የግጥም መድበል
Статистикаእናንተ ለግጥም ጆሮ የሰጣችሁ እናንተ ለግጥም የበራ አይናችሁ እናንተ ግጥምን ያከበራችሁ ይሔው ማረፊያ ቤታችሁ። ኑ! ጉልበታችሁን እጠፉት። ግጥም አስተያዬት ካላችሁ @Tilahunab48 ላይ ማድረስ ተፈቅዶአል።
- Последний пост
- 2 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 106
- 1/48двое суток
- 121
- 1/72трое суток
- 131
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አለም ውጥንቅጣም አለም ቁንጥንጣም አለም እንቶ ፈቶ አትጨበጥ ከቶ ይሔው ደስ ይላታል ፤ ቀን ሲያንገዳግደኝ ስኖር አልጥማትም ፤ ስሞት የምትወደኝ።
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ° ብሸፍትም ሰው ስገድል.. ስትጠራኝ ሳትሸነግል.. ቀስቴን ጥዬ ተሸነፍኩኝ አንተን ሳይህ 'ረገፍኩኝ፨ ድንገት ራደች ሰዉነቴ፣ ተፈታልኝ ሰንሰለቴ፨ ° ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትለውጥ ለካ እንዲ ነህ ሰው ስትጠራ፣ ጨካኙን ልብ ደግ ያልሰራ፣ ታኖራለህ ስታራራ፨፨ ° ለካ እንዲ ነህ ስታንኳኳ፣ ጻዲቅ ሆነ ገዳዩ እንኳ፨! [ዓለም] @myPoems396
ዞረው አላዩትም ፤ መድረሻ ሲጠፋው እኔን-ም መቼ አሉት ፤ እንቅፋት ሲያዳፋው ሲኖር በምድር ላይ ፤ ስሙን ቢረሱትም ሲሞት ቀብር ሔዱ ፤ ተጥራርተው ከየትም። ዘመድ ግድ የለውም ፤ የቆመን ይረሳል ግን ደግሞ፤ ህይወት እየገፋ ፤ ለሞት ይደግሳል። ✍እኔን ባይ
ብዙ ነው ጉዴ፤ ቢነገር እንኳን ፤ መች ተጨርሶ እኔ እንደዚህ ነኝ፤ ቀብር የምደርስ ፤ ለራሴ ለቅሶ። አይገርምም
ካጋደልኩበት ተነሳሁ ፤ ልወድቅ ተንገዳግጄ በግሮቼ መራመድ ያዝኩኝ ፤ ቢሆንም ትንሽ አርፍጄ መጎዳት ቢያመረቅዝም ፤ ይድናል ቁስሉ ጠግጎ መጥኔ ብያለሁ ላንች ግን፤ ለቻልሽው ሰውን መበቀል ፤ እንዳይሞት እንዳይሽር አርጎ።
እንዳውም ዘንድሮ ፤ያደርገኝ ጀምሯል ፤ እንደመንገዳገድ መውደቄ ካልቀረ ፤ ባክሽ አንድ ጊዜ ፤ ሳሚኝ እና ልበድ። ሳቅሽ ያሽኮርምመኝ፤ ፈገግታሽ ያድክመኝ፤ ለስላሳ ከንፈርሽ ፤ መሐል ጉንጬን ይንካው በጆችሽ ደባብሽኝ፤ የሰውነቴ ጫፍ ፤ ይጣፍጥ በረካው በደስታ ቀን እንጅ ፤ በዘመን አይደለም መኖር የሚለካው ነበር እስከምባል ፤ አፈር እስኪበላኝ ባንቺ በኩል ልርሳው ፤ መኖሬን ሳይደላኝ ለየለት ተብዬ፤ አበደ ተብዬ፤ ሳልታክት ሳይደክመኝ ፤ ስምሽን እንድጠራ ስንገዳገድ ድረሽ፤ ነይ እንተቃቀፍ ፤ ትንፋሽ እንጋራ ማበዴ እንደሁ አይቀር ለየለት ተብዬም ሰበብ ሁኝ ለማፍቀር። ✍እኔን ባይ
