tgindex
Hawas Jemea

chaanaalii Jama'aa barattoota muslimaa M/B Q.hawaasiin qophaa'e!! በ ሀዋስ መሰናዶ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የተዘጋጀ ቻናል። አድራሻ ፡ አዳማ ፖስታ ቤት H&H ህንፃ መብራት ሀይል መሄጃ ላይ ቢሮ ቁጥር 405 ላይ ያገኙናል። Odeeffannoo dabalataaf @hpsmuslimjemabot 👆👆👆 ለበለጠ መረጃ

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
om
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
561
+2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
342
21 постов
Вовлечённость
61,0%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
3
1/48двое суток
3
1/72трое суток
3

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እናንተዬ ዛሬኮ ጁምአ ነው መልካም ጁምአ ጁምአም አይደል....ዘንጊዎች በዘነጉ፣አሰታዋሾች ባሰታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ በፈሰሰው አሸዋ፣ ሰማይን ባደመቁት ከዋክብት፣ ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ሙሐመድ(ﷺ)ላይ ይሁን! اللهم صل وسلم على سيدنا محمد በኢባዳዎች እንበራታ...🤌🥰 🫀የጁምአ ስጦታ 🎁 فَلَمَّا ذَهَبُوا بِهِ، وَأَجْمَعُوا أَن يَجْعَلُوهُ فِي غَيْبَتِ الْجَبِ ) «እርሱንም ይዘውት በሄዱና በጉድጓዱ ጨለማ አዘቅት ውስጥ እንዲያደርጉት በቆረጡ ጊዜ፣» (ዩሱፍ :15) ያ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው በባልዲ ተንጠልጥሎ ከጉድጓዱ የወጣው እና በርካሽ ዋጋ የተሸጠው ገው፣ ኋላም ሚኒስቴር ሆኖ፣ ቀጥሎም የግብፅ ዋና ገዥ ሊሆን ሊሆን ጥቂት ቀርቶት የነበረው ነቢዩ ዩሱፍ (ዐ.ሰ.) ታሪኩ ምን ያስተምረናል መሰለህ... የሚያጋጥሙህ ከባባድ የሕይወት ገፆች ሁሉ፣ በዘመንህ ውስጥ በሕይወት ውስጥ ወደፊት የሚመጣውን፣ እጅግ ውቡን ሕይወትህን መንገድ ለመጥረግ የተላኩ መቅድሞች ሊሆኑ ይችላሉና ❤️በአላህ ላይ መልካምን ብቻ ጠርጥር!። ታገስ!🥰 ታገሺ የኔ አበባ 🤌🥰 በምርጡ ዱአችሁ አትርሱኝ 😊 በድጋሚ መልካም ጁመአ መልካም የኢባዳ ጊዜ

  • እናንተዬ ዛሬኮ ጁምአ ነው መልካም ጁምአ 🥰ጁምአም አይደል ሠላዋት እናብዛ አላህ ያግራልን 🥰🤌 اللهم صل وسلم على نبينا محمد....ﷺ 😍የጁምአ ስጦታ 🎁 وَكَلْبُهُم بَاسِطٌ ذِرَاعَيْهِ بِالْوَصِيدِ ) «ውሻቸው ሁለት ክንዶቹን በዋሻው በር ላይ ዘርግቷል» (አል-ከህፍ፡18) ደንቅ እኮ ነው! መልካሞችን በመጎዳኘቱ ምክንያት በቁርኣን ውስጥ ውሻ ለዘላለሙ ተወሳ! አይገርምም ወይ!? ልብስህን እንደምትመርጠው ሁሉ ጓደኛህንም በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ አረቦች እንዲህ ይላሉ “ወዳጅ ጎታች ነው!” አዎ -አንድም ወደ ጀነት አሊያም ወደ እሳት ይጎትታል። ወደ ምርጥ ባህሪ እቀይረዋለሁ ብለህ ያሰብከው ሰው፣ ወደ መጥፎ ሁኔታ ሊቀይርህ ይችላል። አስተካክለዋለሁ ብለህ የቀረብከው፣ ወስዶ ሊያጠምህ ይችላል፡፡ ባይቀይርህ እንኳ በርሱ ወዳጅነት መወሳትህ ራሱ ውርደት ነው። አንድ ሰው በሰዎች እይታ መሠረት፣ በወዳጁ ዲን ላይ ነው ተብሎ ነው የሚታሰበው። ሰው ከውሎው ነውና ባህሪን የሚወርሰው። የራስህም ሆነ የሰዎች እይታ ይስተካከል ዘንድ ጥሩ ጓደኛ ያዝ። ዐረቦች ለመንገድ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ሁነኛ ጓደኛ ያፈላልጉ ነበር። ቤት ከመግዛታቸው በፊት ስለጎረቤቱ ሁኔታ ይጠይቁ ነበር። መልካም ጓደኛ ከዚህች ዓለም ምርጥ መጣቀሚያዎችና ፀጋዎች መካከል አንዱ ነው። አላህ መልካም ጓደኛዎችን ያብዛልን🤌🥰 በድጋሚ መልካም ጁምአ በ ሷሊህ ዱአችሁ አትርሱኝ 🤌🥰

