tgindex
EdMap Community

EdMap, Powered by PiSpace Inc. A one-stop destination platform for Ethiopian students. For further information @contact_edmap Our website: 🌐 www.edmap.et

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
07:04
Постов за неделю
2
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ангНиКскиК
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 309
−8 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
1 553
22 постов
Вовлечённость
46,9%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всогО 22
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
403
1/48двое суток
461
1/72трое суток
498

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የቤልጂየም መንግስት የስኮላርሺፕ እድል ለኢትዮጵያውያን! ለኢትዮጵያ ተማሪዎችና ባለሙያዎች፤ በእርግጥም ሊያመልጣችሁ የማይገባ አሪፍ እድል ነው። የ2027-2028 የቤልጂየም መንግስት ስኮላርሺፕ በቤልጂየም ሀገር በልዩ ባለሙያነት የዲግሪ፣ የማስተርስ እና የሙያ ስልጠናዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ለመማር ያስችላል። ምን ምን ይሸፍናል? - የትራንስፖርት ወጪ - ወርሃዊ የኑሮ አበል - የትምህርት ክፍያ - የጤና እና የህይወት መድን - የቪዛ ወጪዎች - በቆይታ ጊዜ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ናት። የጥናት መስኮች: - ሰብአዊ መብቶች (Human Rights) - ዓለም አቀፍ እና የልማት ኢኮኖሚክስ (International & Development Economics) - ማይክሮ ፋይናንስ (Microfinance) - የህዝብ ጤና (Public Health) - የምግብ ዋስትና (Food Safety) - የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) - የአደጋ እና ስጋት አስተዳደር (Disaster & Risk Management) - ዲጂታል አቅርቦት ሰንሰለት (Digital Supply Chain) እና ሌሎች ተጨማሪ መስኮች የማመልከቻ መጨረሻ ቀን፡ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት (የቤልጂየም ሰዓት አቆጣጠር)። ሙሉ የትምህርት መስኮቹን፣ የማመልከቻ መስፈርቶችን፣ የሚጠየቁ ሰነዶችን እና የአመልካች አሰራር ሂደቱን አጠቃላይ መመሪያ አዘጋጅተንላችኋል። ሙሉውን ጽሁፍ በEdMap website ላይ ያንብቡ፡ https://www.edmap.et/belgium-government-scholarships-20272028/

  • Internship በጀርመን በቴክኖሎጂ፣ መረጃ አስተዳደር እና ዲጂታል ሥራዎች ላይ አለም አቀፍ የሥራ ልምድ ማግኘት ይፈልጋሉ? የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከኅዳር 2026 እስከ ሚያዝያ 2027 ባሉት 24 ሳምንታት ውስጥ በጀርመን በርሊን ከተማ የሚከናወን የኢንተርንሺፕ ዕድል አቅርቧል። ይህ የኢንተርንሺፕ የሚከተሉትን ተግባራዊ የሥራ ልምዶች ይሰጣል፦  • Information management and digital workplace technologies • Microsoft 365 and collaboration tools • Meeting and event support • AI-enabled workplace platforms • Documentation and reporting • IT and audiovisual technologies ጥቅማጥቅሞች፦  • የኑሮ አበል  • የምግብ ድጋፍ • የሕክምና እና የጉዳት ዋስትና (ኢንሹራንስ) • በታላቅ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ጠቃሚ የሥራ ልምድ የመስፈርቶች ማጠቃለያ፦ • ዕድሜዎ ቢያንስ 20 ዓመት የሆነ • ቢያንስ የሶስት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ያጠናቀቁ • የትምህርት ዝግጅትዎ በComputer Science, IT, Information Management, Data and Information Systems, ወይም ከእነዚህ ጋር በተያያዙ መስኮች የሆነ • እንግሊዝኛ ቋንቋን በጥሩ ሁኔታ መናገር የሚችሉ • - ማይክሮሶፍት 365 እና ዲጂታል የትብብር  መሣሪያዎችን(Collaboration platforms) ማወቅ የመመዝገቢያ የጊዜ ገደብ፦ ነሐሴ 15 ቀን 2026 ሙሉ መስፈርቶችን፣ ጥቅማጥቅሞችን፣ የመመዝገቢያ ሂደቱን እና ሌሎች ጠቃሚ ዝርዝሮችን ለማግኘት https://www.edmap.et/who-internship-2026-in-germany/

