- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 437
- 1/48двое суток
- 500
- 1/72трое суток
- 540
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
@HAKiKA1
ምሳር እና ችግኝ (ልዑል ሀይሌ) ድምፅ ሰምረ የሽዋስ @HAKiKA1
ስለፊልም Join and Share🫠 @FilmCocktail @FilmCocktail @FilmCocktail
ጓደኛዬ ከሀብታሞች መለስ ከደሀዎች ቀለስ የምትል ከወሽመጧ ጠበብ ብላ ሶስት በሰውነታቸው ጠጪውን የሚያጣብቡ ጋርዶች ባሉበት መሸታ ቤት ውስጥ ሁለት ቢራ ጋብዞ እንዲህ ሲል አበረታታኝ። "ይኸውልህ አብሬ አንተ እምቅ አቅም አለህ...እምቅ አቅም...ቲክ ቶክ ክፈት"! ወድያው እኔም ተወጣጥሬ ከፈትኩ ከፍቼም አልቀረሁ ፎቶዬን በዘፈን አቀናብሬ ለጠፍኩ...። ይሄ እስኪሆን ስድስተኛ ቢራ ላይ ነበርኩ። አንድ ሰው ነው ቪዲዮውን ያየው... እሱም እንዲህ አለና ኮመተ "ሄዋንን ያሳታትን እባብ በትንሳኤው ቀን አየሁ የአለም መጨረሻ ደረሰ" ወሽመጤ ሰባት ቦታ ተከፈለ። ሞቅታዬ ሁሉ ጠፋ። ሞቅታ ነበረ ስካር?....ብቻ መካሪ ጓደኛዬን ካቀረቀርኩበት ስልኬ ቀና ብዬ ፈለኩት። ከአንዷ ጋር ይደንሳል። እሷ ትስቃለች... እሱ በርሃ ላይ ጊንጥ ያስደነበራት ግመል ይመስል በሀይል እየተቀነጣጠሰ ይውረገረጋል። በሳቀች ቁጥር ያበረታታችው እየመሰለው መውረግረጉንና መቀነጣጠሱን በአምስት እጥፍ ያህል ከፍ አደረገው። መቼም ወንድ የሴት ጥርስ አይከፈትለት...የገነት በር ተከፍቶ በደስታ እየዘለልክ ግባ ተብሎ የሚዘል ይመስል ሰው ሁሉ እንዳበደ ይመለከተው ጀመር። 'ይሄ ጊንጥ... እኔን እምቅ ችሎታ አለህ ብሎ ጉድ ይስራኝ። እኔማ ተውም አልለው ይዋረዳት።ምን አገባኝ' ብዬ በውስጤ ዝም ብዬ ማየት ጀመርኩ። ቆየት ብሎ የቤቱ ጋርድ መጣና "ብራዘር...ጀለስህን አረጋጋው የዳንስ ወለሉን እኮ ብቻውን አጨናነቀው።" ብሎ በደረቱ አጨናንቆኝ ሄደ። ለሀጣን የመጣ ለፃድቃን ይተርፋል ነውና ነገሩ "አንተ ወረታው... አንተ ወረታው ...ወረታው...ወሬ...ና ቁጭ በል" ብዬ ከልጅቷ አላቀኩት። በስካር አንደበቱ "እሙዬ...የኔ እናት..ሌላ ግዜም እምቅ ችሎታዬን አሳይሻለሁ...ተመችቻታለሁ እኮ" እያለ ስልኳን ተቀብሎ ተቀመጠ። እንደተቀመጠ ስልኬን አዙሬ "እምቅ ችሎታ አለህ ብለህ የሰራኸኝን አየኸው?" አልኩት ቆጣ ብዬ " ፐ...." አለኝ "ፐ!....