tgindex
E

EoDB (Ease of Doing Business)

Статистика

በንግድ ላይ መሰማራት ይፈልጋሉ? የአገልግሎት ጥያቄዎቹን በበለጠ ፍጥነት እና ብቃት ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ በማሳየት ሁሉንም አገልግሎትች ከግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማግኝት፣ የንግድ ምዝገባ እና የፍቃድ አገልግሎቶችን በቀላሉ የሚያገኙበትን መንገድ ማሳየት ነው።

Последний пост
6 сент. 2025 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 990
+15 за 4 дн.
Сутки
+4
+0,10%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
10,7 тыс
21 постов
Вовлечённость
269,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://t.me/EthioEoDB ሥለ ንግደዎና መንግስት ለሕ/ተሰቡ የሚሰጣቸው አገግሎቶች

  • 12 янв. 2025 г.22,3 тыс188255

    የኢትዮጲያን በጀት ዓመት የሚጠቀሙ ንግዶች በእያንዳንዱ የንግድ ፍቃድ እድሳት ጊዜ ማብቃትን ተከትሎ የሚከፈለውን ቅጣት መጠን ያውቃሉ? EoDB (Ease of Doing Business) ከ ጥር 1 እስከ ጥር 30 ብር 2,500.00 ከ የካቲት 1 እስከ የካቲት 30 ብር 4,000.00 ከ መጋቢት 1 እስከ መጋቢት 30 ብር 5,500.00 ከ ሚያዚያ 1 እስከ ሚያዚያ 30 ብር 7,000.00 ከ ግንቦት 1 እስከ ግንቦት 30 ብር 8,500.00 ከ ሰኔ 1 እስከ ሰኔ 30 ብር 10,000.00 ከሃምሌ 1 ጀምሮ ለሚመጣው 1 አመት 20,000.00 ከ 1 ዓመት በኋላ ፍቃዱን በአዋጅ ይታገዳል በተጨማሪም ነጋዴው ለ 1 አመት በታገደው የፍቃድ መስጫ መደብ ፍቃድ ማውጣት እንዳይችል ይታገዳል። ማሳሰቢያ አብዛኛውን ጊዜ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ ለማደስ ወሩ መጨረሻ ላይ ስለሚመጡ ቀድመው በማደስ ፈጣን አገልግሎት ያግኙ!!!

  • 15 авг. 2024 г.19,2 тыс9634

    ‼️‼️------------------- ግብር ከፋይ ኖት? እንግዲያውስ ግብርዎን በወቅቱ በመክፈል በፍጥነት ንግድ ፍቃድዎትን ያድሱ!!!! ‼️‼️------------------- የንግድ ፍቃድዎን ለምን በወቅቱ ያድሳሉ? ህጋዊ ተገዢነት፡ ጊዜው ባለፈበት ፍቃድ ንግድ ስራ መስራት ህገወጥ ነው እናም ለቅጣት አልፎ ተርፎም ንግድዎን ሊያዘጋ ይችላል። የአገልግሎቶች መዳረሻ፡- እንደ የባንክ ብድር፣ የመንግስት ውል ወይም የንግድ ስምምነቶች ያሉ አንዳንድ አገልግሎቶች ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማረጋገጫ ያስፈልጋቸዋል። መልካም ስም፡ ህጋዊ ፍቃድ ንግድዎን ከደንበኞች፣ አጋሮች እና አቅራቢዎች ጋር ያልዎትን ግንኙነት እና ታማኝነት ያሳድጋል።

