መሰረተ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ
Статистика"ቤተክርስቲያንን አየኋት፣ አወኳት፣ወደድኳት" ቅዱስ ያሬድ “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” ኤፌሶን 2፥20 "ሳትማሩና መጻሕፍት ሳታነቡ የምታገኙት ዕውቀት አይኖርም" መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 208
- 1/48двое суток
- 238
- 1/72трое суток
- 257
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የፖርኖግራፊ ዋጋ The cost of pornography The Hidden War Ep. 2 https://youtube.com/watch?v=2waL0XF-Ylk&si=e-0JE7TCKOPa5iKZ
https://youtu.be/6c_UPBU9oJg?si=IUvfJ5WE8q3WlPvg
https://youtu.be/84Zl8tKGS2g?si=DTJ0a4uI0tCMSOfq በዘመናችን ከሲጋራ ፣ ከመጠጥ እና ከሌላ ሱሶች በላይ ፈተና ስለሆነው ሱስ ወንድማችን እዮብ ትምህርት ጀምሯል ፣ ስሙት ለሌሎችም ላኩላቸው ። ክፍል 1 ተለቋል ሁላችንንም እግዚአብሔር ይርዳን 🙏
ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለእግዝትነ ማርያም በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች። የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄምና ሃና ይባላሉ። እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም:- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ፤ ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች። እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ሃናም አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው። ከዚያም በኋላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፤ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም "7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ" አየሁ አላት፤ ሃናም እኔም አየሁ አለችው ምን አየሽ ቢላት "ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ" አለች። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡ እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች፡፡ ምልጃዋ በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን፡፡
አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ማንበብ ፣ መጻፍ ፣ መስማት እና መናገር ከቻለ ባሉት አማራጮች እነዚህን ትምህርቶች ማወቅ አለበት ክፍል 1 1.አምስቱ አእማደ ምስጢራት 2.ሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን 3.የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ እና በዓለም መድረክ 4.ነገረ ድኅነት 5.ነገረ ክርስቶስ 6.ነገረ ማርያም 7.ነገረ ቅዱሳን 8.ነገረ መላእክት 9.ሥርዓተ ቤተክርስቲያን 10.ክርስትያናዊ ሥነ-ምግባር(ተግባራዊ ክርስትና) 11.ክርስትና እና ፍልስፍና 12.ሥነ አመክንዮ እና ክርስትና ክፍል 2 13.የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ብሉይ እና አዲስ ኪዳን 14.ሐዋርያነ አበው ፣ ሐዋርያዊ አስተምህሮ ፣ሐዋርያዊ ትውፊት ፣ ሐዋርያዊ መተካካት (ክህነት) 15.ቅዳሴ 16.በዓላት 17.ቅዱስ ታቦት 18.ቅዱሳት ሥዕላት 19.ሃልዎተ እግዚአብሔር እና ስነ ፍጥረት 20.የትምህርተ ሃይማኖት መግቢያ 21.ነገረ ቤተክርስቲያን(ህንጻ ቤተክርስቲያን እና ንዋያተ ቅድሳትንም ጭምር) 22.አዋልድ መጽሐፍት 23.አጽዋማት 24.ኦርቶዶክሳዊ የጋብቻ ህይወት 25.ነገረ ዕቅበተ እምነት 26.አገልግሎት እና መሪነት "ለመዳን ማወቅ ለማወቅ ደግሞ መማር ያስፈልጋል!!!" (መሰረተ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ)
ወደ መጀመርያው ፖስት ለመሄድ እና ከመጀመርያው ትምህርት ጀምሮ ለመማር "pinned message" የሚለውን ተጫኑት