ምንድነው ፐ?" አልኩት "አብርዬ የምር ደስ ብሎኛል።አካውንትህ ሊተኮስ ነው" አለ ጮክ ብሎ... የተኩስ ነገር ያሳሰባቸውና... አካውንት ሲባል ገንዘብ የሚያባንናቸው ገልመጥ ገልመጥ አድርገው ወደ ወንበራችን ተመለከቱ። ጋርዱ ድጋሚ ጠጋ አለኝና " ጀለስህን አረጋጋው....ፖለቲካ ማውራት አይቻልም።" ብሎ ሁለተኛ አስጠነቀቀኝና ዞር አለ። "ወረታው ድምፅ ቀንስ.... " አልኩት "ለምን ብዬ በሀገሬ....አንተም በአንድ ጡንቻ ራስ እባብ መባልን..." "...ኧረ ወረታው በማርያም ዝምበል" ብዬ ተማፀንኩት "አብርዬ ሙት....እደግመዋለሁ ...በአንድ ጡንቻ ራስ ኮመንት እባብ መባል ከብረት የጠነከረ አለት ሊያደርግህ ይገባል እንጂ አያስደንብርህ። አብርሽ አለት ነህ....የምር አለት ነህ" ብሎ ጠረጴዛውን በኃይል ደቃው ጋርዱን ሸረፍ አድርጌ እያየሁት " ወረታው....አዎ አለት ነኝ በቃ....ስለ እምቅ ችሎታችንም ውጪ እንመክርበታለን...ጠጣ ዝም ብለህ.." ጋርዱ ትዕግስቱን እንደጨረሰ ያስታውቃል " ምክክር .... ወይ ምክክር.... ይሄሄሄ አሁን እራሱ ምክክር ብለው ሊመካከሩ የገቡት ሁላ ስድስቱ ይሄኔ እየተጣሉ ነው። ምንም ምክክር አያስፈልግም...እንደ ሀገር" ጋርዱ መጣና "ኑ እስቲ ውጪ እናውራ" አለ "ወንድሜ እዚህ ብናወራስ..." አልኩት ወረታው ከእኔም ከጋርዱም አፍ ቀድሞ "ምንድነው ኧ ፀብ ነው?...እንደ አለት የጠነከርን መሆናችንን አላወቀ። ና ውጣለት..…የወንዱ ልጅ" ብሎ ቀድሞ ወጣ። እኔም ተከተልኩ። እንግዲህ ይሄን ፅሁፍ ስከትብ 'አለቶቹ' እኔና ወረታው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በአንድ ክፍል ጎን ለጎን ተኝተን መሆኑ እንዳይረሳ። Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
እንዴት እንደዚህ አይነት መዘፈቅ ውስጥ እንደገባሁ አላውቅም። ተገናኝተን እንደተለያየን 'ከዚህ በኃላ ይሄን ነገር አቆማለሁ' እያልኩ ለራሴ መሀላ እንደደረደርኩ ነው።ሳገኘው ግን ሁሉም ነገር በእኔ ብሶ ቁጭ ይላል። ማህሌት እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ትገባለች ብሎ ማን ያስባል? እንኳን ሌላ ሰው እኔም አላስበውም ነበር። የጠሉት ይወርሳል ሆነና መገኘት ያልፈለኩበት ላይ ተገኘሁ። አብረን ተኝተን እያለ ስልኩ ጮኸ እያቀበልኩት ጥሪውን ስመለከት "ሚስቴ" ይላል። ማቀበሌን ትቼ ቀዩን ተጭኜ ዘጋሁት። "ያምሻል