ኢትዮ ካቶሊክ🇻🇦
Статистикаሰላም ካቶሊኮች እንኳን ደና መጡ✝️። ➾የካቶልክ መዝሙሮችን ➾ካቶሊከዊ ትምህርቶችን ➾የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ➾ስለ ካቶሊክ የተለያዩ ነገሮችን ምታገኙባት ቻናል ነዉ።
- Последний пост
- 4 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 489
- 1/48двое суток
- 560
- 1/72трое суток
- 604
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
መዝሙረ ዳዊት 8 : 2 አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ ምን ያህል ገናና ነው፥ ክብርህን በሰማዮች ላይ የምታኖር። @eth_Catholic @eth_Catholic
🙏🤲
የድሮ እኔነቴን
በደመና ተራመደ በደመናት ተራመደ : በእሳት አምድ ሰረገላ በሃይል መጣ : በዙሪዬ ክብሩ ሞላ ሠንሠለቴን በጣጠሰው : ጠላቴንም ስሬ ጣለ ያለ የሚኖር የነበረ : እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አለ በምስጋና ሠረገላ የሚቀመጥ በአምልኮ የሚመጣ የሚገለጥ አለ አለ እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ሊያተልቀኝ እየሰራ / ድል ሊያወርሰኝ እየሰራ የማንሰውን አከበረኝ አዘጋጀኝ ለሱ ስራ መሸነፌን አሸንፎ ፅኑ አረገኝ እንዳልፈራ በነገሬ በጉዳዬ እግዚአብሔር ቀድሞ ወጣ ተዋግቶልኝ ተሻምቶልኝ ድሉን ለኔ ይዞ መጣ ታማኝ አምላክ የታመነ እንደ ቃሉ ያደረገ ከኔ ጋር ነው ይሄ ጌታ ያስጨነቀኝ እየረታ/ ጠላቴንም እየመታ ተስፍ ባጣ በሃጥያቴ ፣ በጠላቴ ሴራ ብወድቅ ከግፍ ሸንጎ የሞት ፅዋ ሊፈርዱብኝ ስጠባበቅ የኔ ነገር በቃ አበቃ አለቀ ስል አከተመ እግዚአብሔር ጠበቃዬ ፣ በማዳኑ ለእኔ ቆመ በምህረቱ እየቀደመ አለቀ ስል ያስጀመረ አለ እግዚአብሔር ከኔ ጋራ በህይወቴ እየሠራ /2/ በደመናት ተራመደ …. @eth_Catholic @eth_Catholic
→→ ካቶሊክ እና ካቶሊካዊነት →→ ካቶሊክ ማለት ምን ማለት ነው? ካቶሊክ የሚለው ቃል የተገኘው ካቶሊኮስ (Catholicos) ወይም ካቶሊኪስሞስ (Catholikismos) ከሚሉት የግሪክ ቃላት ነው፡፡ ትርጓሜውም ሁሉንም የሚያካትት፣ ሁሉንም ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባና የሁሉም የሆነ ማለት ነው፡፡ ወይም ሁሉንም የሚያካትት ማኅበረሰብ እንደማለት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው Universal or according to the whole በሚል መልክ ይተረጐማል፡፡ →→ ካቶሊክ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው ማን ነው? ካቶሊክ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግናጢዮስ ነው፡፡ ካቶሊክ የሚለው ቃል የተጠቀመውም በ107 ዓ.ም. ስሚርና (በዛሪዪቱ ቱርክ) ውስጥ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በጻፈው መልእክቱ ውስጥ ነው፡፡ ቅዱስ ኢግናጢዮስ በዚህ መልእክቱ ክርስቲያኖች ከጳጳሳቸው ጋር ምን ዓይነት ግንኙነትና ወዳጅነት ሊኖራቸው እንደሚገባቸው ይመክራል፡፡ ሲመክራቸውም “ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች፤ እንደዚሁም ጳጳስ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ሕዝቡ መገኘት አለበት” ብሎአል፡፡ ቅዱስ ኢግናጢዮስ “ኢየሱስ ክርስቶስ ባለበት ስፍራ ሁሉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አለች” ማለቱ “ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ነው፤ በቦታ፣ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በሕዝብ የተወሰነ አይደለም፤ ሁሉንም ይቀበላል፤ ሁሉም በእርሱ ዘንድ ቦታ አለው፡፡ በአጠቃላይ ለሁሉም የተከፈተ በር አለው” እንደማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ቤተ ክርስቲያንም በሁሉም ስፍራ የምትገኝ፣ ሁሉንም የምታካትት፣ በርዋን ከፍታ ሁሉንም የምትቀበል እንደማለት ነው፡፡ → → ቅዱስ ኢግናጢዮስ ካቶሊክ የሚለው ቃል እንዲጠቀም ምክንያት የሆነው ምንድን ነው? ቅዱስ ኢግናጢዮስ ካቶሊክ የሚለው ቃል እንዲጠቀም ምክንያት የሆነው ወይም ካቶሊክ የሚለው ፅንሰ ሐሳብ እንዲፈጠር ምክንያት የሆነው ከዚያ በፊት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የነበረውን የሰዎች የአኗኗር ሁኔታ ነው፡፡ ይህም የአይሁድ ማኅበረሰብ (እስራኤላውያን) ዝግ ማኅበረሰብ ነበር፡፡ ካቶሊክ ብሎ ቃሉ ሲጠቀም ግን የተከፈተ (ለሁሉም ክፍት የሆነ) እንደማለቱ ነው፡፡ አይሁዳውያን ከሌላ ወገን በትዳር፣ በአምልኮና በማኅበራዊ ሕይወት ሳይተሳሰሩ እርስ በርሳቸው ብቻ ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ሕይወታቸውን አጠናክረው መኖርን የሚመርጡ ነበሩ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርቱና በተግባሩ ይህንን የአይሁድ ማኅበረሰብ እንዲከፈትና ሌላውንም እንዲያካትት አደረገው፡፡ ለምሳሌ ከአይሁድ ማኅበረሰብ ውጭ የሆኑትን በመቀበል፣ በመፈውስና እንዲሁም በማኅበረሰቡ ውስጥ ክብርና ቦታ እንዲኖራቸው ማድረጉ ተጠቃሽ ነው፡፡ ቀጥሎም ከጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ ሐዋርያት በተቀበሉት የጌታ ትእዛዝ መሠረት(ማቴ 28፡19-20) በዓለም በሁሉም አቅጣጫ በመሔድ፣ ሁሉንም ሕዝብ የሚያካትት፣ ለሁሉም የተከፈተና ሁሉንም የሚያቅፍ የክርስቲያን ቤተሰብ አስፋፉ፡፡ ካቶሊካዊነትም እየተቀጣጠለ ሔደ፡፡ →→ የእስክንድርያው ቅዱስ ቄርሎስ “ካቶሊካዊት” ማለቱ ምን ማለት ነው? በአራተኛውና በአምስተኛው ክፍለ ዘመን (ከ376 እስከ 444 ዓ.ም.) የኖረው፣ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው፣ የነገረ መለኮት ሊቅ እና የቤተ ክርስቲያን ዶክተር በሚል የሚታወቀው የእስክንድርያው ቅዱስ ቄርሎስ በሚያስተምርበትና በሚጽፍበት ጊዜ ካቶሊክ የሚለው ቃል ተጠቅሞአል፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ በጻፈው ሦስተኛው መልእክቱ ላይ “ካቶሊክ እና ሐዋርያዊት” በሚል የክርስትናን እምነት ሲገልጽና ሲሟገት ነበር፡፡ በዚህ አገላለጹ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ካቶሊካዊት ማለትም ሁሉንም የምታካትት ዓለም አቀፋዊት ባህርይ የተላበሰች መሆንዋን አመላክቷል፡፡ →→ መደምደምያ በአጠቃላይ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና አራት መቶ ዓመታት ካቶሊክ የሚለው ቃል “የአዲስ ኪዳን ሰዎች (የክርስቶስ ተከታዮች) ወሰን ወይም የድንበር ከለላ የላቸውም፤ ሕይወታቸው ከሁሉም ጋር ነው፤ ለሁሉም ክፍት የሆነ ነው፤ በቦታ፣ በዘር፣ በቋንቋ፣ በፆታም ሆነ በኑሮ ሁኔታ አይወሰኑም” ከሚል አኳያ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በተጨማሪም ክርስቶስ ያስተማረው እውነታ ሁሉንም የሚያቅፍ፣ ሁሉንም የሚያካትት፣ ሁሉንም የሚመለከትና ለሁሉም በሁሉም ስፍራ መዳረስ ያለበት እንደሆነ ለመግለጽ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ካቶሊክ የሚለው አሳብም ከዚህ ዘመን ማለትም የአንጾኪያው ቅዱስ ኢግናጢዮስ (በ107 ዓ.ም.) ከተጠቀመበት ጊዜ ጀምሮ በተግባር ላይ የዋለ፣ በኑሮ ሒደት የዳበረና የተስፋፋ ቃል ብቻ ሳይሆን የእምነትና የቤተ ክርስቲያን መጠሪያ ስም ጭምር ነው፡፡ ቢያንስ ለአንድ ካቶሊክ መላክ እንዳለባችሁ አትርሱ! @eth_Catholic @eth_Catholic