  • 8 авг. 2024 г.17,5 тыс4520

    ‼️‼️------------------- ነጋዴው በተመን ለወጥ ምክንያት የተፈጠረበትን የቀረጥ ጭማሪ እንዴት ይሸፍን? ‼️‼️------------------- ነጋዴው ድሮም እቃ የሚያስመጣው በጥቁር ገበያ ተመን ነበር። ታዲያ የምንዛሪ ዋጋ ለውጥ ከሌለ የእቃ ዋጋ ለምን ይጨምራል ? የሚል መከራከርያ በስፋት እየተሰማ ነው። ይህ አቀራረብ ሁለገብ ምልከታ የጎደለው ስለሆነ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የሚረዳ አይደለም። ነጋዴው ሚያስመጣው እቃ ዋጋ የሚወሰነው ጉምሩክ ባዘጋጀው የእቃዎች የዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ተመስርቶ ሲሆን ቀረጥ የሚከፍለው ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የእለቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት በማድረግ ነው። ይህ ማለት ነጋዴው ከሳምንት በፊት በ100 ዶላር ለጫነው እቃ ቀረጥ የሚከፍለው በወቅቱ በነበረው የብሔራዊ ባንክ የአንድ ዶላር ተመን ብር 58 ብር ተሰልቶ ሲሆን ዛሬ ላይ ቢጭን ደግሞ በባንኮች በሚያወጡት የውጭ ምንዛሪ አማካይ ተመን ላይ ተመስርቶ በሚሰላ ዋጋ 100 ብር ገደማ ነው። ይህ ማለት የቀረጥ መጣያ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል ማለት ነው። ' ዋጋ እንዳትጨምር ማለት' ብቻ ሳይሆን ነጋዴው በተመን ለወጥ ምክንያት የተፈጠረበትን የቀረጥ ጭማሪ እንዴት ይሸፍን የሚለው ጥያቄ መመለስ ይስፈልጋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊታሰብበት የሚገባው ፦ ° የአውሮፕላን ትኬት፣ ° ኢንሹራንስ፣ ° የጭነት ዋጋ፣ ° የኮንቴይነር ኪራይ በእቃዎች ዋጋ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም። በመመርያና በአስተዳደራዊ እርምጃ የሚተመን ዋጋ የግብይትና የአቅርቦት ስርዓትን በማፋለስ፣ የጥራት ጉድለትና የዋጋ ንረት በአጠቃላይ የገበያ ውጥቅጥን ማባባሱ የሚጠበቅ ነው። በአስተዳደራዊ ውሳኔ አከፋፋዩም ሆነ ቸርቻሪው ዛሬ እጁ ላይ ያለውን ምርት በውሳኔው ዋጋ አጣርቶ ሊሸጥ ይችላል። እጁ ላይ ያለው ምርት ካለቀ በኋላ ግን ነጋዴው እንደሚከስር እያወቀ እቃ ለማስመጣትም ሆነ ለማከፋፈል ፍላጎት እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ይህ ደግሞ የእቃ እጥረትና ተጨማሪ የዋጋ ንረት/ግሽበት ፣ እቃ መሰወር፣ ጥራት የጎደለው ምርት ማቅረብና ለኮንትሮባንድ ንግድ መጋለጥን ሊያስከትል ይችላል። ጊዜያዊ በሆኑ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና በደንብ አስከባሪዎች ማዋከብ ነጋዴው ማህበረሰብ ስጋት እንዳያድርበት፣ እንዳይበረግግና ከገበያው እንዳይወጣ፣ በዚህ ምክንያትም ገበያው ይበልጥ እንዳይታወክ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

  • 5 авг. 2024 г.11,9 тыс3014

    ‼️‼️------------------- አስፈላጊ ሸቀጦችን የአለግባብ የማከማቸት ተፅእኖዎች ‼️‼️------------------- የአገር ውስጥ የገንዘብ የመግዛት አቅም በተከታታይ መመናመን ምክንያት ነጋዴዎች አስፈላጊ የሆኑ መሰረታው ሽቀጦችን እና ዕቃዎችን በማጠራቀም በኢኮኖሚውና በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። እነዚህን ተፅእኖዎች ለመቅረፍ እና ለሁሉም ዜጎች አስፈላጊ የሆኑ እቃዎች መገኘት እና ተደራሽነት ለማረጋገጥ አጠቃላይ የቁጥጥር፣ የገንዘብ፣ የፊስካል እና የህዝብ ግንዛቤ ስትራቴጂዎች ያስፈልጋሉ። አስፈላጊ ሸቀጦችን የአለግባብ የማከማቸት ተፅእኖዎች 1. የዋጋ ግሽበት እና የዋጋ ተለዋዋጭነት  ነጋዴዎች አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን ሲያከማቹ፣ በገበያው ውስጥ ያለው አቅርቦት መቀነሱ የዋጋ ጭማሪን ያስከትላል። ይህ የዋጋ ግሽበት በተለየ ሁኔታ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እና ከገቢያቸው ከፍተኛውን ድርሻ ለመሠረታዊ ፍላጎቶች የሚያውሉትን ዜጎች ይጎዳል  የተደራሽነት ጉዳዮች፡ ነጋዴዎች አስፈላጊ የሆኑ እንደ ምግብ፣ መጠጥ እና መድኃኒት ያሉ አስፈላጊ ሸቀጦችን ሲያከማቹ በገበያ ላይ ያለውን ተደራሽነት ይቀንሳል። የመድሃኒት እና የጤና እንክብካቤ አቅርቦቶች የላግባብ ማከማቸት እና ከንግዱ ዝውውር መሰወር እነዚህን መዳኒቶች በአፋጣኝ እና በተከታታይ ማግኝት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል፣ ። 2. ኢኮኖሚያዊ ብቃት ማጣት  የሀብት አመዳደብ፡- ሀብትን ማጠራቀም ውጤታማ ያልሆነ የሃብት ድልድልን ያስከትላል፣ ምክንያቱም እቃዎች በምርታማነት ከመጠቀም ይልቅ ስለሚከማቹ። ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገትን እና ምርታማነትን ያደናቅፋል 3. ማህበራዊ አለመረጋጋት  የህዝብ ቅሬታ፡ ሰፊ እጥረት እና የዋጋ ንረት ህዝቡን እርካታ ሊቀንስ እና ለማህበራዊ ውጥረት ሊዳርግ ይችላል።

  • 31 июл. 2024 г.10,3 тыс2713

    ‼️‼️------------------- የብር የመግዛት አቅም ከውጭምንዛሬ አንጻር መዳከም ‼️‼️------------------- አንድን ኢኮኖሚ ለመለካት የንግድ ድርጅቶችን አጠቃላይ አፈጻጸም መገምገም በራሱ የሚጠቁመው ነገር አለ። በዚህ ዕርስ ስር ሰሞኑን እየታየ ያለው የብር የመግዛት አቅም ከውጭ ምንዛሬ አንጻር መዳከም ከንግድ ሥራ አፈጻጸም አንፃር ያለውን ጥቅም እና ጉዳት እናያለን። የብር አቅም ከውጪ ምንዛሪ አንጻር መዳከሙ ያለው ጥቅም ፡- የብር የመግዛት ዋጋ ቅነሳ የአንድን ሀገር እቃዎች እና አገልግሎቶች ለውጭ ገዥዎች ርካሽ ያደርገዋል። በዓለም አቀፍ ገበያ ዝቅተኛ ዋጋ መኖሩ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ንግዶች ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል። ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋቸው እየጨመረ በመምጣቱ ሸማቾች በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን እንዲገዙ ያበረታታል። ይህም የውጭ ኩባንያዎችን ፉክክር በመቀነስ በአገር ውስጥ ገበያ ላይ የሚያተኩሩ ቢዝነሶችን ሊጠቅም ይችላል። የብር አቅም ከውጪ ምንዛሪ አንጻር መዳከሙ ያለው ጉዳት፡- ከውጭ በሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች፣ ክፍሎች ወይም መሳሪያዎች ላይ የተመሰረቱ ንግዶች ለሚሰሩ ኩባኛዎች ከፍተኛ ወጪ እኒዲኖራቸው ያደርጋቸዋል ይህ በተለይ ንግዱ እነዚህን ወጪዎች ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ካልቻለ የትርፍ ህዳጎችን ለቀንስ ይችላል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ መጨመር፤ በሃገር ውስጥ ገንዘብ ገቢ የሚያገኙ ሸማቾችን የመግዛት ሃይል በመሸርሸር የመግዛት አቅማቸውን ያዳክማል። ይህ ደግሞ የንግድ ሽያጭ መጠንን በመቀነስ ትርፋማነትን ሊቀንስ ይችላል ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ሲጨምር የዋጋ ንረቱ በከፍተኛ መጠን ይጨምራል፣ ይህ ደግሞ የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለምሳሌ እንደ ደሞዝ እና ኪራይ የመሳሰሉትን በመጨመር በንግዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል። ምርቱን/አገልግሎቱን ሃገር ውስጥ የሚያመርት ኩባንያ በውጪ ምንዛሬ ብድር ቢኖርበት፣ ብድሩን ሃገር ውስጥ እየሸጠ ለመክፈል አስቸጋሪ ያደርግበታል ምክንያቱም የብር የመግዛት አቅም በተዳከመ ቁጥር ያለበት እዳም እየጨመረ ስለሚሄድ ነው። ንግዶች ወጪዎችን፣ ገቢዎችን እና ትርፍን በትክክል በመተንበይ ረገድ ተግዳሮቶች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። የጉልበት/የሰራተኛ ደምዝ በአገር ውስጥ ገንዘብ ሲከፈል አብዛኛው ጥሬ እቃ ደግሞ በውጭ ምንዛሬ ይገዛል። ምርታቸውን ወደ ውጪ ለሚልኩ እና ገቢ በውጭ ምንዛሬ ለሚያገኙ ድርጅቶች የብር የመግዛት አቅም ሲቀንስ አንጻራዊ የሠራተኛ ደሞዝ ደግሞ እየቀነሰ ይሄዳል። ይሄ በአጭር እና መካከለኛ ጊዜ ጥቅም ቢሰጥም በደንብ ካልታሰበበት እና የዋጋ ንረቱ ያለአግባብ ከጨመረ፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ቢመጣ ወይም የወለድ ተመኖች ቢጨምሩ የጨመረው የካፒታል ዋጋ ከርካሹ የሰው ኃይል ሊበልጥ ይችላል ይህ ደግም በረጅም ጊዜ የራሱ የሆነ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

