእግር ኳስ ቡድኖች የተቋቋሙ ሲሆን ውጤታማ ከሆኑና አሁንም በስኬታማ ጎዳና ላይ እየተጓዙ ከሚገኙት መካከል ቀዳሚው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግርኳስ ቡድን ነው። በኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማው እና ገናናው የሆነው ይህ ቡድን በይፋ የተመሰረተው ነሐሴ 24 ቀን 2003 ዓ/ም ነው። ክለቡ ከሀገር ውስጥ ውድድሮች አልፎ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) የክለቦች ውድድር ዋንጫ በማምጣት ደማቅ ታሪክ የሰራ ብቸኛው ክለብ ነው። በሀገር ውስጥ ውድድሮች ዘጠኝ ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በማንሳት የሚስተካከለው ቡድን የሌለ ሲሆን ለተከታታይ 6ጊዜ ሊጉን በማሸነፍ ሌላ ደማቅ አዲስ ታሪክም ሰርቷል። በሴቶች እግር ኳስ ወደ 30 ዓመት የሚጠጋ የአሰልጣኝነት ልምድ ባለው ብርሀኑ ግዛው የሚመራው ይህ ቡድን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ 60 ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ የክብረወሰን ባለቤት ሲሆን ይህም የቡድኑንን ጥንካሬና የአይበግሬነት መንፈስ በጉልህ የሚያሳይ የጠንካራ ስራ ውጤት ነው። በተደጋጋሚ ጊዜ ኢትዮጵያን በመወከል በሴካፋ የሴቶች ውድድር የሚሳተፈው ቡድኑ ኢትዮጵያ በአስተናገደችው 2024ቱ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ(የሴካፋ)ዞን ውድድር ሻምፒዮን መሆን በሴቶች የአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏል። ከዚህ ሁሉ የቡድኑ ጠንካሬና ስኬት ጀርባ ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ምልክት የሆነው አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በ2004ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በኢትዮጵያ መደረግ ሲጀመር ከተሳፉ አምስት ክለቦች አንዱ ነበር። ቡደኑ ስኬታማ የሆነባቸው ውድድሮች:- -የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ(ሴካፍ)የክለቦች ውድድር 1ጊዜ ሻምፒዮን እና የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሲሆን በተጨማሪም የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ነው። -የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን 9ጊዜ -የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ 1 ጊዜ -የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ 2 ጊዜ -የሰሜን ማዕከላዊ ዞን ዋንጫ 3 ጊዜ -የአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ዋንጫ 1 ጌዜ በአጠቃላይ 17ዋንጫዎችን በማንሳት በሀገራችን የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ስመ ገናና መሆን ችሏል። የቡድኑ ስኬት በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም በርካታ ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድን በማስመረጥ አቻ አይገኝለትም ከተጨዋቾች ባሻገር አሠልጣኝ ብርሀኑ ግዛው እና ሌሎች የአሰልጣኝ ቡድን አባላትንም አሰመርጧል። የዚህ ውጤታማ ቡድን ተጫዋቾችና አሰልጣኞች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን(ሉሲዎችን) ለሴቶች አፍሪካ ዋንጫ በማሳልፍ ዘመን አይሽሬ ደማቅ ታሪክን ሰርተዋል። የቡድኑ ተጫዋቾች ከሀገር አልፈው ፕሮፌሽናል እንዲሆኑ በር የከፈተ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 7 የቡድኑ ተጫዋቾች የነበሩ በውጭ ሀገራት እየተጫወቱ ይገኛሉ። በየዓመቱ ከውጤት በተጨማሪ ለሀገራችን እግር ኳስ እድገት የራሱን አሻራ እያኖረ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ የሴቶች ቡድኖች ታሪክ ከ17 እና ከ20ዓመት በታች ቡድኖችን በማቋቋም ብቸኛ ባለ ታሪክ መሆን ችሏል ይህ የቡድኑ ወሳኝ እርምጃ ለሌሎች ቡድኖች ማስተማሪያ እና ተተኪዎችን ለማፍራት ትልቅ ተስፋ ያለው ተግባር ነው። ቡድኖቹ በተቋቋሙበት የመጀመሪያ ዓመት ከ20ዓመት በታች ቡድን አንድ ግብ ጠባቂ ማሳደግ የቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ 6ተጫዋቾች የሙከራ ዕድል ተሰጥቷቸው ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ በመሥራት ላይ ይገኛሉ ። እነዚህ የተቋቋሙት ታዳጊ ቡድኖች የዋናውን ቡድን የአሸናፊነት መንፈስ በመላበስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት ውድድር ከ17ዓመት በታች ቡድኑ የአዲስ አበባ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል። ሲሆን ኮከብ ተጫዋች ፣ግብ አግቢ ፣ግብ ጠባቂ እና አሠልጣኝ በማስመረጥ ውድድሩን አጠናቋል። ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ ደግሞ በአዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ውድድር 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ኮከብ ግብ አግቢ አስመርጧል። ይህ በሀገራችን የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ እጅግ ውጤታማ የሆነው ቡድን ለሀገራችን ኢኮኖሚ ትልቅ ድርሻ ባለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቋም የሚመራ ሲሆን ድርጅቱ ለሀገራችን የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ እየሠራ ያለው ተግባር በእጅጉ የሚያስመሰግን ሲሆን ከወንዶች ተጫዋቾች እኩል ለሴቶች ተጫዋቾች ደሞዝ የሚከፍል ትልቅ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋቾች እንደተቋማቸው በማህበራዊ ተሳትፏቸው እጅግ የሚወደዱና የሚመሰገኑ ሲሆኑ ለውድድር በሚጓዙባቸው ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ይታወቃሉ። ለተቸገሩ ግለሰቦችና ተቋማት በተለያዩ ጊዜያትድጋፍ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በቅርቡ በሩዋንዳ ኪጋሊ በሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የክለቦች ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፍ ሲሆን ለዚህም ይረዳው ዘንድ ካለፈው ሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በአዳማ ከተማ ዝግጁትን በማድረግ ላይ ይገኛል። ውድድር ከነሐሴ 15 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 01/2018 እንደሚካሄድ ይታወቃል። ፍራኦል ረቡማ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - 🇵🇹🗣️ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፦ ነሐሴ 11፤2018 - “ይህ ምናልባት በእግር ኳስ የምጫወትበት የመጨረሻው ዓመት ሊሆን ይችላል፣ እናም አስደናቂ የሆነ ታሪክ ትቼ መሄድ እፈልጋለሁ።” “የወደፊት ሕይወቴን በሙሉ አቅዳለሁ። ራሴን የማዝናናባቸውና በስረኣ የምጠመድባቸው ብዙ ነገሮች አሉኝ፤ አንዱን ብቻ መጥቀስ እንኳን ከባድ ነው።” “ምክንያቱም እግር ኳስን ስትተው ትልቅ ክፍተት ሊፈጠር ስለሚችል፣ ያንን ጊዜ በአንድ ነገር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ነገሮች መሙላት አለብህ።” “የበለጠ መዝናናት፣ ብዙ መጓዝ፣ ፓዴል መመልከትና መጫወት—በጣም የምወደው ነው—እንዲሁም በደከምኩበአት 25 ዓመታት ያገኘሁትን ሁሉ በመደሰት መኖር። ምክንያቱም ከሁሉም በላይ ይህ 25 ዓመት ብዙ መስዋዕትነትን የጠየቀ ጉዞ ስለነበር።” ፍራኦል ረቡማ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - ✍ባርሴሎና ስፔናዊዉን አማካኝ ሮድሪን ለማስፈረም ተስማማ። የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሮድሪን ለማስፈረም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ታዉቋል። ብሉግራናዎቹ ለተጫዋቹ ዝዉዉር 76.5 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ገንዘብ እንደሚከፍሉ ሲገለፅ ማንችስተር ሲቲ 60 ሚልዮን ዩሮውን በቀጥታ ሲቀበል11ሚልዮን ዩሮ ወደፊት የሚከፈል ክፍያ መሆኑ ተነግሯል። ሮድሪም በባርሴሎና ቤት የአራት አመት ኮንትራት እንደሚፈራረም ይጠበቃል። ✍በተፈራ ታመነ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - የካሜሮን ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የ 2026 ሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር አሸናፊ ሆነ። ካሜሮን ከማላዊ ጋር ያደረገችውን የፍፃሜ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች። ከዚህ በፊት በሶስት የፍፃሜ ጨዋታ የተሸነፈችው ካሜሮን በመጨረሻው የአፍሪካ ዋንጫውን በታሪክ ለመጀመሪያው ጊዜ አሳክታለች። ካሜሮን ከዚህ በፊት 2004 ፣ 2014 እና 2016 የፍፃሜ ጨዋታዋን በናይጄሪያ ተሸንፋ እንደነበር አይዘነጋም። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በታሪክ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ያደረገ ሲሆን በካሜሮን በሰፊት የውጤት ልዩነት ተሸንፏል። ✍️በአህመዲን ከማል #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 11፤2018 - ውድ የ-#መሴ_ሪዞርት አድማጮች አዲሱን የ facebook ገጻችን like, share እና Comment በማድረግ ሃሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። የመወያያ ነጥቦች፦ ከማን ጋር መዝናናት ይወዳሉ?? ለብቻዎስ የመዝናናት ልምድ አለዎት? እውነት ጥቁር ድመት የመጥፎ እድል ምልክት ነው ብለው ያምናሉ? ዛሬ የጥቁር ድመቶች ቀን ተከብሮ ይውላል፡፡ መሬት ሲከዳ የሚያቅፉ እጆች ከምን ያስጥሉ ይሆን? በመላው #ዓለም በዩቲዩብ ገፃችን ይጠብቁን። 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Bisrat_Fm_101.1 #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Messe_resort #መሴ_ሪዞርት የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm TikTok: https://www.tiktok.com/@bisrat.fm
ነሐሴ 10፤2018 - 🇳🇬✨ቪክቶር ኦሲሜን አርሰናልን ለመቀላቀል በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል! ናይጄሪያዊው ኮከብ ቪክቶር ኦሲሜን በዚህ ክረምት ከጋላታሳራይ ወደ አርሰናል ለመዘዋወር ፍላጎት እንዳለው ተዘግቧል። አርሰናልም ለተጫዋቹ ዝውውር ሊከፈል የሚችለውን ክፍያ እና የዝውውሩን ሁኔታዎች እያጣራ መሆኑ ተገልጿል። አርሰናል አሁን ዝውውሩን በንቃት እያሰላሰለ ሲሆን፣ ኦሲሜንም ለሰሜን ለንደኑ ክለብ ፊርማውን ለማኖር ቋምጧል። የዝውውሩ ዋጋ ደግሞ በ60 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ሊሆን ይችላል ተብሎ ቢገመትም፣ የቅርብ ዘገባዎች ጋላታሳራይን ለማሳመን አርሰናል ከ£60 ሚሊዮን በላይ ማቅረብ ሊኖርበት እንደሚችል ይጠቁማሉ። ✍️ በአቤኔዘር አዳነ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101
ነሐሴ 10፤2018 - 🇦🇷📞ሚኬል አርቴታ ጁሊያን አልቫሬዝን ለማሳመን እንደገና ደውለዋል! (ESPN) እንዳስነበበው አርሰናል የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ ጁሊያን አልቫሬዝን በዚህ ክረምት ለማስፈረም ያለውን ጥረት እያጠናከረ መሆኑ ተዘግቧል። ከዚህ በፊትም አርሰናል አልቫሬዝን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ይታወቃል። በተለይም የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ከጁሊያን አልቫሬዝ ጋር እንደገና በስልክ ተነጋግረዋል። የአርቴታ ዋና ዓላማም አርጀንቲናዊውን አጥቂ የአርሰናልን ፕሮጀክት እንዲቀላቀል ማሳመን ነው። ነገር ግን አልቫሬዝ ለአርቴታ የሰጠው መልስ ለአርሰናል ተስፋ ሰጪ አይደለም። አጥቂው ከሌሎች አማራጮች ሁሉ በላይ ባርሴሎናን መቀላቀል እንደሚፈልግ እንደገና አረጋግጧል። በቅርብ ጊዜ የተዘገቡ ዘገባዎችም አልቫሬዝ ከአርሰናል እና ባርሴሎና ጋር በተያያዘ የባርሴሎናን አማራጭ እንደሚመርጥ ጠቁመዋል። ስለዚህ አርሰናል አልቫሬዝን ለማስፈረም በግል ደረጃ ጥረቱን ቢቀጥልም፣ የተጫዋቹ የመጀመሪያ ምርጫ ባርሴሎና መሆኑ ዝውውሩን ለሚኬል አርቴታ እና ለአርሰናል ከባድ ፈተና አድርጎታል። ✍️ በአቤኔዘር አዳነ #BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ… Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400 Website: https://www.bisrattv.com/ Telegram: https://t.me/Bisrat101fm YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB Twitter: https://twitter.com/Bisrat101