ድንግል ማርያም ሀይለ አርያማዊት ናት ወይ? ይሔ ጥያቄ ከሕጻንነቴ ያደከመኝ ጥያቄ ነው ሞኝ የተከለው እንዲሉ ብዙ ተደጋግሞ ይሰማል ያለምንም በቂ ጥናት ጭፍን ነገር ይዞ አንዴ በታተመ መናፍቃንና ማንነታቸው የምትል መጽሐፍ ምክንያት እስኪሰለቸን ተጠይቀናል እንዳው እንዲት ወዳጄ ይሔንን እስኪሰለችህ ሳትጠየቅ ካቶሊክ መሆንህ አይረጋገጥም ብላ ቀልዳ አስቃኝ ነበር። እስቲ ይሔንን ከዛሬ የተሻለ የምመልስበት ቀን ያለ መስሎ ስላልተሰማኝ እንሂድበት። 1 ድንግል ማርያም ከአዳም ኃጢአት ነጻ ነች ማለት ሰው አይደለችም ማለት አይደለም ኢየሱስ ምንም አይነት ኃጢአት የለበትም ሰው ነው አዳምና ሔዋንም ከውድቀት በፊት ሰው ነበሩ ስለዚህ ይሔንን ጠቅሶ ማንም ሰው አይደለችም እንደምንል አድርጎ ሊያሳይ አይችልም። ምክንያታዊም አይደለም ኢየሱስን ሰው እያሉ እሷ ሰው አይደለችም ብንል ስጋውን ከማን ነሳው ልንል ነው ይሔ የአላዋቂ ክስ ነው። 2 በዛሬው እለት በላቲን ስርዓት የሚከበረው የቅድስት ሐና እና የቅዱስ ኢያቄም የእናትና የአባቷ በዓል ነው ከሰው የተወለደ መቼስ ሰው ነው እና ሰው አይደለችም ትላለችሁ እያሉን ይሔን በዓል የምናከብር መሆናችን የተለየ አለም ከሳሾች መሆናቸው ማሳያ ነው። አከባበራቸው ከምስራቁ ወደ ምዕራቡ የተስፋፋ ሲሆን ቢያንስ ቢያንስ በርግጠኝነት እስከ መካከለኛው ዘመን ድረስ በምዕራቡ አለም አከባበራቸው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ነበር ለዚህም ከጊዜ በኋላ የመጣ ነው ብሎ ማንም ሊከስ አይችልም ማለት ነው። 3 ቤተክርስቲያን ያለ አዳም ኃጢአት መጸነሷን እና የኃጢአት ዝንባሌ እና ኃጢአት እንደሌለባት ብታስተምርም ይሔ ሰው ከመሆኗ የሚለያት ነገር ነው ማለት አይደለም ሰብአዊ ስሜቶች እድገት ሰብአዊ ውስንነት ነጻነት እና ነጻፍቃዷ ሰብአዊ በሐሪ እንደመያዟ ነው ሙሉ በሙሉ የተጠበቀና ያልተነካ። በጸጋ የሆነላት ነገር ደግሞ ከእግዚአብሔር እንጂ ከራሷ አይደለም። ደግሞም እርሷ ራሷ መድኃኒቴ ብላ እንደጠራችው በልጇ የዳነች የተቤዣት ነች ነገር ግን ከሁሉ ላቅ ባለ መንገድ ለመስቀሉ ቅድመ እይት አስቀድሞ በጸጋ ሞልቷታልና። እንዲሁም ሰው ካልሆነች የአምላክ እናት ተብላ በሰብአዊነት አምላክን ወለደች የሚል ዶግማ ልንይዝ ስለማንችል ይሔ ክስ በኛ ላይ ሊቀርብ ቀርቶ ሊታሰብ አይገባም። 4 ቤተክርስቲያን የማርያምን እናትና አባት ከቀኖናዊ ባልሆኑ ጽሁፎች ስማቸውን የወሰደች ሲሆን ኢያቄም ማለት ያሕዌ ያዘጋጃል ማለት ሲሆን እንዲሁም ሐና ማለት ደግሞ ጸጋ ማለት ነው በዕብራይስጥ።ኢያቄም በቋንቋው ውስጥ ትርጉሙ ከኤሊ እና ከኤሊያቄም ጋር እንደሚተሳሰር እና በተለዋዋጭነት ጥቅም ላይ ውሏል በማለት የሉቃስ ወንጌል የዘር አቆጣጠር ላይ ኢያቄም ነው የተጠቀሰው የሚሉም አሉ በትውፊት። በዓላቸውም በላቲኑ ስርዓተ አምልኮ በዛሬው እለት በሊጡርጊያ የሚታሰብ ነው።እናት እና አባት ያለው መልአክ ወይ ከሰማይ የመጣ የለም ኢየሱስም ቢሆን ከእርሷ ስለተወለደ ነው ሰው የተባለው ስለዚህ ይሕ ክስ ልክ አይደለም። 