እንዴ..." ብሎ በቁጣ ስልኩን ከእጄ ወሰደው። እንደተናደደ "ሳታውቂ የገባሽበት አታስመስይ..." እያለ ድጋሚ ለሚስቱ ሊደውል ስልኩን መነካካት ጀመረ። ቃል ሳላወጣ ተነስቼ መታጠቢያ ቤት ገባሁ። ሻወሩን እስከመጨረሻው ከፍቼ ውሀ ውስጥ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። ያቺ ሀይማኖተኛዋ፣ ትጉዋ፣ በራሷ የምትተማመነዋ፣ ከአቋሟ ዝንፍ የማትለዋ፣ ለክብሯ የማትደራደረዋ ማህሌት በየት ቅያስ አምልጣኝ ዛሬ እዚህ ጋ እንዴት እንደቆምኩ አላውቅም። ሰውነቴን ተጠየፍኩት። በሴክረተሪ ተመርቄ በአንድ ድርጅት ስራ ስቀጠር የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እሱ ነበር። "ኦ አንቺ ነሽ ፀሀፊያችን Welcome welcome...አሮን እባላለሁ" ብሎ ተዋወቀኝ.....ምኑም ደስ ይላል ቁመቱ፣ አለባበሱ፣ ሳቁ፣ ጨዋታ አዋቂነቱ... እንዲህ እያልኩ ብዘረዝርም አይበቃውም። የድርጅቶቹ ባለቤቶች እሱን በሚሰራበት ቦታ ላይ ለማስቀጠል ሲሽቆጠቆጡለት ሳይ ደግሞ ምን ያክል ቁልፍ ሰው እንደሆነ ለመረዳት ቀላል ነበር። በኃላ ስሰማ መኪና እራሱ በስጦታ አበርክተውለታል። በአጠቃላይ የታደለ ነው። ከስራ ወጥቼ መንገድ ላይ "ፀሀፊያችን ግቢ እንጂ..." ብሎ መኪናውን አቆመልኝ ገባሁ። "ስምሽን አልነገርሽኝም ወይስ ፀሀፊያችን እያልኩ ልቀጥል?" ሳቀ...እየሳቅኩኝ "ማህሌት..." ብዬ እራሴን አስተዋወኩ "ኧረ ባክሽ... የባለቤቴም ስም ማህሌት ነው። ግን ሚስቴ ቆንጆ ናት " ሳቀ። ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ገባኝና ዝም ስል "አንቺም ቆንጆ ነሽ ስቀልድ ነው" ደግሞ ሳቀ...እየተሽኮረመምኩ ሳቅኩ (በህይወቴ ለመጀመሪያ ግዜ ተሽኮረመምኩ).... የግራ እጅ ጣቱ ላይ ቀለበቱን ለማየት መሪው ከለለኝ። ሸኝቶኝ ከመኪናው ስወርድም ጣቱ በግልፅ ሊታየኝ አልቻለም "እስቲ እጅህን" አልለው ነገር... ጠዋት ቢሮ ስገባ የመጀመሪያ ስራዬ የሆነው ጣቱን ማየት ነበር። ጣቶቹ ዘለግ ብለው ያምራሉ። ያደረገው ቀለበት ጣቱ ላይ ይበልጥ ያምራል። ምንም ነገሩ ላይ ውበት አለ። ከቢሮው ወጣሁ 'ትዳር እንዳለው አወቅሽ አይደል? ምን ይፈጠር ነው የምትይው ፈጣጣ አትሁኚ ማህሌት' እራሴን ወቀስኩ በሶስተኛ ወር ከንፈሩን ሳምኩት ቢሮ ውስጥ.... ከዛ ሁለታችንም ተፋፈርን። እኔ ስለገፋፋሁት ደሞ ይበልጥ አፈርኩ። በሌላኛው ቀን እሱ ሳመኝ። መሳሳም ኖርማል ሆነ። በ አምስተኛ ወር room ያዝን።