El-shaddie🔥
Статистика=> እየሱስ ዛሬም ነገም እስከ ዘላለም ያው ነው :: እዚህ Channel ላይ እየሱስ ክርስቶስ ይነሳል ከ እርሱ ውጪ ሌላ ርዕስ ስለሌለን !!!
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 21
- 1/48двое суток
- 24
- 1/72трое суток
- 25
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የማቴዎስ ወንጌል ጥናት ክፍል 66 የማቴዎስ ወንጌል 11:7-11 "ታላቅነት" በአገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ @heavenarmyy #elsabaothchurch
ተለቋል!! https://youtu.be/rc3jGLQavt8
የማቴዎስ ወንጌል ጥናት ክፍል 65 የማቴዎስ ወንጌል 11:1-6 "እንዳትሰናከሉ ተጠንቀቁ!" በአገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ @heavenarmyy #elsabaothchurch
ብቸኝነት አይሰማኝም... ዮሐንስ 14:16 NASV እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ብቻችሁን መሆን የሚከብዳችሁ አላችሁ? ወይ ደግሞ ጓደኛ ስለሌላችሁ በጣም ባዶነት የሚሰማችሁ...? አዎ ከባድ ሊሆን ይችላል። ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ ስለ መለየት መናገር ሲጀምር ይሄ ስሜት ነበር የከበባቸው። በጣም የሚወዱት እና ሁሉን ትተው የተከተሉት ጌታ በስጋ ሊለያቸው ነበር። ገና መናገር ሲጀምር ቆዘሙ። እርሱ ግን ታላቅ የምስራች ነገራቸው። ሌላ ረዳት ፥ አጽናኝ የሆነ ቅዱስ መንፈስ ከእነርሱ ጋር ብቻ ሳይሆን በእነርሱ ውስጥ ሊሆን። እና ለብቸኝነት መፍትሄው ይሄ ነው። እናንተ ይሄን መንፈስ ከተቀበሉ በኋላ እንደ ምስኪን እና እንደ ብቸኛ መሆን አልታየባቸውን። እንደ አንበሳ በድፍረት ወንጌል ሰበኩ። አማኝ ብቸኝነት ከተሰማው የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅነትን በሚገባ አልተለማመደም ማለት ነው። ሰው እና መንፈስ ቅዱስ አብረው የኖሩ ሰው እንዴት ብቸኝነት ይሰማዋል? እንደውም ከብቸኝነት ለመዳን ከእርሱ ጋር ለብቻ መሆንን መለማመድ ነው መድሃኒቱ!! ብቸኝነት አይሰማኝም ብሎ የዘመረ... @heavenarmyy #elsabaothchurch
ጸሎት ከከበደህ እንዲህ አድርግ! እንግዲህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ፤ ላለው ይጨመርለታልና፤ ከሌለው ሁሉ ግን ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።” ሉቃስ 8:18 ብዙ ጊዜ መልካም የሆኑ መንፈሳዊ ልምምዶቻቸውን ያቆሙ ሰዎች ያጋጥሙኛል። አሁን ከምታነቡት እንኳ ብዙዎቻችሁ ይህ ይመለከታችኋል። እናም ጸሎት ፣ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ፣ ህብረት ማድረግ ...ወዘተ ካቆሙ በኋላ ቆይተው እንደ ትናንት መሆን ይሳናቸዋል። መጸለይ ዳገት ይሆናል ፣ የቃል ግልጠት ይጠፋል። ከዚህ የተነሳ ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ያቆማሉ። ጌታችን ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ አስረድቶናል። መንፈሳዊ አለም ላይ አንድ ነገር ተሞልቶ ታሽጎ አይቀመጥም። ወይ 'የሞላ ይሄዳል ወይ ደግሞ የጎደለ ይሄዳል። ልምምዳችሁን ካቆማችሁ ይወሰድባችኋል። ጥቂት መስፈርያ ይዛችሁም ከተገኛችሁ ጥቂት ይሰጣችኋል። ከእንደዚህ አይነት ድካም መውጣት ትፈልጋላችሁ? ዛሬ ባይጥማችሁም ተምበርከኩ ፥ ቃሉን ክፈቱ ...ነገም ጨምሩ በእርግጠኛነት ግን ነገ እንደ ዛሬ አይሆንም። ከነገ ወድያ ደግሞ እንደ ነገ አይሆንም። ለሚጸልይ ይበልጥ የመጸለይ አቅም ይሰጠዋል። ስለዚህ ይበልጥ ለመጸለይ መፍትሄው መጸለይ ነው። ቃሉን ለሚያጠና ይበልጥ የማጥናት ኃይል ይሰጠዋል። ቃሉን ለሚያሰላስል ይበልጥ መረዳት ይሰጠዋል። ለሚሰማ ይበልጥ ምስጢሩ ይነገረዋል። ተቃራኒውም እውነት ነው። ካልጸለይክ ይበልጥ መጸለይ የማትችል ትሆናለህ። ድሮ እንኳን ሚደነቅ ልምምድ ያለህ ቢሆን ምንም ልምምድ እንደሌለው ትሆናለህ። መፍትሄው ውስብስብ አይደለም። አሁኑኑ ጀምር!! አገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ #elsabaothchurch @heavenarmyy