5 ከመጽሐፍ ቅዱስ ጀምሮ ኢየሱስ ሰው መሆኑን የሚያስረዱ ጥቅሶች እንዲሁም የቤተክርስቲያን አባቶች እንደ ኢራንዮስ ኤፍሬም ዮሐንስ አፈወርቅ ዮስጢኖስ ሰማዕቱ ድንግል ማርያምን አዲሲቷ ሔዋን የሔዋን ተሀድሶ ብለው ማለታቸው ከክሱ በተቃራኒው የተከበረ እና የሚጠበቅ ትውፊት ነው። ከአባቶች ደግሞ በልዩነት ጎርጎርዮስ ዘኒሳ ጀርማኑስ ዘቁስጥንጥንያ ፉልበርት ዘቻርተርስ ወዘተ እናትና አባቷን በስም በመጥቀስ የጻፉ አባቶች ናቸው እንዲሁም ነገረ ክርስቶስንና ነገረ ማርያምን የዳሰሱ እንዲሁም የጉባኤያት ውሳኔ እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምሕሮ የሆኑ ጽሁፎች እስከ ዘመናችን ድረስ አሉ። በተለይም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በዚህ በዓል ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቶቻችንን ጨምሮ በየደብሩ የተሰበኩ ማስረጃወች ጽሁፎችና መልዕክቶች አሉ በተለይም በጣልያን የዛሬው በዓል ትልቅ በአል ተደርጎ ይከበራል በጀርመን ጥንታዊ የመዓድን አውጪወች ባልደረባ ተደርጋ ስለምትወሰድ በትልቁ ቅድስት ሀና በዚሁ እለት ትከበራለች። (ከሳጥኑ ውጪ ከማዕድን አውጪነት ወደ ገበሬነት ከተለወጠ ቤተሰብ የተወለደው ሉተር የመነኮሰው ለቅድስት ሐና ከመብረቅ አደጋ ለመትረፍ ተስሎ እንደነበር ልብ ይሏል)። 6 በጣም የሚያስጠላው ከሳሾቻችን ማስረጃ ሲጠየቁ (ሁሉንም አይደለም) ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራሷን በጊዜ እያሻሻለች ስለመጣች ማስረጃ ስላጠፋች ማስረጃ ማግኘት አይቻልም ይሉናል። አንተ አጊኝተኸው እኛ ሳናውቀው ከሚል ድፍረታቸውን ከሚመጥን ቀልድ በቀር ለዚህ መልስ ያስፈልገዋል ብዬ አላስብም። ማስረጃ እና የማረጋገጥ ግዴታ ሲጠየቅ እኮ ማቅረብ አለበት ጋፍኛ ሁለተኛ ክስ ከመክሰስ። ይቅርታ እኮ ያባት ነው አላውቅም ማለትስ ማንን ገድሏል ። 7 በሰለጠነ ዘመን ሰው ጥቂት ፈልጎ ብዙ በሚያገኝበት ዘመንም ያልቆመ ክስ መሆኑ አሳዛኝ ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች እና አልፎም መምሕራን ዘንድ ልዩነት ሲባል የሚጠራ ቁጥር አንድ ሐሳብ መሆኑ በዘንድሮ አመት የታተመ መጽሐፍ እንኳን (የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማትን የመዝሙር አስተዋጽኦ የሚቃኝ መጽሐፍ) ሐሳቡን ይዞ መገኘቱ እስከዛሬ የቀጠለ ክስ መሆኑን ያሳያል ይሔ ደግሞ እንኳን ላለን ግንኙነት ለእነሱ ለራሱ ውሸት ልክ ባለመሆኑ ሊታረም እና ሊያስታውሉት ይገባል ። ድንግል ማርያም ሀይለ አርያማዊት ናት አንልም። ከዚህ ስር ታዲያ የበለጠ ማወቅ ለሚፈልግ ማግኘት የሚቻልበትን ማስረጃወች አስቀምጣለሁ። ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ለምኑልን Catholic Encyclopedia Immaculate Conception /The Encyclopedia Press CCC 491 Fulgens Corona/ Pope Pius XII Ineffabilis Deus/ Pope Pius IX General Audience of 12 June 1996/ Pope John Paul II Catholic Encyclopedia St. Joachim/ The Encyclopedia Press The Gospel of the Nativity of Mary Chapter1/ Unknown author Pius IX, "Ineffabilis Deus", December 8, 1854. CCC 487 To the 3rd Public Session of the Pontifical Academies (November 7, 1998) 3/ Pope John Paul II Encyclopedic Dictionary of the Christian East Theotokology / Edward G. Farrugia Catholic Encyclopedia St. Joachim / The Encyclopedia Press Catholic Encyclopedia St. Anne / The Encyclopedia Press Catholic Encyclopedia The Blessed Virgin Mary / The Encyclopedia Press Catholic Encyclopedia Apocrypha / The Encyclopedia Press The Gospel of the Nativity of Mary Chapter 1 / Unknown author An Exposition of the Orthodox Faith Chapter 14 / John of Damascus Contra Faustum Book 23. 