  • 27 апр. 2024 г.10,1 тыс1817

    без подписи

  • 15 мар. 2024 г.11,3 тыс148

    https://youtu.be/vf3BnWolciw

  • 5 мар. 2024 г.14,9 тыс2448

    ‼️‼️------------------- የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ምን ይላል? ‼️‼️------------------- በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ የሚመለከታቸው ነጋዴዎች ላይ በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ (ቁጥር 813/2006) መሰረት ቁጥጥር እየተደረገባቸው ይገኛል። አዋጁ ለሻጭ መብቶችን እና ግዴታዎችን ሲያስቀምጥ ሸማቹን በተመለከተ…

  • ‼️‼️------------------- የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ምን ይላል? ‼️‼️------------------- በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ የሚመለከታቸው ነጋዴዎች ላይ በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ (ቁጥር 813/2006) መሰረት ቁጥጥር እየተደረገባቸው ይገኛል። አዋጁ ለሻጭ መብቶችን እና ግዴታዎችን ሲያስቀምጥ ሸማቹን በተመለከተ ግን መብቶችን ብቻ አስቀምጦ አልፎአል። ይህ ሊሆን የቻለው የግብይት እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ሻጩ ያለውን ልምድ ተጥቅሞ በድንጋጌው የተመለከቱትን መብቶች ማወቅ እና መስፈጸም አልበት ተብሎ ነው። የነጋዴ ግዴታዎች 1. የሚሸጠውን ዕቃ ጥራት፣ አይነት በተመለከተ በቂ እና ትክክለኛ መረጃ ወይም ማብራሪያ መስጠት። 2. ገዢውን በትህትና እና በአክብሮት ለመያዝ እና እንደ ስድብ, ዛቻ, ብስጭት ወይም ስም ማጥፋት የመሳሰሉ ድርጊቶችን ከመፈጸም መቆጠብ 3. የሚነግዱባቸው እቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋ በተመለከተታክስን ያካተተ ዋጋ ለህዝብ ማሳየት. 4. የሚሸጠውን ዕቃ ላይ የሚለጠፈው ይዘት የአቃውን ስም፣ ዕቃው የተመረተበት ወይም የመጣበትን አገር፣ የሸቀጦቹ ጠቅላላ እና የተጣራ መጠን፣ የዕቃው ጥራት፣ ዕቃውን በሚጠቀሙበት ጊዜ ሊታሰብባቸው የሚገቡ የደህንነት እርምጃዎች፣ የምርት ቀን፣ የሚያበቃበት ቀን , አንድ ባለበት ቦታ ዋስትና እና ሌሎች አስፈላጊ ዝርዝሮች የሚያመላክት መሆን ይኖርበታል. 5. የተሸጡ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በተመለከተ ደረሰኝ መስጠት 6. የንግዱን የንግድ ስም በግልጽ በሚታይበት ቦታ መግለጽ። የሸማች መብቶች •በሚገዛው ዕቃ እና አገልግሎት ጥራት እና አይነት ላይ በቂ እና ትክክለኛ መረጃ ወይም ማብራሪያ የማግኘት •እቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን አማርጦ የመግዛት ወይም የመጠቀም •የሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን ጥራት ወይም አማራጮችን ስለመረመረ ወይም የዋጋ ድርድር ስላደረገ ብቻ እንዲገዛ ያለመገደድ •በማንኛውም ነጋዴ በትህትና እና በአክብሮት የመስተናገድ እና ከነጋዴው ከሚደርስበት እንደ ስድብ፣ ዛቻ፣ ብስጭት እና ስም ማጥፋት ጥበቃ ማግኝት •በሸቀጦች እና አገልግሎቶች ግብይት ምክንያት ለደረሰበት ጉዳት ካሳ ማግኝት •ቅሬታውን ለንግድ አሰራር እና ለሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ለፍርድ ማቅረብ

