- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- турецкий
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 273
- 1/48двое суток
- 1 458
- 1/72трое суток
- 1 573
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ዛሬ በሶሻል ሚዲያ ሰውን ማዋረድ ከመጽሐፍ መጻፍ የበለጠ ገንዘብ ሊያስገኝ ይችላል።ስድብ ከእውቀት በላይ ትኩረት ያገኛል። ግን ችግሩ እነሱ ብቻ ናቸው? ወይስ እኛ የምናጋራውን እና የምንወደውን ነገር እያበረታታን ነው? አሉታዊ ይዘት ለምን ብዙ ትኩረት ያገኛል? ከአዕምሮ ሕክምና አንፃር እናያለን ሙሉውን በዶክተር ኃይለልዑል የዩትዩብ ቻናል ያገኙታል 👇👇 https://youtu.be/Gje1vj2fc3o?si=6MlZHVmRnhNTuvao
ሶሻል ሚዲያ ትኩረታችንን፣ ስሜታችንን እና የህይወት ልምዳችንን እንዴት እየተቆጣጠረና እየቀየረ ነው? ለምን በጥልቅ ማሰብ አቃተን? ሶሻል ሚዲያ አዕምሯችንን እየሰረቀ ነው? ሙሉውን በዶክተር ኃይለልዑል የዩትዩብ ቻናል ያገኙታል 👇👇 https://youtu.be/x9SpF0HF48w?si=X8cPRIOQOEpsl1JX
በውጥረት (Stress)፣ ፍርሃት (Fear) እና ጭንቀት (Anxiety) መካከል ያለው ዋና ልዩነት • እርዳታ መፈለግ ያለብን መቼ ነው? ሙሉውን በዶክተር ኃይለልዑል የዩትዩብ ቻናል ያገኙታል 👇👇 https://youtu.be/T2aQO7Br6XU?si=9suHSRjqxYMz1-Xa
የተበላሹ ግንኙነቶች መቼ እናቁም? | ያበቃለት የፍቅር ግንኙነት ምልክቶች ✅ የፍቅር ግንኙነት እየተበላሸ መሆኑን የሚያሳዩ ዋና ምልክቶች ✅ መቼ ግንኙነቱን ለማዳን መሞከር እንደሚገባ ✅ መቼ መለያየት ጤናማ ውሳኔ ሊሆን እንደሚችል ✅ ከመለያየት በኋላ ራስን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ✅ በቀጣይ ጤናማ ግንኙነት ለመገንባት ምን መማር እንደሚገባ ሙሉውን በዶክተር ኃይለልዑል የዩትዩብ ቻናል ያገኙታል 👇👇 https://youtu.be/CinAzlA7faQ?si=eekLgHqGHq50p7TE
በስነ-ልቦና ማጭበርበር (Gaslighting) እየተጠቁ ይሆን | የዚህ ችግር ተጠቂ መሆንዎን የሚያሳዩ 5 ቁልፍ ምልክቶች። • ጋዝላይቲንግ ምንድን ነው? ምልክቶቹስ ምን ምን ናቸው? • እነዚህ ሰዎች ለምን ይህን ያደርጋሉ? • ከጋዝላይተሮች ጋር በሚኖር ግንኙነት ማድረግ ያለብዎት ጥንቃቄዎች። • አዕምሮዎን እና እውነታዎን መልሰው የሚቆጣጠሩባቸው ተግባራዊ መንገዶች። ሙሉውን በዶክተር ኃይለልዑል የዩትዩብ ቻናል ያገኙታል 👇👇 https://youtu.be/9-leO3nOQh0?si=ycKnlMjiztr4cdMP
የቁስ-አምላኪነት ዘመን… “ይሄን የመሰለ መልክ ይዤ” ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አንዲት ቲክቶከር ይሄንን ስትናገር ሰማሁ።“እኔ ቆንጆ ሆኜ ነገር ግን መልክ የሌላቸው (ገርዳሜ) ሴቶች መኪና እየነዱ፣ እኔ ግን በእግሬ እሄዳለሁ። ለመሆኑ ህይወት ፍትሃዊ ናት?” የተናገረችው ሃሳብ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ቢሆንም ለእኔ ግን እንደ አንድ የአዕምሮ ሀኪም በትውልዱ ላይ እየደረሰ ያለውን የማንነት ቀውስ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ንግግር ነዉ ብዬ አስባለሁ።ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ወደ ቁስ-አምላኪነት እና ወደ ፈጣን እርካታ ፈላጊነት እያዘገምን ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። ዛሬ ላይ በርካታ ወጣቶች (ሴቶችም ሆኑ ወንዶች) ህይወትን እና ስኬትን የሚመዝኑበት መነጽር እየተቀየረ ያለ ይመስላል።’