  • 🇸🇰 የአውሮፓ ስኮላርሺፕ ዕድል — እስከ €15,000 የገንዘብ ድጋፍ! 🇪🇺 በስሎቫኪያ (Slovakia) ታዋቂ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በBachelor's ወይም Master's ዲግሪ ለመማር ለምትፈልጉ አለምአቀፍ ተማሪዎች የተዘጋጀ ምርጥ ዕድል ነው። 💡 የስኮላርሺፑ ጥቅሞች፡- - አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፍ፡ እስከ €15,000 (በዓመት €5,000) ይሰጣል። - አውሮፓ መኖር፡ ወጪያቸው በጣም በርካሽና ምቹ በሆኑ የስሎቫኪያ ከተሞች መኖር። - Erasmus+ ዕድል፡ በፕሮግራሙ አማካኝነት ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ተጉዞ የመማር ዕድል። - ደረጃውን የጠበቀ ዲግሪ፡ በመላው አውሮፓ ህብረት (EU) ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት። 👥 ማነው ማመልከት የሚችለው? - የትኛም ሀገር ዜጋ የሆነ - ለባችለርስ (የመጀመሪያ ዲግሪ) ወይም ለማስተርስ ማመልከት የሚፈልግ። - የዕድሜ ገደብ የለውም! - የSAT ወይም SCIO ፈተና ውጤት ያለው/ያላት። 📅 የማመልከቻው ማጠቃለያ ቀን (Deadline): July 31, 2026 🔗 ሙሉ መረጃውን ለማንበብና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/slovakia-scholarships-20262027/

  • 24 июн.1 175312

    🌍 የአውሮፓ ህብረት የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም (European Union Volunteer Program 2026) ወጣቶች በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በሚገኙ የበጎ ፈቃድ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉ በሩን ከፍቷል። ይህ ፕሮግራም በተለይ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በማህበረሰብ ልማት፣ በባህል፣ በማህበራዊ ስራ እና በወጣቶች እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶችን ያካትታል። 💡 ፕሮግራሙ ምን ምን ነገሮችን ይሸፍናል? አብዛኛዎቹ እድሎች የሚከተሉትን ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ይሸፍናሉ፦ 🏠 የመኖሪያ ቤት እና ምግብ 🏥 የጤና መድን (Insurance) 🚌 የሀገር ውስጥ የመጓጓዣ ወጪዎች 💵 ለግል ወጪ የሚሆን የኪስ ገንዘብ (Pocket money) 🎓 ማን ተጠቃሚ ይሆናል? ተማሪ፣ ተመራቂ ወይም ሲቪዎን (CV) ማጠናከር እና አለምአቀፍ ትስስርዎን (Network) ማስፋት የሚፈልጉ ወጣት ባለሙያ ከሆኑ ይህ እድል ለእርስዎ ነው! - በአለምአቀፍ መድረክ ላይ አዳዲስ ክህሎቶችን ለመቅሰም ይህንን ወርቃማ አጋጣሚ አይለፉ። 📋 ስለ መስፈርቶቹ፣ ስለሚያገኟቸው ጥቅማጥቅሞች እና ስለ ማመልከቻው ሂደት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ሙሉ መመሪያውን በድረ-ገጻችን ያንብቡ፦ 🔗 https://www.edmap.et/eu-volunteer-program/

