tgindex
የእውነት ሚዛን(ቴቄል)

የእውነት ሚዛን(ቴቄል)

Статистика

በዚህ ገጽ የተሃድሶን ምንፍቅና በእውነት ሚዛን እየመዘንን ቴቄል እንላለን። "ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀለህም ተገኘህ ማለት ነው" (ት. ዳን 5፡27) YouTube https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት @AbuNak @beorthodox

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
27
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 085
−4 за 5 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
415
27 постов
Вовлечённость
19,9%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 27
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
45
1/48двое суток
51
1/72трое суток
55

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • እቺ ትንሽ ለጸበልም ታስቸግራለች ሎል..

  • እቺ ትንሽ ለጸበልም ታስቸግራለች ሎል..

  • የክርስትና መልስ.apk

  • አፑ ጊዜ ስለሌለ ምንም ማሻሻያ አላደረኩበትም ባለበት ሁኖ ከለያ እስካሁን የተጻፉ ያለተጨመሩበትን ወደ 13 ተጨማሪ አርቲክል ብቻ ተጨምሮበታል

  • ካሁን በኃል እዚህ ቻናል ስለሥራ የማንለቅ ስለሆነ ስለሥራ የምትፈልጉ ይሄን ቻናል ተቀላቀሉ በቅርቡ ሥራ የምታገኙባቸው በታችሁ ሁናችሁ የምትሰሯቸው ሥራዎች እንለቅ አለን እንዲሁም ትሬደር ከሆናችሁ ሴት አፕ በነጻ ነው የምንለቀው @CryptotradersEth

  • 📢 ከቤት ሆናችሁ በስልካችሁ ዶላር መስራት የምትፈልጉ በሙሉ! 📢 ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ ወይም ካፒታል ሳይጠይቅ፣ በየቀኑ በስልካችሁ ማስታወቂያዎችን በማየት፣ አጫጭር ቪዲዮዎችን በመመልከት እና ቀላል ስራዎችን (Tasks) በመስራት ብቻ በዶላር የሚከፍል ታማኝ ዌብሳይት ይዥላችሁ መጥቻለሁ። እስካሁን ያልተመዘገባችሁ አሁኑኑ እድሉን ተጠቀሙበት! 👇 ለመመዝገብ ሰማያዊውን ሊንክ ይጫኑ፡ 👇 እዚህ በመንካት አሁኑኑ ተመዝገቡ! https://timebucks.com/?refID=221104254 ⚠️ አካውንታችሁ እንዳይታገድ እና ቦነሱ እንዲቆጠር እነዚህን 3 ነገሮች በጥብቅ ተግብሩ፡ 🔴 በGoogle (Gmail) ብቻ ተመዝገቡ፦ ከላይ ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ ስትገቡ በኢሜይል እና ፓስወርድ መፃፍ ሳይሆን "Sign up with Google" የሚለውን ቀይ ቁልፍ በመንካት ብቻ ተመዝገቡ። አለበለዚያ ሲስተሙ አካውንታችሁን ውድቅ ያደርገዋል። 🔴 VPN በፍጹም አትክፈቱ፦ ቪፒኤን (VPN) ወይም ፕሮክሲ (Proxy) አብርታችሁ ከገባችሁ፣ ሲስተሙ ወዲያውኑ ይይዛችኋል፤ የሰራችሁትም ሳንቲም አይከፈልም፣ አካውንታችሁም ይታገዳል። 🔴 በራሳችሁ ኢንተርኔት (ሞባይል ዳታ) ስሩ፦ በአንድ ዋይፋይ (WiFi) ወይም ሆትስፖት (Hotspot) ከአንድ በላይ ሰው አካውንት ከፍቶ መስራት አይችልም። ሲስተሙ ማጭበርበር አድርጎ ስለሚቆጥረው እባካችሁ እያንዳንዱ ሰው በራሱ ስልክ እና በራሱ የሞባይል ዳታ ብቻ ይስራ። 🎁 በየቀኑ እስከ $5 ዶላር የሚደርስ "Daily Streak" ቦነስ በቀላሉ ለማግኘት፡ ሳታቋርጡ በየቀኑ እየገባችሁ "Check-In" ስታደርጉ፣ ሲስተሙ ከቀን 1 እስከ ቀን 90 ድረስ በየቀኑ ተጨማሪ ነፃ ቦነስ ይሰጣችኋል። ቀን 90 ላይ ስትደርሱ ብቻ የምታገኙት የዕለቱ ቦነስ $5.00 ዶላር ነው! አጠቃላይ ከ 90 ቀኑ ብቻ $66.59 ዶላር ተጨማሪ ነፃ ቦነስ ይሰበሰባል። 📌 ነገር ግን ቦነሱ እንዳይቋረጥባችሁ ይህንን ህግ እወቁ፦ ከቀን 10 ጀምሮ፣ በየቀኑ "Check-In" ከመጫናችሁ በፊት ቢያንስ 1 ማናቸውንም አይነት የገቢ ስራ (Earning Activity) (ለምሳሌ ማስታወቂያ ማየት ወይም ታስክ መስራት) ማጠናቀቅ አለባችሁ። ዝም ብሎ ክሊክ ማድረግ አይሰራም። በአንድ ቀን ውስጥ መግባት ከረሳችሁ፣ የነበራችሁ የዕለት ቆጠራ ሙሉ በሙሉ ተሰርዞ ወደ ቀን 1 (Rookie ደረጃ) ይመልሳችኋል። ስለዚህ በየቀኑ መግባታችሁን አትርሱ! 🛠 ምዝገባውን እንደጨረሳችሁ አሁኑኑ ይህንን አድርጉ፡ 1️⃣ መጀመሪያ ወደ አካውንታችሁ ግቡና Settings -> User Profile ውስጥ በመሄድ ሙሉ ስማችሁን፣ አድራሻችሁን እና የልደት ቀናችሁን በትክክል ሙሉ (ይህንን ካላደረጋችሁ ሰርቬዮችና ብዙ ታስኮች አይከፈቱላችሁም)። 2️⃣ በመቀጠል "Earn" የሚለው ውስጥ በመግባት ያሉትን ቀላል ማስታወቂያዎች ማየት (Clicks)፣ ቪዲዮዎችን ማየት እና ታስኮችን መስራት መጀመር ትችላላችሁ። አሁኑኑ ተመዝገቡና ስራ ጀምሩ! 💰🔥 🔗 የምዝገባ ሊንክ፡ https://timebucks.com/?refID=221104254 check-in በማለት ብቻ በ90 የምትሰሩት 66.59 ዶላር ነው ብሮ 😁 የምትሰሩትን ሳይጨምር እንኳን  ሰነፍ ሰው እራሱ በ90 ቀን ይሄን መሥራት ይችላል