  • без подписи

  • 1 мар. 2024 г.12,9 тыс11

    без подписи

  • без подписи

  • 1 мар. 2024 г.7 030179из motri_gov_et

    без подписи

  • የተሻለ የቢዝነስ ሀሳቦችን የያዙ የተለያዩ 15 ስታርትአፖች ተሸላሚ ሆኑ፡፡ ========================= የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኮሪያ አለም አቀፍ ኤጀንሲ (KOICA) ጋር በመተባበር ለፈጠራ ሃሳብ ውድድ ር ካመለክቱ 119 አመልካቾች ውስጥ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው የተመረጡት 15 ስታርትአፖች ተሸልመዋል። በኢንኖቤዝ-ኬ (Innobiz-K Ethiopia) ኢትዮጵያ ማዕከል  ለአንድ ሳምንት በፈጠራ ሃሳብ ሞጎልበት፣ በቢዝነስ ሞዴል፣ በፋይናንስ እና የፒቺን ስልጠና ሲሰጥ የቆየው የኢኖቬሽን እና የንግድ ስራ ስልጠም በስኬት  ተጠናቋል። አይ.ሲ.ትን መሰረት ያደረገ የኢኖቬሽን የቢዝነስ ሃሳብ  በማመንጨት ሀገርን የመገንባት ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጾዖ ለማበርከት የተዘጋጁ 15 ጀማሪ ስታርታፖች  መካከል ከ1ኛ-3ኛ የወጡት እንደ ቀደም ተከተላቸው 1500፣ 1000 እና 500  ዶላር እና  የምስክር ወረቀት ሲያገኙ  ሌሎች 12ቱ እያንዳንዳቸው የ 500  ዶላር  ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰላማይሁን አደፍርስ ድጋፉ የፈጠራ ፅንሰ-ሀሳቦቻቸውን በመደገፍ ወደ አዋጭ ቢዝነስ ለማሸጋገር እና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ጉዞ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡ አያይዘውም የኮሪያ አለም አቀፍ ኤጀንሲ ስልጠናውን በማገዝ፣ በቢዝንስ ማማከር እና በመምራት ላበረከቱት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ የኮሪያ አለም አቀፍ ኤጀንሲ ኃላፊ ሊ ሽንግ ያንግ (Lee Shinyoung) በበኩላቸው ኢኖቬሽን የዘመኑ ሀብት ፈጠራ ዋነኛ መንገድ መሆኑን ጠቁመው ዘርፉን ይበልጥ በማጠናከርና ዩኒቨርሲቲዎች ላይ  ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከተሰራ የኢትዮጵያን ዕድገትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ Source:- Innovation and Technology official page.