  • 4 мая1 518722

    🇯🇵 የጃፓን መንግስት የ2027 የመጀመሪያ ዲግሪ (Undergraduate) ነፃ ትምህርት ዕድል ጥሪ የጃፓን ትምህርት፣ ባህል፣ ስፖርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጃፓን በሚገኙ ታዋቂ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለመከታተል ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች የ2027 የትምህርት ዕድል ማመልከቻ መክፈቱን አስታውቋል። የስኮላርሺፑ ጥቅሞች፡ ✔️ ሙሉ የትምህርት ክፍያ፡ የማመልከቻ፣ የመግቢያ እና የትምህርት ክፍያዎችን ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል:: ✔️ ወርሃዊ ድጎማ፡ ለተማሪዎች ወርሃዊ 117,000 የጃፓን የን (¥) የኪስ ክፍያ ይሰጣል። ✔️ የአየር መንገድ ትኬት፡ የደርሶ መልስ የኢኮኖሚ ክላስ የአየር መንገድ ትኬት ያካትታል። ✔️ የቋንቋ ስልጠና፡ መደበኛ ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ ዓመት የሚቆይ ከፍተኛ የጃፓንኛ ቋንቋ ስልጠና ይሰጣል። ይህ ዕድል ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ትምህርት እንዲቀስሙ ከመድረጉም በላይ፣ በጃፓን የሥራ ዕድሎችን ለማግኘትና ባህላዊ ልምዶችን ለመቅሰም ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው። 🔗 ሙሉ መረጃዎችን፣ መስፈርቶችን እና የማመልከቻ ቅጾችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/mext-undergraduate-scholarship-2027-in-japan-fully-funded/ ማሳሰቢያ፦ ማመልከቻው የሚከናወነው በኢትዮጵያ በሚገኘው የጃፓን ኤምባሲ በኩል መሆኑን ተገንዝበው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

  • 🇯🇵የጃፓን መንግስት የ2027 የነፃ ትምህርት ዕድል (Master’s እና PhD ፕሮግራሞች ) የጃፓን መንግስት ለኢንተርናሽናል ተማሪዎች የሚሰጠውንና ሙሉ ወጪን የሚሸፍነውን ታዋቂ የነፃ ትምህርት ዕድል ይፋ አድርጓል። ይህ የትምህርት ዕድል በጃፓን በሚገኙ የሁለተኛ ዲግሪ (Master’s) እና የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች የቀረበ ነው። የስኮላርሺፑ ጥቅሞች፡ ✔️ ሙሉ የትምህርት ክፍያ (Full Tuition Coverage) ✔️ ወርሃዊ የኑሮ ድጎማ (Monthly Stipend) ✔️ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት (Travel Expenses) ✔️ በጃፓን በታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የመማርና የምርምር ዕድል ይህ የትምህርት ዕድል በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው ትምህርት ለመቅሰም እና በላቁ የምርምር ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ትልቅ አጋጣሚ ነው። 🔗 መስፈርቶችን ለማንበብ እና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/mext-scholarship-2027-in-japan-fully-funded/ ማሳሰቢያ፦ ማመልከቻው የሚከናወነው በኢትዮጵያ በሚገኘው የጃፓን ኤምባሲ በኩል መሆኑን ተገንዝበው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

  • 🇪🇪 የኢስቶኒያ (Estonia) መንግስት ነፃ የትምህርት ዕድል 2026 አውሮፓ መማር ወይም ምርምር መስራት ለሚፈልጉ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች አሪፍ አጋጣሚ መጥቷል! የኢስቶኒያ መንግስት ለተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ማመልከቻ መቀበል ጀምሯል። ምን ምን ዕድሎች አሉ? ✔️ የክረምት እና የበጋ አጫጭር ስልጠናዎች (Summer & Winter School) - ክፍት ነው! ✔️ ለተመራማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጡ ግራንቶች - ክፍት ነው! ✔️ ለዲግሪ እና ለኤክስቼንጅ ፕሮግራሞች - በቅርቡ ይከፈታል ጥቅማ ጥቅሞቹ፦ • እስከ €700 የሚደርስ የትምህርት ክፍያ ሽፋን • የመኖሪያ ቤት ድጋፍ • በየወሩ እስከ €660የሚደርስ የኪስ ወጪ (Stipend) ⏰ የማመልከቻ ማብቂያ ቀን፦ May 1, 2026 – ለአሁኑ ክፍት ለሆኑት ፕሮግራሞች 🔗 ዝርዝር መረጃዎችን ለማንበብና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/estonia-government-scholarships-2026/ ለጓደኞቻችሁ አጋሩ

  • እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!