https://youtu.be/JEo0pnnkmfs?si=e1gLcsxzxEBkowrZ
https://youtu.be/RT8ogj5kGZ4?si=-KRbzrj-sFD-K5jj
የመጽሐፍ ጥቆማ : - "ኦርቶዶክሳዊ የንግግር ጥበብ" (Orthodox Art of Rhetoric) (መሰረተ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ)
видео или голосовое, без подписи
የመጽሐፍ ጥቆማ (መሰረተ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ)
ስልካችሁን ወደ ጎን አድርጋችሁ እዩ 😍 (መሰረተ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ)
видео или голосовое, без подписи
የመጽሐፍ ጥቆማ :- "ንቡ ተሜ" በመምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ አስተያየት :- በአማን ነጸረ ሰቶበታል። በቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ከሚያንገበግቡኝ የብዙ ችግሮቻችን ምንጭ አንዱ የሆነውን ጉዳይ በዚ መጽሐፍ ውስጥ ማካተታቸውና ለሚያስተውለው ሰው ችግሩን ከእነ መፍትሄው በልብ ወለድ መልክ ማስቀመጣቸው እና የመጽሐፉ አጨራረስም ልብን የሚያንጠለጥል መሆኑ እስከ ዛሬ ሳላነበው ለምን ቆየሁ ? እንድል አድርጎኛል ግዙ እና አንብቡ መልካም ንባብ ! (መሰረተ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ)
መጽሐፍ ማንበብ በሰዎች ሕይወት ፣ አስተሳሰብና ስኬት ላይ ታላቅ አዎንታዊ አስተዋፅኦ አለው :: 📖 የሚያነቡ ሰዎች ከማያነቡ ሰዎች የዕውቀት አድማሳቸው ሰፊና ጥልቅ ሲሆን አስተሳሰባቸውም የበሰለ ነው ። መጻሕፍትን ባነበቡ ቁጥር ወደ ተለያዩ ዓለማት የመጓዝ ፣ የሰዎችን ሕይወት የመረዳትና ጥልቅ ጥበብን የመቅሰም ዕድል ያገኛሉ ። ንባብ የቃላት እውቀታቸውንና የንግግር ክህሎታቸውን ከማሳደጉም በላይ ፣ ለማንኛውም ችግር ምክንያታዊና ስልታዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ ይረዳቸዋል ። እነዚህ ሰዎች በራስ መተማመናቸው ከፍተኛ ነው፤ ምክንያቱም በውስጣቸው የማይነጥፍ የዕውቀት ስንቅ አላቸው ። ንባብ ለእነሱ አእምሯቸውን የሚያድሱበት፣ ጭንቀትን የሚቀንሱበትና ሁልጊዜም ራሳቸውን የሚያውቁበት የብርሃን ጎዳና ነው። በአጭሩ ፣ የሚያነቡ ሰዎች ትላንት ከነበሩበት የተሻሉ ለመሆን በየቀኑ የሚተጉ የሕይወት መሐንዲሶች ናቸው ። 🛑 የማያነቡ ሰዎች በአንጻሩ ዕውቀታቸውና አመለካከታቸው በአካባቢያቸው በሚሰሙትና በሚያዩት ጥቂት ነገሮች ላይ ብቻ የተገደበ ይሆናል ። ዓለም በየቀኑ በሚፈጥራቸው አዳዲስ እውነታዎችና የዕድገት ለውጦች ውስጥ በፍጥነት የመራመድ ዕድላቸው ጠባብ ነው። ንባብን ሕይወታቸው ያላደረጉ ሰዎች ለአድልዎ ፣ ለተሳሳቱ መረጃዎችና ለወሬ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፤ ምክንያቱም ነገሮችን በምክንያትና በማስረጃ የማመዛዘን ልምዳቸው አልዳበረም ። ይህም በሰዎች ላይ ጥገኞች እንዲሆኑና የራሳቸውን ጠንካራ አቋም እንዳይገነቡ ያደርጋቸዋል ። አእምሯቸውን በአዲስ አስተሳሰብ ሳያድሱ ስለሚኖሩ፣ የሕይወት እይታቸው አሰልቺና ከተለመደው አስተሳሰብ የማይወጣ የመቀጨጭ ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። የንባብ ልምድ በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለው ዓይነት የሕይወት ልዩነትን ይፈጥራል ። 📖📖📖📖📖 ጃዕፈር መጻሕፍት !
https://youtu.be/pQOrLH_Jch0?si=7oF-0FTdeOqIoJ-Z
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን 🙏 ጾሙን ንስሐ የምንገባበት ፣ የምንቆርብበት፣ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ፣ የበረከት ጾም ያድርግልን 🙏 (ጾመ ፍልሰታ ለማርያም 2018 ዓ.ም) (ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት)
https://youtu.be/cG2n9UwhCgg?si=7PCHUy83DLjLH2wh
ወደ መጀመርያው ፖስት ለመሄድ እና ከመጀመርያው ትምህርት ጀምሮ ለመማር "pinned message" የሚለውን ተጫኑት
አኰቴተ ቍርባን በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