✨ Noor Path ✨ | طريق النور
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 19
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 25
- 1/48двое суток
- 28
- 1/72трое суток
- 30
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
👆👆👆👆👆 5⃣ነገሮችን ከ5⃣ነገሮች በፊት ተጠቀማቸው 1⃣,ህይወትህ ከመሞትህ በፊት 2⃣,ጤንነትህ ከመታመምህ በፊት 3⃣,ክፍት ጊዜህ ከመወጠርህ በፊት 4⃣,ወጣትነትህ ከማርጀትህ በፊት 5⃣,ሀብትህ በመደህየትህ በፊት
አላህ ካንተ ጋር ከሆነ እጅህ ከሁሉም ነገር ባዶ ቢሆን እንኳ አንተ ከሰዎች ሁሉ የተብቃቃህ ሀብታም ነህ።
አላህ የማይወዳቸው አላህ የሚወዳቸው
አል ፉደይል ኢብኑ ዒያድ رحمه الله ሙእሚን ንግግሩ ያነሰ ስራው የበዛ ነው ሙናፊቅ ንግግሩ የበዛ ስራው ያነሰ ነው ይላሉ። أخبار الشيوخ وأخلاقهم للمروذي👉ምንጭ
''በአላህ ስም እምላለው! አላህ ወዳጆቹን እሳት አያስገባቸውም። ረሱል -ﷺ-📕፦ ሶሒሁል ጃሚዕ (7095)
видео или голосовое, без подписи
"በዚህች ምድር ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ትኖራለህ፤ ስለዚህ ሕይወትህን ለትውልድ የምትተረክ ውብ ታሪክ አድርጋት።
«አላህ ለአንድ ወንድ ከሚሰጣቸው ፀጋዎች መካከል የምትወደው ሚስት መስጠቱ ነው።».
видео или голосовое, без подписи
ጅማሮው ላይ ሁሉም አንተኮ ይሄን አትችለውም ይሉሀል በስተመጨረሻ ግን በመደነቀ ሁሉም ተክቢራ ይሉልሀል።، በዚህም ላይ እርግጠኛ ሁን። ..🌸
ጅማሮው ላይ ሁሉም አንተኮ ይሄን አትችለውም ይሉሀል በስተመጨረሻ ግን በመደነቀ ሁሉም ተክቢራ ይሉልሀል።، በዚህም ላይ እርግጠኛ ሁን። ..🌸
آمين يارب
видео или голосовое, без подписи
ለአላህ ሀጃችን አልቅሰንና ተዋድቀን በራሱ ምንኛ መታደል ነው።
⭕️ኢብኑል ጀውዚይ رحمه الله ሰይዱል ኻጢር(صيد الخاطر) ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፦ "ወደ ኢልም የተጠጉ ህዝቦችን አይቼ ነበር… ከሰዎች በሚገለሉበት ወቅት የታላቁን ጌታ እይታ ችላ አሉ እና አላህ ይፋ በሆኑ ቦታዎች ላይ መልካም ትውስታቸውን አጠፋባቸው፤እያሉ እንደሌሉ ሆኑ፤እነሱን በማየት ውስጥ ጥፍጥና አልነበረም፤ልቦችም አይናፍቋቸውም ነበር። እውነት የሆነውን ጌታችሁን እይታ በመጠባበቅ ላይ አደራችሁን! አደራችሁን አላህ ፍሩት! የሱ የፍትህ ሚዛን ትንሿንም ይገልጻል፤የወንጀለኛ ምንዳ ቢዘገይም ያገኘዋል።በርካቶች ወንጀላቸው የተማረ ይመስላቸዋል ግና ማዘናጊያ ነው፤ ወንጀሎችም አስቀያሚ መጨረሻ አላቸው። ከሰዎች ስትገለሉ አላህን ፍሩ! በድብቅ ሁኔታዎቻችሁ አላህን ተጠንቀቁት! ድብቅ ሁኔታችሁን እና የውስጥ እሳቦታችሁንም አደራ! አደራ! በነዚህ ላይ አላህን ተጠንቀቁት! የአላህ ተመልካች አይን አለባችሁ፤በቻይነቱ እና ትዕግስተኝነቱ እንዳትታለሉ ተጠንቀቁ! ስንቶች ተሳስተዋል! ስንቶች ተዘናግተዋል! ወንጀሎችን የምትጠነቀቁ እና ወንጀሎችን በመሰረዝ ላይ የምትታገሉ ሁኑ፤ወንጀልን ከመጠንቀቅ ጋር አላህን እንደመማጸን እና ለሱ እንደመዋደቅ ጠቃሚ ነገር የለም።" إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًۭا አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡
"ረሱል ባይመጡ እኮ ሴት ልጅ ከነህይወቷ ትቀበር ነበር.... ጣዖት እናመልክ ነበር " ይሄ ብቻ ነው ? ሀቢቢኮ የለወጡት የአለምን የፍሰት ቦይ ከመሰረቱ ነው ! ሪሳላውን ይዘው የፈጠሩት እኮ ሌላ አለም ነው ። ባይመጡስ ? እምነቶች የሰውን ልጅ ስግብግብነት ለመግታት በዚህ ልክ ለፍተው እኳ የሰው ልጅ ትልቁ አደጋ "የሰው ስግብግብነት" ነው ። የሰው ልጅ ስውር ባርነቱን ይዞ በድን እሱነቱን ታቅፎ በመንፈስም በአካልም ባርያ ሆኖ በመኖር ውስጥ እየገፋ ... ሰው የመሆኛው ልኬት ጠፍቶ አለም ጉልበተኞች የሚያስተዳድሯት የማፍያ መንደር በሆነች ነበር ። እምነቶች ያልገደቡት የዳሬዊን survival theoryን ያለ ኢስላም አስቡት ! ስልጣንን ማስጠበቅ ላይ ብቻ ያተኮረው የፖለቲካው ጨዋታን ያለ ኢስላም አስቡት ። ያለኢስላም ሴትን አስቡማ ! በስልጣኔና ነፃነት ስም ከእምነት እየፈለቀቁ የሚያወጧቸውን እንስቶች ሳሉማ .... አካሏን ከፋፍለው ለእቃ ማሻሻጫነት ...ውበቷን በሴሰኝነት ውስጥ አጉልተው ለአለም ያጋለጧትና ሴትነቷን ክብሯን በፍቃዷ የነጠቋትን ሸያጢኖች ያለ ኢስላም አስቧቸውማ ። መንቀሳቀስና መስራት የሚችሉትን እየጠለፈ ጥቂቶቹን የሚያበለፅገውን ሲስተም ያለኢስላም አስቡት ! ግብረገብነትን ከድክመት ቆጥሮ ስግብግብነትን የስኬት መንገድ ያረገውን መንገድ ያለኢስላም አስቡት ። አስቡት ኢስላም እያለ በራሱ ነገሮችን እያበላሹ ያሉ አካሎች ትልቁ ጠላታችን የሚሉት ኢስላም ባይኖር አስቡት ! ኢስላም የጠበቀው ክብራችንን ... የመኖር ነፃነታችንን... ሰው መሆናችንን ነው ። ረሱል ከመምጣታቸው በፊትና በኋላ ያለው ለሚዛን የሚቀርብም አይደለም ... የለወጡት የአለምን ስርዓት ነው ። ሰሉ አለል ሀቢብ🤍