ኢትዮጵያ አውታር - Ethiopia Awtar
Статистикаኢትዮጵያዊነት በመስበክ ኢሉሚናቲ የምታጋልጥ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ መገናኛ ብዙኅን ። 2001 ዓ/ም ተመሠረተች! ከ፩ ዓመት በላይ በጦርነት ምክንያት የዓለም አቀፍ ግንኙነት አውታርተ (internet) በትግራይ በመቋረጡ @ethiopiaawtar መስመራችን ጠፍቷል ። በዚህ ምክንያት ይህ አዲስ መስመር ለመክፈት ተገደናል።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 48
- 1/48двое суток
- 55
- 1/72трое суток
- 59
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ቢቢሲ ስለ ምክክር ኮሚሽን ተብዮው መሰንበቻ ዛሬ ያወጣው ዘገባ፣ መድረኩን በየዋህነት “አገራዊ ምክክር” የሚደረግበት ገለልተኛ መድረክ ነው ብለው ለሚያምኑት ሁሉ፣ በውስጡ እየተፈጸመ ያለውን ዐቢይ አሕመድ መር ኦነጋዊ ሸፍጥ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/08/blog-post_589.html
ቴዎድሮስ
без подписи
ታሪክን፣ የስነ-ሕዝብ (ዲሞግራፊ) መረጃዎችን እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የሕግና የዲፕሎማሲ ሁኔታዎችን በጥልቀት ከተመለከትን፤ በኃይል ፍላጎትን ከመጫን ውጭ አዲስ አበባን የአንድ ወገን ወይም ቡድን ብቻ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረግ ጥረት ብዙ ርቀት አያስኬድም። በመካከለኛው ዘመን በዐፄ ዳዊት "በርበራ" ተብላ ትጠራ የነበረችው አዲስ አበባና አካባቢዋ፣ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና የተቆረቆረችውና የተደራጀችው በዐፄ ምኒልክና በኢቴጌ ጣይቱ አማካኝነት መሆኑ ይታወቃል። https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/08/blog-post_877.html
ጋብቻውን ፈፅመህ በጽዮን የተመሰሐችውን ስብዕና ያዝክ ማለት አየለ ወይም ከበደ መባልህ ይቀራል፡ ስትኖርም እንደአየለ እና ከበደ መሆኑ ይቀራል። በውስጥህ ያለው እኔ የምትለው ሥጋዊ ፈቃድ ይሞትና በፈጣሪ ፈቃድ መኖር ትጀምራለህ፣ የፈጣሪ መኖሪያው ትሆናለህ፣ ይሁን ያልከው ይሆናል፡ አይሆንም ብለህ የዘጋኸውን ማንም አይከፍተውም፤ የምታዘው አንተ ሳትሆን በውስጥህ ያለው መንፈስ ነው። https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/08/blog-post_10.html
በአሁኑ ወቅት «ዘመናዊነትን ለመከተልና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ለመናበብ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር መቀየር አለበት» የሚሉ ድምፆች ሲደመጡ ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህ ወገኖች «አቀላጣፊና ደረጃውን የጠበቀ» አድርገው የሚቀበሉት የጎርጎሪዮሳዊው (Gregorian) አቆጣጠር፣ ምን ያህል በፖለቲካዊ ሽኩቻ፣ በንጉሣውያን ፍላጎትና በሒሳባዊ ውዝግብ የተሞላ እንደሆነ ታሪኩንና ሳይንሳዊ መሠረቱን ያውቁት ይሆን? https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/08/blog-post.html?m=1