ሔድሽ አሉኝ እሰየሁ ፤ መራቅሽን ሰማሁ ድሮም አትመጥነው ፤ አሉኝ ሰፈር ታማሁ። የምል መሠላቸው ፤ ስብርብር እንክትክት እኔ እንደው ለመቆም ፤ ከመጣር አልታክት የሔደን መርሳት ነው ፤ የማሰብ ምልክት። ✍እኔን ባይ
ዝም ስል ጠልቸሽ አይደል ከፍቅርሽ አላውቅም መጉደል ናፍቀሽው ባትገቢ እቅፌ ከመምጣት መቼ አርፌ። ባይፈጥንም እግሬ እንደ ፈረስ አልቦዝን ካንቺ ለመድረስ። እቅፍሽ ሲያጣኝ ቢበርደው ለብቻ ማደር ቢከብደው ምኑንም ምኑን ባይለምደው በምሬት መተው ሲዳዳሽ አስቢያት........... ነፍሴ ናት የምትረዳሽ። ✍እኔን ባይ
ከ2 ጃሞቦ በኋላ የተፃፈ ግጥም ከመጠጥ አልቦዝን ፤ ከስካር አልጎድል ሰው ቁሞ ይስቃል ፤ ራሴን ስበድል እኔ እንደሁ አይገደኝ የጃምቦ አልጣ እንጅ፤ ማደሪያዬን አልስት እያወላገደኝ። ደግሞ እኔ የለኝ ማዕረግ፤ እኔ ምስኪን ሀረግ፤ በጅማቴ የቆምኩ ፤ እኔ ነፍሰ ቀጭን ህይወትም አትገደኝ ፤ እንኳንስ ያንቺ ጭን።
ባል እና ሚስት ተጣልተው ሚስት ከላይ ሆና በቡጢ ስትለው አረ ተጋደልን ብሎ መጮህ ሚስትም አፍንጫ አፍንጫውን እያለች አብራው መጮህ ከዛ ጎረቤት እየተሯሯጠ ሲመጣ በላይ አደረገችውና ባል ከላይ ሚስት ከስር ሁነው ይደርሳሉ። ይሔን ጊዜ ጎረቤት 'በል ልቀቃት ልትገላት ነው' ሲሉት አረ እኔ አድስ ግልብጥ ነኝ አለ አሉ።
ሰው ድካምህን አይቶ ፤ አይታክት መጠቆም በመኖር መካከል ፤ ስንገዳገድ ልቆም ከወዳ ከወድህ ፤ ህይወት ሲፈትነኝ ካንድ አንች በስተቀር፤ ማን ነበረ ደርሶ ፤ ከመውደቅ ያዳነኝ ~~~~~ ቆርጨ እንዳልጣልሁት ፤ ተስፋ ይሉት ገመድ የለኝም እንዳላልሁ ፤ ተቆርቋሪ ዘመድ ራሴን ጣጥዬው ፤ የትም በየ ሜዳ ስሜ ነበር ሊሆን ፤ ከመኖር ሰሌዳ ሳጣጥር ሳቃስት ፤ እንዳይሆን ታምሜ በከንፈርሽ ጉልበት ፤ ስንቴ በረታ አቅሜ። ✍እኔን ባይ
ዕድል ወይም እጣ፤ ሔደን ስንመጣ፤ አልፈን ስናገድም፤ በዛም በዚህ ግድም፤ ድጋፍ ምርኩዝ አጠን ፤ መቆም የቸገረን ሠጠነው የማያልቅ ፤ ሙሉ ልብ ነበረን። ~~ ህይወት ስንክሳሯ ፤ አልፎ ሰው ባይረካም ነይ እና ገላግይኝ ፤ ከመገፋት ድካም።