የትም ፍጪዉ ዱቄቱን አምጪዉ’ የሚለው አስተሳሰብ የትውልዱ ዋና መመርያ እየሆነ መጥቷል። የኛ ትውልድ ትልቁን የስነ-ልቦና ቀውስ እየተጋረጠ ያለው በማህበራዊ ሚዲያ በሚለቀቁ የተቀነባበሩ ይዘቶች ምክንያት ይመስለኛል። ውድ መኪናዎች፣ ዘመናዊ ቤቶችና የቅንጦት አልባሳት የንጽጽር ህይወት ውስጥ ከተውታል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው ህይወት የሰዎችን የዕለት ተዕለት እውነታ ሳይሆን የተመረጠና የተቀነባበረ “አሪፉን ገጽታን” ብቻ እንደሆነ እዉን ነው። ነገር ግን ወጣቱ ይህንን የውሸት ድራማ ከራሱ ህይወት ጋር በማነጻጸር እራሱን እንደ ተሸናፊ መቁጠር ይጀምራል። ይህ ስሜት ደግሞ “እኔስ ለምን እንደ እነሱ አልሆንም?” የሚል አላስፈላጊ የውስጥ ጭንቀት ይፈጥራል። ይህ ቁሳዊ ጫና ወጣቶችን (በተለይም ሴቶችን) ወደ አልሆነ መንገድ እየመራቸው ይገኛል። ውበት እና አካላዊ ገጽታ እንደ ትልቅ የንግድ ካፒታል የሚቆጠሩበት አዝማሚያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በሂደት ሰርቶ ስኬታማ መሆን አድካሚ እና ጊዜ የሚወስድ መስሎ ስለሚታይ የራስን አካላዊ ውበትና ስብዕና ለገበያ በማቅረብ ፈጣን ገቢን ማግኘት እንደ ብቸኛ መንገድ መቆጠር ይጀምራል።ታዲያ ቁሳዊ ነገሮችን በፍጥነት ለማግኘት ሲባል የሚከፈለው ዋጋ ቀላል አይሆንም። እንደ ባለሙያ መሬት ላይ በየቀኑ የምናያቸው እውነታዎች እንደሚያሳዩት በዚህ የቁስ-አምላኪነት አዙሪት ውስጥ የገቡ ወጣቶች ለአጭር ጊዜ ያሰቡትን ቁስ ቢያገኙ እንኳ የረጅም ጊዜ ስነ-ልቦናዊ ቀውሳቸው የከፋ ነው። ከእነዚህም የውስጥ ባዶነትና የአዕምሮ ጤና መታወክ ዋነኞቹ ናቸዉ። ትውልዱን ከዚህ የስነ-ልቦና ቀዉስ ማዳን የሚቻለው መሬት ላይ ያለውን እውነታ በግልጽ ስናሳየው ብቻ ነው። ማራኪ መስሎ የሚታየው የቀላሉ መንገድ መጨረሻው የህሊና ባርነት እና የአዕምሮ ቀውስ መሆኑን ለይቶ ማስተማር የሁላችንም የጋራ የቤት ስራ ነው። ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን | የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት
እናቱንና ሚስቱን በአንድ ለሊት የገ*ደ*ለዉ ወጣት ነሐሴ 1 ቀን 1966 ዓ.ም በአሜሪካ ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ሰማይ ስር አንድ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ። አንድ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ረጅም የሰዓት ግንብ ላይ ወጥቶ ለ96 ደቂቃዎች ያህል በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንደ በረዶ ጥይት አዘነበ። ይህ ሰው ቻርለስ ዊትማን ይባላል። ቻርለስ በልጅነቱ ጎበዝ ተማሪ ነበር። በ12 ዓመቱ የ"ኢግል ስካውት" ማዕረግን በመቀዳጀት በታሪክ ትንሹ ልጅም ነበር። በኋላም የአሜሪካ ባህር ኃይልን ተቀላቅሎ በልዩ ተኳሽነቱ ምስክር ወረቀት አግኝቷል። በትምህርቱም ቢሆን የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረ ሲሆን ባለትዳርና በሰው ዘንድ ተወዳጅ ነበር። ቻርለስ በከባድ ራስ ምታትና "መቆጣጠር በማልችላቸው ክፉ ሀሳቦች እየተሰቃየሁ ነው" በሚል ጭንቀት ይናጥ ነበር። አልፎ ተርፎም አንድ ቀን ወደ ግንቡ ጫፍ ወጥቶ ሰዎችን ላይ የመተኮስ ምኞት ቢጤ እንደመጣበት ለሀኪም ቢያማክርም ማንም ግን ትኩረት አልሰጠውም ነበር። ከጥቃቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቻርለስ በማስታወሻው ላይ እንዲህ ሲል ጻፈ "ራሴን ማወቅ አቅቶኛል በአእዕምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱትን ምክንያታዊ ያልሆኑ ሀሳቦች ለመቋቋም ትልቅ ትግል እያደረግሁ ነው።"በዚያው ምሽት መጀመሪያ እናቱን በመቀጠልም የተኛችውን ባለቤቱን በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ገደ*ላቸው። በማግስቱ ነሐሴ 1 ቀን በርካታ ጠመንጃዎችን በሳጥን ጭኖ ወደ ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ግንብ አመራ። 