ሁኔታችን የእብደት ይመስል ነበር። ደጋገምነው። ከሆነ በኃላ እሱም እኔም እንፀፀታለን ማቆም ግን አልቻልንም። ሁለት ዓመት ይሄ ነገር ቀጠለ ሚስቱን ይወዳታል። ከእሷ ሁለት ልጆች አሉት። እኔን እንዴት እንደሚመለከተኝ አላውቅም.….ብቻ... ፎጣ ጣል አድርጌ ከሻወር ወጣሁ ልብሱን ለባብሷል ሱፍ ያዘወትራል ተጠጋሁትና ባሏን ወደስራ እንደምትሸኝ ሚስት ከረቫቱን አስተካከልኩለት..…"ቢቀርብንስ" አለኝ። ለ መቶኛ ግዜ እንዲህ ሲለኝ እኔም ለመቶኛ ጊዜ "ከዚህ በኃላ አይደገምም" አልኩት። ልብሴን ለባብሼ ቤት አድርሶኝ ወደቤቱ ሄደ። በቀጣይ ቀን ቢሮ ተገናኘን...እንደተነፋፈቅን በዓይናችን አወራን... በድብቅ የምንገናኝበት ቦታ እንድንገናኝ በዓይናችን ተነጋገርን። ተገናኘን ድጋሚ ወደቅን...አበድን። ምን አይነት ሴጣን መሀላችን እንደገባ አላውቅም። ይሄ ሰይጣን ነው እንጂ ሰው እንዴት እንዲ ይሆናል? #ሰይጣን:- "አልቀረብሽም....ምን አባሽ ላድርግሽ ስሜን እንዳትጠሪ። አሁንስ አልበዛም እንዴ... እዛው በፀበላችሁ...ሰበበኛ" Abrham F. Yekedas
без подписи
Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
@HAKiKA1 #አለሁ
@HAKiKA1
@HAKiKA1
የቀሬናው ስምዖን ድንገት በመንገዱ ከክፉ ቀን ግማሽ ከደግ ቀን በአንዱ ሄዶ ተረማምዶ መንገዱን ሳይጨርስ ተብሎ ተጎተተ "ና... ይሄን ሰው አግዝ" አቅማምቶ ተጠጋ ከአንድ ምስኪን ገላ ደም ከለዋወሰው በአዳናቸው ሳይሆን በሚገርፉት ብቻ በተከበበ ሰው ግማደ መስቀሉን እንደቻለው አቅም አብሮ ተሸክሞ ከባለ ፍዳው ጋር ገፍቶ ያንን ዳገት... ወጣ ቀራንዮ ተመልከት እንዲ ነው አንዳዴ የህይወት ጎዳና የግድ ተጎትተህ ድንገት ከመከራው ገፈት ትቀምስና ካሰብከው ዘግየተክ ከአለምከው አርፍደህ መድረሻህ ይርቃል ለፅድቅ መታጨትን አንተ አትረዳውም የእግዜር ልብ ግን ያውቃል። እንግዲህ ለባለ መንገዱ ለቀሬናው ስምዖን በገጠመው ሲሳይ በስቃይ እንዲያ መሆን ምን ይሆን ምላሹ ለዚህ ኩነት ምንዳ? አምላኩን ለረዳ... Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
@HAKiKA1