  • 🥰ዛሬኮ ጁምአ ነው.....🥰 ❤️መልካም ጁምአ በኢባዳ የደመቀ ጁምአ ይሁንላችሁ ሡረቱል ካህፍን መቅራትና በተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ላይ ሶለዋት ማውረድ አትርሱ! 🫶የጁምአ ስጦታ 🎁 إِنَّ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِالْغَيْبِ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ ) <<እነዚያ ጌታቸውን በሩቁ የሚፈሩ፣ ለነርሱ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አላቸው: (۸۵-۰۰۵۶ : ۱2) እነርሱ እውነተኞቹ አላህን ፈሪዎች ናቸው፣ ከሰዎች ዐይን የራቁ ቢሆንም፣ አያየንም ብለው ኃጢአትን አይዳፈሩም፣ የአላህ ዐይን እንደምትከታተላቸው ያውቃሉና። ዕድሉ ተመቻችቶላቸው መፈፀም እየቻሉም፣ ከሐራም ነገር ራሳቸውን ይቆጥባሉ የሚስቧቸውና የሚማርኳቸው ነገሮች ቢኖሩም፣ ስሜቶቻቸውን ይገታሉ፤ መንገዱ ሁሉ የተገራ ቢሆንም ከኃጢአቶች ሁሉ የሸሹ ናቸው፡፡ የፍላጎቶቻቸውን መፈፀም ያልቻሉት ጠልተው አይደለም፤ ከሐራም ገንዘብ የተብቃቁት ገንዘብ የማይወዱ ኾነው አይደለም፣ አላህ የከለከለውን ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው የተዉት፤ ከስሜታቸው ይልቅ የአላህ ውዴታ ስለበለጠባቸው ነው። ከፍላጎታቸውም የአላህ ፍላጎት መቅደም ስላለበት ነው፤ ከመሻታቸውም መሻቱን ስለመረጡ ነው። አላህ እያየኝ ነው ብለው አሰቡና ከርሱ አፈሩ!🤌 በሩቅ እሱን ሳያዩ አላህ መፍራት ማለት ይህ ነው። የመዋረድና የመጋለጥ ዕድሉ ዜሮ መሆኑን እያወቁ ጭምር፣ኃጢአትን ይሸሻሉ። በ special ዱአችሁ እንዳትረሱኝ😊 በድጋሚ ፏ ያለ ጁምአ ተመኘሁ 🤗