28ኛ ፎቅ ላይ ወጥቶ ለ96 ደቂቃዎች በፈጀው በዚያ አስከፊ ጥቃት 15 ሰዎችን ሲገድል 31 ሰዎችን ደግሞ በማቁሰል በመጨረሻም በፖሊሶች ጥይት ህይወቱ አለፈች። ከመሞቱ በፊት በጻፈው ደብዳቤ "ከሞትኩ በኋላ አካሌ ተመርምሮ ምን እንደሆነ ይነገረኝ" ብሎ ነበር። ምርመራው ሲደረግ በአንጎሉ ውስጥ እንደ ለውዝ የምታክል እጢ ተገኘ። ይህች እብጠት ያለችው ደግሞ የአንድን ሰው ስሜትና ቁጣ በሚቆጣጠረው የአዕምሮ ክፍል አሚግዳላ ላይ ተጭና ነበር። ጥቃቱን የፈጸመው በገዛ ፍቃዱ ነው ወይስ በአንጎሉ ውስጥ በበቀለችው እጢ ተገፍቶ? ይህ ታሪክ የአዕምሮ ጤና ምን ያህል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና ትንሽ የጤና ችግር የሰውን ልጅ ወደ ምን ዓይነት አረመኔነት ሊቀይረው እንደሚችል ትልቅ ትምህርት ጥሎ አልፏል። በዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን
ሲቀርበኝ እሸሻለሁ... ሲርቀኝ እፈራለሁ | ይህ ምን ዓይነት ፍቅር ነው? “Anxious-Avoidant Attachment” በመባል ይታወቃል። በፍቅር ግንኙነት ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያሳድራል? ሙሉውን ለማየት 👇👇 https://youtu.be/rX8rufYjSCI
አለማወቅ ደፋር ያደርጋል! ይህ አባባል እንደ ዛሬው እውነት ሆኖ የሚያውቅበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። በየፖድካስቱና በየቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ የምናየው ነገር ይሄንኑ ነው። ስለ ጤና፣ ስለ ታሪክ፣ ስነ-ልቦና፣ ስለ ኢኮኖሚ... በቃ ስለ ሁሉም ነገር የሚያውቁ የሚመስሉ ግን ደግሞ ጥልቀት የሌላቸው ሰዎች ማይክ ይዘው በድፍረት ሲናገሩ እናያለን። የሚገርመው ደፋር መሆናቸው ብቻ አይደለም። ዓመታትን ሙሉ በትምህርት እና ልምድ ያሳለፉትን ባለሙያዎችን በድፍረት ሲያጣጥሉ እና ስህተት እንደሆኑ ሊያስረዱን ሲሞክሩ ስናይ... ነገሩ ግርምትንም ቁጭትንም ይፈጥራል። አንድ ሰው ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ያለው እውቀት ወይም ብቃት በጣም ዝቅተኛ በሆነ ቁጥር የራሱን ድክመት እና አለማወቅ የመገምገም አቅሙም አብሮ ይጠፋል።ግለሰቡ ስለ ጉዳዩ ጥልቀት ስለማያውቅ እራሱን "ከፍተኛ አዋቂ" አድርጎ ይገምታል። በዚያ ምክንያት ንግግሩ ውስጥ ምንም አይነት ጥርጣሬ ወይም ፍርሃት አይታይበትም። በተቃራኒው ደግሞ አንድ ሰው ስለ ጉዳዩ እያጠና እና እያወቀ በሄደ ቁጥር ነገሩ ምን ያህል ሰፊ እና ውስብስብ እንደሆነ መረዳት ይጀምራል። ያን ጊዜ ገና ብዙ መማር አለብኝ፣የማላውቀው ነገር ብዙ ነው ብሎ እራሱን ዝቅ ያደርጋል፣ ንግግሩም ጥንቃቄ የተሞላበት ይሆናል። አሁን የምናየዉ ድፍረት ማህበረሰባችን ውስጥ የሚያመጣው ትልቁ አደጋ ማህበረሰቡ ዓመታትን ሙሉ ለፍተው እውቀት ካካበቱ ባለሙያዎች ይልቅ፣ ማይክ ለያዙ ቦታ መስጠት ሲጀምር...የእውቀት እና የባህል መዋቅር መናጋት ይጀምራል።ይህ በሚሆንበት ጊዜ ወጣቱ ትውልድ ምን ይማራል? "ለመታወቅ፣ ለመከበር እና ሰው እንዲያዳምጠኝ መማርና መልፋት አያስፈልገኝም፤ ዝም ብዬ በድፍረት መናገር ብቻ ይበቃኛል" የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ይይዛል። ስለዚህ አንድ ሰው በከፍተኛ በራስ መተማመን ስላወራ ወይም ድምጹን ከፍ ስላደረገ ብቻ... ያ ሰው "አዋቂ" ነው ማለት እንዳልሆነ መረዳት አለብን። የእውቀት ትልቁ ጠላት አለማወቅ ሳይሆን፣ አዋቂ መምሰል ነው ። ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን | የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት
እውነተኛ ታሪክ! በእንጀራ አባቷ የመደፈር ጥቃት ደርሶባት ከጊዜ በዃላ ከራሱ ፍቅር ይዟት በስነልቦና ቀውስ ምክንያት ወደ ሕክምና የመጣችው ታካሚ። ይህ በአዕምሮ ሕክምናው “Trauma Bonding” ወይም በጥቃት ላይ የተመሰርተ ትስስር በመባል ይታወቃል። - Trauma Bonding ምንድን ነው? - አዕምሮአችን ጥቃትን ለምን እንደ “ፍቅር” ይተረጉመዋል? - ተጎጂዎች ከአጥቂያቸው መለየት ለምን ይከብዳቸዋል? - ከTrauma Bonding እንዴት መውጣት እና መታከም ይቻላል? ይህ ቪዲዮ በተለይ ለወላጆች በጣም አስፈላጊ ነው ሙሉውን ለማየት 👇👇 https://youtu.be/hyj4g769R2s