  • ብዙ ግዜ ስልክ ይዞ ሰው 500 ብር ፣ 1000 ብር አበድሩኝ የምትሉ ሰዎች በቃ ስልክ ይዛችሁ ከምትቸገሩ ለምን ይሄን አትሰሩም የምበላው የለኝም የሚልም አለ ስማርት ስልክ ይዙ ብሮ ወይ ሽጠው አሁን ስማርት ስልክህ ይዘህ የምበላው የለኝም አይመጣውም እኮ ለማንኛውም ከስልኩ ፍቅር ከያዘህ ይሄን ሥራ በቃ wifi እየፈለጋችሁ በዚህ ተመዝግባችሁ መሥራት ትችላላችሁ ምንም ሥራ ከሌላችሁ ደግሞ ይሄን ብቻ መሥራት ትችላላችሁ ከ5000 ብር በላይ በወር ታስክ መሥራት ብቻ ነው https://timebucks.com/?refID=221104254

  • አንድን ትውልድ በጠመንጃ ሳይሆን በሃሳብና በሞራል መግደል ይቻላል። እነዚህ ሰዎች ዝም ሲባሉ የሚከተሉት ጥፋቶች ይከሰታሉ፡- ዝሙትና ምንዝርና የሚበረታታበት ማኅበረሰብ ውስጥ ጠንካራ ቤተሰብ ሊኖር አይችልም። ቤተሰብ ካልኖረ ደግሞ የተረጋጋና በሥነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ አይወጣም። ይህ በቀጥታ የአገርንና የወደፊቱን ትውልድ መሠረት መናድ ነው። ባለሀብት ቢደፍረኝ በደስታ እቀበላለሁ" የሚለው ንግግር ለገንዘብ ሲባል ክብርን አሳልፎ የመስጠትን፣ ለቁስ መገዛትንና ራስን አለማክበርን ያስተምራል። ይህም ወጣቶች ለሥራና ለጥረት ሳይሆን ለብልሹ አቋራጭ መንገድ እንዲጓጉ ያደርጋቸዋል። ለክፉ ሰዎች መበራከት ምክንያት የሚሆነው የደግ ሰዎች ዝምታ ነው" እንደሚባለው፣ እንዲህ ያሉ አሳሳች ንግግሮች ሲሰሙ ዝም ማለት እንደ መተባበር ይቆጠራል። እውነትን ይዞ ዝም ማለት ሐሰት እንዲነግሥ መፍቀድ ነው። ዝም ስንል ወጣቱ ትውልድ "ይህ ነገር ትክክል ስለሆነ ነው ማንም የማይቃወመው" ብሎ እንዲያስብ እናደርገዋለን። እንደነዚህ ያሉ አስተማሪዎች ትውልድን የሚገድሉት በዝግታ በሚሰራ መርዝ ነው። ፍቅርን ከዝሙት፣ ደስታን ከኃጢአት፣ ክብርን ከውርደት ጋር በማደባለቅ ወጣቱን ግራ ያጋባሉ። ስለዚህ እንዲህ ያሉ አሳሳች ትምህርቶች ሲሰሙ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትና በማኅበራዊ ዕውቀት መቃወም፣ ትውልዱን ደግሞ ከእንዲህ ዓይነት "መንፈሳዊ መርዝ" መጠበቅ የሁላችንም ድርሻ ነው። Ezekiel 33 አማ - ሕዝቅኤል 8: ኃጢአተኛውን፦ ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ፡ ባልሁ ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። አይ በአደባባይ ልጅቷን ምናምን እንዴት የሰው ኃጢአት የሚሉ ሰውን ቀና ብለው የማያዩ ጻድቃን እና ትሁታን ሊኖሩ ይችላሉ ልጅቷ እኮ በአደባባይ ኃጢአቷን የገለጸችው እራሷ ነች የተገለጠን ኃጢአት እሸቱ እንደገለጠው አድርጎ ማቅረብ ምን ማለት ነው 😁 ኃጢአትን ልክ አድርጕ ለትውልድ ያቀረበን አካል መንግሥት ቢኖረን እንደውም ይች ልጅ መታሰር ነበረባት

  • https://youtube.com/playlist?list=PLauKSCsZrzHSFTpuFYWOFQQAYI-qMvo28&si=eFaBvo-i5VawD7eH