  • 26 мар.1 929228

    🇷🇴 የሮማኒያ መንግስት ነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) ለ 2026! 🎓 የሮማኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሉንም ወጪ የሚችል (Fully Funded) የትምህርት ዕድል ለዓለም አቀፍ ተማሪዎች ክፍት አድርጓል። ✨ ጥቅማጥቅሞቹ ✔️ ሙሉ የትምህርት ክፍያ (Tuition Fee) አይጠየቅም። ✔️ ነፃ የመኝታ አገልግሎት። ✔️ በየወሩ የሚሰጥ የኪስ ገንዘብ (Stipend)። ✔️ የሮማኒያ ቋንቋን በነፃ የሚማሩበት የ 1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ። 📚 የሚሰጥባቸው የትምህርት ደረጃዎች፦ - የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's) - ሁለተኛ ዲግሪ (Master's) - የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) 👉 የማመልከቻ ማብቂያ ቀን፦ መጋቢት 22፣ 2018 ዓ.ም (March 31, 2026) ሙሉ መረጃውን ለማንበብና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/romania-scholarship26/

  • ዒድ ሙባረክ! 🌙 EdMap ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች መልካም የዒድ-አልፈጥር በዓል እንዲሆን ይመኛል!

  • 5 мар.1 867446

    🇦🇺 የአውስትራሊያ ነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) ለኢትዮጵያውያን! የ2027 የአውስትራሊያ መንግስት ሙሉ ወጪን የሚሸፍን (Fully Funded) የትምህርት ዕድል አመልካቾችን መቀበል ጀምሯል። ይህ ዕድል በተለይ ለኢትዮጵያውያን ክፍት በመሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው የአውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor’s) ወይም ማስተርስ (Master’s) ለመማር ወርቃማ አጋጣሚ ነው። ጥቅማጥቅሞቹ ምንድን ናቸው? 💰 የአውስትራሊያ መንግስት የሚከተሉትን ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፦ - ሙሉ የትምህርት ክፍያ - የደርሶ መልስ የአየር መንገድ ትኬት - ወርሃዊ የኪስ ወጪ (Living allowance) - የጤና መድን (Health insurance) - ለጥናትና ምርምር የሚያስፈልጉ ድጋፎች 📅 የማመልከቻው ማብቂያ ቀን: ሚያዝያ 22፣ 2018 ዓ.ም (April 30, 2026) ጊዜው ሳይረፍድ አሁኑኑ መረጃዎችን በማንበብ ማመልከት ትችላላችሁ። ዕድሉ እንዳያመልጣችሁ! 🔗 ዝርዝር መረጃውን ለማግኘትና ለማመልከት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://www.edmap.et/auscholarships-2027/ እንደተለመደው ለጓደኞቻችሁ ሼር ማድረጋችሁን እንዳትረሱ! 🎓

  • 2 мар.1 24131

    ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል! እንኳን ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል ቀን በሰላም፣ በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ !! " ዓድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት መቼ ተነሱና የወዳደቁት ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች " - ጂጂ የዓድዋ ድል ከባርነት ነፃነትን፣ ከመለያየት አንድነትን፣ እና ከመገዛት ክብርን የመረጡ ህዝቦች የማይበገር መንፈስ ማረጋገጫ ነው። መልካም የድል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ !!

  • 🇮🇩የኢንዶኔዥያ መንግስት (KNB) የ2026 ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የትምህርት ዕድል (Fully Funded Scholarship) ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ክፍት አድርጓል። ይህ ዕድል ለBachelor’s፣ ለMaster’s እና ለPhD ፈላጊዎች የሚሆን ሲሆን፤ በደቡብ ምስራቅ እስያ ምርጥ በሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የመማር ዕድል ይሰጣል። ✨ ጥቅማጥቅሞቹ ምን ምን ናቸው? ✔️ የትምህርት ቤት ክፍያ (Full Tuition Fee) ✔️ የወርሃዊ የኪስ ድጎማ (Monthly Allowance) ✔️ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት ✔️ የጤና መድን (Insurance) ✔️ የ1 አመት የኢንዶኔዥያ ቋንቋ ስልጠና (BIPA) ✔️ የምርምር እና የመጽሐፍ አበል 📚 የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች፦ ኢንጂነሪንግ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ ህክምና፣ ማህበራዊ ሳይንስ፣ አርክቴክቸር፣ ማኔጅመንት እና ሌሎችም በርካታ ዘርፎች ተካተዋል። 🗓 የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: መጋቢት 22፣ 2018 ዓ.ም (March 31, 2026) ኢንዶኔዥያ ባላት ውብ ተፈጥሮ እና ጥራት ባለው ትምህርት ትታወቃለች፤ ይህን ወርቃማ ዕድል እንዳያመልጣችሁ! 👉 ሙሉ መረጃውን ለማንበብ እና ለማመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ 🔗 https://www.edmap.et/knb-scholarship/ ለጓደኞቻችሁ ሟር ማድረጉን እንዳትረሱ! ✈️📚