ሰላም፣ እንዴት ናችሁ! በአዕምሮ ጤና፣ በማህበራዊ ጉዳዮች እና በስነ-ልቦና ዙሪያ በቅርብ ቀናት ውስጥ በዩትዩብ ይዤላችሁ እመጣለሁ። እስከዚያው ድረስ የYouTube ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። https://youtube.com/@drhaileleulmekonnen?si=-nZTbkTVEjrP5VK8
“ባሌ ካልመታኝ እና ካልተቆጣኝ የሚወደኝ አይመስለኝም!” በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) ይህንን ንግግር ስንሰማ አብዛኞቻችን እንዴት እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ይኖራል? ብለን መገረማችን አይቀሬ ነው። ነገር ግን በአእምሮ ሕክምና ውስጥ ከሚገጥሙን ታሪኮች መካከል አንዱ ይሄ ነው። አንዲት ሴት የትዳር አጋሯ ካልተቆጣት ወይም አካላዊ ጥቃት ካላደረሰባት “አይወደኝ” ብላ እንድታስብ የሚያደርጋት ይሄ ያልተለመደ ስሜት ከጀርባው ያልታከመ የቆየ ቁስል እንዳለዉ እንረዳለን። አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃትን ከፍቅር ጋር እንድታቆራኝ የሚያደርጋት ይሄ ምስጢር ምንድን ነው? ነገሩን በጥልቀት ለመረዳት ወደ ልጅነት እና የመጀመሪያውን የወላጅ ትስስር ማየቱ አስፈላጊ ነው። ይህ አይነቱ የፍቅር መገለጫ በልጅነታቸዉ በወላጅ ወይም አሳዳጊዎች በተደጋጋሚ አካላዊ እና የስሜት ጥቃት የደረሰባቸዉ ልጆች ላይ ይስተዋላል። ፍቅርንና ትኩረትን ያገኙት በሰላማዊ መንገድ ሳይሆን በቁጣ ወይም በቅጣ ሊሆን ይችላል። ወላጅ ከደበደባቸው በኋላ አቅፎ ሲያባብላቸው ያላደገው የልጅነት አእምሮአቸው ሳያውቀው “ትኩረትና ፍቅር የሚመጣው ከቅጣት በኋላ ነው” የሚል ትርጉም ይሰጣል። ለእነሱ ፍቅር ማለት ትኩረት ነው፤ ትኩረት ደግሞ በቁጣና በዱላ ይገለጻል የሚል የተዛባ እምነት በድብቁ የአእምሮ ክፍል ውስጥ ይሰረጻል። ወላጅ ሲቀጣቸው ወይም ሲቆጣቸው “ትኩረት አገኘሁ” ብሎ የተረጎመው የልጅነት አእምሮአቸው ሳያውቁት በትልቅነታቸውም ፍቅርን ከጥቃት ጋር አቆራኝቶት ያድጋል። ድብቁ የአእምሮ ክፍል የትዳር አጋራቸውን ወይም የትኛዉንም ጥልቀት ያለዉ ግንኙነት ልክ እንደ ወላጅ ማየት ይጀምርና ሳይቀጣቸው ሲቀር “አልተፈለግኩም፣ ተረስቻለሁ” የሚል የባዶነት ስሜት ይፈጥርባቸዋል። በተጨማሪ በልጅነት የደረሰ አካላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት አእምሮን ከተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ ይልቅ በጭንቀትና በትርምስ ውስጥ እንዲላመድ ያደርገዋል። በትዳር ህይወታቸው ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ሲሰፍን አእምሮአቸው እንግዳ ይሆንበታል። አጋራቸው ተቆጥቶና በቶሎ ስሜታዊ ሆኖ ጉዳት ሲያደርስባቸው “ይህ ፍቅር ነው” የሚል የውሸት የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል። ስለዚህ ይህ አስተሳሰብ የመደብደብ ፍላጎት ሳይሆን ያልታከመ የልጅነት ቁስል እና የስሜት መጎዳት ውጤት ሊሆን ይችላል። እነዚህ ሰዎች ጥቃት አድራሹን ሳይሆን በጥቃቱ ውስጥ የሚያገኙትን ያንን የለመዱትን ትኩረት ነው የሚናፍቁት። ለዚህም አይነቱ ችግር የአእምሮ ሕክምና እጅግ ወሳኝ ነው።የህክምና ቀጠሮ ለመያዝ( t.me/hakimu4) ወይም በ0994633335 ይደዉሉልን።
አዕምሯችንም ይደክማል! በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) ብዙዎቻችን የአካላችንን ድካም በቀላሉ እንረዳዋለን ለምሳሌ እግራችን ሲደክም እንቀመጣለን፣ ትከሻችን ሲዝል ደግሞ ጋደም ብለን ለማረፍ እንሞክራለን። ነገር ግን አዕምሯችን የሰውነታችን ሁሉ መሪ ሆኖ 24 ሰዓት ያለእረፍት እንዲሠራ እናስገድደዋለን።