  • "ክርስቶስ 'እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን' ሲል አምላኪ (ፍጡር) መሆኑን ያሳያልን?" ለሚለው ጥያቄ፣ የቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያንና አምብሮስን ትምህርት መሠረት በማድረግ የቀረበ ምላሽ እነሆ፦ በዮሐንስ ወንጌል 4፥22 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሳምራዊቷ ሴት “እኛስ ለምናውቀው እንሰግዳለን” ማለቱ፣ በሥጋዌ ምስጢር ውስጥ ያለውን ድንቅ ትሕትና እና የባሕርይ አምላክነቱን በአንድነት የሚገልጥ እንጂ፣ እርሱ እንደ ፍጡራን የአምልኮ ዕዳ ያለበት መሆኑን የሚያሳይ አይደለም። ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ እንደሚያስተምረው፣ ወልድ ቃል በባሕርዩ አምላክ በመሆኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚመለክ እንጂ በአምላኪዎች ተርታ የሚመደብ አይደለም። ነገር ግን ሰው በሆነ ጊዜ የሥጋዌው ሥርዓት (Dispensation) እንደ ሰው ሆኖ መናገርንና መመላለስን ይጠይቅ ነበር። ክርስቶስ የባሪያን መልክ ለብሷል፤ የባሪያን መልክ መልበስ ደግሞ የባሪያን ተግባር መፈጸምን ያካትታል። ስለዚህ “እኛ” ሲል ራሱን በሥጋ ከአይሁድ ወገንና ከፍጡራን ጋር በመቁጠር ተናገረ። ይህም የሆነው አምላክነቱንና ጌትነቱን ትቶ ሳይሆን፣ የለበሰው ሥጋ የሚሻውን ሥርዓት ለመፈጸም ነው። ቃል ብቻ በነበረበት ጊዜ (ከሥጋዌ በፊት) ግን ለአብ ሲሰግድ የሚያሳይ አንድም ጥቅስ የለም፤ ምክንያቱም የባሕርይ አምላክ ስለሆነ። ጌታችን ስለ አምልኮና ስለ ግብር ያለው አቋም በባሕርዩ አምላኪ አለመሆኑን ያረጋግጣል። በሕገ ኦሪት እያንዳንዱ አይሁዳዊ ለቤተ መቅደስ ግብር (ዲድራክማ) እንዲከፍል ታዟል። ይህ ግብር እግዚአብሔር ገንዘብ ፈልጎ ሳይሆን፣ ሰው ሁሉ የራሱ ጌታ እንዳልሆነና ለአንድ ጌታ በባርነት የተመዘገበ መሆኑን ለማስተማር የተሠራ ሥርዓት ነው። ጌታችን በኢየሩሳሌም ሳለ ግብር ሰብሳቢዎች ጴጥሮስን በጠየቁት ጊዜ፣ ክርስቶስ አስቀድሞ “የምድር ነገሥታት ግብርን ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው ወይስ ከእንግዶች?” በማለት ጠየቀው። ጴጥሮስም “ከእንግዶች” ባለው ጊዜ፣ ኢየሱስ “እንኪያስ ልጆቻቸው ነጻ ናቸው” (ማቴ 17:26) አለው። እዚህ ላይ ጌታችን በግልጽ እንዳረጋገጠው፣ እርሱ የአብ የባሕርይ ልጁ በመሆኑ ለቤተ መቅደስ ግብር የመክፈል የባርነት ዕዳ የለበትም። ግብር ለመክፈል "ነጻ" የሆነው ጌታ፣ እንዴት ለባሪያ የተገባውን አምልኮ በባሕርዩ ያቀርባል? አምልኮ ራሱ "መንፈሳዊ ግብር" እና የባርነት አገልግሎት መጀመሪያ አይደለምን? መስገድና መንበርከክ የባሪያ ተግባር መሆኑ የታወቀ ነው፤ ክርስቶስ ግን የባሕርይ ጌታ ነው። አምብሮስም እንዲህ ይላል በክርስቶስ ሰብአዊ ስሜቶች ውስጥ እንኳ መለኮታዊ ግርማውን እናያለን። እርሱ እንደ ሰውነቱ “እኛ እንሰግዳለን” ይላል፤ እንደ አምላክነቱ ግን በአምላኪዎች ይሰገድለታል። ማርያም መግደላዊት በእግሩ ላይ ወድቃ ስትሰግድለት (ማቴ 28:9) አምልኮውን ተቀብሏል። ክርስቶስ "እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን" ማለቱ የትሕትናው ውጤት እንጂ የባሕርዩ መገለጫ አይደለም። እርሱ የማያውቁትን ያሳውቅ ዘንድ እንደማያውቅ መሰለ፤ የደከሙትን ያሳርፍ ዘንድ ደከመ፤ ወልድ እንደ እውነተኛ አምላክ ይመለክ ዘንድ ደግሞ እንደ አይሁዳዊ "እሰግዳለሁ" አለ። ስለዚህ ክርስቶስ እንደ ሰው ያመልካል ተባለ ፤ እንደ አምላክ ግን ይመለካል። "ልጆች ነጻ ናቸው" ያለው ቃሉ፣ እርሱ ከአምልኮ ዕዳ በላይ የሆነ የሰማይና የምድር ጌታ መሆኑን ለዘላለም የሚያረጋግጥ ነው።