እንዲ ነበር እንዴ? የእሷነቷ ፊደል ውስጥ ሀሳቧ ሁሉ ያውቅ ነበር ወይ በደል እንዲ ነበር እንዴ? ስቀምሰው የእሷ ጣ'ም (... ገረመቺኝ በጣም) ከሰቀልኳት ሰማይ አራሷን ፈጥፍጣ ከውሸቷ ጭብጥ እውነት ተፈልቅቃ እንዳላሰብን በፍቅር የነገን ጎዳና እንዳላወጋነው ስንቱን ቀና ቀና እንዳልታየን ሁሉ የተስፋችን ፋና ዛሬ ሲሆን ባዶ ደርሶ ሲሆን ወና ነገሯ ሲገባኝ..... ከቅኔ ህብረቃል ሰም ወርቋ ሲረዳኝ እኔና እሷ ብዬ ስንቱን እያሰብኩኝ ልብ ልቧን ታይቶኝ እጅግ ተደንቄ ታዝቤያት አበድኩኝ። Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
#March_21 @HAKiKA1
አሁን በቀደም ለት ማጣት አስከፍቶኝ ጭምት ትክዝ አርጎ ከጎዳና ጥሎኝ... አላፊ አግዳሚውን ቁጭ ብዬ እየታዘብኩ አልፎ አልፎ ሲበላኝ ጀርባዬን እያከኩ እንደተኮራመትኩ በተቀመጥኩበት ደስታ ባጣ አርኪ ሀዘን እንደገባኝ ፊቴ መጣ ድንገት ልጅ እግር ሰባኪ አቋሙን በሚያስንቅ በአስገምጋሚ ድምፁ ፀሀይ በዋለበት በጠቆረ ገፁ መንፈሳዊ ሞራል ባጀገነው አቅም "ገንዘብ ደስታ አይገዛም ንዋይ አያስቅም፤ አታልቅስ በችግር አትሳቅ በጥቅም!" ብሎ አዥጎደጎደው ሰበካውን ሁሉ በቆንጆ ቆንጆ ቃል፤ ሰማሁ ሰማሁና እኔ ምርር ብሎኝ ጮሄ ተናገርኩኝ የራሴን አባባል... "ስሙኝ ወገኖቼ ከፊሉ ስህተት ነው የዚህ ሰባኪ ቃል፤ በመኖር ኡደት ውስጥ ህይወት ተዘርቶበት ሰው ለምድር ሲጣል፤ ገንዘብ ደስታ አይገዛም ነገር ግን...ማጣት ደስታ የሳጣል። አይጣል... (ይሄ ነው እውነታው...) (ስማኝ) ቃሌ "እህ..." አስብሎ ሰሚ ባገኝ ጆሮ ተቸግሬም የሰው ዓይን ባይርቀኝ ኖሮ ስለሌለኝ ብስቅ ማጣት ቢያስደስተኝ እዚ ጎዳና ጥግ ምን አኮራመተኝ? በዝምታ ልኑር አሁን በቃ ተወኝ! ...ተወኝ" Abrham F.Yekedas @HAKiKA1
"ታውቂያለሽ? ለመጀመሪያ ግዜ ስመለከትሽ የወደድኩልሽ አይንሽን ነው" ፀጉሯን እየነካካሁ ስላት "እኔ ደግሞ ፈለግህን..." አለችኝ። "ፈለግ...ማለት ...?" "ማለትማ የኔ ካጠገቤ ተቀምጠህ እኔ ጎንበስ ብዬ መፅሀፍ እያነበብኩ አልነበር። ወደአንተ ለማየት ዓይኔ ሂደቱን ሲጀምር ከማርያም ጣትህ ነበር፤እዛች ጣትህ ላይ ፈለግ ነበረች..ከጥፍርህ ስር ሆና ከጣትህ ህይወት ተነጥላ ገንጠል ያለች ልውደቅ አልውደቅ የምትል ፈለግ ከዛ ወደድኳትና አንተን ማየት ትቼ ብዕሬን አውጥቼ 'ፈለግ' የሚል ሶስት ገፅ ግጥም ፃፍኩ።" "አይ በጣም ጎበዝ.... ያኔ ጨምድደሽ ስትጥይው ያቀበልኩሽ ወረቀት ስለፈለጌ የፃፍሽው ነው?" " አዎ አንጓው አልጥም ስላለኝ ጣልኩትና ሌላ ጀመርኩ....አቀብለኸኝ በዛው ተግባባኸኝ....ነፍስህ ጥበባዊ ስለሆነ ደስ አልከኝ። ማን አጎንብሶ የወደቀ ያቀብላል?" ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ገብቶኝ... ዝም አልኩ። "ቆይማ ላንብብልህ...?" "ምን..?" "ፈለግን ...." "ፈለግ?...እ ግጥሙን አይ ይቅር እማ ተይ ..... ስንጋባ" ተማፀንኩ። "ውይ ትንሽ እኮ ነው....አስፋፍቼው ስድስት ገፅ ሆኗል እንጂ..." ቦርሳዋን ከፍታ ቀይ አጀንዳዋን ብቅ አደረገችው። እንግዲህ የተቀመጥንበት ካፌ ሊበጠበጥ ነው። "ተይ እማ....ሌላ ቀን ተይ....ይሄን ቀይ አጀንዳ መልሺው ....እያጥወለወለኝ ነው" "አይ እንግዲህ አነብልሃለው... ።...የግጥሜ ርዕስ ፈለግ.... አንቺ የጣት ፈለግ ተበጠሽ ከጣቴ፤ ዝርፍፍ አትበዪ ከማርያሟ ጣቴ፤ ጥፊልኝ ከፊቴ....ከወጣትነቴ..." ''ወይኔ በላቸውውውው.... ምን ብበድል ነው ያንቺ መጫወቻ ያረገኝ።" ከገጣሚ ጋ መፋቀር ትርፉ ይሄ ይሁን በቃ?😒 Abrham F.Yekedas @HAKiKA1
"ቁርስ ምንድነው እማ?" አልኳት....ከተጋባን ጀምሮ ሚስቴን እንዴት 'እማ' ማለት እንደጀመርኩ አላውቅም...ብቻ ከየት እንደሰማሁት እንጃ ምላሴ ላይ ታትሟል። "ፍርፍር ነው አባ..." አለች ከሁለት ክፍል ቤታችን ጓዳ ውስጥ ሆና እያንጎዳጎደች። 'ስትንጎዳጎድ ዶሮ የምትሰራ አትመስልም?' ብሎ ውስጤ ሀሜት ጀመረ። 'ተው እንጂ አብርሃም! ገና በሶስት ወር አፍላ ትዳር ሚስትህን በውስጥህ ልታማት?' ብዬ እራሴን በራሴ ገሰፅኩና ዝም ብዬ ማሰላሰል ጀመርኩ። ' 3 ወር ....90 ቀናት... የመጀመሪያ 10 ቀናት የጫጉላ ሽርሽር ደብረዘይት ሄድን። ምግብ ካረፍንበት ሆቴል ስንበላ ነበር። ከተመለስን በኃላ 10 ቀናት እናቷ ታመው ልታስታምም በመሄዷ ምግብ ውጪ ስበላ ነበር። ከዛ እናቷ ተሽሏቸው ከመጣች በኃላ ለ 70 ቀናት ቁርስ ፍርፍር፣ ምሳ ውጪ፣ እራት ፍርፍር ...እንዴት እንዴት ነው ነገሩ ጎበዝ?.... ትዳሬ ላይ ጥልቅ ተሀድሶ ማድረግ እንዳለብኝ እያሳሰበኝ ውስጤ 'አካሄድ...' አለ። "እ...እማ" አልኩ ውስጤ ፈራ ተባ እያለ "ወዬ አባ..." እሷም አባ ማለት በቅርቡ ያመጣችው ነው። ምን አልባት እኔ 'እማ' ስል ለትክክለኛው አፀፋዊ ምላሽ ብላ ይሆናል። "እንደው ግን ....እንደው... ይሄ ነገር አልበዛም..." "ምኑ...?" ድምፅዋ በጣም ትንሽ የሆነ መጠነኛ ቁጣን አዝሏል። ሌላ ሰው ቢሆን አይረዳውም። ባል በመሆኔ ብቻ የሚገባኝ እኔ ብቻ ነኝ። "ፍርፍሩ.....ጨጓራዬ ተፈረፈረልሽ እኮ....