አዕምሮ ልክ እንደ አካላችን ካልተንከባከብነውና ተገቢውን እረፍት ካልሰጠነው መድከሙ የማይቀር ነው። በየቀኑ በኑሮ እና በሥራ ሩጫ ውስጥ ስንሆን አዕምሯችን “ደክሞኛል፣ እረፍት እፈልጋለሁ!" እያለ በተለያየ መንገድ ድካሙን ይገልፃል። አንዳንዴ በእንቅልፍ ማጣት፣ አንዳንዴ የማተኮር አቅም በማጣት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለምክንያት ቶሎ በመበሳጨትና በስሜት መለዋወጥ ሊገለፅ ይችላል። ታዲያ እነዚህን ምልክቶች እንደ ቀላል አይቶ ችላ ማለት ለከፍተኛ የአዕምሮ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል። የአዕምሮ ጤናን መጠበቅ የሚጀምረው ራስን ከማድመጥና ለራስ ጊዜ በመስጠት ነው። ለአዕምሯችን ጊዜ መስጠትና ማሳረፍ ስንል ምን ማለታችን ነው? - በቂ እንቅልፍ ወስደን አዕምሯችን ራሱን እንዲያድስ እድል በመስጠትና ከመተኛታችን በፊት ከስልክና ሶሻል ሚዲያ በመራቅ አዕምሮ በአግባቡ እንዲያርፍ ማድረግ። - ብቻችንን ከመብሰልሰል ከሰዎች ጋር ተገናኝቶ የውስጥን ጫና እና ጭንቀት ማውራት፤ ስሜትን ለምናምነው የቅርብ ሰው ወይም ለባለሙያ በማጋራት የአዕምሮን ሸክም በማውረድ። - ከዕለት ተዕለት ጩኸት ራቅ ብሎ በንጹህ አየርና በተፈጥሮ መካከል ጥቂት ደቂቃዎችን በማሳለፍ እንዲሁም ከአደንዛዥ እፆች፣ ከጫትና ከአልኮል ጊዜያዊ መጠለያነት በመራቅ የአዕምሮን ጤና መጠበቅ እና መንከባከብ እንችላለን። የህክምና ቀጠሮ ለመያዝ( t.me/hakimu4) ወይም በ0994633335 ይደዉሉልን።
ቪዲዮ ኤዲተር እና ፖስተር ዲዛይነር እንፈልጋለን! ለዩቲዩብ እና ለማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን የቪዲዮ ኤዲቲንግ (Long-form & Shorts) እንዲሁም የዩቲዩብ Thumbnail እና የፖስተር ዲዛይን ስራዎችን በጥራት የሚሰሩ ባለሙያዎችን አብሮን እንዲሰሩ እንፈልጋለን። ፍላጎት ያላችሁ በዚህ የቴሌግራም አካዉንት ( @hakimu4 )ያናግሩን!! We are Hiring Video Editors & Poster Designers! We are looking for talented professionals to join us in creating high-quality, creative video edits (both long-form & shorts) as well as YouTube thumbnails and poster designs for our YouTube channel and social media platforms. If you are interested, please contact us via this Telegram account (@hakimu4)
ወንድ አይደለህ!! ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና ካዉንስሊንግ ሳይኮሎጂስት) በማህበረሰባችን ለወንድነት ከሰጠነው መለኪያዎች መካከል የማያለቅስ፣ ስሜት አልባ፣ ምንም እንኳን ጫና ቢደርስበትም ወንድ ስለሆነ ብቻ ዋጥ እና ቻል አድርጎ እዲያልፍ ይጠበቅበታል። ይህ በተለምዶ ለወንዶች የተሰጠ ማንነት ነው። በአጋጣሚ ከአቅሙ በላይ ሆኖ ካለቀሰ "ወንድ አይደለህ ጠንከር በል እንጂ የምን መልፈስፈስ ነው" ይባላል። ታዲያ ይህ የማህበረሰብ ጫና የሚሰማውን እና እያሳለፈ ያለዉን ከመናገር በራሱ እንዲወጣው እና እልፍ ሲል እርምጃ እንዲወስድ ይገደዳል። በዓለማችን በየዓመቱ ራሳቸውን ከሚያጠፉ 700,000 በላይ ሰዎች መካከል ከ450,000 በላይ የሚሆኑት ወንዶች ናቸው። በሰዓት 60 ወንዶች፣በቀን 1,500 ወንዶች ፣በሳምንት 12,000፣በወር 45,000 በላይ ወንዶች ራሳቸውን ያጠፋሉ።ይሄ ቁጥር ታዲያ ሙከራ የሚያደርጉትን ሳይጨምር ነው፡፡ ማልቀስ እና ስሜትን በግልጽ መናገር ሰው የመሆናችን ተፈጥሯዊ መገለጫዎች እንጂ የወንድነት መለኪያዎች አይደሉም።የሚሰማንን ለሌሎች ማጋራት የደካማነት መገለጫ አይይለም፤ እርዳታ መጠየቅ እና የአዕምሮ ህክምና ማድረግም ከወንድነት ጋር አይገናኝም ። ስለዚህ ወንዶች በየትኛውም የህይወት ጫና ዉስጥ እያለፍቹ ቢሆንም ብቻችሁን አይደላችሁም፤እርዳታ መጠየቅ ደግሞ የሽንፈት ወይም ያለመቻል ምልክት አይደለም። የህክምና ቀጠሮ ለመያዝ( t.me/hakimu4) ወይም በ0994633335 ይደዉሉልን። የአዕምሮ ጤና ለሁሉም!! #የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር #MentalHealthAwarenessMonth
ኢድ አል-አድሃ ሙባረክ!