አፍራሽ የሆነ ትውልድ አንሁን እባካችሁን እንንቃ! ይህን ያክል ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጠላት መሆን ያዋጣልን? ጸባችሁ ከእውነት ጋር ስራችሁም ግፍ ስለሆነ ዋጋ እንደሚከፈላችሁ አትዘንጉ:: ደግሞ የዘመን አቆጣጠር ቢቀራችሁ እሱንም የጥፋት እጃችሁን ልትዘረጉበት አሰባችሁ? በነገራችን ላይ የውጩ ዘመን አቆጣጠር ስህተት ከመሆኑም በተጨማሪ የወራቱ ስያሜዎች ከባዕድ አምልኮና ከጣዖት ስሞች ጋር የተያያዙ ናቸው! የእኛ የዘመን አቆጣጠር ግን ወራቶቹና ስያሜዎቹ መንፈሳዊ የሆኑና የሀገራችንን የወቅቶች ጸባያትንም የያዙ ግሩም የሆነ መልእክት ያላቸው ናቸው:: https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/07/blog-post_31.html?m=1
Dystopia = ገንዘብ አምላኪ መንግሥት (✍ መስከረም ለቺሳ (ዶ/ር) | ዮቶጵያ) ገንዘብ የሚያመልክ ሰው፡ ድሃ ነው። ምክንያቱም፡ ገንዘቡ ካለቀበት፡ ሌላ ነገር የለውም። ገንዘብ የሚያመልክ መንግሥትም፡ ድሃ ነው። ምክንያቱም፡ ገንዘቡ ካለቀበት፡ ሌላ የሚቆምበት እሴት፣ መርኅ፣ ዓላማ ወይም ታሪክ የለውም። መርኁ ገንዘብ ብቻ ስለኾነ፡ ከሕዝብም ኾነ ከሌላ፡ እንዴት ገንዘብ እንደሚሰበስብ ብቻ ያስባል። ገንዘቡን (አምላኩን) ደግሞ በአደባባይ ማምለክ ይወዳል። አምላኩን የሚያመልከበት የዐደባባይ ሥርዓቱም፡ ይፋዊ ቅንጦት ነው። እንዲያም ኾኖ ግን፡ ውስጡ ገንዘብ በማጣት ስጋት የተመታ ነው። ምክንያቱም፡ ገንዘቡ ካለቀ ምንም የለውም። ከገንዘቡ ውጪ፡ እሱ ማንነት የለውም። ገንዘቡ እሱ፥ እሱም ገንዘቡ ናቸው። ይኽ "መካከለኛው ዘመን" ብለው በሚጠሩት በጨለማው ዘመን (Dark Age)፡ የአውሮፓ ነገሥታት የነበሩበት የወደቀ ስነ ልቦና ነው። ነገሥታቱ፡ ከሕዝባቸውና ከወረሯቸው አገራት፡ ገንዘብ መሰብሰብ፣ መዝረፍ፣ መማረክ፣ መቀጮ መጣል፣ መውረስ ላይ ተጠምደው ነበር። ሕዝቡም፡ ከነሱ ተምሮ፡ ገንዘብ ወዳጅ ኾኖ፡ ከመሥረቅ በቀር፡ ሌላ ሥራ አልነበረውም። ለዳቦ ብሎ ይገድላል፤ ለዳቦ ብሎ ይገደላል። በወቅቱ፡ በአውሮፓ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደሩ የነበሩት እምነቶች ደግሞ፡ እስልምና፣ ካቶሊክ፣ እና gnosticism/hermeticism (ኮከብ ቆጠራ) ናቸው። በኋላ ግን፡ ሕዝቡ፡ "በቃኝ!" አለና፡ ከቄሱ ዮሓንስ አገር ኢትዮጵያ፡ ከነላሊበላና ይምርኃነ ክርስቶስ፡ ብዙ ክርስቲያናዊ የአስተዳደርና የአኗኗር ትምህርቶችን እየተማረ፡ ወደ Utopianism ገሠገሠ። ተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ አገርን ከጨለማ ዘመን ሥርዓት ነፃ ታወጣለች። በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ የሚመለከው፡ ገንዘብ ሳይኾን፡ ሰው ነው። በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ ሰው ክቡር ነው። ምክንያቱም፡ የሚመለከው፡ ሰው የኾነው አምላክ ነውና፡ የሰው ባሕሪው ከብሯል። በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ ትግሉ ኹሉ፡ ሰውን፡ ወደ ሰብአዊ ብቻ ሳይኾን፡ ወደ አምላካዊ ክብሩ መመለስ ነው። ሰው፡ በክርስቶስ ምክንያት፡ የፀጋ አምላክ ኾኗልና። በተዋሕዶ/ዩቶፕያ፡ ገንዘብ፡ የሰው መጠቀሚያ ብቻ ነው። የሰውን ባሕሪ የማማሰን (የማበላሸት) ዓቅም ስላለውም፡ ከትልልቅ ሰዎች በቀር፡ ልጆች ምን እንደኾነ እንዲያውቁት አይደረግም ነበር። "ልጅ ፍራንክ አይዝም!" አሁን ግን፡ ዕድሜ ለሌሎች እምነቶችና ለኮከብ ቆጣሪው ዓለም፡ ገንዘብ በቄሱ ዮሓንስ አገር አምላክ ኾኖ፡ ሰው ስለገንዘብ ጭዳ ግብር ይደረጋል። ተዋሕዷዊ/ዩቶፕያዊ ዐብዮት ያስፈልገናል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ፡ የኢሉሚናቲ ዐብዮት አስጀማሪዋ ካቶሊኳ ፈረንሳይ ግን፡ በላሊበላ ምን እየሠራች ነው?