  • እናንተዬ ዛሬኮ ጁምአ ነው 🥰 መልካም ጁምአ😊 ጁምአም አይደል ሠላዋት ማብዛት ሌሎች ኢባዳዎች(ዱአ,ዚክር,ዚያራ,ቁርአን) ላይም እንበራታ 🥰 ሰሉ አለ ነቢይና ሙሀመድ 🫀🥰 وَرُسُلًا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ ) «ከመልእክተኞችም ባንተ ላይ ያልተረክናቸው አሉ።» (አን-ኒሳእ፡164) ሰዎች ስለ በጎነትህ አመድ አፋሽ ቢያደርጉህ፤ መልካምነትህን አፈር ቢያለብሱ፤ ተስፋ አትቁረጥ፤ አንተ ማን እንደሆንክ አላህ ካወቀ ይህ ብቻውን በቂ ነው፡፡ ከአላህ መልእክተኞች ጭምር አላህ ስለነርሱ ያልነገረን አሉ፡፡ እኛ ባናውቃቸውም አላህ ግን ያውቃቸዋል። ነቢዩ ኑሕን (ዐ.ሰ.) እኛ ስላወቅነው በመልካም ሥራ ሚዛኑ ላይ የምንጨምርለት ምንም ነገር የለም። አንዳንድ ነቢያትን አላህ ስላልነገረንና እኛም ስላላወቅናቸው ብቻ ከመልካም ሥራ ሚዛናቸው ምንም የሚጎድል ነገር የለም የሃሩን አር-ረሺድ ጦር 20ሺ ሙጃሂድ ነበረው። ሙጃሂዶቹ በሠራዊቱ መዝገብ ላይስማቸውን አይጽፉም ነበር። ከአላህ ውጭ ማንም እንዳያውቃቸው ስለሚፈልጉ ደሞዛቸውን ሁሉ አይቀበሉም ነበር። አስ-ሳኢብ ኢብኑ አል-አቅረዕ በነሃውንድ ጦርነት ላይ ስለተሰዉ ሙስሊሞች ለያኔው ኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ ነገራቸው። ትልቅ ስም ያላቸው እና ታዋቂ፣ ብር ባለቤት የሆኑትን ግለሰቦች ቆጠረላቸው፡፡ የክብር ቀጥሎም “ከተርታው ሰው የሆኑ እና የ9 አላት ላቸው፡፡ የምእመናን መሪ የማያውቋቸው ብዙዎች አሉ" በዚህን ጊዜ ዑመር አለቀሱና እንዲህ አሉ፡- “ዑመር ቢያውቃቸው ባያውቃቸው ምን ይጠቅማቸዋል! አላህ ካወቃቸው በቂ ነው!” አስተሳሰብ ከአለባበስ በላይ ሲያምር.. መልካምነት ከተቀባነው ሽቶ በላይ ሲሸት.. .....🥰 ስነምግባር ከመልክ በላይ ውብ ሲሆን.. ያ ነው የሰውነት ጥግ🤌 ደሞ በምርጡ ዱአችሁ አትርሱኝ❤️

  • 🥰እናንተዬ ዛሬኮ ጁምአ ነው የሳምንቱ ኢድ በኢባዳ የደመቀ የደስታ 🥰ፏ ያለ ጁምአ ይሁንልን በዚህች በላጭ ቀን በውዱ ነብያችን ላይ ሠላዋት እናብዛ اللهم صل وسلم على نبينا محمد🥹❤️ ❤️የጁምአ ስጦታ🎁 ስራዎች በኒያ ነው የሚለኩት!!? ❤️የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) “ሥራዎች የሚለኩት በኒያ ነው። ለያንዳንዱ ሰውም የነየተው አለለት።” አሉ፡፡ 😊ስራዎች ሊመሳሰሉ ይችላሉ፡፡ ግና ኒያዎች ደግሞ የሰማይና ምድር ያክል የሚለያዩበት ሁኔታ አለ። ❤️‍🩹ያኔ ዩሱፍም ሆነ ዙለይኻም ወደ በሩ በሮጡ ጊዜ የሩጫቸው ምክንያት የተለያየ ነበር። ዩሱፍ ኃጢአት እየሸሹ፤ ዙለይኻ ደግሞ እያሳደደች፡፡ ❤️‍🩹ሒጃብ/ኒቃብ ለአላህ ብለው የሚለብሱ ሴቶች ብዙ ናቸው የሆነ የወደዱት ሰው ሙተነቂብ ይወዳል ስለተባለ ብቻ የሚለብሱ አሉ፡፡ መስጂድ የሚመላለስ እንዳለ ሁሉ፤ አንዲት የወደዳት ሴት አባት ልጃቸውን እንዲሠጡት ብሎ የአላህ ፍራቻ ያለው ለማስመሰል እርሣቸው ፊት ለአላህ ብሎ የሚመላለስም አለ። ለአላህ ብሎ ህመምተኛን የሚዘይር እንዳለ ሁሉ፤ ለዲኒያዊ ጥቅም ብሎ የሚዘይርም አለ። የሰዎችን ሥራ፤ ፀሐፊ መላእክትን ጨምሮ የአንድን ሰው ኒያ ማንም ሊያውቅ አይችልም። አላህ ብቻ ነው ከውስጥ አይቶን ለያንዳንዳችን የኒያችንን የሚሠጠን። እናማ ኒያችንን እናሳምር ሁሌም...🥰 😊በመጨረሻም አላህዬን ስትጠይቁ በትልቁ ጠይቁ አላህዬ የሚሆኑ ብቻ ሳይሆን የማይቻል የሚመስሉ ነገሮችም ጌታ ነው🤗 በ special🤌 ዱአችሁ አትርሱኝ😊