ቁርስ በልቶ ምሳ መድገም ለማይችል ህዝብ ኳስ ምኑ ነው! ጨርሳችሁ በትግስት አንብቡት! በትላንትናው ዕለት አርሰናል ከ22 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ በኢትዮጵያውያን ደጋፊዎች ዘንድ የታየው ደስታ ብዙዎችን "በስም እንኳን ለማያዉቀን ክለብ እንደዚህ መሆን ምን የሚሉት ስሜት ነው?" የሚል መደነቅና ወቀሳ በማህበራዊ ሚድያዎች ታዝበናል። የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ እውነታን በቀጥታ ፊት ለፊት ማየት አይችልም። ይልቁንም ሁሉንም የህይወት ገጽታዎች በቋንቋ፣ በባህል፣ በህግጋት እና በምልክቶች ነው የሚረዳው።ማንኛውም ቁስ በራሱ የተለየ ዋጋ የለውም። ዋጋ የሚያገኘው በምልክቶች ሥርዓት ውስጥ በሚሰጠው ቦታ ልክ ነው። በኪሳችን ውስጥ ያለው ገንዘብ ዝም ብሎ ወረቀት ነው፤ ነገር ግን የማህበረሰቡ የምልክት ሥርዓት "መቶ ብር ነዉ”የሚል ህግ ሲያወጣለት ወረቀቱ አቅም ይኖረዋል። በተመሳሳይ የአንድ ሀገር ባንዲራ ጨርቅ ነው፤ ነገር ግን ያ ጨርቅ የክብር፣ የነጻነትና የማንነት ምልክት ስለሚሆን ሰዎች ህይወታቸውን ይሰጡለታል። ዋንጫውም እንዲሁ የድል፣ የጽናት እና ከተሸናፊነት ወደ አሸናፊነት የመሻገር ትልቅ ስነ-ልቦናዊ ምልክት ተደርጎ ስለተሰየመ አዕምሮ እንደ ትልቅ ነገር ያየዋል። ለአርሰናል ደጋፊዎች ላለፉት 22 ዓመታት በትችት፣ በመሸነፍ እና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ አልፈው ያዩት ድል ነው። ይህም ለአንድ ሰው አዕምሮ "ምንም ያህል ብትወድቅና ጊዜው ቢረዝምም አንድ ቀን ማሸነፍህ አይቀሬ ነው" የሚል ተስፋን የሚሰጥ ህያው ምልክት ይሆናል። “ቁርስ በልቶ ምሳ መድገም ለማይችል ህዝብ ኳስ ምኑ ነው?" እያሉ የሚወቅሱ ወገኖች ጉዳዩን በምክንያታዊነት ብቻ ስለሚመለከቱት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ በምክንያት ብቻ አይኖርም፤ሕይወታችን በምልክቶች የተሞላች ናት። እኔ የየትኛውም ክለብ ደጋፊ አይደለሁም ነገር ግን ለመላዉ የአርሰናል ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት)
የሕፃናት አዕምሮ ጤና! (በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን -የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) ብዙዎቻችን የአዕምሮ ህመም ትልቅ ሰዎችን ብቻ የሚያጠቃ ይመስለናል። ነገር ግን ልክ እንደ አዋቂዎች ሁሉ የሕፃናትም አዕምሮ ይጨነቃል፣ ይቆስላል፣ ይታመማልም። በአደጉት ሀገራት እንኳ ከ7 ሕፃናት ውስጥ አንዱ ቢያንስ በአንድ የአዕምሮ ጤና እክል ውስጥ እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ። በሀገራችን ደግሞ ይህ ቁጥር በተለያዩ ማህበራዊ ጫናዎች ምክንያት ከዚህ ሊበልጥ ይችላል። የሕፃናት አዕምሮ ሕክምና ትልቁ ፈተና ሕፃናት እንደ አዋቂዎች ስሜታቸውን በቃላት መግለጽ አለመቻላቸው ነው። የውስጣቸውን ስሜትና ህመም የሚገልጹት በባህሪያቸው ነው። ነገር ግን ወላጆችና መምህራን አብዛኛዉን ጊዜ ይህንን የባህሪ መለዋወጥ "ያልተቀጣ፣ ምግባር የጎደለዉ፣ እልኸኛ ወይም ሰነፍ" እንደሆኑ አድርጎ የመቁጠር ዝንባሌ ይስተዋላል። ነገር ግን ይህ ባህሪ የሕፃኑ አዕምሮ የዉስጡን ህመም የሚገልፅበት መንገድ ሊሆን ይችላል። በሕፃናት ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ ዋና ዋና የአዕምሮ ጤና እክሎች ምንድን ናቸው? (ለግንዛቤ ያክል የተወሰኑትን እንመልከት) 1. የትኩረት ማጣት እና ከመጠን በላይ መቅበጥበጥ (ADHD): በአንድ ቦታ ላይ ረግቶ መቀመጥ ያቅታቸዋል።