  • ‼‼------------------- በዛሬው ይዘታችን ላይ የግል ድርጅትን(sole proprietorship) ማዋቀር ምን ጥቅም እና ጉዳት እንዳለው እንዳስሳለን። ‼‼------------------- በግል ድርጅት አንድ ግለሰብ ብቻ ሁሉንም ንብረቶች በባለቤትነት የሚይዝበት እና በግል አቅሙ የሚሰራበት ንግድ ነው። የግል ድርጅት በጣም ርካሹ እና ለመጀመር ቀላሉ የንግድ አይነት ሲሆን አብዛኛዎቹ ጥቃቅን እና አንስተኛ ስራ ፈጣሪዎች ይመርጡታል ምክያቱም ስራ ፈጣሪው እራሱ ባለቤት እና የንግዱ ስራ አስኪያጅ ሆኖ ሊያስተዳድረው ስለሚችል ነው። በንግድ ድርጅቶች ውስጥ (ከአንድ ሰው ኩባንያ በስተቀር) አንድ ሰው የንግድ አጋሩን ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት ስለሚጠበቅበት ተስማሚ መስሎ የታየውን ውሳኔ በቀላሉ ማድረግ አይችልም። ነገር ግን፣ በግል ድርጅት ውስጥ ብቸኛ ባለንብረቱ ከባልደረባው(ዎች) ህልውና የሚነሳ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳይኖር የራሱን ፍላጎት በተመለከተ በነፃነት ውሳኔ መስጠት ይችላል። ነገር ግን፣ በግል ባለቤትነት ውስጥ፣ ባለቤቱ ከንግድ ሥራው አሠራር ለሚነሱ እዳዎች ወይም ሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች በግል ተጠያቂ ነው። ይህ ማለት አበዳሪዎች ወይም ሌሎች ከንግድ ንብረት የማይመለሱ እዳዎች ወይም የይገባኛል ጥያቄዎች በብቸኛ ባለንብረት የግል ንብረት ላይ ሊጠይቁ ይችላሉ። ሌላው ደግሞ በዚህ ዘርፍ የሚሰማሩ የግል ድርጅት ባለቤቶች ወደ ንግድ ሥራ ሲገቡ የራሳቸው ሀብት ያስፈልጋቸዋል። ምንም እንኳን ንግዱ ትርፍ ሊያመጣ የሚችል እንኳን ቢሆን ስራውን ከመጀመሩ በፊት አንዳንድ ወጪዎች መደረግ አለባቸው። ለንግድ ስራ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች እና ሌሎች ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ግብዓቶች፣ የቤት/የቦታ ኪራይ የመሳሰሉት መሸፈን ያስፈልጋል። በግል ድርጀት ውስጥ ደግሞ ባለንብረቶች ገንዘብ ለመሰብሰብ አክሲዮኖችን ወይም ድርሻዎችን መሸጥ አይችሉም ወይም ከብድር ሰጪ ተቋምት በቀላሉ እና በትንሽ ወለድ ብድር ማግኝትም ያስቸግራቸዋል። ይሄ ደግሞ ሰዎችን የግል ድርጅት እንዳይመሰርቱ እንቅፋት ሲሆን ይታያል።