  • አዳምና ሔዋን ገና ሳይበድሉ እግዚአብሔር "ብዙ ተባዙ" (ዘፍ 1:28) ብሎ ማዘዙ፣ እርሱ ገና ሳይበድሉ መበደላቸውን፣ ሳይሞቱ መሞታቸውን፣ ሳይወልዱ ደግሞ በምን መንገድ እንደሚወልዱ አስቀድሞ ስለሚያውቅ መሆኑን በሚከተሉት አሳማኝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ማረጋገጥ ይቻላል። እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ የሰጠው በጊዜ ገደብ ውስጥ ሆኖ ሳይሆን በዘለዓለማዊ ቅድመ-ዕውቀቱ (Foreknowledge) ሆኖ ነው። ማስረጃዎቹም እነሆ፦ ፩. እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው ያውቃል (ኢሳይያስ 46:10) እግዚአብሔር በኢሳይያስ ላይ እንዲህ ይላል፦ "ከመጀመሪያው መጨረሻውን፥ ከጥንቱም ገና ያልተደረገውን እናገራለሁ።" አዳምና ሔዋን ገና ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር እንደሚበድሉ ያውቅ ነበር። ስለዚህ "ብዙ ተባዙ" ሲላቸው፣ ከውድቀት በኋላ በምን ዓይነት ሁኔታ (በሥጋዊ ልደት) እንደሚባዙ አስቀድሞ አይቶ የተናገረው ትንቢታዊ ትእዛዝ ነው። ትእዛዙ የተሰጠው በገነት ቢሆንም፣ አፈጻጸሙ ግን ከገነት ውጭ ላለው ዓለም የታሰበ ነበር። ፪. መድኃኒት የተዘጋጀው ዓለም ሳይፈጠር ነው (1ኛ ጴጥሮስ 1:20) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ክርስቶስ ሲናገር፦ "ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ የታወቀ" ይለዋል። መድኃኒት የሚዘጋጀው ለሕመምተኛ ነው። ሰው ገና ሳይበድል እግዚአብሔር መድኃኒት (ክርስቶስን) አዘጋጅቶ ከሆነ፣ ሰው እንደሚበድልና እንደሚወድቅ አስቀድሞ ያውቅ ነበር ማለት ነው። ሰው እንደሚበድልና እንደሚሞት ካወቀ ደግሞ፣ የሰው ዘር እንዳይጠፋ "ተተኪ" የሚያስፈልግበትን የመራቢያ መንገድ (ብዙ ተባዙ የሚለውን) አስቀድሞ ማዘዙ የጥበቡ መግለጫ ነው። ፫. "ብዙ ተባዙ" እና "ምድርን ሙሉአት" የሚለው ትእዛዝ አገባብ እግዚአብሔር "ብዙ ተባዙ" ካለ በኋላ "ምድርንም ሙሉአት" አላቸው (ዘፍ 1:28)። በዚያን ጊዜ አዳምና ሔዋን የነበሩት በኤደን ገነት ውስጥ ነው። ገነት ደግሞ ከገኛ ምድር ተለይታ የምትታወቅ የቅድስና ስፍራ ናት። "ምድርን ሙሉአት" ማለቱ፣ ገና ከገነት ወጥተው ወደ ምድር እንደሚወርዱና በዚያም በሥጋዊ ልደት እንደሚባዙ የሚያሳይ የቅድመ-ዕውቀት ትእዛዝ ነው። እንጂ በገነት ከሆነ ጌታ ያዘዘው ትዛዝ በገነት አልተፈጸመም ማለት ነው። ስለገነት ከሆነ በገነት እንደዚህ አይነት መራባት መቼ ተፈጸመ እግዚአብሔር ገና ያልተፈጠሩ ሰዎችን በስም ጠርቶ ሥራቸውን ይናገራል። (ኢሳ 45:1)። (1ኛ ነገሥት 13:2)። ትምህርቱ፦ ገና ያልተወለዱ ሰዎችን በስም ጠርቶ ሥራቸውን የሚያዝ አምላክ፣ አዳምና ሔዋን ገና ሳይበድሉ፣ ከበደሉ በኋላ የሚኖራቸውን የመራባት ሁኔታ "ብዙ ተባዙ" ብሎ ቢያዝ ምንም የሚገርም አይደለም። እግዚአብሔር በቅድመ-ዕውቀቱ የሰው ልጅ የቅድስናን መንገድ (የመላእክትን አኗኗር) ትቶ ወደ ቁሳዊ ነገር እንደሚያዘነብል ስላየ፣ ዘሩ እንዳይጠፋ የእንስሳትን የመራቢያ መንገድ አስቀድሞ አዘጋጀለት። ማለትም፦ ትእዛዙ የተሰጠው ለሰው ልጅ ክብር ሲባል ቢሆንም፣ አፈጻጸሙ ግን ሰው ወደ እንስሳዊ ባህርይ ዝቅ እንደሚል ታሳቢ ያደረገ ነበር። እግዚአብሔር "ብዙ ተባዙ" ያለው አዳምና ሔዋን ሳይበድሉ ቢሆንም፣ ትእዛዙ ግን እግዚአብሔር በዘለዓለማዊ ዕውቀቱ ያየውን የወደፊቱን የሰው ልጅ ታሪክ የሚመለከት ነው። አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ ሆነው ትእዛዙን ያልፈጸሙት፣ ትእዛዙ ከውድቀት በኋላ ለሚኖረው "የሞት ዓለም" መፍትሔ እንዲሆን የታሰበ ስለነበረ ነው።እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን "ብዙ ተባዙ" (ዘፍ 1:28) ብሎ ያዘዛቸው ገና ሲፈጥራቸው ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ፣ አዳም ሚስቱን ሔዋንን አውቆ (ተገኝቶ) የወለደው ከገነት ከወጣ በኋላ መሆኑን በግልጽ ይናገራል። "አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፤ ቃየንንም ወለደች" (ዘፍጥረት 4:1)። ይህ የሚያሳየው በገነት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ይህ ዓይነቱ ግንኙነትና ውልደት እንዳልነበረ ነው።በገነት ውስጥ ሳሉ "ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩምም ነበር" (ዘፍ 2:25) ይላል። ይህ የሚያሳየው እንደ ሕፃናት ያለ የየዋህነት (Innocence) ሕይወት እንጂ፣ አሁን ወዳለው ጾታዊ ፍላጎት የሚያመራ ስሜት እንዳልነበራቸው ነው። ዓይኖቻቸው የተከፈቱትና ዕራቁትነታቸውን ያወቁት (ማለትም የሥጋ ፍላጎት ያደረባቸው) ከበደሉ በኋላ ነው።እግዚአብሔር ሔዋንን ሲቀጣት "በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ልጆችን ትወልጃለሽ" አላት።አሁን ያለው "በጭንቅና በምጥ" መውለድ ግን የኃጢአት ውጤት መሆኑን ያረጋግጣል።እግዚአብሔር ሰው ወደፊት እንደሚበድልና እንደሚሞት አስቀድሞ ስላወቀ፣ የሰው ዘር እንዳይጠፋ "ተተኪ" የሚገኝበትን የእንስሳትን የመራቢያ መንገድ (ጾታዊ ግንኙነትን) በሰው ውስጥ አኖረ።

  • አዳምና ሔዋን ለምን በገነት አልወለዱም? 💥የማይሞት አካል መውለድ አያስፈልገውም፦ መራባት (Procreation) ያስፈለገው ሞት ወደ ዓለም ስለገባ ነው። የሚሞተውን ፍጡር የሚተካ ሌላ ትውልድ ያስፈልጋል። በገነት ግን አዳምና ሔዋን ባይበድሉ ኖሮ አይሞቱም ነበር፤ የማይሞት ፍጡር ደግሞ ተተኪ አያስፈልገውም። 💥ገነት የቅድስና ስፍራ ናት፦ አሁን ያለው የሰው ልጅ ውልደት ከፍትወትና ከሥጋዊ ደስታ ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ደግሞ በቅድስና ለተሞላችውና የእግዚአብሔር ክብር ለሚገለጥባት ገነት የሚስማማ አልነበረም።ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (St. Gregory of Nyssa) እንደሚለው እንዲሁም ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚለው ጌታችን በወንጌል "በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም" (ማቴ 22:30) ብሏል። ትንሣኤ ደግሞ ወደ ቀድሞው የገነት ክብር መመለስ ስለሆነ፣ በገነትም ጋብቻና ሥጋዊ መራባት እንዳልነበረ እንረዳለን።

  • በብሉይ ኪዳን የሚመጣው መሲህ እግዚአብሔር ወልድ የእግዚአብሔር ባሪያ ተብሏል ኢሳ 53÷11 ይህን ከምን አንጻር ነው የምንፈታው? ይህ ጥቅስ ከውርደት በኋላ ከፍ የሚለውንና ለሌሎች ቤዛ ሆኖ የሚሞተውን አካል ይተነብያል።ቀደምት አባቶች ይህንን በቀጥታ ከክርስቶስ ጋር ያያይዙታል፤ ለምሳሌ በማቴዎስ 8:17 ላይ "እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ" (ከኢሳይያስ 53:4 የተወሰደ) እና በዮሐንስ 12:38 ላይ ተጠቅሷል።በነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት (53፥11) ላይ "ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል" ተብሎ ስለ መሲሁ የተነገረው ቃል፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንደሚያስተምሩት የአምላክን የባሕርይ ዝቅታ ሳይሆን የሥጋዌን (ሰው የመሆኑን) ድንቅ ምስጢር የሚያበስር ነው። ይህንን ነጥብ በሚከተሉት አራት ዓቢይ ምስጢራት እንረዳዋለን፦ ፩. የባሕርይ ሳይሆን የግብር ስም በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት፣ ስም በሁለት ይከፈላል፤ የባሕርይ ስም እና የሥራ ስም (የግብር ስም)። "ባሪያ" የሚለው ቃል የክርስቶስ የባሕርይ ስሙ አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ በባሕርዩ "ጌታ" ነው። ነገር ግን እኛን ለማዳን ሲል የባሪያን መልክ ስለነሳ (ስለለበሰ) "ባሪያ" ተባለ። አባቶች እንደሚሉት "ባለጸጋ ሲሆን ስለ እኛ ድሃ ሆነ፤ ጌታ ሲሆን ስለ እኛ ባሪያ ሆነ"። ይህ የሚያሳየው ባሪያ የሆነው በትሕትናው እንጂ በባሕርዩ አለመሆኑን ነው። ልክ አንድ ንጉሥ የጦር ምርኮኞችን ነፃ ለማውጣት የወታደር ልብስ ለብሶ ወደ ጠላት ሰፈር እንደሚገባ፣ ክርስቶስም እኛን ከሰይጣን ባርነት ሊያወጣን የባሪያን (የሰውን) ሥጋ ለበሰ። ፪. "ባሪያ" ማለት "ታዛዥ" ማለት ነው (ሁለተኛው አዳም) የመጀመሪያው አዳም ባለመታዘዙ ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ሆኖ ነበር። ክርስቶስ ግን "የሁለተኛው አዳም" ሆኖ መጣ። እርሱ "ባሪያ" የተባለው እስከ መስቀል ሞት ድረስ በመታዘዙ ነው። "እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" (ማቴዎስ 20፥28)። እዚህ ጋር "ማገልገል" (Service) የባሪያ ተግባር ነው። ክርስቶስ ለሰው ልጅ ፍቅር ሲል ራሱን ዝቅ አድርጎ አገልግሎናል፤ አጥቦናል፤ ሞቶልናልም። ስለዚህ "ባሪያ" መባሉ የእርሱን ታላቅ ታዛዥነትና አገልጋይነት እንጂ አምላክ መሆኑን የሚቃረን አይደለም። ፫. የአምላክ "ክንድ" እና "ቃል" መሆኑ በኢሳይያስ 53 መጀመሪያ ላይ "የእግዚአብሔር ክንድ ለማን ተገልጧል?" ይላል። በሊቃውንት ትርጓሜ "ክንድ" የተባለው ወልድ (ክርስቶስ) ነው። አንድ ሰው በክንዱ እንደሚሰራ፣ እግዚአብሔር አብም በልጁ በኩል ዓለምን ፈጠረ፣ ዓለምንም አዳነ። ክንድ ደግሞ ለባለቤቱ ይታዘዛል። ክርስቶስ ከአብ ጋር በመለኮት አንድ ቢሆንም፣ በሥጋዌው (በሰውነቱ) ግን ለአብ ይታዘዛል ክንድ ለባለቤቱ እንደሚታዘዘው ክርቶስ የአብ በቃልነት የባሕርይ ገንዘቡ ነው ስለዚህ የአብ ቃል ለአብ ይታዘዛል። ይህ ታዛዥነቱ ደግሞ በትንቢቱ ቃል "ባሪያዬ" በሚል ተገልጧል። ባሪያው "በእውቀቱ ብዙዎችን ያጸድቃል" ተብሏል፤ ይህ እውቀት ደግሞ የሕግ እውቀት ሳይሆን ሰውን ለማዳን የተቀበለው የመስቀል መከራ እውቀት (የፍቅር እውቀት) ነው። ፬. የተዋሕዶ ምስጢር (የባሕርያት አንድነት) በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት "መለኮትና ትስብእት (ሰውነት)" ያለ መለወጥና ያለ መደበላለቅ አንድ ሆነዋል። ስለዚህ "ባሪያ" የሚለው ቃል የሚነገረው ለሰውነቱ (ለትስብእቱ) ነው። ክርስቶስን ባሪያ ስንለው በነሳው ሥጋ ነው፤ ጌታ ስንለው ደግሞ በቀደመ አምላክነቱ ነው። በተዋሕዶ ምክንያት ግን "ባሪያው አምላክ ነው፤ አምላኩም ባሪያ ሆኗል" እንላለን። ይህ ማለት አምላክነቱ ተለውጦ ባሪያ ሆነ ማለት ሳይሆን፣ በባሪያ መልክ (በሰውነት) ተገለጠ ማለት ነው። እኛ ስለ ክርስቶስ "የእግዚአብሔር ባሪያ" ስንል አምላክ ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ ራሱን ዝቅ ማድረጉን (ትሕትናውን) ለመግለጥ ነው። ባሪያው ተራ ሰው ቢሆን ኖሮ "በደላችንን ተሸክሞ" ሊያድነን አይችልም ነበር። ባሪያው ተራ ሰው ቢሆን ኖሮ ኢሳይያስ "እጅግ ከፍ ከፍ ይላል" (52፥13) አይለውም ነበር። ስለዚህ በኢሳይያስ 53፥11 ላይ ያለው "ባሪያ" የአምላክነቱ መጥፋት ሳይሆን፣ የፈጣሪ ወደ ፍጡር ዝቅ ማለት ነው። አምላክ እኛን ለመፈለግ ባሪያ ሆኖ መጣ፤ እኛም በእርሱ ባርነት (መታዘዝ) ምክንያት የእግዚአብሔር ልጆች ሆንን።

