🍂 ዲነል ኢስላም 🕌
Статистика♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)ﷻ (ﷺ) « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...» ቁርኣን[ 3:104 ] መወያያ ግሩፓችን ☞ @Dinel_islam_Group ✔ ሀሳብ አስተያየት ካሎት 👉 @DinelIslam1Bot 📩
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 35
- Всего постов
- 45
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Религия
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 375
- 1/48двое суток
- 429
- 1/72трое суток
- 463
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ሰይዲ አህለን ወሳህላ ያ ሙሸሪፈ ረቢዒ 💚
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ይረገም ይህ ልቤ! ዓቅል መከመያው፣ ካሰቡት መድረሻው፣ የሻቱትን ማግኛው፣ የዓለማቱ፣ የሲራጥ አቀበቱ፣ የለህድ የመህሸሩ፣ የጅስም የሩሑ፣ የቀልብ የዓይኑ ብርሃን አንቱ መሆንሁን ዘንግቶ አይረቤ ሻማ ፍለጋ ሲኳትን ጨለማ የወረሰው፣ ወደ ጌትዬው ከፍታ መወጣጫ አንቱ መሆንሁን ስቶ ሌላ መሰላል ሲደገፍ ወድቆ የተሰበረው፣ የደፋሁለትን የልቅና ቆብ የጫንኩለትን የንግስና ዘውድ አውልቆ የባርነትን ቀንበር የተሸከመው፣ የደረብኩለትን የግርማ ካባ አውልቆ እርቃኑን የቀረው፣ ከዒናያ ዓይንሁ ተሰውሮ በሰው ዓይን የተገረፈው፣ ከጥላ ከአጥርሁ ሸሽቶ ሀሩር የገረፈው ቁር የጠበሰው፣ የጥጋብ ማ’ድሁን ገፍቶ በራ’ብ አንጀቱ ያረረው፣ ከጀነትሁ ወጥቶ በዓዛብ የተሞሸለቀው፣ ከነሻጣው ጎራ ወደ ጘፍላው ገደል የተፈጠፈጠው፣ ከለምለሙ ደጅሁ ወደ ድርቁ ቀዬ የተሰደደው፣ ሁሉን አሻሪ፣ የሁሉ ደዋዕ መሆንኩን ቸል ብሎ የማይሽር ህመም የሸመተው፣ ሿሚ ሞሻሪውን አንባሪ አክባሪውን ትቶ የደኸዬው የከሰረው፣ ካንቱ ከማዕረጉ ከባለ ሚዕራጁ ጉያ ተንሸራትቶ ከአራጁ ጋር የዋለው፣ የዱንያ አኸራ ዚነት መገኛው ካንቱ ሆኖ ሳለ ሌላ ጌጥ ፍለጋ ሸመታ የወጣው፣ ተቀርቶ ከማያልቀው የዒልምሁ ባሕር ርቆ የጅህልናን ኪታብ ገልጦ የሞጠለው፣ ከአህለል በይት ጎጆ ኮብልሎ ጎዳና ወጥቶ ባይተዋር ሆኖ የሚንከራተተው፣ ጌትዬው ወሃሱነ ኡላኢከ ረፊቃ ብሎ ካወደሰው ከደጋግ ባልደረቦችሁ፣ ከነብዮቹ ከሙርሰሎቹ፣ ከሲዲቆቹ ከሹሃዳኦቹ ሊቃዕ፣ ከዓሪፎቹ፣ ከአካቢሮቹ፣ ከወሊዮቹ መጅሊስ አፈንግጦ አጉል ወዳጅ ያበጀው፣ ጦሐራውን ፋናሁን ስቶ በሃራም የጨቀዬው ልቤ! እናማ መደድ መደድ ያሰይዲ ያረሱለሏህ! አንተ ጢብቢል ቁሉቢ ወደዋኢሃ! በእዝነት ዓይንሁ ተመልከቱኝኛ፣ የራሕመት ጥላሁን አጥሉብኝና ይሄ ልብ የሌለው ልቤ ይሻር! ከወንጀል ስካር መላቀቅ ያቃተውን ልጅ እጅሁን ደረቱ ላይ አስቀምጠሁ ሒክማ እንደሞላሁት እኔንም ደገፍ አድርጉኝና ሰይድ ጂብሪል ላንቱ እንዳደረገው የልቤን ቆሻሻ ደም አለቅልቁልኝ! የቀታዳን ዓይን ባሻረው እጅሁ ዓይኔን አብሰሁ ግለጡልኝ! ለሰይድ አህመደል በደው እንዳደረግኩት እጅሁን ለሰላም ዘርጉልኝና ከውን ይታረቀኝ|! ለሰይድ ቡሰይሪ እንዳለበስኳቸው ያለ የዓፍያ ካባ ለኔም ደርቡልኝና ላልደክም ልጀደድ! እንደ ሙስዓብ በዱንያ ኑር፣ በቀብር ከፈን የሚሆን ሱንዱስ አልብሱኝ! ለ’ነ ሰይድ ጫሌ ከሰፋሁት የመደድ ቁና አዘግኑኝ፣ ለ’ነ አንይ የዘረጋሁትን የከረም ኩታ ጫፍ አስይዙኝ! ደጋጎቹ የወዙበትን ከሐውድ ከከውሰሩ ከዘምዘም ከተሕሊሉ የላቀ ቱፍታሁን አቅምሱኝ! ያሲራጀን ሙኒር ያሚስባሁ ዞላም! የጥሜቱ ሌሊት በዊላዳሁ እንደነጋ ይኔም የቀልብ ደመና በጀማልሁ ይገፈፍ! ያቀመረል መካ መዒሸተን ዾንካ በዓይሸ ሱዓዳ ይተካ! አርሒቡ ነብዬ! መርሐበን ረቢዕ ለምለሙ! እንኳን ለኑር ሱንዱቁ ረቢዑል አንዋር አደረሰን! #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
#የረቢዕ_ኒያዎች #የረቢዐል አወልን ወር በምን ዓይነት ኒያዎች እንቀበለዋለን? በሸይኽ ሐቢብ ዑመር (አላህ ይጠብቃቸው) 1. ሱናቸውን ሕያው ማድረግ በራሳችን፣ በቤተሰባችን፣ በልጆቻችን እና በመላው ሙስሊሞች ዘንድ የነቢዩን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ለማነቃቃት እና በተግባር ለማዋል ማቀድ! 2. የቤተሰብን ልብ ከእርሳቸው ጋር ማያያዝ የቤተሰቦቻችንን እና የልጆቻችንን ልብ ከእውነት እና ከመልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፍቅር ጋር ማያያዝ። 3. ታሪካቸውን ማንበብ ስለ ነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተነገሩ ነገሮችን ማጥናት፣ የሕይወት ታሪካቸውን (ሲራ) እና መልካም ሥነ-ምግባራቸውን (ሸማኢል) በብዛት ማንበብ እና ማጥናት። 4. ሶለዋት ማብዛት በነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት እና ሰላምታ ማውረድን ማብዛት። 5. ኢማንን እና ፍቅርን ማሳደግ ለአላህ) እና ለነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያለንን እምነት (ኢማን)፣ ፍቅር እና አክብሮት ማላቅና መጨመር። 6. እርሳቸውን አርአያ ማድረግ እና መከተል ነቢዩን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አርአያ ማድረግ፣ በሂዳያቸው መመራት እና መንገዳቸውን መከተል። 