  • 🤌የኔ ተወዳጅ ሰዎች ዛሬ እኮ ጁምአ ነው🥰 በኢባዳ በሰላዋት የደመቀ ያማረ ጁምአ ይሁንላችሁ😊 ❤️ጁምአም አይደል ሰለዋት እናብዛ አላሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሙሃመድ ወአላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰሊም🥰 🤗የጁምአ ስጦታ 🎁 🥰ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲናገሩ “አላህ አንድን ሰው ሲወድ ጅብሪልን ይጠራና እኔ ይህን ሰው እወደዋለሁ፡፡ አንተም ውደደው" ይለዋል። ጅብሪልም ይወደዋል። ጅብሪልም የጀነት ሰዎችን ይጠራና “አላህ ይህን ሰው ይወደዋል። እናንተም ውደዱት” ይላቸዋል። የጀነት ነዋሪዎችም ይወዱታል፡፡ ይህ ፍቅር ወደ ሰዎች ልብ ይወርዳል። አላህ "በእርግጥም እነዚያ ያመኑና መልካም ስራን የሚሰሩ ሰጪው ፍቅርን ይሰጣቸዋል” ሲል ይህንን ማለቱ ነው፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም) 🥺🥰ያ አላህ ምንኛ ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ አላህ በሰማያት “እወደዋለሁና ውደዱት” በማለት ስምህን ይጠራዋል።🥰 ዙበይር ኢብኑል አዋም (ረ.ዐ) “ኸይር ስራውን በድብቅ ማድረግ የቻለ ሰው ያድርገው” ብሏል። የሚስጥር ኢባዳ በተለያዩ መንገዶች ሊፈፀም ይችላል፡፡ የለይል ሶላት ሳያቋርጡ በመስገድ ሊፈፀም ይችላል፡፡ በየቀኑ አንድ ረከዓም ቢሆን፡፡ ለምሳሌ ከኢሻ ሰላት በኋላ ወይም ከመኝታ በፊት ወይም ከፈጅር ሰላት በፊት ሊፈፀም ይችላል፡፡ አላህ ዘንድ የለይል ሰላት ከሚሰግዱት ሰዎች ጋር ለመታወቅ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “አላህ ዊትር ነው፡፡ ዊትርን ይወዳል፡፡ ስለዚህ (በምሽት) ዊትር ሰላቶችን ስገዱ የቁርዓን ህዝቦች ሆይ!" ብለዋል። ❤️ከድብቅ ኢባዳዎች አንዱ በሰዎች መካከል ሰላም መፍጠር። ለምሳሌ የተጣሉ ጓደኞችህን፣ ጎረቤቶችህንና ባልና ሚስቶችን ማስታረቅ፡፡ በሰዎች መካከል ሰላም መፍጠር ነው:: 🥰 ሌላው የድብቅ ኢባዳ አላህን አብዝቶ ማስታወስ ነው፡፡የሰው ልጅ የሚወደውን ነገር ሁሌም ያስታውሰዋል፡፡🥰 በመጨረሻም አላህዬ ይውደደን ወዶም ያስወድደን....በምርጡ ዱአችሁ አስታውሱኝ❤️