ትንሽ ሌላ ነገር ቀልቀል ብታደርጊስ ካልሆነልሽም በርበሬዋን ቀነስ... አለ አይደል" አልኩ በትህትና እና በቀልድ ለማለዘብ እየሞከርኩ... "ምን?" እያለች ከጓዳ ወጣች። አስተያየቷ ያስፈራል.... ጆሮዋ ላይ ጣል ጣል ካረገቻቸው ሁለት የሽንኩርት ልጣጮች፣ ከሻሿ አምልጠው የወጡ የፀጉር ዘለላዎች መንጨባረር ጋ አስፈሪነቷ ይበልጥ ሆነብኝ። "አይ ማለቴ እኮ ለጨጓራችን እኮ ነው። ደሞ...." "ደሞ ምን?" አይኗ ፈጠጠ "ፍር...ፍር ...ፍርፍር..ሙያ አይጠይቅም ይሉ የለ...." አስተያየቷ አንገቴን አሰበረው "ምን ማለት ነው....ፍርፍሩ ስሰራ ውሀውን በሙያዬ መሠረት ባላመጣጥነው እንደ ጫጩት ፍትፍትህን ትበላ አልነበር?" ወገቧን ያዘች... "አሃሃ....የወንዱ ልጅ!...ማንን ነው ጫጩት አንቺ?....እኔ ሌላ ሙያሽን አሳይኝ ባልኩ ነው ጫጩት የምትይኝ። 70 ቀን ሙሉ ፍርፍር ስትቀልቢኝ እኮ ዝም ያልኩት ካንቺ ይምጣ ብዬ ነው። ቴስቲሶያ እንደጉድ በሞላበት ሀገር አንድ ቀን እንኳን እሱን ልስራ ብለሽ አታውቂም።... ቴስቲሶያ ይቅር ኢንዶሚ እንኳን ቀቅሎ ማቅረብ ያቅትሻል?....I'm really sorry... አዝናለሁ።....ጆሮሽ ላይ ያረግሽውን ደሞ አንሺ....ሴት ልጅ ሽንኩርት አያቃጥላትም። ምን እዛ..." የ70 ቀን ብሶት ድንገት ፈንቅሎኝ ከአፌ ተዥጎደጎደ። "አሃ ...እኔ ሜላት ሴት በመሆኔ ለአንተ አጥሚት....ጭኮ...ቡላ...ገንፎ እያልኩ መኖርና መቀለብ አለብኝ?.... አለብኝ ወይ!?" አለች እዛው በቆመችበት ወገቧን ይዛ "ጭኮማ...በምን ዕድሌ...." ብዬ ዝም አልኩ....ቅድም የለፈለፍኩት ቁርስ ካለመብላቴ ጋ አድክሞኛል። ጭኮ በፊቴ ውል አለብኝ። "ትሰማኛለህ?...እንግዲያውስ በዓይነት በዓይነት የምትቀልብህ ጋ መሄድ ነዋ....እንደውም ይሄ ትዳር ሰልችቶኛል...በቃኝ።" ቀና ብዬ ዓይኗን አየሁዋት.... "ምን...በሶስት ወር ትዳራችን በቃሽ?..... ለካ ይሄ ሁሉ ቀመር ለዚህ ነው። በፍርፍር አማረሽ እኔን ለማብረር የተነሳሽው። ህምም... እኔም ይሄ ትዳር በቃኝ ጨርሻለሁ። እክክክክ..." ተነስቼ ከቤት ወጣሁ ከዛ ወዲህ ትዳራችን ቀዝቅዞ....ቀስ በቀስ ለፍቺ ደረሰ። የፍቺ የምስክር ወረቀት ልንቀበል ወሳኝ ኩነት ወረፋ ይዘን ባሎች በግራ ሴቶች በቀኝ ተቀምጠናል። ከጎኔ ያለው አንድ ፊቱ መጠጥ ያለና ፀጉሩ እስከመሀል አናቱ ጥሎ የሸሸው ሰውዬ በእጁ የያዛትን ጉርድ ፎቶ ቀና አድርጎ እያሳየኝ "አሁን እኔ እመስላለሁ?" አለኝ። " እንዴ...