без подписи
የሰንደቅ ዓላማውን ቀለማት የሚቃወመው ማነው? (✍ መስከረም ለቺሳ (ዶ/ር) | ዮቶጵያ) ፖለቲከኞች፣ ብሔርተኞች፣ ጽንፈኞች ወዘተ... አረንጓዴ-ቢጫ-ቀዩን ሰንደቅ ዓላማ የሚቃወሙት፡ "የምኒሊክ" ወይም "የአማራ" ወይም "አቢሲንያውያን" ስለኾነ አይደለም። የሚቃወሙት፡ የቅድስት ድንግል ማርያም መቀነት ስለኾነ ነው። የአገሪቱ ባለቤትና ባለርስት፡ እርሷ መኾኗን የሚያሳይ የቃል ኪዳን ምልክት ስለኾነ ነው። ለዐሥራት ልጆቿ በመንፈስ የምትሰጣቸው ምልክት ስለኾነ ነው። በርሷ እናትነት አምነው፥ በልጇ ደም ታትመው ወደርሷ የሚመጡትን፡ ነፍሳቸውን የምትቀበልበት የፍቅር ማሠሪያዋ ስለኾነ ነው። ጠቡ ከርሷ ጋር ነው። ተቃዋሚዎቹ የሚቃወሙት ደግሞ፡ በዋናነት፡ ኦሮሞ ስለኾኑ፣ ወይም ኩሽ ስለኾኑ፣ ወይም ሙስሊም ስለኾኑ፣ ወይም ፕሮቴስታንት ስለኾኑ (ብቻ) አይደለም። የ666 አባላት ስለኾኑ ነው። ዋና ጽንፈኛ የሰንደቅ ዓላማ ተቃዋሚዎች የሐሳዌ መሢህ መንገድ ጠራጊዎች፥ የሴቲቱ ጠላቶች፥ የዘንዶው መጠቀሚያዎች ናቸው። ለሰበብነት የሚጠቀሙት ግን ብሔርን፣ ወይም የውሸት የጭቆና ትርክትን ነው። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚኾነን፦ በጥንቆላ ውስጥ የተሰማሩና ከደብተራው ዓለም ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች፡ የፈለገ "አማራ" ወይም "ኦርቶዶክስ" ነን ቢሉ፡ ለዚችው ሰንደቅ ዓላማ፡ ከጽንፈኞች ፖለቲከኞች ያልተናነሰ የጠላትነት ስሜት ያላቸው መኾኑ ነው። በግልጽ ወይም በሥውር ሰንደቅ ዓላማውን ይዋጉታል። ወደ 666ቱ ዓለም ተጠቃልለው ገብተዋልና። "ዘንዶውም፡ በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን፡ የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን፡ ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።" (ራእ 12:17) እነዚህ ከዘርዋ የቀሩት የኢየሱስ ምስክር ያላቸው የተመረጡ የዐሥራት ልጆቿ ደግሞ፡ ምልክታቸው ሰንደቅ ዓላማው ነው። በመንፈሳዊ ዓይን ሲታዩ፡ ቀስተ ደመና ሰውነታቸው ላይ ተተክሎ ይታያል። ክርስቶስ በሰውነታቸው ላይ ነግሧልና። የርሱ ዙፋን ደግሞ፡ ምልክቱ ቀስተ ደመና ነው፦ «ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።» (ራእ 4:3) ዘንዶው ባያቸው ቁጥር በቁጣ የሚወራጨው ለዚያ ነው። በአገሪቱ ላይ ያለው የ666 መንፈስና አጠቃላይ ኔትወርክ፡ በይሁዳው አንበሳ፡ በመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀሉ ኃይል የተቀጠቀጠ ይኹን! አሜን!