  • የክረምት ስልጠና (SUMMER COURSES) 🕌 በሀዋስ ጀመዓ እና አል-ራስኹን መድረሳ 🗓 የሁለት ወር ቆይታ ያለው ስልጠና 📚 የትምህርት አይነቶች፦ • ዑምደቱል አሕካም • ተፍሲር (ጁዝዕ ዐምማ) • አረብኛ ቋንቋ • አጫጭር የክህሎት ኮርሶች (ሳይኮሎጂን ጨምሮ) 📞 ለመመዝገብ፦ +251936912439 / +251960946072 /+251963920243

  • Oduu gammachisa Ganna kan haala kamin dabarsuuf yaadan ? Jamaa'an Hawaas fi Al rasikun waalin ta'uun sagantaa leenjii gannaa Akkuma kanaan duraa qophesse jira isinis sagantaa kan irratti hirmmadhaa 📚 Gosoota barnoota 📖Tafsira 📖Hadisa 📖Afaan arabaa Odeeffanno dabalataf +251960946072 +251936912439

  • 🤌ዛሬኮ ጁምአ ነው እናንተዬ🤗 መልካም ጁመአ ይህችን በላጭ ቀን በኢባዳ እናሳልፋት አላህ ያግራልን..😊 🥰ጁምአም አይደል የዉበት ቁንጮ በሆኑት የውቦች ውብ ነብይ ላይ ሶለዋት አውርዱ ❤️ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين ❤️የጁምአ ስጦታ 🎁 ዛሬ ከአላህ ስሞች ስሰማው ልቤን ስለሚሰነጥቀው ስለ አል-ጀባር ትንሽ ልበላችሁ.....❤️ ❤️‍🩹አል-ጀባር...ማለት የተሰበሩት የሚጠግን ማለት ሲሆን ባጠቃላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች በግፍ ለተበደሉት,ለተናቁት,ለተዘለፉት ለሁሉም የሚደርስ ማለት ነው...በማንኛውም መልኩ በሞራልም ይሁን በአካል ወይም በሌላ ነገር የተሰበረና ጉዳት ያገኘው ሰው ሁሉ ጠጋኝ ወደሆነው አምላክ ይሂድ ያ ጀባር..ብሎ ይጣራ,ይለምን,ይማፀን ❤️ንፅህናሽን ጠብቀሽ እያለ በሐሰት ስምሽ የጠፋ እህቴ ሆይ! ከ አል-ጀባር ውጪ ማን አለልሽ..የላብህን ውጤት የሆነውን ገንዘብህን በጠራራ ፀሐይ የተካድከው ወንድሜ!....በባለቤትሽ ክፉኛ የተበደልሽ እመቤት!...በዚህች ምድር ላይ የተበደላችሁ ሁሉ ከ አል-ጀባር...ውጪ የሚረዳቹም ሆነ የሚደርስላችሁ ማን የለም...አል-ጀባር...አንድም ቁስላችሁን ይጠግናል..አሊያም የተሰራባችሁን ግፍ ይበቀልላቹሃል ❤️አንድ ሰው ችግርና መከራ ገጥሞት ወደ አል-ጀባር..የማይጠጋ ከሆነ ይህ ሰው በርግጥም ወደ አላህ በመቃረብ የሚገኘውን እጅግ ጣፋጭ ዕድልና ውድ የሆነ ፍቅር እንዳያገኝ ሸይጣን ጋርዶበታል ማለት ነው...በፊት የራቀ ሆኖ ሳለ በችግር ጊዜ ወደ አላህ የተመለሰ መናፍቅ እንደሆነ አድርጎ ያሳምነዋል....በዚህ ጊዜ አደራችንን እንንቃ..ለሸይጣን ጉትጎታና ማሳሳቻ እጅ እንዳንሰጥ የማይበጀኝን መንገድ ስመርጥ፣ እኔን ለማዳን ሲል እቅዴን የሚያበላሽብኝ እርሱ ምንኛ መሐሪ ጌታ ነው! አሁንም እዝነትህን የኔ ጌታ። ጌታዬ ሆይ ውስጤን ጠግንልኝ...ጌታዬ ሆይ ውስጤን ጠግንልኝ ከአፋችሁ ከዱአቹ አይጥፋ..የሙሳን እናት,የረሱላችንን ልብ የጠገነ ጌታ የኛንም ልብ ይጠግንልን 🥰 በድጋሚ መልካም ጁመአ በውዱ ዱአችሁ አትርሱኝ😊