7. የአላህን እርዳታ እና እፎይታን መመኘት በነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በረካ አላህ ለሕዝበ ሙስሊሙ ጥበቃውን፣ ድሉን እና ሰፊ እፎይታውን እንዲሰጥ ተስፋ ማድረግ እና መማጸን። *** በረቢዕ የሚደረጉ መውሊዶች ኹሉ በእነዚህ መልካም ኒያዎች ይከናወናሉ። በከተማችን የሚገኘው ታላቁ አንዋር መስጀድ ረቢዕን ቀድሞ አስጀምሯል። እነ በኒን እነ ቢላል፣ በመላው ከተሞች ረቢዕ ከወትሮ በተለየ መልኩ እንደሚደምቅ ይጠበቃል። #ረቢዕ በመግባቱ የመረቀናችሁ ኹሉ እነዚህን ኒያዎች በልባችሁ አሳድሩ! የረቢዕ ኸሚስ ምሽት ገባ ♥
#1501መውሊድ አሽሞንሙኖ ነው ሲኸልቅሁ ሲያዘልቅሁ በኸልቁ ላይ!🤎 ሰይዲ አህለን ወሳህላ ያሙሸሪፈ ረቢዒ!💚 መርሀበን አህለን ወሳህላ ያረቢዕል አንዋር!🤎
#ረቢዕ በየአመቱ ያብባል ♥ ግብጽ ውስጥ ባሉ መስጂዶች ሁሉ የረቢዕን መግባት አስመልክቶ በአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ወሩን ሙሉ ሰለዋት ማውረድ ይጀምራሉ። ይህ የሚኾነው ለመጀመሪያ ጊዜ እንደኾነ የካይሮ 24 አውቃፍ (የእስልምና ጉዳዮች ሚኒስቴር) ምንጮች ዘግቧል። ይህ ጥሩ ዜና ነው፤ መስጂዶች በሰለዋት በመውሊድ ሲያሸበርቁ ሰውም ወደ ጥሩ መንፈስ ይመለሳል ♥
ረቢዑ ዛሬ ለይሉን ይገባል አልሐምዱሊላህ። እንኳን አደረሰን💚 እንደተለመደው እንደ ከዚህ ቀደሙ ረቢዑን በኸይር ሥራዎች እናስውበው 💐 ከተቻለ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ለአንድ ቤተሰብ በመሸፈን 💐 በዕዳ ለተጨነቁ ሰዎች እዳቸውን አውፍ በማለት 💐 ወይም ዕዳቸውን ከፍሎ በማስደሰት 💐በፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገኙ ታማሚዎችን በሆስፒታሎች ደጅ የጠኑትን በመዘየር በማባሸር 💐 ለጎዳና ልጆች በማብላት የታረዙትን በማልበስ 💐 ትላልቅ ኡለማዎችን ሸሆችን ታማሚዎችን በመዘየር 💐 ደም ልገሳ በማድረግ 💐 ለአንድ ተማሪ አንድ ጫማ በመግዛት 💐 ቦርሳ በመግዛት 💐 ደብተር በመግዛት 💐 ለአንድ ሰውም ቢሆን በመመገብ ወሩንም የወሩን ባለቤትም እናክብር ይህቺን ቆንጆ ቢዳአ ያሰራንማ🤲💚 سَيِّدِي أَهْلًا وَسَهْلًا يَا مُشَرِّفَ رَبِيعِ💚💐
#የንጋቱ ትንፋሽ የአዲስ ተስፋ ምልክት ነው! በቁርኣን ላይ አላህ "ወሱብሒ ኢዛ ተነፈስ" ንጋት በተነፈሰ ጊዜ! ብሎ ይምላል። የሌሊቱ ጨለማ ተገፎ ንጋት እፎይ ብሎ ሲተነፍስ፣ ተፈጥሮ በሙሉ አዲስ ህይወትና ብርሃን ትላበሳለች። ያንን ንጹህ የንጋት ነፋስ ጥቂት ደቂቃ እንኳን ውስጣችንን ሞልተን እንተንፍሰው፤ መንፈሳችንን ያድሰዋል። ይህ ድንቅ ሰአት በእንቅልፍ አያምልጥህ! ይህ ሰአት በሩ ክፍት ነው።ቀንህን በዚክርና በዱዓ በአዎንታዊ እይታ ጀምር! መልካም እና የበረከት ቀን ይሁንልን!