без подписи
ሰሞኑን አህ*መዲን ጀ*በል የተባለ ሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሲያጣጥጥል እያየሁ በጣም እየገረመኝ ነበር:: "አይጥ ዝሆንን አክላለሁ ብላ ፈንድታ ሞተች" ብለው ምሳሌ የሚናገሩ አባቶቻችን ምንኛ እውነተኞች ናቸው! https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/07/blog-post_28.html
без подписи
እንኳንስ አሁን ወይም ድሮ፥ ለወደፊትም ዓለሙን የሚያስተው ሐሳዌ መሢህ መጥቶ እምነትን ካጠፋ በኋላ እንኳ፡ ጌታ እንደተናገረው፡ ንግስተ ሳባ (የዐፄዎቹ እናት)፡ የክርስቶስን የባሕሪ አምላክነት ካልተቀበሉ ትውልዶች ጋር ስትፋረድ ትታያለች እንጂ፡ ምንፍቅና ወይም እስልምና አሸንፎ የሚታይበት ትንቢት የለም። https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/07/blog-post_374.html
በዓለም ላይ ከ190 በላይ አገሮች ሲኖሩ 30 አካባቢ የሚሆኑት ብቻ ናቸው የተለያየ አይነት የፌደራል ሥርዓት የሚጠቀሙት። የፌደራል ሥርዓት ያስፈለገበት ዐብይ ጉዳይ የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋትና ዜጎች እንደ ፈለጋቸው ነጻነታቸውን እንዲጠቀሙና የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት ነው። https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/07/190-30.html
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅል እና ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በአገራችን በኢትዮጵያም ላይ ጥልቅ የሆነ መዋቅራዊና ርዕዮተ-ዓለማዊ ጫና እየፈጠረ ይገኛል። https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/07/blog-post_576.html
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በኦርቶዶክሳውያንና በታሪካዊ ገዳማት ላይ እየተፈጸመ ያለው ውድመትና ጭፍጨፋ ይፋዊ በሆነ መልኩ የተቀናጀ አካሄድ ነው:: ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ሃይማኖት ጠል በሆነው አምባገነን አገዛዝ ቤተክርስቲያኗን ለማዳከምና ለማጥፋት የተቀመረና አደገኛ ዘመቻ ነው:: https://ethiopiaawtar.blogspot.com/2026/07/blog-post_22.html
"ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ፈተናዋ" (✍ ዳንኤል ተጫኔ) ይህ ዘመን የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን በሰይጣን እና በጭፍሮቹ በብዙ እየተፈተነች ያለችበት ወቅት ነው። ይሁን እንጂ ቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት ናትና፥ የገሀነም ደጆች አይችሏትም እንደተባለላት፡ የገጠሟትን ፈተናዎች ሁሉ አልፋ በክብር በሞገስ እያበራች እስከ ቀኑ ፍጻሜ ትኖራለች። ቅድስት ቤተክርስቲያን በሰይጣን ወጀብና አውሎ ተገፍታ የምትወድቅ የሚመስለን አርቀን ማሰብና ማስተዋል የተሳነን የኔ ብጤ ሞኞች አንታለል። እኛ እንጂ ቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን አትወድቅም። ከእውነተኛይቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመለየት በማውጣት የእግዚአብሔር ብቸኛ ልጅ የሆንን አስመስሎ የሚነግረንና የሚያሳየን ሁሉ እርሱ ከክፉው እንጂ ከእግዚአብሔር እና ከእውነት አይደለምና በቅድስት ቤተክርስቲያን አጸድ ጸንተን እንቁም። ቅድስት ቤተክርስቲያንን እናጠፋታለን ያሉ ሁሉ እነርሱ ዛሬ የሉም ጠፍተዋል። ሞተዋል በስብሰዋል። የእግዚአብሔር ማደሪያ፡ የገሀነም ደጆች የማይችሏት ቅድስት ቤተክርስቲያን ግን የገጠማትን ፈተና ሁሉ አልፋ፥ እናጠፋሻለን ያሏትን ሁሉ ደምስሳ ዛሬም በሞገስ በክብር አለች። የዛሬውንም ፈተና አልፋ ነገ በሞገስ በክብር ትኖራለች።