  • 31 янв.2 110533

    ✈️ 🇹🇷 የቱርክ መንግስት "ኑ ተማሩ፣ ሙሉ ወጪ በእኔ ነው!" እያለ ነው። የ 2026 የ Türkiye Bursları ስኮላርሺፕ በይፋ ተከፍቷል! 🎓 Programs - ለዲግሪ (Undergraduate) - ለማስተርስ - እና ለPhD ተማሪዎች። ጥቅሞች - ሙሉ የትምህርት ወጪ - ዶርም፣ - ወርሃዊ ክፍያ - የቲኬት ወጪ በተጨማሪም የቱርክን ቋንቋ እና ባህል የምታውቁበት ትልቅ አጋጣሚ! 📍 ጊዜው ሳይረፍድ አሁኑኑ መረጃውን አይታችሁ መዘጋጀት ጀምሩ። ⏰ Deadline: የካቲት 13፣ 2018 (Feb 20, 2026) ሙሉ ዝርዝሩን እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል እዚህ ጋር ይመልከቱ፦ 🔗https://www.edmap.et/turkiye-scholarships-2026-turkiye-burslari-fully-funded/

  • 2 янв.2 429431

    ጉዞ ወደ ሲንጋፖር ? የNUS Young Fellowship ዕድል ክፍት ሆኗል! 🇸🇬 በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በሆነው National University of Singapore (NUS) ውስጥ ለአንድ ወር የሚቆይ የFellowship ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ዋናው ነገር ደግሞ IELTS/TOEFL አይጠይቅም፣ የማመልከቻ ክፍያም (Application Fee) የለበትም! ✨ የፕሮግራሙ ጥቅሞች ምንድን ናቸው? 🏨 ነፃ መኝታ: ሲንጋፖር በሚቆዩበት ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ነፃ መኝታ ይቀርባል። 💵 የኪስ ገንዘብ: ፕሮግራሙን ሲጨርሱ የ 500 SGD (የሲንጋፖር ዶላር) የጉዞ ድጎማ ይሰጥዎታል። 🤖 AI & Research: ስለ Artificial Intelligence እና ስለ ምርምር ከታዋቂ ፕሮፌሰሮች ጋር አብረው ይማራሉ። 🏙 ጉብኝት: እንደ Gardens by the Bay ያሉ የሲንጋፖር አስደናቂ ቦታዎችን የመጎብኘት ዕድል ይኖራችኋል። ማን ማመልከት ይችላል? - በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ (Major) ያለ የ3ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ። - ጥሩ የትምህርት ውጤት ያለው። - ከትምህርት ውጪ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች (Extra-curricular activities) ላይ የሚሳተፍ። 📅 ወሳኝ ቀናት: የቆይታ ጊዜ: ከJune 22 እስከ July 24 ቀን 2026 (በአካል እና በኦንላይን)። የማመልከቻ መጨረሻ: መጋቢት 15 ቀን 2026 (March 15, 2026)። 👇 ሙሉ መረጃውን እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ለማወቅ ይህንን ሊንክ ይጫኑ: https://www.edmap.et/the-nus-2026/