  • ዛሬኮ ጁምአ ነው መልካም ጁምአ 🥰 ደሞ የጠፋ ሰው አትፈልጉማ😔 ጁምአም አይደል በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሠላዋት አውርዱ.. الف الصلاة والسلام عليك يا رسول الله محمد ❤️ የጁምአ ስጦታ 🎁 አንድ ሙስሊም ሲያዝንና ሲተክዝ ሸይጧን በእጅጉ ይደሠታል። ስለሆነም ጠላታችሁ ሸይጧን ይደሠት ዘንድ ዕድል አትስጡት። ደስ ይበላችሁ፣ ጥሩ ተናገሩ ጥሩ አስቡ.... ወደ አላህ ቅረቡ.... ❤️ፀሀይ የተውበትን ያህል አታበራም። ፀሀይ ብርሀኗ ውስጥ ማቃጠል አለው፣ ተውበት ግን አያቃጥልም፣ ይልቁኑ ምንም በማይጎረብጥ መልኩ ይሞቃል፣ ያሞቃል። የፀሀይ ብርሀን የሚደርስበትን የርቀት መጠን የሰው ልክ ተመራምሮ ሊያውቅ ይችላል። ተውበት ግን ረቂቅ ነው የሚደርስበትን ርቀት ከአላህ በቀር ማንም አያውቅም! ፀሀይ ልብ ውስጥ አትበራም። ተወበት ግን ሁሉም ነገር በሚመሰጠርበትና አላህ ብቻ በሚመለከተው ልብ ውስጥ በርቶ ሰዎች መመልከት በሚችሉት ገፅታ ላይ ይንፀባረቃል። ፀሀይ እጅ የምትሰጥለት ጽልመት አለ፣ ተውበት ግን ድል የማያደርገው አንድም ጽልመት የለም። በምንም ነገር ውስጥ አልፈው፣ በስተመጨረሻ ወደ አላህ ተመልሰው ንፅህናን በደረቡ፣ ውበትን በጨመሩ፣ በመልካሙ መንገድ ላይ በፀኑ ላይ ሁሉ የአላህ ሰላም ይስፈን። » አላህ ያማረ መጨረሻን ይስጠን❤️ በድጋሚ በኢባዳ የደመቀ ጁመአ ተመኘው 🤌 በዱአችሁ አትርሱኝ...❤️

  • ማስታዎሻ‼ ነገ ዓሹራእ ነው፣ እንጹም። በዛው ላይ ሐሙስ ነው። ሁለቱንም እንነይት – ኢንሻ አላህ! እንደ'ኛ ወንጀል ብዛት መሰል አላህ ያመቻቸልልን የወንጀል ማበሻ አጋጣሚዎች ካልተጠቀምንባቸው ተሸውደናል።

  • ✋የዘንድሮው የዐሹራ ፆም (የሙሐረም 10ኛው) ቀን ሐሙስ ሰኔ 18 ላይ ይውላል። ይህንን ታላቅ ቀን መፆም ያለፈውን የ365 ቀናት (የአንድ ዓመት) ወንጀል ያስምራል። ​በላጩና ተመራጩ አፆፃም...ነብዩ (ﷺ) አይሁዶችን ለመለየት ዘጠነኛውንም ቀን አብሮ ለመፆም አስበው ስለነበር፣ በላጩ መንገድ ረቡዕ (ሰኔ 17) እና ሐሙስን (ሰኔ 18) አከታትሎ መፆም ነው። ሌሎችንም በማስታዎስ የአጅሩ ተጠቃሚ ያድርጓቸው! ደሞ በዱአችሁ🤌 🥰

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • Galatoomaa!

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • #Sagantaa_Hawataa_ture. Jama’aan baratootta mana Barumsa qopha’ina Hawaas sagantaa ifxara Adda Taasisee jira 💪