ወንበር ላይ እያሉ እጅና እግራቸውን ማንቀሳቀስ፣ መጠማዘዝ ወይም ያለ ቦታው መሮጥና መውጣት ያዘወትራሉ።ጥያቄ ተጠይቆ ሳይያልቅ መልስ ለመስጠት መቸኮል፣ የሌሎችን ጨዋታ ወይም ወሬ ጣልቃ እየገቡ ማቋረጥ እና ፍላጎታቸው ወዲያውኑ ካልተሟላ ከፍተኛ መበሳጨት ማሳየት። መምህራን ወይም ወላጆች ሲያናግሯቸው በቀጥታ የማይሰሙ ይመስላሉ። ትንንሽ የቤት ስራዎችን እና መመሪያዎችን ጨርሶ ከመፈጸም በፊት ቶሎ ይረሳሉ ወይም ይዘናጋሉ። 2. የጭንቀት ህመም(Anxiety Disorders): ከወላጅ መለየትን አጥብቆ መፍራት፣ አዳዲስ ቦታዎች ላይ ከመጠን በላይ መደንገጥ ወይም ያለምክንያት የሆድ እና የራስ ምታት ማዘውተር። 3. የድባቴ ህመም (Depression): ከወትሮዉ የተለየ ብስጭት እና ንዴት ወይም ማልቀስ፣ ቀድሞ ይጫወቱባቸው ከነበሩ ነገሮች መራቅ እና ከሰዎች መገለል እንዲሁም በትምህርታቸው ላይ የነበራቸው ፍላጎትና ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል። 4. ኦቲዝም (Autism Spectrum Disorder): ከሰዎች ጋር የዓይን ለአይን ግንኙነት አለማድረግ፣ በዕድሜያቸው ልክ መናገር አለመቻል፣የተደጋገሙ ድርጊቶችን ማዘውተር እና የእለት ተዕለት ልምዳቸው ትንሽ እንኳ ሲቀየርባቸው ከፍተኛ መረበሽ ማሳየት ዋና ምልክቶች ናቸዉ። እነዚህ ምልክቶች በአንድ ሕፃን ላይ ለተከታታይ ሳምንታት ሲታዩ እና የልጁን የትምህርት፣ የቤት ውስጥ እንዲሁም የማህበራዊ ህይወት ሲያስተጓጉሉ የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው የአዕምሮ ጤና ጉዳይ መሆኑን ተረድተን ወደ ባለሙያ በመውሰድ በጊዜ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነዉ። የህክምና ቀጠሮ ለመያዝ @hakimu4 ወይም በ0994633335 ይደዉሉልን #የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር #የሕፃናት_አዕምሮ_ጤና #MentalHealthAwarenessMonth
አግቢ እንጂ፤ ቆመሽ ቀረሽ እኮ! በዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) አንዲት ሴት በህይወቷ ስኬታማ ሆና ራሷን ለመለወጥ ስትጥር ማህበረሰቡ ዕውቅና ከመስጠት ይልቅ የትዳር ሁኔታዋን እንደ ዋነኛ መመዘኛ ሲወስደዉ ይስተዋላል። የቱንም ያህል ብትማር፣ ብትመራመርና ተፅዕኖ ፈጣሪ ብትሆኖም ትዳር እስካልያዘች ድረስ እንደ "ጎዶሎ" እንድትቆጠር ይደረጋል። ይህ የስነ ልቦና ጫና ሴቷ በራሷ እንዳትተማመንና ማንነቷን በትዳር መስታወት ውስጥ ብቻ እንድትፈልግ ትገደዳለች። “አግቢ እንጂ፤ ቆመሽ ቀረሽ እኮ!” የሚለው አባባል ለብዙ ሴቶች ሰላማቸውን የሚነሳ የጭንቀት ምንጭ ሊሆን የሚችልና በራሷ ላይ ያላትን እምነት እንድታጣ በማድረግ ሥር የሰደደ ማህበራዊ ውጥረት ሊያስከስት ይችላል። ሴቷ የጎደለኝ ነገር አለ ወይም ቤተሰቦቼን እያሳፈርኩ ነው የሚል የጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ እንድትወድቅ ከማድረጉም በላይ ለድብርት እና ለጭንቀት ህመም በር ይከፍታል። የማህበረሰቡ ንዝነዛ ከሚፈጥራቸው አስከፊ ውጤቶች አንዱ ሴቶች ካልተዘጋጁበትና ካልወደዱት ሰው ጋር