  • ‼‼------------------- እርስዎስ ንግድ ከመክፈትዎ በፊት ምን አይነት ህጋዊ አቋም መምረጥ እንዳለብዎት አቅደዋል? የእያንዳንዱን ህጋዊ አቋሞች ጥቅም እና ጉዳት በሚገባ ለይተው ያውቃሉ ወይስ በተለምዶ ዝም ብለው ይሰራሉ? ‼‼------------------- ሰዎች የራሳቸውን ንግድ ለመክፈት የሚፈልጉበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንዳንዶች የራሳቸው አለቃ መሆን ይፈልጋሉ, ሌሎች ለራሳችው የሚመች የስራ ስዓት ለመፍጠር ወይም የሚወዱትን ስራ ለመስራት ሲፈልጉ ነው። ለአንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ንግድ መጀመር ማለት ነፃነት ማለት ነው፣ ለሌሎች, የተሻለ የሥራ/የሕይወት ሚዛን፣ ከፍተኛ የገቢ አቅም፣ እንደ የንግዱ ዓይነት ተለዋዋጭ የስራ ቦታ ወይም በተለያዩ ቦታዎች የሚጓዙበትን ልምድ መፍጠር መፈለግም ሊሆን ይችላል። ንግድ ለመጀመር ብዙ መሰናክሎች ማለፍ ያስፈልግዎታል። ይህም የገበያ ጥናት ማካሄድ፣ የንግድ እቅድ ማውጣት፣ ካፒታል መፈለግ ወይም ሌላ ዓይነት የገንዘብ ድጋፍ ማግኝት፣ ቦታና የንግዱን ህጋዊ አቋም መምረጥ፣ ትክክለኛ ስም መምረጥ፣ የግብር ከፋይ መለያ፣ የንግድ ምዝገባ ማግኝት፣ እንዲሁም ፈቃድ ማውጣትን ይጨምራል። ስኬታማ የንግድ ሥራ ባለቤቶች በማቀድ እና በመፈጸም ላይ የተሳካላቸው መሆናቸው ግልጽ ነው። ይህም ማለት ንግድ ከመክፈታቸው በፊት ባለው እቅዳቸው በመመራት እቅዳቸውን ያሳካሉ። ------------------- ንግዶች በተለምዶ የግል(sole proprietorship) እና ማህበራት ቢባሉም ንግድን ለማደራጀት ከ 12 ያላነሱ የተለያዩ ህጋዊ አቋም እና የግብር አወቃቀሮች አሉ። እነዚህ ህጋዊ አቋሞች የራሳቸው የሆነ ጥቅም እና ጉዳት አላቸው። እያንዳንዱ ህጋዊ አቋም ከሌላው በምን ይለያል፣ ምን ጥቅም አለው እንዲሁም ጉዳቱ ምንድነው የሚለውን ወደፊት ይዘን እንመጣለን!!!! -------------------

  • ‼‼------------------- በንግድ ስም እና በንግድ ምልክት መሃከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ? ‼‼------------------- የንግድ ምልክት ዋና ዓላማ ምርቱን ከሌሎች ምርቶች ለመለየት በአምራች ወይም ሻጭ የሚቀርበውን ምርት እና አገልግሎት ትክክለኛነት ማረጋገጥ ነው። በሌላ በኩል የንግድ ስም መልካም ስም(Good Will) ለመፍጠር እና አንድን የንግድ ሥራ ከሌላው ለመለየት ይረዳል። አንድ ንግድ ፍቃድ አንድ የንግድ ስም ብቻ ሊኖረው ሲችል ከአንድ በላይ የንግድ ምልክቶች ግን ሊኖሩት ይችላሉ። ይሄም ማለት ለሚያመርታቸው የተለያዩ ምርቶች የተለያየ አይነት የንግድ ምልክቶች ሊጠቀም ይችላል። ብዙ ጊዜ የንግድ ስም የንግዱን በተገልጋዩ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ያመለክታል። ይሁን እንጂ በብዙ አጋጣሚዎች የንግድ ስምን ከንግድ ምልክት መለየት አስቸጋሪ ነው, በተለይም የንግድ ምልክቱ ወይም ስሙ በምርቱ ላይ በሚታተምበት ጊዜ። አንዳንድ ድርጅቶች ተመሳሳይ ስምን እንደ ንግድ ምልክት እና እንደ ንግድ ስም ይጠቅማሉ፣ ይህ ሁኔታ ደግሞ በንግድ ባለቤቶች እና ሸማቾች ላይ ግራ መጋባት ሊፈጥር ይችላል። ይሁን እንጂ ዋናው ችግር የሚፈጠረው የአንድ ድርጅት የንግድ ስም የሌላ ድርጅት የንግድ ምልክት በሚሆንበት ጊዜ ነው። የንግድ ምልክት አዋጁም ሆነ የንግድ ህጉ ይህንን ጉዳይ ግልጽ በሆነ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል አንቀፅ አላካተቱም። የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የንግድ ስምን እያስተዳደረ ሲሆን የንግድ ምልክትን ደግሞ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ሥር ነው። የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት የንግድ ምልክትን ከመስጠቱ በፊት ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር የንግድ ስም የመረጃ ቋት የሚያጣራበት እና ተመሳሳይ ይዘት ሲኖራቸው ያንን ስም የሚከለክልበት መንገድ የለም። በተመሳሳይ የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚንስቴር የንግድ ስም ከመስጠቱ በፊት ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ጋር ተቀናጅቶ የሚያጣራበት መንገድ ስለሌለ ተገልጋዩን ላልተፈለገ እንግልት እንዲሁም ሸማቹን ለተጨማሪ ግራ መጋባት የሚያግልጥበት ጊዜ አለ። ‼‼------------------- በነዚህ ሁለት መስሪያ ቤቶች ባለው የአስተዳደር ትብብር ማነስ ወይም ህጉ ላይ ባለው ክፍተት እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲፈጠሩ እንዴት ይዳኛሉ የሚለውን ደግሞ ከዚህ በፊት የተፈጠሩ ጉዳዮችን ዋቢ አድርገን ወደፊት ይዘን እንመጣለን። ‼‼-------------------