ነገን ብቻ ፤ እስክለወጥ በእምነት ፀንተን ፤ እንቀመጥ ልጠብቅሽ ፤ ታገሽ አንችም ከወደድሽኝ ፤ አይሰለችም። እያልክ ከርመህ ፤ እስኪደላህ የስንቷን ሴት ፤ እድሜ በላህ?።
አረጋጋኝ እንጅ መኖር እንደ ፈቃድ እሱ ያውቃል ብሎ ስንት ነገር ነበር ልቤን ያስቧጠጠው የማያልፍ መስሎ።
ሻማዬን አበራሁ ፤ ጨለማው መች ጠፋ እሳቱን ባያይዝ ፤ ብርዱ ይባስ ከፋ እድሜዬን ስቆጥረው ፤ ወደ ሞት ተገፋ። ያልቀጠርኩትን ሰው ፤ መጠበቅ ደከመኝ ተስፋ ያረኩበት ፤ ተስፋ ቆርጦ አመመኝ። መቼ ነቃህ ቢሉኝ ፤ መቆሜን አላውቅም ከሔድሽ ጀምሮ ፤ መኖር አልናፍቅም። ድሮም... ንጉስ ያለዘዉዱ ፤ በምንም አይደምቅም። ✍እኔን ባይ
አልተሰናበትሽኝ ፤ በስራት በወጉ ምልክት አልተውሽም ፤ ለማፈላለጉ ዳናሽ አልተሰማ ፤ ከቤት ስትወጪ መቼ ጠረጠርኩኝ ፤ እንደምታመልጪ። ብቻ ግን ቀስ በቀስ ፤ ሲጨልም ይታያል እንደት ሰው በድብቅ ፤ ከወዳጅ ይለያል። እንዴ መጣሁ ብሎ፤ እንደት ልብን ጥሎ፤ እንደት ቃል ሳይጥሉ፤ ሩቂ ሒያጅ ሳይመስሉ፤ በድንገት ይተዋል ፤ የለመዱት ጠረን ተባብለን ነበር ፤ እንዘልቃለን አብረን። በመስኮት ትዝታሽ በበራፌ ነፋስ ፤ ሽውሽው ሽው ሽው ሲወዱሽ መራቅን ፤ ከቶ እንደምን ቻልሽው። ✍እኔን ባይ
በቅቶኛል ከእንግድህ አትበለኝ ወድህ የተማረ ይግደል በማን ሆነ እና ነው ይሔ ሁሉ በደል
ደርባባ ነሽ አንችም ልክ እንደወላጅሽ ስንት ጊዜ አልፌ ስንት ጊዜ አገደምኩ ላታይኝ በደጅሽ።
እንዳልሞት አረግሺኝ (በድሉ ዋቅጅራ) በትላንት አንቀልባ፣ ጊዜ ቢቸግረን፣ ከርመን ልንገናኝ፣ ቀጠሮ ነበረን፡፡ ደመናው ሲገፈፍ፣ ክረምቱ ሲወጣ፤ መርገምታችን አልፎ፣ ብሩህ ቀን ሲመጣ፤ በሚነጋው ጀምበር፣ ሰው መሆን ካደለን፤ ዛሬ የሳቀብንን፣ ጊዜን አሸንፈን፤ ከርመን ልንገናኝ፣ ቀጠሮ ነበረን፡፡ ግና ምን ያደርጋል፣ ከእድሜ የረዘመ፣ ቀጠሮ ሰጥተሽኝ፤ ቢከፋኝ ቢነደኝ፣ እንዳልሞት አረግሽኝ፡፡ ----------------
ካች አምና በከንፈር ገደፍኩት ሁዳዴን አምን ባጋማሹ አወቅኋት መውደዴን ዘንድሮም ለም'ረት ድጋሜ ቢመጣም መውደቅ ነው እጣዬ ምክንያት አላጣም ወይ አንቺ ቀርበሽኝ ወይ እኔ ፈቅጄ ስንት ጊዜ አለፈ በረከት በደጄ መድከሜን ታዝቦት እያዬኝ በሩቁ እስከ መች መቀጠል በመናፈቅ ሰበብ ሞት ላይ እየነቁ?። ✍እኔን ባይ