እንዴ...አንተ ነህ?" አልኩት አንዴ ፎቶውን አንዴ እሱን እያየሁ በመገረም። ጎፈሬው ግጥም ያለና ፊቱ ሞላ ያለ መልከ መልካም ወጣት አሁን በዚህ ልክ መለውጡ እየገረመኝ ጠየኩት... " ታድያሳ...የሚመጥ ይምጠጣት። እንደ ቀሰም ምጥጥ አርጋ ጨረሰችኝ....በቀደም በህልሜ ነጭ መልአክ መጥቶ .... 'ሰውዬ አልቀህ መሞትህ ነው። የፍቺ ሰርተፍኬት በእጁ አድርጎ እያሳየኝ አምልጥ...አምልጥ...አምልጥ' ሲለኝ አደረ...ይኸው በፍቺ ላመልጣት ነው። አንድዬ ትቶ አይተወኝ" "ምን ነገረኛ ሆናብህ ነው?" አልኩት "እሱም አንድ ነገር ነው። ግን ዋነኛው ሌላ ነው።ምኑን እደብቅሀለው ወንድሜ፤ አብረን ቁጭ አልንም አይደል? ቁስሌ ቁስልህ ነው።....ለሊት አገላብጠኝ ነው፤ጠዋት ፍርፍር....ለሊት አገላብጠኝ ነው፤ ጠዋት ፍርፍር...ለሊት አገላብጠኝ ነው፤ ጠዋት ፍርፍር....ዘይቴም ጨጓራዬም እኩል ተቃጠሉ። ሆ ብሎ ምድሩን ቀውጢ አድርጎ በዳረን ሰፈርተኛ ፊት በሽታ እንደያዘው እያደር በመሀል ሾቅኩ....ህምምም " በጣም ግብግብ እያለና እግሩን መሬቱ ላይ እየተመተመ ነው የሚያወራኝ... ትንሽ ፋታ ወሰደና "አንተስ ምን ሆነህ ነው?" አለኝ። የእኔን ለፍልፌለት የእሱን ሳልሰማ እንዴት አለ መሰለኝ በውስጡ... "ያው...ምን ባክህ....የኔም ፍርፍር ነው" አልኩት ፈገግ እያለ"ወዳጄ ሙት አታምነኝም እንጂ ፍርፍር ብዬ ጠርጥሬ ነበር፣... አመላቸው እ ሳት ...ፍርፍራቸው እሳት... ይሄኔ እኔና አንተ እዚህ ጋ ለፍቺ በተቀመጥንበት ቅፅበት ስንቱ እየተዳረ ነው 'አልሰሜን ግባ በለው'። እዛጋ የተቀመጠውን አየኸው..." አለኝ ወደአንዱ ገርዠፍ ብሎ ወደተቀመጠ ወንድ እያመለከተኝ... "አዎ...." አልኩ ወደ ሰውየው እየተመለከትኩ "እሱም እንዲሁ....በፍርፍር ጉዳይ ነው ፍቺው...ግን ከእሷ ውጪ እንዴት ልኖር ነው ብሎ ልቡ አዝኗል... " "ይገርማል...." ብቻ ይሄን ፍርፍር ግን ከሃገር የሚያሶጣልን ከሌለ ምናምን ፐርሰንት ትዳር እየተፈረፈረ ማለቁ ነው። ነጋቲ! Abrham F. Yekedas @HAKiKA1
без подписи
አልተገላገልኩት... በዕንባ ተንሰቅስቄ ወይ "እፎይ" አላልኩት... ከት ብዬ ስቄ ጨክኜ አልጨለጥኩት... ልክ እንደውሀ ጥም ሃክ እንትፍ አላልኩት... ለአፍ እንደማይጥም እንደ ክፉ ሽታ... ወይ አልሰነፈጠኝ ለአፍንጫ ተስማምቶ... መዓዛ አላወደኝ መሀል አቁሞ ነው ጊዜ 'ሚሸውደኝ። Abrham F. Yekedas @HAKiKA1