  • ‼‼------------------- በንግድ ስም እና በድርጅት ስም ምሃከል ያለውን ልዩነት ያውቃሉ? ‼‼------------------- ድርጅቶ የሚጠሩበት ስም ለድርጅትዎ ስኬት ወይም ውድቀት ምክያት ሊሆን ይችላል። እርግጥ ነው፣ ድርጅትዎ ስኬታም እንዲሆን ሚና የሚጫወቱ ብዙ ነገሮች አሉ ከነሱም ውስጥ አንዱና ዋነኛው ግን የንግድዎ ስም ነው። የንግድ/የድርጅት ስምዎት የአገልግሎቶት/የምርቶት ተጠቃሚዎች ስለ ድርጅቶት ከሚያስተውሏቸው የመጀመሪያ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። ጥሩ የድርጅት ወይም የንግድ ስም መምረጥ ለንግድዎ ስኬት አንድ እርምጃ መቅረብ ነው። ንግድ ሲጀምሩ ትክክለኛውን ስም በመምረጥ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ - ነገር ግን የመረጡት የድርጅት ስም እና ንግድዎ የሚታወቅበት የንግድ ስም ማለያት ቢፈልጉስ? ‼‼------------------- የድርጅት ስም ማለት ምን ማለት ነው? ‼‼------------------- የድርጅት ስም የንግድዎ ህጋዊ ስም ነው። ግለሰብ ነጋዴ ከሆኑ ስምዎት እስከ አያቶ ስም ድረስ ካልሆን ደግሞ አንድ በንግድ እና ቀጠናዊ ምኒስቴር የተጣራ ስም ሲሆን ይህንን ስም በሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤት ቅፆች እና በንግድ ስራ ወረቀቶችዎ ላይ የሚጠቀሙበት ስም ነው። ይህ ስም በግብር ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀትዎ ላይ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ግብር ሲገብሩ፣ የሰራተኛ ተቆራኝ ሲያስገቡ፣ የግብር ተመላሽ ሲጠይቁ ወይም ሌሎች የመንግስት አገልግሎቶች ሲያገኙ የሚጠቀሙበት ስም ነው። ‼‼------------------- የንግድ ስም ምንድን ነው? ‼‼------------------- አንድ የንግድ ድርጅት ባለቤት ከድርጅቱ ህጋዊ ስም ውጪ በሌላ ስም መስራት ከፈለገ በምትኩ የንግድ ስም መጠቀም ይችላል። የንግድ ስም ማለት ንግድዎ በተለምዶ የሚታወቀው ስም ወይም ማስታወቂያ ሲሰሩ ወይም ሲያሰሩ የሚጠቀሙበት ስም ነው። በተለምዶ፣ አንድ ንግድ አንድ ህጋዊ የድርጅት ስም እና አንድ የንግድ ስም ይኖረዋል። ህጋዊው, እንደተጠቀሰው, በህጋዊ ሰነዶች እና በመንግስት ቅጾች ላይ ይታያል. በሌላ በኩል የንግድ ስም በአጠቃላይ በማስታወቂያዎች እና በንግድ ምልክቶች ላይ ይታያል.

  • без подписи