  • 19 док.1 896826

    🇹🇼 ታይዋን ICDF Scholarship- ሙሉ ወጪ የተሸፈነ የትምህርት ዕድል የታይዋን ICDF Scholarship ምዝገባ መጀመሩን አብስሯል። ይህ ስኮላርሺፕ በታይዋን በሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በማስተርስ (Master’s) እና በዶክትሬት (PhD) ደረጃ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ለሚፈልጉ አመልካቾች ሙሉ ወጪን የሚሸፍን ዕድል ይሰጣል። ተመራጭ የሚያደርጉት፦ 🔹 ሙሉ ወጪ የተሸፈነ፦ ትምህርት ቤት፣ መኖሪያ፣ የጤና ኢንሹራንስ እና የመጽሐፍት ወጪዎችን ያካትታል። 🔹 የጉዞ ወጪ፦ የደርሶ መልስ አውሮፕላን ትኬት ይቀርባል። 🔹 ወርሃዊ ድጎማ (Stipend)፦ ለኑሮ ወጪ የሚሆን እስከ 20,000 NT$ በየወሩ ይከፈላል። 🔹 በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው 32 በእንግሊዝኛ ቋንቋ በሚሰጡ ፕሮግራሞች (እንደ Engineering, MBA, Public Health, ICT) መማር ያስችላል። የማመልከቻ መስፈርቶች፦ - የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው/ያላት። - የሚመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠይቁትን የትምህርት ዝግጅት የሚያሟላ። የማመልከቻ ማብቂያ ቀን፦ March 15, 2026 የአመላለከቱን ሂደት፣ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን እና የትምህርት አይነቶችን ዝርዝር ለማግኘት ድህረ-ገጻችንን ይጎብኙ፦ 🔗 https://www.edmap.et/taiwan-scholarship-2026/

  • 🇭🇺የEdMap ቤተሰቦች፣ እውነተኛ እና ነጻ የትምህርት ዕድሎችን ብቻ እንደምናቀርብ እያስታወስን፣ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ፣ በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅና ሙሉ በሙሉ በገንዘብ ከተደገፉ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የስቲፐንዲየም ሀንጋሪኩም ስኮላርሺፕ በይፋ ተከፍቷል! ✨ የስኮላርሺፑ ጥቅሞች - ከክፍያ ነጻ ትምህርት። - ወርሃዊ ድጎማ (Monthly Stipend): - ለመጀመሪያ ዲግሪ እና ማስተርስ ተማሪዎች ወርሃዊ 43,700 የሀንጋሪ ፎሪንት (HUF)። - ለዶክትሬት (PhD) ተማሪዎች እስከ 180,000 HUF ወርሃዊ ድጎማ። - የመኝታ ክፍል (Dorm) የማግኘት ዕድል ወይም ለመኖሪያ ቤት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ። - ሙሉ የጤና መድን 🎓 የፕሮግራም አይነቶች በዚህ ስኮላርሺፕ የሚከተሉትን የትምህርት ደረጃዎች መከታተል ይቻላል፦ 🎓የመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's Degrees) 🎓ሁለተኛ ዲግሪ (Master's Degrees) 🎓አንድ-ደረጃ ማስተርስ ፕሮግራሞች (One-tier Master’s Programs) 🎓የዶክትሬት ፕሮግራሞች (PhD Programs) 🎓ከዲግሪ ውጪ የሆኑና የቅድመ ዝግጅት ፕሮግራሞች (Non-degree & Preparatory Programs) አብዛኛው የትምህርት ክፍሎች የሚሰጡት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሆን፣ ተማሪዎች የ1 ዓመት የሀንጋሪ ቋንቋ የቅድመ ዝግጅት ኮርስ የማግኘት ዕድልም አላቸው። ✔️ ኢትዮጵያውያን ለማመልከት ብቁ ናቸው! 📝 ለበለጠ መረጃ እና ማመልከቻውን ለማስገባት የሚያስችል ዝርዝር አቅጣጫ በሚከተለው ሊንክ ያግኙ፦ https://www.edmap.et/sh-scholarship/ 📅 Deadline: January 15, 2025 ይህን ታላቅ እድል እንዳያመልጥዎ! ለሌሎችም በማጋራት መልካም ነገርን ያካፍሉ!