እምነት!? የምትለምነው ነገር ከሰጪው ከበለጠብህ ጸሎትህ የሚነዳው በእምነት ሳይሆን በስጋ ምኞት ነው። እውነተኛ እምነት ፍቅርን ይገልጣል። አብርሃምን የእምነት አባት የምንለው ሰጪውን ከይስሃቅ በላይ ስለሚወደው ነው። እምነት መሰሉ የስጋ ምኞት ግን አላማው እግዚአብሔርን መጠቀም ነው። አገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ #elsabaothchurch @heavenarmyy
መጽደቅ ይቻላል! #መንፈሳዊ_ትራክት ስለዚህ አስደናቂ የጽድቅ ጸጋ ማወቅ ለሚገባው ሰው ላኩለት!! #elsabaothchurch @heavenarmyy
ደካሞች ሆይ...ኑ!! “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” — ማቴዎስ 11፥28 ወደ ክርስቶስ ሰዎች እንዳይመጡ እና እንዳያርፉ ሴይጣን የሚመክራቸው አንዱ እና ትልቁ ውሸት "ኢየሱስ ጋ ተስተካክለህ ሂድ" የሚል ነው። ይህ ትልቅ የጠላት ተንኮል ነው። ምክንያቱም ሁለት መሠረታዊ ችግር ያስከትላል። 1. የማናሸንፈው ጋር ትግል ገጥመን ዘመናችንን እንድንጨርስ ያደርገናል። እስካሁን ታግለህ ያላሸነፍከውን መቼ ታሸንፋለህ? በራስህ ትግል ከጀመርክ መቼም አታሸንፍም። ኃጢአትን ማሸነፍ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ብቻ ስለሆነ ወደ እርሱ መምጣት ያለብን አዳኝ እንደሆነ አምነን እስከነ ድካማችን ነው። ማሳረፍ የእርሱ ጸጋ ስራ ነው። ለኢየሱስ በጣም ቆሽሾ የሚባል የሚከብደው በደል የለም። 2. በመታበይ ጸጋን አለመቀበል። በራስህ ስትታገል እችላለሁ እያልክ ነው። በራስህ ጉልበት የተመካህ ነው። ይህ ደግሞ መታበይ ይባላል። ትዕቢት ደግሞ የጸጋ ጠላት ነው። እግዚአብሔር ጸጋን የሚሰጠው ለትሁታን ነውና። “ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።” — ያዕቆብ 4፥6 #elsabaothchurch @heavenarmyy
видео или голосовое, без подписи
If anyone wants this you can dm me
የመስቀሉ ቃል ፍሬህይወት አበባው NEW ALBUM | 3 MB | @Spiritual_s0ngs | @Spiritual_s0ngs ◈◈ JOIN US ◈◈
"The Lord is close to the brokenhearted; and those who are crushed in spirit he saves." Psalm 34:18 📖. 🙏| Share The Word Of God. 🙏| Daily Bible Quotes, Songs And Motivation. in English, Afaan Oromoo and Amharic ✝️Sharing Jesus everyday https://t.me/zioneba
ሐጢያት ከባዱ ሸክም ሲሆን የእግዚአብሔር ይቅርታና ምህረት ግን ነፃ መውጫ መንገዳችን ነው። ምንም አይነት ድካም ውስጥ ብትሆኑ እንኳን ቤተክርስቲያን አትቅሩ። ሰናይ ሰንበት 🤌🥰
“ በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም .... ሆሴዕ 7፥14 በመኝታ (በስውር) ሆኖ ማልቀስ ቀላል እና ተፈጥሯዊ ነገር ነው ፤ በእግዚአብሔር ፊት ችግርን ማስቀመጥና አግዘኝ ማለት ግን መንፈሳዊነት ነው። መዝ 88:1-2
መሬት ላይ የተኛ ሰው ወድቃለው ብሎ እንደማይሰጋ እግዚአብሔር የተደገፈ ሰውም እንዲሁ ነው...... ከተደገፋቹ ላይቀር እርሱ ላይ ከታመናችሁም ላይቀር እግዚአብሔርን 🥰😊
🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼 በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። መዝሙር 65፥11
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በርባን ተፈታ ከእስር በምህረት በደም በሀጥያት ከጨቀየበት የኔን የእርሱን የሁላችንን ኢየሱስ ወስዶት ደዌአችንን እኔ ተፈታሁ የሱስ ተክቶኝ በደሌን ወስዶ ሞቴን ሞቶልኝ እንዴት በማይባል ግሩም ፍቅር ተቀየረ ውርደት በክብር
ከፍርሀቶች ሁሉ ውዱ ፍርሀት ከአባታቹ ጋር ያላቹ ህብረት ሲቀዘቅዝ እና መፀለይ ሲያቅታቹ የሚሰማቹ ፍርሃት ነው፤ ጌታ በሌለበት መዋል ስታበዙ፣ ከፍቃዱ መስመር ስትርቁ የሚሰማቹን ፍርሃት ውደዱት።