  • ቁርዓን መለኮታዊ ቃል እንዳልሆነ የሚያሳዩ ነጥቦች ይህ ጽሑፍ እህቴ/ወንድሜ እንድታስቡባቸውና እንድትመራመርባቸው የቀረቡ ነጥቦች ናቸው፦ 1. "የሰይጣን ጥቅሶች" እና የመልእክቱ መበከል (Satanic Verses) አንድ መለኮታዊ ቃል በምንም ተአምር ከሰይጣን ጋር ሊቀላቀል አይችልም። ሆኖም ቁርዓን ራሱ ሰይጣን በነቢዩ ንባብ ውስጥ ቃላትን ሊጨምር እንደሚችል ያምናል። ማስረጃው፦ ሱረቱ አል-ሐጅ 22:52 ላይ እንዲህ ይላል፦ "ከአንተ በፊትም ከመልክተኛም ሆነ ከነቢይ፤ (ተምኝቶ) ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ (ውሸትን) የጣለ ቢሆን እንጅ አንድንም አልላክንም።" ሙግቱ፦ ሙሐመድ ጣዖታትን የሚያወድስ ቃል ተናግረው በኋላ "ሰይጣን ነው የከተተብኝ" ማለታቸው የታወቀ የታሪክ ሀቅ ነው (ምንጭ፦ Tafsir al-Jalalayn እና History of al-Tabari Vol. 6)። አምላክ መልእክተኛውን ከሰይጣን ጣልቃ ገብነት መጠበቅ ካልቻለ፣ ዛሬ በእጅሽ ያለው ቁርዓን በሙሉ ከሰይጣን ንክኪ ነፃ መሆኑን በምን ማረጋገጥ ይቻላል? 2. ቁርዓን የሙሐመድን የግል ፍላጎት ለማርካት መውረዱ (Tailor-made Revelations) በቁርዓን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ጥቅሶች የዓለምን ሕዝብ ለማዳን ሳይሆን፣ የሙሐመድን የግልና የሥጋ ፍላጎት ለማሟላት የወረዱ ይመስላሉ። የሚስቶች ጉዳይ፦ ሙስሊሞች ሁሉ እስከ 4 ሚስት ብቻ እንዲያገቡ ተገድበው ሳለ፣ ለሙሐመድ ግን ያልተገደበ ቁጥር ተፈቅዶላቸዋል። (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33:50) የዘይነብ ታሪክ፦ ሙሐመድ የአሳዳጊ ልጃቸውን (ዘይድን) ሚስት በፈለጉ ጊዜ፣ ያን ለማመቻቸትና ትችቱን ለማስወገድ ጥቅስ ወርዷል። (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33:37) የአይሻ ምስክርነት፦ የገዛ ሚስታቸው አይሻ እንኳ ሳይቀር ጥቅሶቹ ለሳቸው ፍላጎት ሲሉ እንደሚወርዱ ታዝባ እንዲህ ብላለች፦ "ጌታህ ያንተን ስሜት/ፍላጎት ለማርካት የሚቸኩል ነው የሚመስለኝ።" (Sahih al-Bukhari 4788)። አምላክ የሰውን ሥጋዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥቅስ ያወርዳል ወይ? 3. የመልእክቱ ምንጭ እርግጠኛ አለመሆን (Lack of Witnesses) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሲናገር ሕዝብ ምስክር ነበር። በቁርዓን ግን ምስክሩ ሙሐመድ ብቻ ናቸው። ሙግቱ፦ ሙሐመድ መጀመሪያ መልእክት ሲመጣላቸው በድንጋጤ ወደ ቤታቸው ሮጠው "ሰይጣን ያዘኝ/ሊገድለኝ ነው" (I fear for my life) ብለው ነበር። (Sahih al-Bukhari 3)። ራሳቸው መልእክቱ ከማን እንደሆነ ተጠራጥረው ሳለ፣ እኛ እንዴት የአምላክ ነው ብለን እናምናለን? መልአኩ ገብርኤል መሆኑን ያረጋገጠላቸውም መለኮታዊ ምልክት ሳይሆን ወረቃ የተባለ የሰው ልጅ ነው። 4. ተቀያያሪና የሚቃረኑ ህጎች (Abrogation) አምላክ ሁሉንም ነገር አስቀድሞ የሚያውቅ ከሆነ፣ ቃሉን ዛሬ ተናግሮ ነገ ለምን ይለውጠዋል? ማስረጃው፦ ሱረቱ አል-በቀራህ 2:106 ላይ አምላክ ጥቅሶችን እንደሚሽርና በሌላ እንደሚተካ ይናገራል። ሙግቱ፦ መጀመሪያ "በሃይማኖት ማስገደድ የለም" ይልና (2:256) በኋላ ግን "ከአላህ ሌላ የሚገዛን ግደሉ" የሚሉ ጥቅሶች ይመጣሉ። ይህ የሚያሳየው ቁርዓን እንደየሁኔታውና እንደ ሙሐመድ ጥንካሬ የሚቀያየር የሰው ሰራሽ ቃል መሆኑን ነው። 5. የታሪክ ስህተቶች (Historical Anachronisms) ቁርዓን የአላህ ቃል ከሆነ ታሪካዊ ስህተት ሊኖርበት አይችልም። ነገር ግን ግልጽ የሆኑ የታሪክ ግድፈቶች ይታዩበታል። የማርያም ማንነት፦ ቁርዓን የኢየሱስን እናት ማርያምን "የአሮን እህት" እና "የእምራን ልጅ" ይላታል። (ሱረቱ መርየም 19:28 እና ሱረቱ አል-ኢምራን 3:35-36)። ሀቁ፦ ሙሴና አሮን የኖሩት ከኢየሱስ እናት ከማርያም 1,500 ዓመታት ቀድመው ነው። ሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለችውን የሙሴን እህት ማርያምን እና የኢየሱስን እናት ማርያምን አንድ ሰው አድርገው በስህተት ቀላቅለዋቸዋል። የሃማን ታሪክ፦ ቁርዓን "ሃማን" የተባለው ሰው በግብፅ የፈርኦን ሚኒስትር እንደነበር ይናገራል። (ሱረቱ አል-ቀሰስ 28:38)። ሀቁ፦ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያረጋግጡት ሃማን የፋርስ (Persia) ንጉሥ የአርታዘርክስ ሚኒስትር እንጂ በግብፅ የፈርኦን ሰው አልነበረም። ይህም ታሪኩ በወሬ እንጂ በመለኮታዊ እውቀት እንዳልተገኘ ያሳያል። 6. የጦር ምርኮና የባርነት ሕግ የጦር ምርኮ ድርሻ፦ ሱረቱ አል-አንፋል 8:41 ላይ ከምርኮው "አምስተኛው እጅ ለአላህና ለመልክተኛው ነው" ይላል። ፈጣሪ ለምን የወርቅና የንብረት ድርሻ ይፈልጋል? ይህ ሙሐመድ ሃብት የሚያገኙበት መንገድ አልነበረምን? የወሲብ ባሪያዎች (Concubines)፦ ቁርዓን ሙሐመድና ሙስሊሞች በጦርነት የያዟቸውን ሴቶች ያለ ጋብቻ "በቀኝ እጃቸው ስር ያሉ" አድርገው ለወሲብ እንዲጠቀሙ ይፈቅዳል። (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33:50 እና ሱረቱ አን-ኒሳእ 4:24)። ቅዱስ የሆነ አምላክ እንዲህ ያለውን ግፍ ይፈቅዳልን? 7. ቁርዓን የተሰበሰበበት መንገድ ሙሐመድ በሕይወት ሳሉ ቁርዓን በአንድ መጽሐፍ አልተሰበሰበም ነበር። የተሰበሰበው ከሳቸው ሞት በኋላ በሰዎች ምርጫ ነው። ሀቁ፦ ኡስማን የተባለው ሦስተኛው ከሊፋ፣ እሱ ካጸደቀው አንድ ቁርዓን ውጪ ያሉትን ሌሎች የተለያዩ ቅጂዎች በሙሉ እንዲቃጠሉ አዝዟል። (Sahih al-Bukhari 4987)። ቁርዓን የአምላክ ቃል ሆኖ ተጠብቆ ቢሆን ኖሮ፣ ለምን ሌሎች ቅጂዎች ተቃጠሉ? በቃጠሎው ውስጥ የጠፉና የተለወጡ ቃላት እንደሌሉ በምን ይታወቃል? እህቴ/ወንድሜ ሆይ፣ እስልምናን የተቀበልሽ/ህው 'የአላህ ቃል ነው' ተብሎ ተነግሮህ/ሽ ነው። ነገር ግን የሰይጣን ንግግር የተቀላቀለበት፣ ለነቢዩ የግል ጥቅም (ሚስትና ምርኮ) የሚመች፣ የታሪክ ስህተቶች ያሉበት መጽሐፍ እንዴት የፈጣሪ ቃል ሊሆን ይችላል? እውነተኛው አምላክ እንዲህ አይሳሳትም፣ ለሰው ልጅ የሥጋ ፍላጎትም አያደላም።(ስታነቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቁራን አታንብቡ እሱ በትክክል አልተተረጎመም 😁)