በክርስቲያኖች መካከል ለምን ጠብ በዛ? (✍ መስከረም ለቺሳ (ዶ/ር) | ዮቶጵያ) ቁም ነገር ተባብረው በመሥራት ፈንታ፡ ለምን ቡድንተኝነት፣ ክርክር፣ ክፍፍል ወዘተ ያዘወትራሉ? ይኽን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች፡ ሰላምና ፍቅር ወዳድ ሰዎች ተብለው ይሞገሱ ይኾናል። አዎ፤ ሰላም ይወዳሉ። ነገር ግን፡ ብዙ ጊዜ፡ ሰነፎች ናቸው። የነገሮችን ጥልቀትና የውትብትቡን ዓይነት ጊዜ ወስደው ለመረዳት ተነሳሽነቱ የላቸውም። በደፈናው ብቻ "ቤተእግዚአብሔር ውስጥ ቁጭ ብለው ይጣላሉ" እያሉ መታዘብ ደስ የሚላቸው ናቸው። "ሃይማኖተኛ ነኝ እያሉ ይጨቃጨቃሉ" እያሉ ያማሉ፤ ያላግጣሉ፤ ይታዘባሉ። "እኔ'ኮ ብዙም አልቀርብም፡ ከውጪ ተሳልሜ ብቻ ስለምኼድ፡ ነገር ውስጥ አልገባም" በማለትም በስንፍናቸው ይመካሉ። በውስጥ ኾኖ ግን፡ የተለያየ ሠርጎ ገብ ዓላማ ይዘው ከገቡ ፖለቲከኞች፣ መናፍቆች፣ ጠንቋዮችና ሌቦች ጋር ትንቅንቅ የገጠመ መኖሩን አይረዱም። ትክክለኛውን ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ለማጥናትና በጠብ የተጎዱትን ወይም ተስፋ ቆርጠው ዝም ያሉትን ለማገዝ ፈቃደኝነት የላቸውም። ብቻ ግን ኹሉ ነገር ሰላም ኾኖላቸው፡ ሆቴል ሲኼዱ ጥሩ መስተንግዶ አግኝተው እንደሚወጡ ኹሉ፥ ቤተክርስቲያንም ሲመጡ ጥሩ መስተንግዶ አግኝተው መውጣት ነው የሚፈልጉት። ጠጋ ብለው ግን አያዩም። Tourist ናቸው። ብዙ ኦርቶዶክሳውያን እንዲህ ናቸው። ጠጋ ብለው፥ ጊዜ ወስደው፥ የቤተክርስቲያንን ትምህርት አጥንተው፥ ነገሮችን በጽሙና ቢገመግሙ ግን፡ ቤተክርስቲያን ብዙም ሰው እንደሌላት ይረዱ ነበር። ግልጽና ሥውር የኾነ ብዙ የዲያቢሎስ ተንኮል መኖሩን ያዩ ነበር። እንደ አገር፡ ከሦስቱ የኢትዮጵያውያን ዋና ዋና መርኆች መካካል አንዱ፡ "ጥበብን እያጠኑ መኖር" ነው። ይኽ፡ ሃይማኖትንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በሚችሉት ዓቅም ሲማሩና ሲያጠኑ መኖርን ያካትታል። ሐዋርያት እንዳስተማሩን፡ ይኽ፡ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ብዙ በረከትን የሚያስገኝ የኹሉ ክርስቲያን ግዴታ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ግን፡ አንድም ነገር ሳይገነዘቡ "ውይይይ! ኹል ጊዜ ጠብ ብቻ! በናታችሁ ተስማሙ?!" እያሉ እየታዘቡ ይኼዳሉ። ሰው በከፈለው መሥዋዕትነት እየኖሩ እንዳሉም አያውቁም። የጥፋት ርኩሰት፡ በተቀደሰው ቦታ፡ ነጠላ ለብሶ፡ ተመሳስሎ፡ ቆሞ ነገሮችን አንቆ እንዳለ አያስተውሉም። በእውነተኛውም፣ በሐሰተኛውም ላይ እኩል ፈርደው ይኼዳሉ። ከዚያም አልፈው፡ ሳያውቁት፡ ክፉውን ወገንም ሊያግዙ ይችላሉ። ብዙዎቹ እንዲህ ናቸው። አቋም ያላቸው ቢኾኑ ግን፥ እውነት ለአምላካቸው ፍቅር ቢኖራቸው ኖሮ፡ ከማን ጋር መቆም እንዳለባቸው ተረድተው፥ በአንድነት ቆመው፡ መኾን ያለበትን አስፈጽመው፥ መኾን የሌለበትን አስቁመው፡ ቤተክርስቲያን፡ ከእለት ጭቅጭቅ ወጥታ፡ በትውልዱ ላይ ያላትን ተልዕኮ መፈጸም እንድትችል ጉልበት ይኾኗት ነበር። የሐዋርያት ትምህርት ያ ነበረ!