  • 🎓 ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የInternship ዕድል! በጀርመን ክረምቱን በጀርመን የዓለም ደረጃ ባላቸው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በመስራት ለማሳለፍ ይፈልጋሉ? ይህ Summer Internship Program በሳይንስ እና ምህንድስና የትምህርት ዘርፎች ለሚማሩ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ የስራ ዕድል ያቀርባል! ማመልከት የሚችሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች: በEngineering ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ የምድር ሳይንስ (Earth Science) ወይም ተዛማጅ መስኮች ተማሪዎች። ✅ ፕሮግራሙ የሚከተሉትን ይሸፍናል - ወርሃዊ ድጎማ (Stipend) - የጉዞ ወጪ ድጋፍ - የመኖሪያ ቤት ድጋፍ (Housing assistance) Note: IELTS ማስረጃ አያስፈልግም! ይህ ዓለም አቀፍ ልምድ ለማግኘት፣ CVዎን ለማጎልበት እና የአካዳሚክ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ወርቃማ አጋጣሚ ነው። 🕒 ከ Nov 30, 2025 በፊት ያመልክቱ 👉 ሙሉ መረጃውን እና ለማመልከት: https://www.edmap.et/summer-internship-in-germany/

  • 21 окт.2 150735

    🇨🇳 የቻይናኛ ቋንቋ ትምህርት እና ሙሉ ወጪ የተሸፈነ ጉዞ ወደ ቻይና! ✈️ ዓለምን ማየት፣ አዲስ ባሕል ማወቅ እና ዘመናዊ ሳይንስን ከቻይና መማር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ይህን ዕድል እንዳያመልጥዎ! 🌍 የUSTC የክረምት ካምፕ በቻይና 📅 : December 22–31, 2025 ይህ ፕሮግራም ከተማሪ ካምፕ በላይ ነው። የቻይናን ባህል፣ ቋንቋ፣ ሳይንስ እና ፈጠራ ለመጎብኘት ለሚፈልጉ የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ነው። ፕሮግራሙ የሚከተሉትን ይሸፍናል፦ - የአውሮፕላን ትኬት (Airfare) - መስተንግዶ (Accommodation) - የሕክምና መድን (Medical Insurance) - የጉዞ አበል (Travel Stipend) - የቻይና ቋንቋ ትምህርቶች። - የአካባቢ ባህል ጉብኝቶች እና የላብራቶሪ ጉብኝቶች። ✅ ማመልከት የሚችሉ: - የመጀመሪያ ወይም የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች - በቅርቡ የተመረቁ 📄 የሚያስፈልጉ ሰነዶች - ፎቶ - ፓስፖርት (Valid Passport) - ሲቪ/ሪዙሜ (CV/Resume) - የትምህርት ውጤት ማስረጃዎች (Academic Transcripts) 🕒 ከ Nov 20, 2025 በፊት ያመልክቱ ቻይናን በተለየ ሁኔታ የመጎብኘት ዕድልዎን እንዳያመልጥዎ! 👉 ሙሉ መረጃውን እና ለማመልከት: https://www.edmap.et/winter-camp-2026-in-china/

  • 🇩🇪 ዕድሉን ተጠቀሙ ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የጀርመን ጉዞ! በማኅበረሰብዎ ውስጥ በዘላቂ ልማት ወይም በአካባቢ ጥበቃ ሼል ላይ የምትሳተፉ ወጣት ለውጥ አምጪ ነሽ/ነህ? ተፅዕኖሽን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለማድረስ ታላቅ ዕድል ይኸው! 🌍 የHSC ወጣት አምባሳደር ፕሮግራም 2026 የሃምበርግ የዘላቂ ልማት ጉባኤ የወጣት አምባሳደር ፕሮግራም ለ2026 ተሳታፊዎችን መቀበል ጀምሯል። ጉባኤው የሚካሄደው ከሰኔ 29-30, 2026 በጀርመን ሃምበርግ ከተማ ነው። 🔹 ምን ይጠብቅሻል/ሃል? - ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የጉዞና የመኝታ ወጪ - ምንም ዓይነት የማመልከቻ ወይም የተሳትፎ ክፍያ የለም - በተሳታፊነት ወይም ተናጋሪነት የመገኘት ዕድል - ከዓለም አቀፍ መሪዎች እና ወጣት ፈጣሪዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር 🔹 ማመልከት የሚችሉ - ዕድሜ: ከ18 እስከ 30 - በማደግ ላይ ካሉ ኢኮኖሚዎች የመጡ ማስታወሻ: ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ካሉ ኢኮኖሚዎች ዝርዝር ውስጥ ስለምትገኝ፣ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ፕሮግራም ማመልከት ይችላሉ። የማመልከቻ መጨረሻ ቀን፡ October 15, 2025 📩 ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት: https://www.edmap.et/youth-amb-program-2026/