  • ጥያቄ፦ ወልድ በብሉይ ኪዳን "የእግዚአብሔር መልአክ" ሲባል፣ በአዲስ ኪዳንም "ከአብ ተልኬ መጥቻለሁ" ይላል። ለመሆኑ "ተላከ"፣ "መልአክ" እና "ተላኪ" የሚሉትን ቃላት ከሦስቱ አካላት (ሥላሴ) አንጻር እንዴት እንፈታቸዋለን? ለምንስ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ብቻ ተላኩ? አብ ለምን አልተላከም? ምላሽ፦ በቅድስት ሥላሴ ትምህርት ውስጥ "መልአክ" እና "መላክ" (ተላከ) የሚሉ ቃላት ሲነሱ፣ እንደ ሰብአዊ ሥርዓት የአዛዥና የታዛዥ ወይም የጌታና የሎሌ ጉዳይ ተደርገው ሊወሰዱ አይገባም። ይልቁንም እነዚህ ቃላት የአካላትን "ዘላለማዊ መገኘት" እና "የማዳን ሥራ" የሚገልጡ ናቸው። ፩. "መልአክ" እና "ተላከ" የሚሉ ቃላት ፍች በብሉይ ኪዳን የሚታየውን "የእግዚአብሔር መልአክ" አባቶች እንደ መለእክተኛ ቢታይም፣ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር የሚናገርና የሚሠራ፣ ከሥጋዌ በፊት የነበረ የወልድ መገለጥ (ቴዎፋኒ) አድርገው ይተረጉሙታል። ይህም እርሱን ከተፈጠሩ መላእክት የሚለየውና በሥላሴ አካላት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገልጥ ነው። ወልድ "የምክር መልአክ" መባሉ የአብን የድኅነት እቅድ ለሰው ልጆች የሚገልጥ "ቃል" በመሆኑ ነው። በሥላሴ ትምህርት "ተላከ" ማለት ከአንድ ቦታ ተነስቶ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ማለት አይደለም፤ መለኮት በሁሉ የመላ ነውና። ይልቁንም "ተገለጠ" ማለት ነው። ለምሳሌ ወልድ ተላከ ሲባል "ሰው ሆኖ በአዲስ መንገድ ተገለጠ" ማለት ነው። ፪. ለምን ወልድና መንፈስ ቅዱስ ብቻ ተላኩ? አብ ለምን አልተላከም? ይህ በሥላሴ ዘንድ ባለው "የአካላት መገኛ" ሥርዓት የሚገለጥ ነው፦ አብ ምንጭ እንጂ ከማንኛውም አካል አልተገኘም። "መላክ" ደግሞ ከአንድ ምንጭ መገኘትን ስለሚያመለክት፣ አብ መገኛ ስለሌለው "ተላከ" አይባልም። "ተላኪ" የሚባሉት ወልድና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ ለዘላለም ከአብ የሚገኙ ናቸው። ወልድ ከአብ ተወለደ፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸ እንላለን። መላካቸው ከአብ መገኘታቸውን (ልደቱንና ሥርፀቱን) ለመግለጥ ነው። ወልድ ከአብ ስለሚወለድ በአብ መላኩ ክብሩን አያሳንሰውም፤ ይልቁንም ከአብ ጋር ያለውን አንድነትና የባሕርይ ልጅነት ያሳያል። ጌታችን "የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው" (ዮሐ 7:28) ማለቱ ከመሬታዊ ወላጆች በላይ መለኮታዊ መነሻ እንዳለው ያረጋግጣል። መላላካቸው በፍቃድ እንጂ በትእዛዝ አይደለም። አብ ወልድን ሲልከው፣ ወልድም በራሱ ፈቃድ ተላከ። ወልድ "ከወዴት እንደሆንሁ ታውቃላችሁ... የላከኝም እውነተኛ ነው" ማለቱ ምንም እንኳ ተላኪ ቢሆንም ከአብ ጋር በባሕርይ እኩል (Consubstantial) መሆኑን ያሳያል።