ወደ ትዳር ዓለም እንዲገቡ መገፋፋታቸው ነው። ከማህበረሰቡ ወቀሳ ለማምለጥ ሲባል ብቻ የሚደረግ እና በፍቅር ሳይሆን በጫና የተመሰረተ ትዳር ዉስጥ እንድትገባ ያደርጋታል። የማህበረሰባችን ትልቁ ስህተት ትዳርን እንደ ስኬት ብቸኝነትን ደግሞ እንደ ውድቀት መቁጠሩ ነው ብዬ አስባለሁ። ትዳር ሁለት ሰዎች በዝግጁነት የሚመሰርቱት ህብረት ሆኖ ሳለ ማህበረሰቡ “ቆመሽ ቀረሽ” እያለ በሚወረውረው ቃል አንዲት ሴት የነገ ህይወቷን ገደል ውስጥ እንድትጨምር እያደረጋት መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል። ስለዚህ እህቴ ሆይ ማንም ሰው ስላንቺ ደስታና ሰላም ካንቺ በላይ ሊጨነቅ አይችልም። በጫና የምትገቢበት ትዳር ደግሞ ነገ ለሚመጣው ስብራት ማንም ሃላፊነት አይወስድምና የአእምሮ ሰላምሽን አስቀድሚ። ወላጆችና ዘመድ አዝማድ የሆናችሁ ደግሞ ትዳር እንዲመሰርቱ የምታደርጉት ግፊት የነገ ስቃያቸውን ሊያፋጥን ይችላልና “መቼ ነው የምታገቢው?” ከማለት ይልቅ “እንዴት ነሽ?” የሚለው ጥያቄ ይቅደም በማለት ሙያዊ ምክሬን ለግሳለሁ። #የአዕምሮ_ጤና_ግንዛቤ_ወር
በጎ አድራጊዎች አልበዙም ? በዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት) በቲክቶክና ፌስቡክ ላይ በጎ አድራጊነት እንደ አዲስ የንግድ ዘርፍ እየተቆጠረ ይመስለኛል። ትናንት የዳንስ ቪዲዮ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ዛሬ በድንገት የችግረኞች ጠበቃ ሆነው ብቅ ማለት ከጀመሩ ሰነባብቷል። በጎ አድራጎት ከልብ የመነጨ ቅዱስ ተግባር መሆኑ ቀርቶ የሰዎችን ስሜት ሰርቆ እይታ የመሰብሰቢያ የማርኬቲንግ ስልት እየሆነ መምጣቱ ግን አሳዛኝም አስቂኝም ነው። ካሜራ ፊት የቆመ እንባ፣ በኤዲቲንግ የተቀነባበረ አሳዛኝ ሙዚቃ እና ሼር አድርጉት የሚል ትዕዛዝ... ይህ በጎ አድራጎት ሳይሆን የሰውን ልጅ ክብር ገበያ ላይ አውጥቶ ለራስ ዝና መሸመት ነዉ። የሰው ልጅ አእምሮ ለችግርና ለለቅሶ ፈጣን ምላሽ ስለሚሰጥ ይህንን ደካማ ጎን የሚያውቁ “የዲጂታል ነጋዴዎች” የሰውን ስሜት በመበዝበዝ የራሳቸውን ተከታይና ገቢያቸዉን ያበዛሉ። የሚገርመው ግን አንዳንዴ እርዳታ ሰብሳቢዎቹ ከሚረዱት ሰው በላይ ቁጥራቸው በዝቶ የነዳያን ፉክክር የተጀመረ ያስመስሉታል። ኧረ ለመሆኑ ይሄ ሁሉ በጎ አድራጊ ከየት መጣ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።በጎ አድራጎት በግራ እጅህ የሰጠኸውን ቀኝ እጅህ እንዳታውቀው የሚያዝዝ የሞራል ሕግ የነበረው ዛሬ ግን በግራ እጅህ የሰጠኸውን ቀኝ እጅህ ካሜራ ይዞ ካልቀረጸው በጎነት አይባልም የተባለ ይመስላል። ይህ ዓይነቱ ድርጊት መበራከት ማኅበረሰቡ በእውነተኛ ፍላጎትና በቅንነት ተነሳስተው ያለ ምንም ድብቅ ዓላማ ሌሊት ከቀን የሚደክሙ እውነተኛ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ግለሰቦችን እምነት እንዲያጣ ማድረጉ ነው። ከዚህም በላይ በእርግጥም ችግር ውስጥ ያሉ እውነተኛ ተረጂዎች ከእይታ ውጪ እንዲሆኑ እያደረገ ነው። በዚህም ምክንያት እርዳታው ለሚገባው ሳይሆን ለቪዲዮ እይታ ለሚመቸው ሰው የመስጠት የተዛባ አዝማሚያ እየተፈጠረ ነው። ስለሆነም ማኅበራዊ ሚዲያውን የተቆጣጠረውን የእይታ ማርኬቲንግ በጥንቃቄ መለየትና ከተራ ስሜታዊነት ወጥተን እውነተኛውን በጎነት ማገዝ የሁላችንም የሞራል ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።