9 / Augustine of Hippo Catholic Encyclopedia Immaculate Conception / The Encyclopedia Press ምንጭ: ዲያቆን ራዕይ ሳሙኤል Facebook page የተወሰደ
видео или голосовое, без подписи
እግዘብሔር ቀን አለው ከምለው የዘማሪት ሜሮን ተሾመ አድሱ አልበም የወደደችሁትን ሶስት መዝሙር ኮሜንት ለይ አስቀምጡ እስኪ ✍✍ የእኔ ፦ #እግዘብሔር ቀን አለው #መልሰን እና #በማለዳ እስካሁን ላልሰማችሁት ደሞ👇 @EgziabherKenAlewBot ገዝታችሁ በማዳመጥ ተባረኩበት! @eth_Catholic @eth_Catholic
#ኢየሱስ . . . የእኔ እውቀት ያልኩት ስኬት አልሆነኝም ሀብትና ስልጣኔ እርካታ አልሰጠኝም እንካ መዳፌን ያዝ ጥራኝ ልከተልህ ካንተ ላንተ ጌታ ላንተው ልኑር ተቀበለኝ እንካ ጌታ ራሴን ውሰድ..... @eth_Catholic @eth_Catholic
ማንም የለም @eth_Catholic @eth_Catholic
2ኛ ሳሙኤል 7 : 22 ²²ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታላቅ ነህ! የሚመስልህ ማንም የለም፤ በጆሮአችን እንደሰማነው ሁሉ፥ ከአንተ በቀር አምላክ የለም። @eth_Catholic @eth_Catholic
የማርቆስ ወንጌል 8 : 34-36 ³⁴ከዚህ በኋላ፥ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ ³⁵ነፍሱን ለማዳን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋት ሁሉ ግን ያድናታል። ³⁶ሰው ዓለሙ ሁሉ የእርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? @eth_Catholic @eth_Catholic
እስኪሞላ አልጠብቅም፡ ላመሰግንህ በቂ ነህ ያላኖርከኝ መቼ ነው፡ እስትንፋሴ እኮ አንተው ነህ የተቀደሰ ቀን ይሁንላችሁ 🙏 @Eth_Catholic @Eth_Catholic
የዮሐንስ ወንጌል 13 : 34 ³⁴እርሱም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። @Eth_Catholic @Eth_Catholic
እግዚአብሔር ልባችንን በፍቅሩ ይሙላው! 🙏🕊️
---ዳንኤል 7፡18--- ¹⁸ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ። መልካም አደር ይሁንላችሁ❤️🙏 @Eth_Catholic @Eth_Catholic
መጽሐፈ መክብብ 12 : 13-14 ¹³የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፥ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፥ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። ¹⁴እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። @Eth_Catholic @Eth_Catholic
የሜሮን ተሾመን አድሱን አልባም ለመግኘት ከታች ያለውን Bot ይጠቀሙ። 👇 https://telegram.me/EgziabherKenAlewBot https://telegram.me/EgziabherKenAlewBot
<unknown> – 6 አትወዳደርም
----አትወዳደርም--- @Eth_Catholic @Eth_Catholic