  • ለምን ሦስተኛው አካል ብቻ "መንፈስ ቅዱስ" ተባለ? መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔር መንፈስ ነው" (ዮሐ. 4:24) ይላል። ሦስቱ አካላት (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) በአንድ መለኮታዊ ባሕርይ አንድ እስከሆኑ ድረስ፣ አብና ወልድም እንደ ሦስተኛው አካል ለምን "መንፈስ ቅዱስ" ተብለው አይጠሩም? ምንም እንኳ አብና ወልድ በባሕርያቸው "መንፈስ" እና "ቅዱስ" ቢሆኑም፣ ለሦስተኛው አካል "መንፈስ ቅዱስ" የሚለው ስም እንደ "ልዩ መጠሪያ" የተሰጠበትን ምክንያት በሚከተሉት ነጥቦች እንረዳለን፦ በቅድስት ሥላሴ ትምህርት ውስጥ በባሕርይ ስም እና በአካላዊ ስም መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ቀዳሚ ተግባር ነው፦ የባሕርይ ስም (Common Name)፦ ሦስቱም አካላት በአንድ መለኮታዊ ባሕርይ ስለሚካፈሉ የሚጠሩበት የጋራ ስም ነው። ለምሳሌ፦ አምላክ፣ ጌታ፣ ፈጣሪ፣ ቅዱስ፣ መንፈስ፣ ብርሃን... እነዚህ ስሞች ለሦስቱም እኩል ይሠራሉ። ስለዚህ "አብ መንፈስ ነው፣ ወልድም መንፈስ ነው" ስንል ረቂቅ ባሕርያቸውን መግለጻችን እንጂ አካላዊ ስማቸውን መጥራታችን አይደለም። የአካል ስም ፦ አንዱ አካል ከሌላው አካል ተለይቶ የሚታወቅበት የግል ስም ነው። አብ "አብ" የሚባለው ወላጅ ስለሆነ ነው፤ ወልድ "ወልድ" የሚባለው ተወላጅ ስለሆነ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም "መንፈስ" የሚባለው ሰራጺ (ከአብ የወጣ) ወይም "እስትንፋስ" ስለሆነ ነው። በሃይማኖተ አበው (ክፍል ፩) ላይ እንደተገለጠው፦ "አብን ስለ ወለደ 'አብ' ብንለው፣ ወልድንም ከአብ ስለ ተወለደ 'ወልድ' ብንለው፣ መንፈስ ቅዱስንም ከአብ ስለ ሠረፀ 'መንፈስ ቅዱስ' ብንለውም፤ የአካላት ስማቸው ግብር የሌለው ከንቱ አይደለም" ይላል። እዚህ ላይ ልንስተው የማይገባን ትልቅ ነጥብ አለ፤ አብን ስለ ወለደ (በእንተ ዘኮነ ወላዲ)፣ ወልድን ስለ ተወለደ (በእንተ ዘተወልደ)፣ መንፈስ ቅዱስንም ስለ ሠረጸ (በእንተ ዘሠረጸ) ስንላቸው እነዚህ ስሞች የግብር ስም መስለው ሊታዩ ይችላሉ። ነገር ግን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሉት ስሞች የአካል ስሞች መሆናቸውን ልብ ሊባል ይገባል። ምክንያቱም አካል ግብርን ያስገኛል እንጂ ግብር አካልን አያስገኝምና። እነዚህም ስሞች አካላት ዘላለማዊ እንደሆኑ ሁሉ ስሞቻቸውም ከዘላለም የነበሩ እንጂ፣ ኑረው ኑረው ኋላ የተጠሩባቸው አይደሉም። መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሲገኝ አወጣጡ "መስረጽ" ይባላል። ይህ አወጣጥ ከአፍ እንደሚወጣ "እስትንፋስ" ስለሆነ "መንፈስ" (Spirit/Breath) የሚለው ቃል ለእርሱ ብቻ ልዩ መጠሪያ ሆነ። አብና ወልድ ምንም እንኳ ቅዱሳን ቢሆኑም፣ "መንፈስ ቅዱስ" የሚለው ስም ለሦስተኛው አካል ብቻ የግል መጠሪያው ሆኗል። በምሳሌ ለመረዳት፦ ልክ አንድ ንጉሥ ብዙ ልጆች ቢኖሩትና ሁሉም "የንጉሥ ልጆች" ቢባሉ፤ ነገር ግን ከአንዳቸው ስም ጋር "አልጋ ወራሽ" የሚል መጠሪያ ቢታከል፣ ያ ስም የእርሱ ብቻ መለያ ይሆናል። ይህም ማለት ሌሎቹ አልጋ አይወርሱም ማለት ሳይሆን፣ ያ ስም እርሱን ከወንድሞቹ ለይቶ የሚታወቅበት ልዩ መጠሪያው በመሆኑ እንደማለት ነው።